October 2, 2023 – ምንሊክ ሳልሳዊ 

ዶክተር ጫኔ በኢዜማ ውስጥ ያለውን አደርባይነት፣ የስልጣን ሽኩቻና አማራ ጠል ፖለቲካ ማሳያ ነው። ገዢዎቹ የሚያራምዱትን የዘር ፖለቲካ እየደገፈ ስለ ዜግነት ፖለቲካ ሊሰብከን የሚዳዳው ኢዜማ አማራን ፅንፈኛ ብሎ ለመፈረጅ ሞራል የለውም።

ኢዜማ ተንቀዠቀዠ የጤና ያድርግለት ….. ኢዜማ አመራሩን ለመፈረጅ በጣም ተጣደፈ ….. ሰሞኑን በየቲክቶኩ ኢዜማ ስብሰባ ላይ የተቀዱ ድምጾችን ለገዢዎቹ አሳልፈው የሰጡት እነብርሃኑ ነጋ የዶክተር ጫኔን ስም ሲያብጠለጥሉ አይተናል ታዝበናል ። በሃገሪቱ የሕግ የበላይነት እንዳይሰፍን ጋሬጣ ከሆኑ አንዱ ኢዜማ መሆኑን አሳይቶናል። ግለሰቡ ተተርጣሪ ናቸው ተብለው ሲያዙ ንፁህም ሆነው እንደሚገኙ ሊታሰብ ይገባ ነበር መግለጫውን ከመጻፉ በፊት፤ ኢዜማ ጤናማ ያልሆነ የአደርባይነት ፖለቲከ ውስጥ መዘፈቁን የሚያሳይ መግለጫ ነው። ብርሃኑ ነጋ በድርጅታችን ውስጥ ያሉ የአማራ ጽንፈኞችን መንግሥት አይታገስም ማለቱ ለአማሮች አፈና ትልቁን ሚና እየመራ መሆኑ ምስክር ነው። ያሳፍራል !

ይህ የሚያሳየው በኢዜማ ውስጥ ያለውን የስልጣን ሽኩቻና አማራ ጠል ፖለቲካ ነው። ጫኔ ከበደን ጽንፈኛ አማራ ነው ብሎ ያሳፈነው ብርሀኑ ነጋ ነው! ተብሎ መፃፉ ይታወሳል። በተባለው መሰረት ይህንን የሚያጠናክርና የሚያረጋገጥ መግለጫ ከኢዜማ ተሰጥቷል። የኢዜማው ጫኔ ከበደ በዐቢይ አሕመድ ደኅንነቶች የታፈነው ንጹሐን ዘመዶቹ ፋኖን ትደግፋላችኹ ተብለው በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሰሞኑ ስለተገደሉበትና መከላከያ ፋኖን ሳይኾን ሰላማዊ ሰዎችን ከቤታቸው እያወጣና በየመንገዱ እያሳደደ ያለ ፍርድ በጭካኔ እንደሚረሽን በግፍ የተረሸኑ ዘመዶቹን እንደ አብነት በኢዜማ ስራ አስፈጻሚ ስብሰባ ላይ አቅርቦ ዝም ማለት የለብንም በማለቱ መታሰሩ እና ይህንንም የስብሰባውን ድምፅ ለአገዛዙ አካላት በማቀበል አሳፋሪ የፖለቲካ ክህደት የፈጸሙት ብርሃኑ ነጋና ጀሌዎቹ ናቸው። ይህ መግለጫ የሚያሳየው ነገር ቢኖር የአብይ አገዛዝ በአማራ ሕዝብ ላይ የከፈተው ጦርነት በኢዜማ እንደሚደገፍ ነው።

ኢዜማ ከዚህ በኋላ ማንንም ማጭበርበር አይችልም፣ ያፈጠጠውና ያገጠጠው በገዢው አብይ ኦሕዴድ ብልጽግና ሕገወጥና ማንአለብኝነት በተለይ በአማራ ሕዝብ ላይ የከፈተው አጠቃላይ ጦርነት እና የአማራው የሕልውና ትግል ፣ ራስን ከጥፋት መከላከል ፣ አገርና ሕዝቡን ከጥፋት ከውድመት ማዳንና አዲስ ሥርዓት ግንባታ መሆኑን መረዳት ሲገባው፣ ቅራኔና ትግሉ በዜግነት ፖለቲካና በብሔርተኝነት መካከል ነው በማለት ከእውነታው ያፈነገጠና ለአብይ ኦሕዴድ ብልጽግና የተበላሸና የጥፋት አካሄድ ሽፋን ለመስጠት ሞክሯል፣ ብርሃኑ ነጋና ጀሌና መንጋው ሆነ ብሎ አውቆ እንጂ ተጨባጭ ችግሩን ባለመረዳት አይደለም ።

ይኸ አቋም ባለፉት ሶስት አመታት ሲወሰዱ ከነበሩት አቋሞችና ሆነ ተብሎ በስሌት ከተጭበረበረው የኢዜማ የውስጥ አመራር ምርጫ ጋር የተያያዘና ቀጣይ ነው፣

በአጠቃላይ የብርሃኑ ኢዜማ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ወቅታዊ ትግል ውስጥ ክህደትና ሸፍጥ በመፈጸም የተቃዋሚውና የዜግነት ጎራው ፖለቲካ እስከመጨረሻው እንዲዳከም፣ እምነት እንዳይጣልበትና አማራጭ ሆኖ እንዳይቀጥል የሞት ፍርድ የተፈረደበት አካሄድና አቋም የተወሰደበት ነው፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግሉን በራሱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እርዳታና አመራር ውጭ ቀጥሏል፣ ይቀጥላልም ። እስከዛሬ ለመጡት ለውጦች ዋገ ከፍሎ ያመጣቸው ቢሆንም የፖለቲካ ፓርቲ አለመኖርና ክፍተት በዘላቂነት የሥርዓት ለውጥ ተደርጎ መፍትሔዎችም አልተገኙም፣ ቢሆንም የሕዝብ ትግል ይቀጥላል ፣ በመጨረሻም ያሸንፋል ፣ የብርሃኑ የፖለቲካ ኩባንያው የሆነው ኢዜማ መሰሎቹ የክህደት ታሪካቸው ተመዝግቦ በታሪክ ቆሻሻ መዝገብ ውስጥ በመጥፎ አርአያነት መማሪያ ይሆናል ። #MinilikSalsawi