October 5, 2023 

በመላው አለም የምንገኝ ኢትዮጵያውን ሁሉ በአማራ ህዝብ ላይ የተከፈተውን ሌላ ዙር ጦርነትና አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ለማክሸፍ ሁላችንም በጋራ እንቁም፣እንታገል፣ እንመክት!! ትግሉን በሁሉም መንገድና በሁሉም አካባቢዎች ማቀጣጠል ወቅቱ አሁን ነው!!( ነዓመን ዘለቀ )

ከሃዲውና ፋሽስቱ አብይ አህመድ በአማራ ህዝብ ላይ የከፈተውን ፍትሃዊ ያልሆነ ጦርነት ለማሸነፍ ከልዩ ልዩ እዞች መጠነ ስፊ ስራዊት በመውሰድ ወደ አማራ ክልል ማስገባቱን የተለያዩ የመረጃ ምንጮች ይፋ አድርገዋል። በ15 ቀን ውስጥ ፋኖን ትጥቅ አስፈታለው ብሎ አማራ ክልልን የወረረው በብርሃኑ ጁላ የሚመራው የአብይ አህመድ ሰራዊት ስድስት ወራት ቢያስቆጥርም በአብዛኛው የአማራ ክልል አካባቢዎች በፋኖ ህዝባዊ ሃይሎች ከባድ ኪሳራና ሽንፈቶች ሲድርስበት ቆይቶአል። ከዚህ መራር የሽንፈት ጽዋ ምንም ትምህርት መውሰድ ያልቻሉት አብይ አህመድ፣ ብርሃኑ ጁላና የጦር አበጋዞቹ አዲስ እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ብዛት ያላቸው የመደበኛና የክልል ሃይሎች ክፍለ ጦርች ወደ ክልሉ እያስገባ ነው።

እንደ አዲስ የነደፉት እቅድ ዋና ዋና ግቦችም

1ኛ የአማራን ክልል ስልክ፣ መብራት፣ ውሃ፣ ህክምና፣ የባንክና ሌሎች አገልግሎቶች በመቁረጥ ህዝቡን በከባባ ውስጥ ማስገባት

2ኛ የገበሬውን ሰብል ማውደም፣ በስነ ልቦና እንዲሁም በኢኮኖሚ ማድቀቅ፣ እንዳይነሳ እድርጎ የህዝብ ቅስም መስበር፣ ማንበርክክ፣

3ኛ፣ ህዝቡን ከፋኖ ህዝባዊ ሃይል መነጠል ፣ የፋኖን መሪዎች መግደል፣ መያዝና ማወረድ፣ መቀጣጫ ማድረግ፣ ፋኖ ህዝባዊ ሃይል መደምሰስ ዋና ዋናዎቹ ናቸው

በቀቢጸ ተስፋና በጀብደኝነት ህሊናውና አእምሮው የተጋረደው ጀብደኛ ፋሽስቱ አብይ አህመድ ፈጽሞ ሊገለጽለትና ሊቀበለው ያልቻለው እንድ ሃቅ ፋኖ ህዝባዊ ሃይል ለማሸነፍ የሚያስችል በቅድሚያ ሞራልና የሚዋጋበት አላማ ጥራት የሌው 2ኛ በአመዛኙ አቅም፣ ብልህት፣ ወታደራዊ ብቃት በሌላቸው በዘረፋ ላይ በተጠመዱ አዛዦች የሚመራ ስራዊት የአማራን ህዝብ ማንበርከክ እይችልም። በመገፋት፣ በተደጋጋሚ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ፣ መፈናቀል፣መዋረድ፣ መዋቅራዊ ባህላዊ ጭቆና፣ መገለልና፣ መገፋት የበገነውን የአማራ ህዝብ ቅስም ከቶውኑ ሊሰብር አይችልም።

ባለፉት ስድስት ወራት የገባው ስራዊት በፋኖ ህዝባዊ ሃይሎች ሽንፈቶችን በተከናነበ ቁጥር በሸዋ ሮቢት፣ በደብረ ብርሃን፣ በማጀቴ፣ በደብረ ማርቆስ፣ በፍኖተ ሰላም በመቶዎች ንጽሃን ዜጎችን በዶሮን በመጨፍጨፍ እጅግ አሰቃቂ የጦር ወንጀሎች ፈጽሞአል፣ በልዩ ልዩ አካባቢዎች ሴቶች፣ ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ ጨምሮ ተደፍረዋል፣ ማሳቸው ላይ የነበሩ ገበሬዎችን በስለት በመቆራረጥ እጅግ አረመኔያዊ በሆነ ሁኔታ ገድልዋል፣ ከተሞችንና የገበሬ ማሳዎችን በከባድ መሳሪያ አውድመዋል፣ ወጣቶችን የፊጥኝ የኋላ አስረው ረሽነዋል።

