የአገዛዙን ሙስና በጭልፋ፣ የረዳት ኮሚሽነር ተከታይ ያዜ የሙስና አባዜ፣
የአብይ አህመድ አገዛዝ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሃገሪቱን አይታው ወደማታውቀው የሙስና ባህር ውስጥ ደፍቋታል የምንለው ያለምክንያት አይደለም። ሙስና በግል ወይም በቡድን በመደራጀት የሚፈጸም ወንጀል ነው። ሆኖም ግን የሙስናው ጥቅም ሁሌም የሚገለጸው በእያንዳዱ ሙሰኛ ግለሰብ የግል፣ የቤተሰብ፣ የዘመዶች፣ የጓደኞች፣ የእውቆች ህይወት ላይ በሚያመጣው ለውጥ ነው።
በመሆኑም የአንድን ሃገር የሙስና ደዌ ማሳየት የምንችለው በሙስና እጁ የተጨማለቀውን ግለሰብ እውነተኛ ታሪክ በማቅረብ ብቻ ነው። በጥቅሉ ሙስና ተስፋፍቷል በማለት አስከፊነቱን ህዝብ እንዲረዳ ማድረግ አይቻልም።
ከመሳይ መኮንን ጋር በአንከር ሚድያ ላይ ባደረግሁት ቃለ መጠይቅ፣ የረዳት ኮሚሽነር ተከታይ ያዜን ታሪክ ለመዘርዘር የተገደድኩት ኮሚሽነር ተከታይ የሃገሩ ብቸኛ ሙሰኛ ወይም የሙሰኞች ሁሉ ቁንጮ ሰለሆነ አይደለም።
የአሳ ግማቱ ከአናቱ እንደሚባለው የሃገሪቱ ባላስልጣናት የቆሸሸ የሞራል ስብእና የሚጀምረው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል። ተከታይ በተለይ የተመረጠው ሰውየው ከተራ ሙስና አልፎ ለነጻነቱና ለመብቱ የሚታገለውን ህዝብ የገንዘብ ምንጭ ለማድረግ የሄደበት ርቀት፣ የከፋ ነውረኛ ፍጥረት ስላደረገው መሆኑ መታወቅ አለበት ።
የረዳት ኮሚሽነር ተከታይ የፌደራል ፖሊስ አለቆች የሙስና ጉድ፣ ከተከታይ የሚበልጥ እንጂ የሚያንስ አይደለም። ሁሉንም ጊዜውን ጠብቀን እናወጣዋለን። የምናውቀው ጉድ ህዝብን በመዝረፍ የሚኖሩትን እጅግ የሚያስደነግጥ ቅንጡ ህይወት ብቻ ሳይሆን በር ዘግተው፣ ሰው አያየንም አይሰማንም ብለው የሚያሴሩትን ሴራ ጭምር እንደሆነ እንዲያውቁት እንፈልጋለን።
ረዳት ኮሚሽነር ተከታይ ያዜ ማነው?
ይህ ግለሰብ፣
የወር ደሞዙ 10500 ብር ብቻ የሆነ ሆኖም ግን ሶስት ልጆቹን አሜሪካን ሃገር ዲሲ፣ አንድ ልጁን ደግሞ አዲስ አበባ ውስጥ ውድ ከሚባሉት ትምህርት ቤቶች አንዱ በሆነው በሊሴ ገብረማሪያም የሚያስተምር ነው።
በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ ኪራይ የሚሰበስብባቸው ሁለት ቅንጡ አፓርትመንቶች አሉት።
ሰልጣኑን ተገን በማድረግና የተለያዩ የሃሰት ሰነዶች በማዘጋጀት ገንዘብ እንደሚሰበስብ በአለቆቹ ጭምር የሚታወቅ ሰው ነው።
የቦሌ ክፍለ ከተማ ሃላፊ በነበረበት ወቅት የመቃሚያ ቤቶችና የቁማር ቤቶች ላይ የደንቦች እና የፖሊስ አባላት ወደ ድርጅታችሁ ለፍተሻ እንዳይመጡ ላድርግላችሁ እያለ ለአንድ መቃሚያ ቤት 250.000 እና ለቁማር ቤቶች 200.000 ብር፣ ናይት ክለቦችን ደግሞ በክለባቸው ፍተሻ እንዳይካሄድ 200.000 ብር ሲሰበስብ የነበረ መሆኑ ከንግድ ተቋማቱ ባለቤቶች በተገኙ ምስክርነቶች የተረጋገጠበት ዘራፊ ነው።
