September 27, 2023 

መረጃ ጎንደር..!

በጎንደር ሶስት ቦታዎች ዛሬ ውጊያዎች ሲደረጉ ውለዋል። ውጊያዎች ሲደረጉባቸው ከዋሉ አካባቢዎች መካከል ማክሰኝት፤ እንፍራንዝና ቆላድባ ይገኙበታል።

1. ቆላድባ በከተማዋ የፋኖ ኃይሎች የሚታዩ ሲሆን ከ5:00 ጀምሮ በሁለት ግንባሮች ማለትም ከቆላድባ ወደ አዘዞ በሚያስወጣው መንገድና ከቆላድባ ወደ ጯሂት በሚያስወጣው መስመር ላይ ውጊያዎች ሲደረጉ ውለዋል!

2. በማክሰኝት ደግሞ በተለምዶ ግራኝ በር (ወደ በለሳ መገንጠያ) ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ውጊያዎች እየተደረጉ ሲሆን አገዛዙ ታንኮችን ጨምሮ የተለያዩ ከባባድ መሳሪያዎችን ወደ ከተማዋ እያሰገባ ይገኛል። በዚች ከተማ ፋኖ በመከላከያ ካምፕ ላይ ባደረሰው የደፈጣ ጥቃት በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች የተገደሉ ሲሆን የተጎዱትን ለማከም ከሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎችን በፓትሮል ወደ ካምፑ ሲያመላልስ እንደተመለከቱ ምንጮቻችን ገልፀውልናል።

3. በእንፍራንዝ ፋኖ ከተማዋን መቆጣጠሩን ተከትሎ ፋኖዎቹን ከከተማ ለማስወጣት መከላከያ ውጊያ የከፈተ ሲሆን ፋኖ የከተማውን የመሳሪያ ዲፖ ጥቃት በማድረስ ስናይፐር እና ብሬን ጨምሮ በርካታ መሳሪያዎችን መውሰዱ የተገለፀ ሲሆን በኮማንድ ፖስቱ ተይዘው ታስረው የነበሩ ከ60 በላይ እስረኞችን ማስለቀቁ ተገልጿል።

ምንጭ  አሻራ ሚዲያ