October 5, 2023 – Abebe Bersamo

የአብይ አህመድ ኤትኖ ፋሺስቱ የኦሮሞ ብልጽግና አገዛዝ፣ በአማራው ላይ በይፋ ጦርነት የከፈተው ሚያዚያ 20 ቀን 2015 ዓ/ም ነበር፡፡ አምስት ወራት አለፉት፡፡ ብርሃኑ ጁላ፣ “አማራዉን ትጥቁን ብቻ ሳይሆን ሱሬዉን እናስፈታለን” ፣ አበባው ታደሰ ደግሞ ፣ “ህወሃትን ልክ እንዳስገባን እነርሱንም (ፋኖዎች) ልክ እናገባቸዋለን” ነበር ያሉት፡፡ አለቃቸው አብይ አህመድን፣ “አማራዉን ትጥቅ ለማስፈታት የሚፈለገውን መስዋትነት ሁሉ ይከፈላል” ሲልም ነበር የዛተው፡፡ ሰዎቹ ጦርነት ሲከፍቱ፣ “የአማራው ማህበረሰብ በቀላሉ እጁን ይሰጣል፣ በሶስት ሳምንት ውስጥ ትጥቁን እናስፈትዋለን፣ የፋኖ መሪዎችን እንገድላለን ወይንም እናስራለን’ ብለው በመደምደም ነበር፡፡
ወደዚህ ድምዳሜ የደረሱትበ ዋና ምክንያት በዋናነት፣ ላለፉት 5 አመታት፣ ህዝቡ መከራና ስቃይ ሲፈጸምባት፣ ለአገርና ለሰላም ሲል በመታገሱ፣ የህዝቡን ትእግስት እንደ ፈሪነት፣ የህዝቡን ለአገር አሳቢነት እንደ ደካማነት በመቁጠራቸውና በህዝቡ፣ “ከወሬና ከጩከት በቀር ምንም አያደርገም” በሚል ትልቅ ንቀት ስለበራቸው ነው፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ከኮረም፣ አላማጣም፣ ከአላማጣ ቆቦ፣ ከቆቦ ወሊድያ፣ ከወልዲያ ደሴ፣ ከደሴ ደብረ ሲና እያለ ሲያራውጧቸው የነበሩትን ህወሃቶች፣ የአማራ ኃይሎች ማስቆም እንደቻለ መርሳታቸውና ፣ እነርሱም ራሳቸው “እኛ አቅቶናል፡፡ በመደበኛ ሰራዊት የመጣውን አደጋ መከላከል አንችልም” ብሎእው የአማራ ኃይሎች ሲማጸኑ እንደነበረ መዘነጋታቸው ነው፡፡
ከሚያዚየ 20 ቀን እስከ ሐምሌ 20 ቀን ድረስ የአማራ ኃይሎች ራሳቸውን በመከላከል ላይ ነበር ያተኮሩት፡፡ ከሐምሌ 20 እስከ ሐምሌ 28 ባሉት ስምንት ቀናት ውስጥ ፋኖዎች የመጀመሪያዉን የማጥቃት ዘመቻ ከፈቱ፡፡ ከደሴ አካባቢ፣ ከምንጃር ፣ ከኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን ፣ ከአዊ ዞንና ከዋገመራ ውጭ ያለውን የአማራ ብልጽግና መዋቅር ሙሉ ለሙሉ አፈረሱ፡፡ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ድ ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ማርቆስ እያሉ ከ46 በላይ ከተሞች፣ ከ187 በላይ ወረዳዎችን ተቆጣጠሩ፡፡ መቅጣት ያለባቸውን ቀጥተው፣ ከወህኒ ማስፈታት ያለባቸውን አስፈትተው፣ አገዛዙ ፊት ለፊት ከመዋጋት ይልቅ ከሩቅ ሆኖ፣ ሃላፊነት በሌለው መልኩ፣ ከባባድ መሳሪያዎች ስለሚተኩስ፣ ህዝብን ለማዳን፣ ቅርሶችን ለመጠበቅ፣ ከትላልቅ ከተሞች፣ ለቀው ወጡ፡፡
የአገዛዙ ሰዎች ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ/ም፣ ሁለተኛው ዙር ጦርነት አወጁ፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያሉት ማለት ነው፡፣”ዘራፊዎች” ያላቸውን ፋኖዎችን እንደመስሳለን ብለው እንደገና ዛቱ ፡፡ ፋኖዎች በፍቃዳቸው ፣ ለቀው የወጡትን ከተሞች አስለቀቅን ብለው ፎከሩ፣ ደነፉ፡፡ “አህያውን ፈርቶ ዳዉላውን” እንደሚሉ፣ የፋኖ ኃይልን መቋቋም ሲያቅታቸው፡ እንደለመዱት በንጹሃን ላይ፣ በማጀቴ እንዳደረጉት ነጻ እርምጃዎችንና ጅምላ ግድያዎችን፣ በፍኖተ ሰላም እንዳደረጉ በድሮን ጥቃት ሰላማዊ ዜጎች ጭፍጨፋዎችን በማድረግ የጦር ወንጀሎችን ፈጸሙ፡፡ ጦርነት በሌለበት፣ በአዲስ አበባና በበርካታ ቦታዎች፣ በሰላም የሚኖሩትን፣ በመቶ ሺሆች፣ አማራ በመሆናቸው ብቻ፣ ፋኖን ደጋፋችሁ እያሉ ማሰር ጀመሩ፡፡