በተለያዩ ወንጀሎች ተከሰውና ተጠርጥረው ጣቢያ የገቡ ሰዎችን በየጣቢያው በመለመላቸው ደላሎቹ አማካኝነት ወደ ፍርድ ቤት ከመሄዳቸው በፊት ጉዳያችሁ እዚህ እንዲያልቅ ላድርግላችሁ እያለ በፍትህ ሰርአቱ ላይ እየተጫወተ ገንዘብ የሚሰራ ሰው ነው።
የፌደራል ፖሊስ አለቆቹን ለማስደሰት ቦሌ አካባቢ ያሉ ውድ ሆቴሎችን ትብብር አድርጉልን በማለት ከክፍያ ነጻ የሆነ ምግብና መጠጥ ሆቴሎች እያስገደደ ለራሱና ላላቆቹ እንዲያቀርቡ በማድረግ የሆቴል ባልቤቶችን ያስመረረ ግለሰብ ነው።
በአለቆቹ ዘንድ ተቀባይነትንና የማእረግ እድገት እንዲያገኝ፣ የተለያዩ ውድና ትልልቅ ስጦታወችን የሚያቀርብ፣ አለቆቹም ከደሞዙ ጋር የማይመጣጠን ውድ ስጦታ ሲሰጣቸው ከወዴት መጣ ብለው የማይጠይቁት ሰው ነው።
ክወያኔ ጋር ተያይዞ በተደረገው ጦርነት የህግ ማስከበሩን ስራ ሽፋን በማድረግ፣ የህወሃት ቀንደኛ ደጋፊዎች ቤት እንዳይፈተሽ በማድረግ ከግለሰቦቹ ገንዘብና ብር ይቀበል የነበረ፣ ገንዘብ ከሌላቸው የትግራይ ተወላጆች ደግሞ ውድ ማጌጫ ወርቆቻቸውን ሲዘርፍ የነበረ ሰው ነው።
በጦርነቱ ወቅት የኤርፖርት ደህንነት መምሪያ ከነበረው ተስፋየ መኮነን ጋር በመተባበር ተፈላጊና ተጠርጣሪ በሚል የተዘጋጀ የትግራይ ተወላጆች የስም ዝርዝር በመያዝ ከ500.000ሺ እስከ 2,000,000 ሚሊዮን ብር አየተቀበለ ከሀገር ሲያሸሽ ነበር።
በህግ ሊዳኙ የሚገባቸውን ደረቅ ወንጀሎኞችን ቢሮው በማስመጣት መፈታታ እንዲችሉ ሲደራደርና ገንዘብ ሲሰበስብ የሚውል ግለሰብ ነው። በቅርቡ ደግሞ በሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በገዛ ስልጣኑ ያጎራቸውን ጋዜጠኞችን፣ አክቲቪስቶችን ።ገንዘብ ያላቸው መሆኑን በደላሎቹ ተነግሮት እንዲታሰሩ ያደረጋቸው የአማራ ተወላጆች በፖሊስ ጣቢያው በሚገኘው ህንጻ፣ 6ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ቢሮ ውስጥ እያሰጠራ የዘረፋ ስራውን አጣጡፎ ቀጥሏል።
በጥቅም ለተሳሰራቸው ባለሃብቶች፣ የትራፊክ ባለስልጣን ሃላፊነቱን በመጠቀም የአዲስ አበባ ትራፊክ አላነቃንቅ ካላቸው፣ ለትራፊኮች ስልክ በመደወል፣ ትራፊኮቹ ባላሃብቶቹን ልክ እንደ ከፍተኛ የመንግስት ባላስልጣናት፣ ሌላውን ባለሚኪና መንገድ እያስለቀቁና መንገድ እያስከፈቱ እንዲያሳልፉ መመሪያ የሚሰጥ ግለሰብ ነው።
ከእርሱ ጋር ተመሳሳይ ማእረግና ሀላፊነት የነበራቸውን፣ ጠንካራ ለሀገርና ለህዝብ ይወግናሉ፣ በሰራዊቱ ጥሩ ስም ያላቸው እና የሱን ብልሹ አሰራር የሚነቅፉትን አመራሮች በመለየት፣ የሃሰት መረጃ በማቀነባበር ከተባባሪዎቹ ከኮሚሽነር ደመላሽና ከኮሚሽነር መላኩ ፋንታ ጋር በመሆን ግለሰቦችን ለአስርተ አመታት ካገለገሉበት ተቋም ያለምንም ምክንያት ከስራ እንዲታገዱ የሚያደርግ ሰው ነው። ኮሚሽነር ወለታውና ኮሚሽነር ሸዋረጋ በእዚህ ሸር ሰለባ ከሆኑት መሃል መጠቀስ የሚችሉ የፖሊስ መኮንኖች ናቸው።
