October 3, 2023 – Zemedkun Bekele
የጀነራሎቹ መልእክት ነው።

“…ይኸውልህ ዘመዴ ትንሽ ስሙ የሚያስፈራው የሪፐብሊካን ጋርድ ተብዬው ነው አይደል? ተወው ገለባ ነው። ጋርዱ የተሰበሰበው 90% ከጅማ፣ 10% ከዐማራ ነው። ጥቂት ከመንዝ ከሰሜን ሸዋና ብዙ ከሰሜን ጎንደር ከአቢይ ሚስት ከዝናሽ ታያቸው ሰፈር ነው የተመለመሉት። የሪፐብሊካን ጋርድ ሥልጠና የወሰዱት፣ በኩዌት፣ በባህሬን፣ በተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ነው። ሥልጠናቸውም የከተማ ውጊያ ሆኖ የታገተ፣ የታፈነ ሰው ለማስለቀቅ ዓይነት የቅንጦት ሥልጠና ነው። እናም ከፋኖ ጋር ገጥመው መዋጋት አይሆንላቸውም። በትግራዩ ጦርነት ወቅት ታይተዋል። ጡንቻ ብቻ ናቸው። ስናይፐር በ3ሺ ብር ሽጦ የሚጠፋ ነው ሪፐብሊካን ጋርድ።
“…ዘመዴ ወታደሩ አሁን ትናንት እንዳልንህ ተርቧል። ምግቡ ስቃጥላ በብስኩት ነው። ጠዋት ሁለት፣ ምሳ ሦስት፣ ማታ ራቱን ሁለት በስኩት ነው የሚበላው። በፊት የዐማራ ሕዝብ ነበር የሚያበላው፣ ውኃ አትጠጣም ብሎ እርጎና ወተት የሚያጠጣው። አሁን ዐማራ ወታደሩን እንኳን ሊያበላው ገና ሲያይ ደሙ ነው የሚፈላው። እንደ ጣሊያን ጦር ነው የሚመለከተው። ሚስቱን፣ እህቱን ልጁን ደፋሪ፣ ለዐማራ ያለው ጥላቻ መደበቅ የማይችል ክፉ አረመኔ ጭራቅ ስለሆነ ይደፋዋል እንጂ ውኃ አይሰጠውም። እናም ወታደሩ ከሽፏል።
“…በተለይ ጎጃምንና ሸዋ ላይ ከባድ ኦፕሬሽን ይሠራ ተብሎ፣ የደቡብ ልጆችና የኦሮሞ ልዩ ኃይል፣ እንዲሁም በፌደራል ፖሊስ የነበሩት የኦሮሞ ተወላጆች የመከላከያ ልብስ ለብሰው ነው እየሄዱ ያሉት። መከላከያው ገንዘብ የለውም። ተሽከርካሪ መኪኖችም የሉትም። አምቡላንሱ ሳይቀር በትግራዩ እና አሁን በዐማራው፣ በወለጋውም ጦርነት ወድሟል። አምቡላንስ እንኳ የለም። አሁን ከቀይ መስቀል ጋር በሆነ ዘዴ ተነጋግረን ልንቀበል ነው እንጂ ተሽከርካሪ የለም። ነዶ አልቋል።
“…አብዛኛው የመከላከያ ሓላፊዎች ጦሩ እየወደቀ መሆኑን እያዩ ለማኝ እንዳይሆኑ ከወዲሁ ከፋኖ ጋር መሥራቱን ምርጫቸው አድርገዋል። እናም ሃገር እያየን ከምትፈርስ ቢያንስ የፋኖ የውጊያ ብቃት ተገምግሞ ይሄ ኃይል የሀገሪቱ ተጠባባቂ ጦር ሊሆን ስለሚችል ከባድ ዱላ አናበዛበትም የሚል ሃሳብም እየተንሸራሸረ ነው። ይሄ እንግዲህ ሀገር ይፍረስ ከሚለው ኦነጋዊ አስተሳሰብ በተቃራኒው ያለነው አካላት ሃሳብ ነው። ኦነግ ሸኔ የአቢይ እና ሽመልስ ተጠባባቂ ጦር መሆኑ ይታወቃል። ሎጀስቲኩም ከፌደራል መንግሥቱ ካዝና በክልሉ በኩል ነው የሚቀርብለት። እናም እኛም ቢያንስ በግልጽ ባይሆንም