September 29, 2023 

ዜና ሰማእታት…! (ዘመድኩን በቀለ)

“…መስከረም 15/2016 ዓም በኦሮምያ ክልል በአርሲ ሀገረ ስብከት በሆንቆሎ ወረዳ ቤተ ክህነት ቦሌ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ዕጣ የወደቀባቸው ምስኪን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ካህናት እና ምዕመናን የኢሬቻ በዓል ከመከበሩ በፊት በኦሮሞ ነፃ አውጪ ሠራዊት የታረዱት የሚከተሉት ናቸው። https://t.me/ZemedkunBekeleZ/22998

“…የካህኑ ሚስትና ልጅ፣ መ/ር ዳዊት ጌታቸው፣ አበጀ ከበደ፣ ሞገስ ክንፈ፣ መርሻ ፣ ሽመልስ ተስፋዬ፣ እመቤት ስሜ፣ ቡሩክ እና መምሬ ዘሪሁን ሲሆኑ ሁላቸውንም በጥይት ደብድበው፣ አርደውም ደማቸውንም ጠጥተውና ተቀባብተው መሄዳቸው ተነግሯል። አምልኮ መሆኑ ነው።

“…ከዚሁ ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት ተጎድተው በሕክምና ላይ ያሉ አገልጋዮች ደግሞ ይርጋ ሞገስ፣ ባዩ ካዳዬ፣ ምሕረት በላይ ይግባው፣ እቡጤ ውብሸት እና አመለ ምሕረት ናቸው።

“…ትናንት እንዳልኩት በግድያው የክልሉ መንግሥት እስከ አሁን ድረስ ጭጭ ያለ ሲሆን ሃገረ ስብከቱም ቢሆን እስከአሁን ያወጣውን መግለጫ አላየሁም። አሰቃቂው ግድያ የመስቀል ደመራ ዋዜማ ምሽት እንዲፈጸም የተደረገው ዜናው ቀደም ብሎ ወጥቶ በመላው ኢትዮጵያ ተሰራጭቶ የትናንቱን የደመራ በዓል ኦርቶዶክሳውያኑ የተዋሕዶ ልጆች በጨለማ እንዲዋሉት ታስቦ እንደነበርም ታውቋል። እደግመዋለሁ ይህን ዜና የለጠፍኩት እንድታለቅሱ ብዬ አይደለም እንድትመዘግቡት ብዬ እንጂ። ይመዝገብ።

“…የዘንድሮው የእሬቻ ግብር በአሩሲ ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆችን በማረድ ተጀምሯል። በቀጣይ ቀናት ደግም አራጆቹ በኦሮሞ ምድርም ሆነ በሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ምን ያሰሙን፣ ያሳዩንም ይሆን…? የሚለውንም አብረን እናየዋለን።

“…እንዲህ ዓይነቱን አራጅ ነፍሰ በላ ለመበቀል መዘጋጀት ግን ተፈጥሮአዊም፣ ሕጋዊም፣ መለኮታዊም ፈቃድ ያለው ነው።

•በረከታቸው ይደርብን…! https://t.me/ZemedkunBekeleZ/22998