ከታክስ ጋር በተያያዘ ደረሰኝ ባለመቁረጥ፣ በህግ የታሸጉ የተለያዩ ድርጅቶችን ከህግና ከሚመለከተው የገቢወች ቢሮ እውቅና ውጭ፣ ከበላይ አለቆች ታዝዠ ነው በማለት በመክፈት ገንዘብ የሚሰበስብ ነው።
ረዳት ኮሚሽነር ተከታይ በሚፈጽማቸው ወንጀሎች በህግ እንዲጠየቅ ከማድረግ ይልቅ በአለቆቹ፣ በደመላሽና በዘላለም እንዲሁም በመላኩ ሽልማት ይሁነው ተብሎ ከቦሌ ክፍለ ከተማ ተነስቶ የአ.አ ፖሊስ የወንጀል ትራፊክ አደጋ መከላከል ኦፐሬሽን ዳሬክቶሬት በምክትል ኮሚሽነር ማእረግ የተሾመ ሰው ነው
ወደ ቢሮው የተለያዩ የሲሚንቶና የብረት ነጋዴዎችን በመጥራት ትብብርና ድጋፍ በመጠየቅ፣ ከነጋዴዎች በነጻና በዝቅተኛ ዋጋ የሚያገኘውን ሸቀጥ ለሌላ ነጋዴ በመሸጥ ገንዘብ የሚሰራ በዚህ ድርጊቱ የተማረሩ ቡዙ ነጋዴዎች ሰልክና አድራሻቸውን እስከመቀየር እንዲገደዱ ያደረገ ግለሰብ ነው።
ይህን ሰው በዚህ ወቅትና በዚህ ደረጃ ገበናው እንድናጋልጥ ወደ አደረጉን ምክንያቶች ስንመጣ፣ በአማራ ህዝብ ላይ የአብይ አገዛዝ ያወጀውን የዘር ጥቃት ሰበብ በማድረግ፣ የከተማውን ህዝብ እንዳሻው እየሰበሰበ በየፖሊስ ጣቢያው ከማጎር አልፎ በተለመደው የማስፈራሪያ ስልቱ ከባላሃብቶች ሰፋፊ መጋዘኖቻቸውን እየወሰደ ሰዎችን በገፍ በገዛ ስልጣኑ እያሰረ የሚያሰቃይ፣ ከተሰቃዮቹ እስረኞች የተለመደውን የገንዘብ ቅሚያ ስራንውን አጠናክሮ የቀጠለ ወንጀለኛ መሆኑ ነው።
የአማራ ባላሃብቶችን የአስቸኳይ ጊዜያው አዋጁን ሰበብ በማድረግ ፋኖ መደገፋችሁን የሚያሳይ መረጃ አለን በማለት በመዝረፍ ላይ የሚገኝ፣ አንዳንዶቹም በስጋት ሃገር ጥለው እንዲወጡ በማድረግ ከፍተኛ በደል በህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለ፣ በስርአቱ ድጋፍ የወንጀል ስራውን እንዲቀጥልበት ድጋፍ የተሰጠው አደገኛ ፍጥረት በመሆኑ ነው።
ይህ ወንጀለኛ እሰካሁን የፈጸመው ግፍ አልበቃ ብሎት ተጨማሪ ግፍ መፈጸም የሚችልበትን ተጨማሪ ስልጣን ለማግኘት፣ ባላንበት ወቅት የደረጃና የወንጀል መከላከል ቢሮ ሀላፊ ሆኖ እንዲሾም የበላይ አለቆቹን በመማፀን፣ መደለያና ሰጦታ በመስጠት ለአለቆቹ ቅርበት ያላቸውን ባለሀብቶችን አማላጅ በመላክ ላይ ይገኛል።
ይህ ፍጥረት በህዝብ እንዲታወቅ ማድረጉ ህዝባዊም ሃገራዊ ፋይዳ አለው ብለን እናምናለን። ተዝናንቶ መኖር የለበትም። የሚያየው ዜጋ ሁሉ ወንጀለኛው ኮሚሽነር መጣ በማለት እንዲጠየፈው ማድረግ ያስፈልጋል። ሌላው ቢቀር የፍርድ ቀን እስኪመጣ የሞራል ቅጣት እየተቀጣ ሊኖር ይገባዋል።
ወንጀለኞች ህዝብን እያሰቃዩ፣ ሳይሸማቀቁ የሚኖሩበት ዘመን እንዲያበቃ ተግተን እንታገል። የሌሎችንም ወንጀለኞች ገበና ማጋለጣችንን እንቀጥላለን።
ሁላችሁም ይህን መልእከት በስፋት አሰራጩ !!
