እናት ፓርቲ

  · 

አስቸኳይ መፍትሔ የሚሻ መረጃ ስለመስጠት!

******

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን አቤ ደንጎሮ ወረዳ ልዩ ስሙ ሎሚጫ ቀበሌ “የአገር መከላከያ ሠራዊት ዩኒፎርም የለበሱ ናቸው” በተባሉ ታጣቂዋች ከማክሰኞ መስከረም ፳፪ ቀን ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጥቃት መከፈቱንና ይኸው ጥቃት እስከዛሬ ድረስ እንደ ቀጠለ ፓርቲያችን ከአካባቢው ነዋሪዎች ለመረዳት ችሏል። የአገር መከላከያ ሠራዊት በጉዳዩ ላይ ማጣራት እንዲያደርግና በነዋሪዎች ላይ የተሰነዘረው ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆም እናሳስባለን።

እናት ፓርቲ

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

መስከረም ፳፬/፳፻፲፮ ዓ.ም

May be a graphic of button, timer, thermostat, stethoscope, ointment, poster and text