
26 መስከረም 2023, 11:12 EAT
ጨቋኙን የነጭ አገዛዝ በመታገል የሚታወቁት የደቡብ አፍሪካ የነጻነት ታጋዩ ኔልሰን ማንዴላ የልጅ ልጅ ዞሌካ ማንዴላ ህይወቷ አለፈ።
በ43 ዓመቷ ህይወቷ ያለፈው ዞሌካ ጸሃፊ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ነበረች።
የአፓርታይድ ስርዓት ከተገረሰሰ በኋላ በደቡብ አፍሪካ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ነበሩ ኔልሰን ማንዴላ።
የልጅ ልጃቸው ዞሌካ ማንዴላ ህይወቷ ያለፈው በካንሰር ህመም መሆኑንም ቤተሰቦቿ አስታውቀዋል።
የቤተሰቡ ቃለ አቀባይ በኢንስታግራም ላይ በሰጡት መግለጫ ዞሌካ ሰኞ ማምሻውን በጓደኞቿ እና በቤተሰቦቿ ተከባ ህይወቷ አልፏል ብለዋል።
ዞሌካ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በካንሰር ህክምናዋ ያጋጠማትን ውጣ ውረድ እንዲሁም በአንድ ወቅት የአደንዛዥ ዕጽ ሱሰኛ እንደነበረች በመናገሯ በበርካቶች ዘንድ ዕውቅናን አትርፋለች።
በተጨማሪም በድባቴ ትሰቃይ እንደነበር እንዲሁም በልጅነቷ የወሲብ ጥቃት እንደደረሰባትም ታሪኳን አጋርታለች።
- በሐኪሞች መሮጥ አትችይም ተብላ ክብረ ወሰን ስለሰበረችው ትዕግሥት አሠልጣኟ ምን ይላሉ?26 መስከረም 2023
- በጦርነት በሞቱ ሰዎች መርዶ ሐዘን ያጠላባት ትግራይ26 መስከረም 2023
- የዘር ማጽዳት እንዳይፈጸምባቸው የፈሩ አርመናውያን የካራባክን ግዛት ለቀው እየሸሹ ነው26 መስከረም 2023
የ13 ዓመት ሴት ልጇ በአውሮፓውያኑ 2010 በመኪና አደጋ መሞቷን ተከትሎ የትራፊክ ደህንነትም ላይ ዘመቻ ስታደርግ ነበር።
የህይወት ታሪኳንም ‘ዌን ሆፕ ዊስፐርስ’ በሚል ርዕስም መጽሃፍ አሳትማለች።
ዞሌካ በካንሰር የተጠቃችው ከአስር አመታት በፊት ነበር። ህክምና ካገኘች በኋላም ተሽሏት ነበር።
ነገር ግን ባለፈው አመት በጉበት እና በሳንባ ካንሰር እንደተጠቃችም አረጋገጠች። ሆኖም በህይወት በመቆየቷ ምስጋናዋን ገልጻ ነበር።
