October 3, 2023 

የቤት ካርታ ለማውጣት 1.5 ሚልዮን ብር ጉቦ!

  ኤሊያስ መሰረት

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ “የማህበራት ማደራጃ” ሚባል ቢሮ አለ፣ ይህ ቢሮ በክፍለ ከተማው ስር ያሉ የማህበር ቤቶችን ይቆጣጠራል።

እና ላለፋት 3 እና 4 አመታት ኦዲት እያረግን ነው ብለው አገልግሎት አንሰጥም ብለው ቆይተዋል። በነዚህ ጊዜያት ታዲያ ጉቦ እየተቀበሉ በውስጥ አገልግሎት ይሰጣሉ፣ አብዛኛው ህዝብ ግን ገንዘብ መክፈል ስለማይችል እየተሰቃየ ይገኛል።

በደረሰኝ መረጃ መሰረት ኦዲቱ ካለቀ ቆይቷል፣ ነገር ግን የሚያስከፍሉት ብር እዳይቀርባቸው የብዙ ሺህ ቤቶች ዶክመንት ቆልፈው ቁጭ አርገዋል።

ህዝብ ሲጠይቃቸው “እንጀምራለን” እያሉ አመት ሊሞላቸው ነው። አሁን ላይ ካርታ ለማውጣት እንኳን ጉቦ እስከ 1.5 ሚልዮን ብር እየጠየቁ ነው። ተገልጋይ ግብር ልክፈል ሲል ደሞ ኦዲት ካላለፈ አናስከፍልም ነው መልሳቸው።

እርምት ለማድረግ የሚፈልግ የመስተዳድሩ አካል ካለ መረጃው ይኸው። ኤሊያስ መሰረት