የዐማራ ፋኖን ቢያንስ በመሣሪያ፣ በሎጀስቲክ እንዴት መደገፍ እንዳለብን የምንቀራረብ ተነጋግረን ሥራ ጀምረናል። የመከላከያው ተዋጊ ኃይል ሲወጣ አስቀድመን ከነታጠቀው መሳሪያ ጭምር መረጃ በማውጣት መከላከያው እንዲኮላሽ የማድረጉን ሥራም በመሥራት ላይ ነን። ጥቂት ከአገው እና ብዙ ከኦሮሞ የሆኑ እንቅፋት እንደሚሆኑን ብንገነዘብም ሌሎቻችን ኢትዮጵያውያን መኮንኖች ወደፊት እየገፋንበት ነው።
“…ባለፈው አንተ ሽመልስ አብዲሳ ቢያንስ በሳምንት አንድ ቀን ከብርሃኑ ጁላ ቢሮ ይመጣል ብለህ ከጻፍክ ወዲህ ሽመልስ አብዲሳ ብርሃኑ ጁላ ቢሮ ደርሶ አያውቅም። አንተን በደንብ ነው የሚያነቡህ። አብረን እያነበብን እንስቃለን። የአቢይ የአሁኑ የጅማ ጉዞም አልሞትኩም አለሁ ለማለት ያህል እንጂ መሸነፉን ከድምጹና ከተክለ ሰውነቱ ማየት ትችላለህ። የኦሮሞ ፖለቲከኞችና የኦሮሞ ጀነራሎች ከባድ ጥያቄና ግፊት ከኦሮሞ አባገዳና ከኦሮሞ ፖለቲከኞች ጋር በማበር እያጎረፈባቸውም ተቸግረዋል። ለምን እንደ ጁንታው ጊዜ በፋኖ ላይ ግልጽ ቅስቀሳ አይደረግም? ለምን በፓርላማ ፋኖ በአሸባሪነት አይፈረጅም? ለምን ለመከላከያ ሠራዊቱ ስንቅና ድጋፍ አይሰበሰብም። ሙዚቃ ለምን አይሠራም? ለምን የውይይት መድረኮች አይዘጋጁም? ለምን መከላከያውን ግንባር ድረስ ሄዶ ሕዝቡ እንዲበረታታ አይደረግም? ለምን ሚዲያዎች ስለፋኖ ጨፍጫፊነት አይዘግቡም። አቢይን ጨምሮ ባለሥልጣናቱ ኦነግ ሸኔና ጁንታው ላይ በፓርላማ፣ በየመድረኩ፣ በእርሻ ጉብኝትም ላይ ሲደነፉ እንደነበረው ለምን አይተነፍሱም? ዳንኤል ክብረትስ የዛሬው ሌሊት፣ የዛሬው ቀን ሲል እንደነበረው ለፋኖ ምነው ልሳኑ ተዘጋ? ቄሶች፣ ሼኮች፣ ፓስተሮች ለምን አንደበታቸው ተያዘ? ያዋረዳችሁን እናንተ ናችሁ። በ3 ቀን አለቀ፣ ዐማራ ውጊያ አይችልም የተባለ ጦርነት ይኸው መንግሥቱ ሊወድቅ ነው። ፋኖ ሊያሸንፍ ነው፣ ፋኖ ሲመጣ ሌላው ሕዝብ ዝም ይላል እንዴ ብላችሁ በአደባባይ በመጠየቅ መልሳችሁ እኛኑ ትጠይቁ ጀመር። ቆይ ለምንድነው ልክ እንደ ጁንታው ጊዜ ከፌደራል መሥሪያ ቤት፣ ከመከላከያው እና ከመረጃ ደኅንነቱ ሥፍራ ዐማሮቹ እንደትግሬዎቹ የማይገለሉት? በማለት ሰቅዘው ይዘዋቸዋል። ጽንፈኞቹ ያለ ዐማራ ሃገሪቱ ባዶ እንደሆነች አልገባቸውም።
