September 27, 2023 – Konjit Sitotaw 

በ Ethio 360 የተለቀቀው የብልፅግና ሰነድ
በመሀመድ ሀሰን
=============================
አብይ አህመድ ከወያኔ የወረሰውንና በሱ አስተዳደር ዘመን ከቀዩ መፅሀፍ ወያኔ መሩ የመከላከያ ሰራዊት ወደ ብልፅግና አረንጓዴ መፅሀፍ መሩ የህዝብ መከላካያ ሰራዊት አድርጌ ቀርጬ በሌሊት የሚያይ፣የሚጓዝና የሚሄድ አድርጌ ከመቼም ጊዜ በተሻለ ቁመና ሰርቼዋለሁ ያለውን የቀድሞውን የኢትዮጵያ መከላካያ ሰራዊት የአሁኑን ኦነግ መር የአብይ አህመድ ሰራዊት ወደ አማራ ክልል ለወራራ አዝምቶ በእቅዱ መሰረት ያመጣው ተጨባጭ ድል ሳይታይ ስድስት ወራቶች አለፉ። ኦነግ መሩን የአብይ አህመድ ሰራዊት በልበ ሙሉነትና በጅግንነት የገጠሙት የአማራ ልጆች (ፋኖዎች) በዚህ ስድስት ወር ውስጥና በተለይ ባለፊት ሁለት ወራቶች በአብይ አህመድ አፍ ብዙ የወራለትን ሰራዊት በወንዶቹ ሜዳ ድምጥማጡን አጥተውታል። ይህ በገዚዎቻችንና በአብይ አህመድ ተላላኪ የሰራዊቱ ከፍተኛ አካላት የሚፈጠረው የስነ ልቦና ቀውስና የመዋረድ ስሜት አማራ ክልልና ህዝብ ላይ ያወጁትን የዘር ማጥፋትና የወረራ ጦርነት እቅድ ከእንደገና በማጤን ጉዳዩን በሰላምና በውይይት ለመፍታትም ሆነ የጦርነት ነጋሪት አቋማቸውን ከማስተካከል ይልቅ የፋኖዎች ትግል ጠንካራ ጎኖች ናቸው ብለው ግምት በሚሰሩባቸው ነገሮች ሁሉ የፋኖዎችን ትግል ወደኋላ ለመጎተት (sabotage) መዶለታቸው የማይቀር የነበረ ሆኖ በዚሁ አግባብ በቅርቡ የአብይ አህመድ መንግስት የተወያየባቸው ሰነዶች በ Ethio 360 አማካኝነት ሰነዱ ለህዝብ ይፋ ሆኗል።

ይህ ሰነድ ያረጋገጠው ሀቅ ቢኖር ህዝባችን በፋኖዎች ትግል ውስጥ በጣም ትኩረት አድርጎ እንዲከታተለውና በፋኖዎች ትግል ውስጥ የአብይ አህመድ መንግስት የፋኖዎችን ትግል ለመጥለፍና ወደኋላ ለመጎተት ሊጠቀምባቸው የሚችሉ ጉዳዬች ይሆናሉ እና ህዝባችን ጥንቃዌ ያድርግ ብለን ቀደም ብለን የፃፍንባቸው ጉዳዮች መሆናቸው ነው።

ከሰነዱ ላይ ያሉ የተወሰኑ ሀሳቦች:-
======================

1) ቡድኑ ዘራፊ፣ቀማኛ፣ሴቶች የሚደፍርና ንብረት የሚያወድም
========================================
አብይ አህመድ በአማራ ክልልና ህዝብ ላይ ወረራ ካወጀበት እለት ጀምሮ ዛሬ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በፋኖዎች ተፈፅሟል የተባለ ዘረፋ፣የሴቶች መደፈርና የንብረት ውድመት ሪፖርት የለም። ይልቅ ይሄ ሁሉ የተባሉት ነገሮች በህዝባችን ላይ እየተፈፀሙ ያሉት በአብይ አህመድ ሰራዊት ነው። በተለያዩ ከተሞች በማጀቴ፣ በፍኖተ ሰላም፣በደብረ ማርቆስ፣በሸዋ ሮቢት፣በራሳ እና ሌሎችም ከተሞች በአብይ አህመድ ሰራዊት የተፈፀሙ ወንጀሎች በአለም አቀፍ ሚዲያዎች ሁሉ የተዘገቡ ናቸው።

