
ከ 9 ሰአት በፊት
እስራኤላዊ ሴት ወታደሮች ከፍልስጤማዊ እስረኛ ጋር ወሲባዊ ግንኙነት ፈፅመዋል በሚል ክስ ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግለት እስር ቤት ጠባቂ ሆነው እንዳያገለግሉ ታገዱ።
የእስራኤል ሚዲያዎች እንደዘገቡት ወታደሯ በእስራኤል ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት ከፈፀመው ፍልስጤማዊ እስረኛ ጋር አካላዊ ግንኙነት እንዳላቸው አምናለች።ሌሎች አራት ሴቶችም ከዚሁ ግለሰብ ጋር የቅርብ ግንኙነት እንደነበራችው ተናግራለች።
ግለሰቧ የውትድርና አገልግሎት እየሰጠች እንደነበር ተገልጿል።
ለአብዛኛው እስራኤላውያን ወታደራዊ አገልግሎት መስጠት ግዴታ ነው።
በእስራኤል ሴቶች ቢያንስ ለሁለት ዓመት ወንዶች ደግሞ ለ32 ወራት ወታደራዊ አገልግሎት መስጠት ይጠበቅባቸዋል።
ድርጊቱን ፈፅማለች የተባለችው ወታደር እና የዕድሜ ልክ እስረኛው ስም አልተገለጸም።
ጉዳዩን እየተመለከተ ያለው ፍርድ ቤትም እስር ቤቱ የሚገኝበትን ቦታ ጨምሮ ሌሎች ዝርዝር መረጃዎች ይፋ መውጣት እንደሌለባቸው ትዕዛዝ ሰጥቷል።
- ኤርትራውያን በእስራኤል ጎዳናዎች ላይ ለምን ወደ ሁከት አመሩ?7 መስከረም 2023
- ኔታኒያሁ በሁከት የተሳተፉ ኤርትራውያን እንዲባረሩ እና አፍሪካውያን ስደተኞችን ለማስወጣት ዕቅድ እንዲወጣ አዘዙ3 መስከረም 2023
- የአሜሪካ ምስጢርን አሳልፎ ሰጥቷል ስለተባለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ አስካሁን የምናውቀው30 መስከረም 2023
ፍልስጤማዊው እስረኛ ቃሉን እንዲሰጥ ከመጠየቁ በፊት ከነበረበት የእስረኛ ክፍል ወደ ሌላ ክፍል እንደተዛወረም የእስራኤል የእስር ቤት አገልግሎት (አይፒኤስ) ገልጿል።
ዐርብ ዕለት የአይፒኤስ ኃላፊ ካቲይ ፔሪ እና የደኅንነት ሚኒስትሩ ኢታማር ቤን ግቪር፣ሴት ጠባቂዎች ከዚህ በኋላ ፍልስጤማውያን “ሽብርተኞችን” በያዙና ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግላቸው እስር ቤቶች እንደማያገለግሉ አስታውቀዋል።
የደኅንነት ሚኒስትሩን ኢታማር ቤን ግቪርን ጠቅሶ የእስራኤል ሚዲያ እንደዘገበው በአውሮፓውያኑ 2025 አጋማሽ አንድም ሴት ወታደር ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግላቸው እስረኞች በሚገኙበት ክንፍ ውስጥ አትቆይም” ብለዋል።
ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግባቸው የእስራኤል እስር ቤቶች የሴት እስራኤላዊ ወታደሮች አገልግሎት እንዲታገድ በተደጋጋሚ ጥሪ ሲቀርብ ቆይቷል።
ሆኖም እነዚህን ሴት ወታደሮች በሚተካቸው የሰው ኃይል እጥረት ምክንያት ጥሪዎቹ ሳይተገበሩ ቆይተዋል።
ባለፈው ዓመት የእስራኤል ሚኒስትሮች ፍልስጤማውያን ፍርደኞች የእስር ቤቱ ጠባቂ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩ ሴት ወታደሮችን ላይ ጥቃት በማድረስና በመድፈር እንዲሁም አንዳንድ የእስር ቤት ከፍተኛ መኮንኖችም ወታደራዊ ግዳጁን “ጥሰዋል” በሚል በአንድ እስር ቤት ውስጥ ምርመራ እንዲካሄድ ትዕዛዝ ሰጥተው እንደነበር ይታወሳል።
