ሶስቱ የኢትዮጵያ የድንበር አካባቢዎች ክፍት በመሆናቸው የባእድ ሀይሎች በቀላሉ እየገቡ እንደሆነ ታውቋል:: በምስራቅ አልሻባብ 95 ኪሎሜትር ዘልቆ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ታውቋል:: በምእራብ በጋምቤላ በኩል የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች እስከ 100 ኪሎ ሜትር ዘልቀው በመግባት የተለያዮ የዘረፋና ግድያ ወንጀሎችን እየፈጸሙ እንደሆነ ታውቋል:: ከህወሃት ጋር በነበረው ጦርነት አጋጣሚውን ተጠቅማ የኢትዮጵያን መሬት የወረረችው ሱዳን አሁን ድረስ የኢትዮጵያን መሬት በቁጥጥር ስር አድርጋ ትገኛለች:: የሱዳኑ አልቡራሃን ቀደም ሲል የኢትዮጵያን መሬት የወረርኩት አብይ አህመድ ፈቅዶልኝ ነው ማለታቸው ይታወሳል::
በምስራቅ አልሻባብ የኢትዮጵያ ወታደሮች እያጠቃና ከፍተኛ ኪሳራ እያደረሰ ሲሆን ክፍት ያገኘውን ድንበር ሰተት ብሎ በመግባት ታጣቂዎቹን አስፍሮ እንዳለ ታውቋል:: ድንበር ጠባቂ የነበረውና በሱማሌ ክልል ሰፍሮ የነበረው ሰራዊት ወደ አማራ ክልል መላኩን ተከትሎ አልሻባብ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት 95 ኪሎ ሜትር ዘልቆ ለመግባትና ለመቆጣጠር አስችሎታል:: በተመሳሳይ በጋምቤላ ክልል የነበረው ሰራዊት በአማራ ክልል እየተካሄደ ላለው ጦርነት ግዳጅ ተሰጥቶት በመዝመቱ የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች 100 ኪሜ ዘልቀው በመቆጣጠር በ ኢትዮጵያውያን መንደሮች ላይ የግድያና የዘረፋ ወንጀሎችን እየፈጸሙ ይገኛል::
ኢትዮጵያ ከኬንያ በሚያዋስናት ድንበር ላይ ምንም አይነት የመከላከያ ሰራዊት ባለመኖሩ የኬንያ የቅኝት አውሮፕላኖች ወደ ኢትዮጵያ አየር ክልል ጥሰው መግባት እንደሚችሉ ታውቋል:: ሀርጌሳ ሱማሌ ላንድ የነበረው ስራዊትም ለአማራ ክልል ጦርነት በሚል እንዲነሳ መደረጉ ታውቋል:: በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን ከኤርትራ ከሚያዋስነው ድንበር በስተቀር ሁሉም ክፍት እንደሆነ ታውቋል:: በቤንሻንጉል ክልል የአባይን ግድብ እንዲጠብቅ የተመደበው ሰራዊት አብላጫው ወደ አማራ ክልል መዝመቱ ይታውቃል: ሀገሪቱ ባለቤት የላትም የውጭ ወራሪ መግባት ከፈለገ የሚከለክል የለውም::
በአማራ ህዝብ ላይ ፋሽስቱ በከፈተው ጦርነት ባለፉት አምስት ወራት ከፍተኛ ቁጥር ያለው እግረኛ ሰራዊት መደምሰሱና ማለቁን ያመነው ብርሀኑ ጁላ ከእንግዲህ ወደ አማራ ክልል የምናዘምተው እግረኛ ሰራዊት አይኖረንም ሲል መናገሩ ይታወሳል:: ሆኖም አብይ አህመድ ከተለያዮ ድንበር ላይ ያሉ ሰራዊቱን በማንሳት ወደ አማራ ክልል አሰማርቶ ጦርነቱን ማስቀጠሉ ይታወቃል:: የፋሺስቱ እግረኛ ሰራዊት የደረሰበት ኪስራ ከፍተኛ በመሆኑ ሀገሪቱ የውጭ ወራሪ ሀይል ቢገጥማትየሚታደግ ሰራዊት ላይኖር ይችላል የሚል ስጋት በመከላከያ አመራሩ መካከል እየተስተጋባ ይገኛል:: ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ የገባው የፋሺስት ቡድን በቂ ስልጠና ያልወሰዱ ሚልሻዎችን ለጦርነት ወደ አማራ ክልል ቢልክም እስካሁን ያሰበው ምንም ስይሳካለት እንደቀረ የሚታወቅ ሀቅ ነው::
ምንጭ: አንከር ሚድያ