መስከረም 3 ቀን 2016 ዓ/ም ፋኖዎች ሁለተኛ ዙር የማጥቃት ዘመቻ ጀመሩ፡፡ በምንጃር፣ በአዊ ዞን የብልጽግና መዋቅር እንዲፈርስ ተደረገ፡፡ በደሴ አካባቢ የነበሩ የብልጽግና አመራሮች መሸሽ ጀመሩ፡፡ በደሴ ዙሪያ በሃይቅና በኩታበር ፣ በአቃስታ መስመር፣ የፋኖ እንቅስቃሴ እያየለ መጣ፡፡ ደሴ በፋኖ እይታ ውስጥ ወደቀች፡፡ በተቀረው የአማራ ክልል ተበታትኖ ያለውን የብልጽግና ጦር መልቀም በተጣነከረ መልኩ ቀጠለ፡፡
የዓለም አቀፍ ማሀብረሰብ፣ “ፋኖን ማሸነፍ አትችልም፣ ተደራደር፣ የሽግግር መንግስት ይቋቋም” በሚል ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዎ ጫና እያሳደሩ በመሆናቸው፣ አገዛዙ የመጨረሻ እስትንፋሱን በመጠቀም፣ ሶስተኛ ዙር ዘመቻ አውጇል:: መስከረም 20 ቀን 2016 ዓ/ም፡፡ የመስከረም ዘመቻ የሚባል፡፡ መስከረም ሳይጠናቀቅ፣ በአስር ቀናት ውስጥ የአማራ ኃይሎችን ኃይል ለማንበርከክ፡፡
አልበርት አነስታይን አንድ የተናገረው ነገር አለ፡፡ አንድን ነገር እየደጋገምን በማድረግ የተለየ ነገር መጠበቅ እብደት ወይንም ድንቁርና ነው የሚል፡፡ አብይ አህመድና ጨቅላ ጀነራሎቹ፣ መጀምሪያ ሚያዚያ 20 ቀን 2015 ዓ/ም፣ ለሁለተኛ ጊዜ ሐምሌ 28 2015 ዓ/ም ካወጁት ዘመቻ የአሁኑ በምንድን ነው የሚለው ? ያኔ ያላቸውን ከባባድ መሳሪያዎች ሁሉ ፣ ድሮን፣ ታንክ፣ ዲሽቃ ወዘተ ተጠቅመዋል፡፡ ያኔ ኤሊት፣ ወይም ምርጥ ጦር ያሉትን፣ ኮማንዶዎቻቸውን፣ ሬፓብሊካን ጋርዶቻቸው ተጠቅመዋል፡፡ ያኔ ያላሳኩትን ታዲያ አሁን እናሰካለን ማለት ድንቁርናና እብደት ካልሆነ ምንድን ነው ሊባል የሚችለው ?
ድንቁርናና እብደት ብቻም አይደለም እኔ የምለው፡፡ እጅግ በጣም ትልቅ ጭካኔም ነው፡፡ ላለፉት አምስት ወራት በተደረገው ጦርነት፣ አገዛዙ ከሁለት መቶ ሺህ በላይ ሰራዊት አባላቱን አጥቷል፡፡ ጦርነቱን እንደማያሸንፉ እየታወቀ፣ በመደበኛ ሰራዊት አባላት ያልቻሉትን፣ ሚሊሺያዎችን እየሰበሰቡ፣ ወጣቶችን በበዛት ከኦሮሞ ክልል እያፈሱ፣ ለሶስት ወራት እያሰለጠኑ፣ የመከላከያ ዩኒፎርም እያለበሱ ለውጊያ መልክላቸው፣ በነዚህ ወጣቶች ላይ የሞት ፍርድ እንደማወጅ ነው፡፡
የኦሮሞ ብልጽግና አገዛዝ እስከ አፍንጫው የታጠቀ ነው፡፡ የአንድ ትልቅ አገር ባጀት የተቆጣጠረ ነው፡፡ ቢሊዮኖች ብር አለው፡፡ ብዙ ሜዲያዎችን፣ ኢቢሲ፣ ፋና፣ ዋላታ እየተጠቀመ ነው፡፡ ብዙ ከፍሎ ያሰማራቸው ዲጂታል ብልጽግናዎች አሉት፡፡ በሁሉም ምነገር የበላይነት አለው፡፡ ታዲያ ለምንድን ነው አገዛዙ እየተሸነፈ ያለው ? በዚህ ዙሪያ ረጅም ትንታኔ መስጠት ይችላል፡፡ ለዛሬ ይሄን ልበል፡፡
ዳዊትና ጎልያድ በውጫዊ አካላቸው አይወዳደሩም፡፡ ዳዊት ግን ጎልያድን ገነደሰው፡፡ ለምን እግዚአብሄር ከዳዊት ጋር ስለነበረ፡፡
“ማኔ ቴቄል ፋሬስ” እንደተባለው፣ አሁንም የኦህዴድ አገዛዝ በእግዚአብሄር ዘንድ ተመዝኖ ስለቀለለ፣ እግዚአብሄር መንግስታቸውን ስለቀደደው፣ ብልጽግናዎች የሚያደርጉት ነገር ሁሉ አይሳካላቸውም፡፡ በህዝብ የተጠሉ በመሆናቸውም፣ ለነርሱ ከልቡ የሚዋጋ የለም፡፡ እርስ በርሳችውም ቋንቋቸው ተደበላልቋል፡፡
በአንጻሩ ደግሞ የተናቁትን የሚያነሳ፣ ግፍን የሚጸየፍ አምላክ፣ የሰፈር ጎሮሞሶች የተባሉት፣ በክፉዎች ላይ በትር እንዲሆኑ አስነሳቸው፡፡ ምንም እንኳን ጎልያድ በጉልበት የበረታ ቢሆንም፣ ምን እንኳን የብልጽኛ ጦር በምሳሪያ፣ በገንዘብ ወዘተ ጉልበት ቢኖረውም፣ አትጠራጥሩ ጎልያድ ይገነደሳል !!!!
