


FDRE Defense Force – የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቅዳሜ መስከረም 19 ቀን 2016 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለሠራዊቱ እና ለቋሚ ሲቪል ሰራተኞች የጋራ መኖሪያ ቤቶች የመሠረተ ድንጋይ ተቀመጠ።
የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ እና የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለሠራዊቱ የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ መሠረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል።
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ለሠራዊቱ አባላት እና ቋሚ ሲቪል ሠራተኞች በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በ26,673 ካሬ ሜትር ላይ ለ1000 አባወራ የሚተላለፍ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የሚገነባ መሆኑ ተገልጿል።
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ብርጋዲየር ጀኔራል ደረጄ መገርሳ እንደገለፁት ለሀገር ህልውና አስጠባቂ ለሆነው መከላከያ ሠራዊት ደረጃውን የጠበቀ የጋራ መኖሪያ ቤት ለመገንባት የዲዛይን ስራው ተጠናቆ ግንባታውም በያዝነው አመት ይጀመራል።
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ምክትል ስራ አስፈፃሚ ኮሎኔል ታደሠ ጌታቸው በበኩላቸው የጋራ መኖሪያ ቡሎኮቹ ከ16 እስከ 18 እንደሚደርሱ ገልፀው አንዱ ብሎክ እስከ G+12 የሚደርስ ባለ 1፣ ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ ቤቶችን አጠቃሎ እንደሚይዝ ተናግረዋል።
የሠራዊቱ አመራሮች በቃሊቲ ክፍለ ከተማ በቁጥር 1 እና 2 ሳይቶች የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶችንም ጎብኝተዋል።
ዘጋቢ ብስራት ፀልይ
ፎቶግራፍ ፉራ አብደላ
