October 3, 2023 

የኢዜማ መግለጫ

በአዳራሽ አምኖ የመረጠውን መሪ አሳልፎ የመስጠት አዲስ ታሪክ!  ( በመንግስቱ ሙሴ )

==========================================

ክቡር አቶ መንግስቱ ሙሴ

ይሁዳ በዚያች ቀን እየሱስ ክርስቶስን ለ 30 ብር ሲል ለማሳየት የሞት ሳም እንደሳመው እና ለገዳዮቹ ማንነቱን እንዳሳየ የሚቆጠር አዲስ ታሪክ

የድርጅቱን ሊቀመንበር ያስያዘ በሚመስል መልኩ እና አስገራሚው ደግሞ ይህን የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ትክክለኛ እርምጃ በሚያደርግ ታስቦ ይህን የተደናበረ ኦነጋዊ እና ፋሽስታዊ መንግስት አስራችሁ አጣሩ የሚል መግለጫ ማየት የባንዳነት ልክ የት ድረስ እንደሄደ አዲስ ተመክሮ እያሳየን ነው።

ከዚህ በፊት የተፈጠሩ አድርባይ የባንዳ ስብስቦች ታሪክ ከዛሬው የኢዜማው በእጅጉ የተሻለ እስኪመስል፤ መሪው የዘር ሀረጉ ዛሬ ጀኖሳይድ የታወጀበት ሕዝብ በመሆኑ ዮሐንስ የተባለው ምክትል ሊቀመንበሩ በአዋጁ መሰረት መንግስት እንዲያጣራ እንደግፋለን የሚል አይን ያወጣ ባንዳነትን ያሳየ እና ዘር ተኮር የሆነውን ሽብር በሚደግፍ ከፋሲል የኔአለም ጋር ቃለምልልስ የሰጠበትን አዳመጥሁ።

“የት ይደርሳል ያለነው ወይፈን ቆዳው ልኳንዳ ደጃፍ ተገኘ” የሚለው የአበው ቃል ኢዜማ ለተባለው የባንዳ ስብስብ አንድ ማሳያ ይሆናል እና ኢዜማ እና መሪው ብርሐኑ ነጋ ይህን ቢያደርግ የሚገርም ባይሆንም ፖለቲካችን የቱን ያህል መዝቀጡን እና መሪ ብለህ በአዳራሽ እጅ አውጥተህ አምነህ የሰየምኸውን ሰው ለአራጅ አሳልፈህ ስትሰጥ ማየት ግን አዲስ መሆኑ ለታሪክ ይመዘገባል። ካለፉት የተማርነው ከዛሬው የተሻለ ሆነ እንድንል እድሜ ሰጦን ዛሬን ያየን ታዝበናል።

ካለፈ የተለየ ስል አዲስ ነገር እያየን ነው ለማለት ነው። በሐገራችን የፖለቲካ ታሪክ አድርባይ የሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶች ተፈጥረው ሽሆችን አስጨርሰው እራሳቸውም በአደሩለት መንግስት ተሰልቅጠው የጠፉ እንደነበሩ የቅርብ ግዜ ታሪካችን ነው በበኩሌ በተአምር የተረፈችው ህይወቴ አሳይታኛለች።

የሰናይ ልኬ ድርጅት ወዝሊግ፤ የባሮ ቱምሳው ኢጨአት፤ ለነዚህ መፈጠር አንጋፋ የነበረው መኢሶን የሚጠቀሱ ናቸው። ለነገሩ አሁን አሁን ሳስበው፤ ኢጨአት፤ መኢሶን፤ ወዝሊግ ሁሉም ኦነጋዊ አስተሳሰብ እንደነበራቸው እውነት ነው። ባሮ ቱምሳ የቀዩ ሽብር ተሳታፊ ከሆነ በሁአላ ኮብልሎ ባሌ በመግባት ያው በራሱ ሰወች መበላቱን ነው የምናውቀው። ሰናይ ልኬ የደርጉ ተራማጅ የነበሩት እና የነጻ እርምጃውን (ፍጅቱን) የተቃወሙትን ከብርጋዴል ጄኔራል ተፈሪ በንቲ እና አለማየሁ ኃይሌን ለማስገደል ላይ ታች ሲል በድንገት ከመቷለቃ ዮሐንስ ጋር ፊት ለፊት ገጥመው እዚያው ቤተመንግስት የተገደለው ሲሆን ገዳዩ የቻለውን አርጎ የጀግና ሞትን ተቀብሏል። የሰናይ ልኬው ድርጅት ወዝሊግ በሁአላ የቀዩሽብር ዋና ተዋናይ ሆኖ ያነን የፍጅት ስራ ከደርጉ ጋር ተሰራ እና የሚችለውን የባንዳነት ተለኮ ከፈጸመ በሁአላ መንጌ ሰናይልኬ የሰየማቸውን መሪወች ጭምር ሰለቀጧቸዋል። የባሮ ቱምሳው ኢጭአት በአንድ ሌሊት ኦነግ ነው የሆነ ልክ እንደ መሪው ባሮ ቱምሳ ከቀዩሽብር በሁአላ እዚህ ገባ ሳይል የማጥፋት ተልእኮውን አድርሶ ተሰውሯል ለዛሬው የኦነጋውያኑ ፋሽስታዊ ተግባራት እርሾ የሆኑትም ያኔ ቀዩን ሽብር ከባሮ ቱምሳ እና ኃይሌ ፊዳ ጋር ያካሄዱት እነ ኦቦ ሌንጮ፤ ገላሳ እና ዳውድ ናቸው። የመኢሶን ታሪክ ያው ከፈረሱ አፍ እንደሚባለው “ዲሞን በዲሞትፈር” ቀይሽብር ይፋፋም” በአንድ የመኢሶን ታጋይ ሞት ሽህ አናርኪስ” በሚሉ መፈክሮች ያነን ፍጅት ከፈጸመ በሁአላ የደርጉ አፎት ወደሱ ዞሮ በአንድ ቀን ጀምበር መጠናቀቁን እውቁ የዚያን ዘመን ባንዳ በመጽሀፉ ሲነግረን በቅርቡ ደግሞ የኃይሌ ፊዳ የምርመራ ውጤት በዚህ በማህበራዊ ሚዲያ ሲዟዟር አግኝተን አንብበናል።

ለማነኛውም የዛሬው የኢዜማው መግለጫም ሆነ ምክትል የተባለው የዮሐንስ አፍ ያሳየን አዲስ የባንዳነት ዳርቻ መሆኑ ወቸው ጉድ አስኝቷል።

የአማራ ሕዝባዊ የሆነው እራስን የመከላከል አመጽ ያቸንፋል!!! ( በመንግስቱ ሙሴ )