ፋኖዎች የአማራ ልጆች፣አማራ በስነ ስርአት ወግና ባህል ኮትኩቶ ያሳደጋቸው ጨዋ፣የሞራል ልእልና ባለቤትና ከላይ በአብይ መንግስት የተዘረዘሩ ወንጀሎችን ለመፈፀም ስብእናቸው የማይፈቅድላቸው ስርአት ያለው ማህበረስብ ያሳደጋቸው መሆኑን አስመስክረዋል።

2) ቡድኑ የአንድ ሀይማኖት የበላይ ጠባቂ እንደሆነ የሚያምን የህበረተሰብ ክፍል በመኖሩ

ይህቺን ሀሳብ በደንብ ያዙልኝ።

መንግስት ራሱ “ፋኖዎች የአንድ ሀይማኖት የበላይ ጠባቂ ናቸው ወይም ስለሆኑ” በሚል ትንታኔ አልሰሩም። ይህ የሚያመላክተው በመንግስት ደረጃ እንኳ ፋኖዎች ለክርስትና እምነት የበላይነት የሚሰሩ ናቸው ተብሎ በስፋት በአንዳንድ አልባሌ ወገኖዎች የሚሰራጩ ዜናዎችን የሚያምንበት አለመሆኑን ሲሆን ይሄን ክስ የሚያምንበት የማህበረሰብ ክፍል ስላለ ብቻ ግን ሀሳቡን አጀንዳ በማድረግ የፋኖዎችን ትግል ለመጥለፍ መሰራት እንዳለበት መስማማት ላይ ደርሰዋል።

ይህ በቀጥታ የሚወስደን: –
==================
ሀ) አብዱልጀሊል ካሳና አዱኛው ሙጬ የተባሉ የወህቢያ መናኛዎች በመካነ ሰላም ፋኖዎች መስጊድ ውስጥ የነበረ መኪናን ለመውሰድ ሞክረዋል በሚል ክስ ሊያስነሱት የነበረውን የተለመደ ግርግር

ለ) አዱኛው ሙጬና የብልፅግና መጅሊስ ለአማራ ክልል እስልምና ጉዳዬች ፀሀፊ አድርገው በሾሙት በአዲሱ ተሿሚ አማካኝነት ሞጣ ላይ ፋኖዎች የሙስሊሙን መሳሪያ እየቀሙ ነበር በሚል ክስ ሊያነሱት የነበረውን የተለመደ ግርግር

ሐ) አሁንም በቅርቡ የኦነግ የፖለቲካ አመለካከትን ተሸካሚ የሆኑት የወህቢያ ደቀመዝሙሮቹ አዱኛው ሙጬ፣ አዲሱ የአማራ ክልል መጅሊስ ፀሀፊና ሌሎች ግለሰቦች በመሽንቲ ፋኖዎች የሙስሊሙን ማህበረሰብ ንብረት እየዘረፉ ነው በሚክ ክስ ሊያነሱት የነበረውን የተለመደ ግርግር እና

መ) በአጠቃላይ ከወያኔዎችም ሆነ ከኦነጋውያን በ50 አመታት የለመዱትን አማራ ህዝብ ላይ ጨቃ የመቀባት ሱስ በተለያየ ጊዜ ፋኖዎች ሙስሊም ጠልና የክርስትና ጠበቃ አድርጎ የማቅረቡ የ boogeyman ፖለቲካ ውጤት የሆነው ትርክት በሙሉ እና መሰል ጉዳዬችን የሚመለከት ነው።