“…ኦሮሙማዎቹ ለጠያቂዎቻቸው ምን እንደመለሱ ባናውቅም፣ ሰሞኑን በግዳጅ ላይ ለነበሩ ጀነራሎችና ኮሎኔሎች ለእያንዳንዳቸው በግ ይሂድላቸው ተብሎ መሄዱን ሰምተናል። እኛም ደርሶናል። በአንድ በግ ደግ ሆነው ለመታየት የሚላላጡ ምስኪኖች እኮ ናቸው። ልብ በል እንደ ትግሬዋ ጁንታ ዐማራም አሁን ዞር ይበል፣ ይገለል ቢባል ስለጦሩ ሁኔታ እንንገርህ። ከመሰረታዊ ወታደር እስከ ሻምበል ድረስ አሁንም ያለው የዐማራ ነገድ 4መቶ ሺ፣ ከሻለቃ እስከ ኮለኔል ወይም መስመራዊ መኮንን ድረስ 2መቶ ሺ ከብርጋዴል ጀነራል እስከ ሙሉ ጀነራል 60 ዐማራዎች አሉ ዘመዴ። የምንጽፍልህ ዋና ዋናዎቹን እንጂ የቢሮ ኃላፊዎች፣ የየዲፓርትመንት ኃላፊዎችን፣ በሀየገሩ ያሉ የሚሊተሪ አታሺዎችን፣ እጅግ ብዙ ጀነራሎች፣ የኮር፣ የክፍለጦር፣ የብርጌድ፣ የሬጅመንት፣ የሻምበል፣ የጋንታ፣ የቲም አዛዦችንም ሳናካትት ማለት ነው።
“…ዕዞችና ምክትሎቻቸውን በከፊል እንመልከት።
1ኛ፥ ማዕከላዊ ዕዝ አዛዥ ሌጀ ዘውዱ በላይ (ሰቆጣ አገው) ማዘዣው ጅማ ለጊዜው ደንቢዶሎና አካባቢው ምክትል አበባው የሚባል (ኦሮሞ)
2ኛ፦ምሥራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌጀ መሐመድ ተሰማ (የወሎ ዐማራ) መቀመጫው ሀረር ምክትሎች ሜጀ ግዛው ኦሮሞ ለጊዜው ሰሜን ሸዋ 1ኮር ይዞ
አሁንም የምስራቅ ዕዝ ምክትል ሜጀ ፍቃዱ
3ኛ፦ ሰሜን ምሥራቅ ዕዝ ዋና አዛዦ ሌጀ አሰፋ ቸኮል (ሰቆጣ አገው) ምክትል ሜጀ ብርሀኑ ጥላሁን (ሰቆጣ አገው) መቀመጫቸው ከአጣዬ እስከ ሰሜን ወሎ ድረስ ኮር አመራሮቹን ተለዋዋጭ ናቸው።
4ኛ፦ ሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌጀ ብርሀኑ በቀለ (ኦሮሞ) ምክትል በቀደም ጎንደር ላይ ለትንሽ ከፋኖዎች ያመለጠው ሜጀ ሙሉዓለም አድማሱ (አገው) ምክትል ሜጀ መሰለ በለጠ (ሰቆጣ አገው) ብጀ ከደቡብ የሆነና ብጀ ማርዬ ከበደ (ዐማራ) መቀመጫቸው ከባሕርዳር እስከ ዳንሻ
5ኛ፦ደቡብ ዕዝ አዛዥ ሌጀ ሰለሞን ኢተፋ (ኦሮሞ) መቀመጫው ሀዋሳ
6ኛ፦ዕዝ አዛዥ ሜጀ ተስፋዬ ወልደማርያም (ደቡብ) ምክትል ሜጀ ነገሪ (ኦሮሞ) መቀመጫው የጎጃም አውራጃዎች
7ኛ፦ኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝአዛዥ ሌጀ ሹማ አብደታ (ኦሮሞ) ምክትሎች ሜል ታገሰ (ደቡብ) ብጀ እሸቱ መንግሥቴ (ኦሮሞ) ብጀ አበባው ሰይድ (ዐማራ) ሌላም ብጀ (ኦሮሞ) መቀመጫቸው የተከፋፈሉ ሰሜንሸዋ፣ እሸቱ አለ የእግረኛ 1ኮር የምሥራቅ ዕዝ አለች።
8ኛ፥መሐንዲስ ዋና መምሪያ ሓላፊ ሌጀ ደስታ አብቼ (ደቡብ) ምክትል ብጀ ያደታ (ኦሮሞ)
9ኛ፦የመከላከያ የሥነልቦና ግንባታ ዋና መሞሪያ ሓላፊ ሜጀ እንዳልካቸው (ኦሮሞ) ምክትሉ ብጀ ኩማ (ኦሮሞ) የመከላከያ ፖሊሲ ጥናትና ምርምር ሓላፊ ብጀ ይታያል (ዐማራ)
