September 30, 2023 – VOA Amharic
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን፣ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል፣ በአፍሪካ የዲያስፖራ ተሳትፎ አማካሪ የሚኾኑ 12 የምክር ቤት አባላትን ስም ዝርዝር፣ በዚኽ ሳምንት መግቢያ ላይ ይፋ አድርገዋል።
ከእኒኽም አንዷ የካሊፎርኒያ ግዛት ነዋሪዋ ትውልደ ኤርትራዊቷ ወሮ. አልማዝ ነጋሽ ናቸው። ወሮ. አልማዝ፣ በዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ዳያስፖራ የትስስር መድረክ መሥራች ናቸው…