እነኚህ አካላት አብይ አህመድ የፋኖዎችን ትግል ለመጥለፍ በሚያደርገው ጥረት በአማራ ክልልና ህዝብ ላይ አሉታዊ የትግል መሰናክሎችን ለመፍጠርና (breeding ground) ለማመቻቸት እየሰሩ መሆናቸው በመንግስት እይታ ውስጥ ገብተው መንግስት በዚህ ላይ የበለጠ በመስራት በማህበረሰባችን መካካል የሀይማኖት ክፍፍልና ቅራኔ በመፍጠር የሞጣና የጎንደር አይነት scenarios እውን በማድረግ በጦር ሜዳ የራቃቸውን ድል በእንዲህ አይነይ እኩይ ድርጊት በፋኖዎች ላይ ድልን መቀዳጀት የሚሹበት ጥረት እየተደረገ ያለ መሆኑን ጠቋሚ ነገሮች አሉ።

በዚህ በሀይማኖይ ጉዳይ ፋኖዎች በተደጋጋሚ መግለጫ የሰጡበት ጉዳይ ቢሆንም አማራ ክልል ላይ ይህ የሀይማኖት ቅራኔ እንዲፈጠር ሳይታክቱ የሚሰሩና የሚፈልጉ የኦነግ ሀሳብ ተሸካሚ ፓራሳይቶች ባሉበት ሁኔታ ፋኖዎችን ወዳልተፈለገ ግርግር  የሚወስዱ ክስተቶች ቢፈጠሩ እንኳ ፋኖዎች በከፍተኛ ጥንቃቄ ማለፍ ያለባቸው ጉዳይ እንደሆነ ደጋግመን ጠቁመናል። ፋኖዎች በወንዶቹ ሜዳ ላይ የማይተካ ነፍስን በሚነጥቀው መሳሪያ ከሚያደርጉት ትግልና ከሚከፍሉት መስዋእትነት ይልው እንዲህ አይነቱ የሀይማኖት አጀንዳ ያለው አሉታዊ ተፅእኖ ከፍተኛ ከመሆኑ አንፃር በዚህ ዙሪያ ከፍተኛ ትከሩት እንደሚሻ በተደጋጋሚ ስናሳስብ ይህ ጉዳይ ፋኖዎች ሳይገነዘቡት ይቀሩ ይሆናል ወይም ትኩረት ላይሰጡት ይችላሉ  ከሚል አመለካከት ሳይሆን በሀይማኖት ስም የኦነግን የፖለቲካ አመላካት ተሽክሞ አማራ ክልል ላይ ያለው ሀይማኖተኛ ባይ የወህቢያ አሽከሮች ቤንዚንና ክብሪት ይዘው በማህበረሰባችን መካከል ብጥብጥ ለመፍጠር በማንኛውም ወቅት በማይከደኑ አይኖች እየጠበቁ ካሉበት ሁኔታ አንፃር ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ ጉዳይ በመሆኑ ነው።

4) አሀዳዊ ስርአት ለመመለስ የሚባለው ክስ
ይህ ከ50 አመት በላይ የተጫወቱበት ሙዚቃ ዛሬ ላይ ደምፁ ጎርንኖ፣ የሙዚቃው ዲስክ ስክራች አድርጎ፣የማጫወቻ መሳሪያቸው ራሱ ልክ የቴፕ ካሴት player እንደሚሆለጉለው የካሴት ክር ይሄን ሙዚቃ በማጫወት የሚያወጣው ድምፅ ለጆሮ የማይጥ despicable bad soundtrack ከመሆን ያለፈ ፋይዳ ባይኖረውም ይሄው ሰይጣናዊ ግብር በግማሽ ምእተ አመት ውስጥም ቆሞ ቀሮች ራሳቸውን ማደስና መቀየር በማይችሉበት  የፖለቲካ ትርክት የተወሰነ ነገር መሞከራቸው እንደማይቀር አሰረጂ ነው።