“…ይሄ ዘረፋ ደግሞ መከላከያ አዲስ ሰልጣኝ እንዳይቀጥር አድርጓል። ያሉትም ወታደሮች ከመራባቸው የተነሣ ጥቁር ክላሽ በእንጀራ እየቀየሩ ነው። ጥቂት ሳምንታት ብቻ መጠበቅ ነው። አይደለም ወታደሩ የሀገሩ ዜጋ ሁሉ ኑሮ የከበደው ሃገር ለማፍረስ በጀቱ ሁሉ ስለዋለ ነው። ሃገሪቱ በራብና በችጋር፣ በጠኔ ዜጎቿ እየረገፉ ነው። የራበው ሕዝብ እስኪበላን ድረስ እየጠበቅን ነው። የላክንልህ የመሬት ባለቤት ያደረገን ካርታ አቢይ አሕመድ ለሁላችንም ለጄነራሎች የሰጠን የመሬት ካርታ ነው። በፈለከው ሰዓት ይፋ አውጣው። ለአፍ ማስያዣ የተሰጠን ነው። ፋኖ ካልቀደመን በቀር አሁን ዐማራ ክልል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ብለን እንድንገባ ጁላ አዞናል። እኛም እንገባለን ጦሩም ወይ ይሾቃል፣ አልያም መሣሪያውን እንደለመደው አስረክቦ ይወጣል።
“…በመጨረሻም ዘመዴ ዐማራ ክልል የሚፈጸመውን ግፍ አትጥሉት። ትናንት እንደነገርንህ እንኳን በጠላት የሚገደል ሕዝብ ይቅርና ህወሓት ደርግን ለማስጠቆርና የትግሬን ሕዝብ ወደ ትግሉ ለመቀላቀል ሃውዜን ላይ ገበያተኛ አስጨፍጭፋ የለም እንዴ? እናም የአገዛዙን ጭካኔ አትጥሉት። የተኛ ዐማራ ያነቃል። ደግሞም ድሮን ሲመታ ፈራሚው ትግሬው መከላከያ ሚንስትሩ ዶር አብርሃም ነው። እሱ በሉት ሲል ነው ድሮን የሚተኩሰው። ጄል ተስፋዬ አያሌው (ዐማራ) ነው ሙየተኞችን አሰልጥኖ፣ አሰማርቶ፣ ሙያተኞች መረጃ ሰብስበው የጠላት ኃይል ይመታ ሲባል የሚያዘው። ሌላው ሌተናንት ኮለኔል አሸናፊ (ዐማራ) የጂአይኤስ ሙያተኛ ነው ፖይንቱን ለክቶ ጣጣ ጨርሶ ለእነ አበባው ታደሰ፣ ጌታቸው ጉዲና፣ ዶር አብርሃም፣ ተስፋዬ አያሌው የሚያቀርበው ይሄ ሰው ነው። በተለየ ሁኔታ ቅዳሜና እሁድ ነው ውሳኔ የሚተላለፈው። ሁሉንም መዝግቡት። የአንዳንዶቹን ፎቶና ስልክም እንሰጥሃለን። አንተም ደውለህ አነጋግራቸው። በቴሌቭዥን ብቻ አቅርበህ በቴሌግራም ያላቀረብከውን የዳንኤል፣ የአቢይና ዶክተር ዳኛቸው ተጠቃቅሰው ከትግሬዎቹ ላይ የዘረፉትን ግማሽ ቢልዮን ብርም ደግመህ ለሕዝቡ ብትለጥፈው መልካም ነው።
~ በተረፈ አዲስ አበባ ተረጋግተው፣ ነገር ግን ተዘጋጅተው ቢቀመጡ መልካም ነው። ሰሞኑን የሚያከብሩት የኢሬቻ በዓለም እንደፈለጉ አክብረው ይውጡ። በትእግስት ትንኮሳዎችን ሁሉ ያሳልፉ። እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይበቀሎች ሊኖሩ ስለሚችሉ በንቃት፣ ነገር ግን በትእግስት ይለፉት። እኛ እንግዲህ መፈክራችን ኢትዮጵያ ናት። ድል ለኢትዮጵያችን…! ኢትዮጵያ ትቅደም…! በማለት ለዛሬ ተሰናብተውኛል። እኔም…
• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…! በማለት ተሰናብቼአቸዋለሁ።
