September 28, 2023 – Konjit Sitotaw 

ቆላድባ ጯሂት እንፍራዝ እና ማክሰኝት የናደው ብርጌድ መሪ ደረጀ በላይ ከሰንጥቅ ብርጌድ ጋር በመሆን የደምቢያ ገበሬ በምሥራቅ እና በምዕራብ ያለውን በማስተባበር ከአራቱ ግምባሮች ውስጥ በሦስቱ ጠላትን ሙትና ቁስለኛ አድርጎታል ።

ቴዎድሮስ ብርጌድ እና ፋሲል ሻለቃ እንዲሁም ገብርየ ብርጌድ በተሳተፉበት የነ ሻለቃ ሀብቴ ወልዴ የማጥቃት ሂደት የታየበት ውጊያ በአራት ሰዓት ውጊያ እንፍራንዝን መቆጣጠር ተችሏል።

የአለፋው መብረቅ ሻለቃ ሸርብ የገባበት የቆላድባው ውጊያ ጠላት የተረፈ ያለ እስከማይመስል ድረስ ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል ከባድ መሳሪያ ይዞ ቆላድባ ተራራ ላይ ሲተኩስ የነበረው የጠላት ኃይል ያለውን ይዞ ለማፈግፈግ ተገዷል ።
ደረጀ በላይ በኩል አንድ ሰው የተሰዋ ሲሆን በሰንጥቅ ብርጌድ በኩል ደግሞ ሁለት ሰዎች መስዋትነት ከፍለዋል ።

የብርጌዶቹ አመራሮች ድሉን ሲገልፁት በትንሽ መስዋትነት ጠላትን ወገብ የቆረጥንበት ውጊያ ነበር ብለዋል ።

ለቀጣይ ተከታታይ ማጥቃቶች እንደሚያደርጉ ያሳወቁት የብርጸጌድ አመራሮች  ወደ ዋናው ማጥቃት እስክንገባ ድረስ በደፈጣ ውጊያ ጠላትን እያወደምን እየማረክን በቡድን መሳሪያ እና በተተኳሽ ራሳችን እናደራጃለን ብለዋል ።

ደረጀ በላይ የበጋው መብረቅ በሚመራው ግምባር ተሸንፎ እንደማያውቅ ባንዳው ጀነራል ማርየ እራሱ ምስክር ነው ።
ውጊያው ዛሬም እንደቀጠለ ነው።