እነዚህ ሁሉ አረሜኔያዊ እርምጃዎች ያመጡት ውጤት በተቃራኒው መሆንን በስፋት ታዝበናል። የአማራን ህዝብ ይብሱኑ እስቆጥቶና አነሳስቶ፣ በአስርቱ ሺ የሚቆጠሩ ወጣቶች ፋኖን እንዲቀላቀሉ እድርጎአል። ፋኖ ህዝባዊ ሃይሎች በአጭር ግዜ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ እንዲጠናከሩ ዋና ምክነያት ሆኖአል። አሁንም እንደ ትላንቱ ፋሽስቱ አብይና አስፈጻሚው ብርሃኑ ጁላ ይህንኑ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ በስፋት በመፈጸም፣ ከዚያም አልፎ፣ የክልሉን ህዝብ መብራት፣ውሃ፣ ህክምና ፣ እንዳያገኝ በማድረግ ህዝብን ለማንበርከክ በእጥፍ ድርብ መከራ በህዝብ ላይ ለማድረስ ቆርጠዋል።

ነገር ግን በቀቢጸ ተስፋ አለም/ዲሉዥን ውስጥ የሚኖረው ፋሽስቱ አብይ አህመድ ፈጽሞ ሊገለጽለትና ሊቀበለው ያልቻለው ሌላው ሃቅ ፋኖ ህዝባዊ ሃይልን ለማሸነፍ የሚያስችል አቅሙም፣ ብልሃቱም፣ ወታደራዊ ብቃቱም የለውም። እንኳን በብርሃኑ ጁላና መሰሎቹ የሚመራው ስራዊት ቀርቶ እነ ፊልድ ማርሻል ሮሜል፣ ሞትጎሞሪና ዙኮቭ መሰል ወታደራዊ ጄኒዎች ቢመጡም ፣ በተደራራቢ ግፍና ፣ ጭፍጨፋ የበገነውን የአማራ ሰፊ ህዝብ ሙሉ በሙሉ የሚደገፍ የህዝብ አመጽ ትግል ማንበርከክ የሚቻልበት ሁኔታ በእጅጉ የተመናመነ ነው። በአለም ዙሪያ ህያላኑን ጨምሮ ሞክረው ከሽፎአል። በህዝብ ውስጥ ያለና ህዝብ በሰፊው የሚደግፈውን ፍትሃዊ የአመጽ ትግል ማንበርከክ ስላልቻሉ በእነዚህ ሀገሮች ሽንፈጥና በውርደት ተጠናቆአል። ዛሬም በኢትዮጵያ የአብይ እህመድ የመጨረሻ እድሉን ለመሞከር በአማራ በህዝብ ላይ ያስመራው ሰፊ ስራዊት የሚዋጋበት አላማ የሌላው ፣ በግፍና በጭካኔ የሚራመድ ኢፍቲሃዊ ጦርነት በመሆኑ መሸነፉ እይቀሬ ነው። የአገዛዙ የመጨረሻው መጀመሪያ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም።

በመሆኑም መላው የአማራ ህዝብ ፣ በሀገር ውስጥም በውጭው አለም የምንገኝ መላው ሀገር ወዳድ የኢትዮጵያን ዜጎች ሁሉ የአብይ አህመድን ፋሽታዊ ወረራ ንጹሃንን የአማራ ክልል ዜጎች ለመጨፍጨፍና ህዝቡን ለከፋ መከራ ለመዳረግ እየወሰደ ያለውን እርምጃዎች አጥብቅን በማውገዝ፣ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ እለት በእለት በማጋለጥ አበክረን እንስራ። ከዚያም አልፎ በሚቻለውና በተገኘው መንገድና አጋጣሚ ሁሉ በሀገር ውስጥ ትግሉን በልዩ ልዩ መንገዶች በማቀጣጠል የአማራ ህዝብ ለህልውናው የሚያደርገውን ፍትሃዊ ትግል ጎን መሰለፍ፣ ወረራውን ፣ ጭፍጨፋውን ለማክሸፍ በጋራ እንቁም ። በዲያስፓራ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ልዩነቶችን ወደ ጎን አድርገን ጦርነት በታወጀበት የአማራ ህዝብ ጎን በመሰለፍ ሁሉንም አይነት የትግል ስልቶች ተግባራዊ ለማድረግ እንተባበር። ሰአቱ አሁን ነው። ይህን ግፈኛ፣ ነውረኛ፣ ዘራፊና ዘረኛ የአብይ አህመድ አገዛዝ ለማስወገድ ትግሉ በሁሉም መልኩ መቀጣጠል ያለበት ወቅት አሁን ነው።

ፍትህ፣ ደህነንት፣ ነጻነት፣ እኩልነት፣ የህግ የበላይነት ለአማራ ህዝብ! ፍትህ፣ ደህንነት፣ ነጻነት፣ እኩልነት፣ የህግ የበላይነት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ድል ለፋኖ ህዝባዊ ሃይል፣ ድል ለአማራ ህዝብ!! ( ነዓመን ዘለቀ )