https://www.bbc.com/amharic/live/67042690
ጭምቅ ሃሳብ
- እስራኤል በሊባኖስ ላይ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት ፈጸመች
- የእስራኤል ጦር በሃማስ ላይ ለሚሰነዘረው የአጸፋ ጥቃት በጋዛ ሰርጥ የሚኖሩ ነዋሪዎች ቤታቸውን ለቀው እንዲለቁ ጠየቀ
- ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ “ጥቁር ቀን” ብለው ለጠሩት ጥቃትም ምላሽ በፍልስጥኤም ታጣቂዎች ላይ “ከፍተኛ የበቀል እርምጃ” እንደሚወስዱ አስጠንቅቀዋል።
- በግብጽ ሁለት እስራኤላውያን ቱሪስቶች በተተኮሰባቸው ጥይት ተገደሉ
- የፍልስጥኤም ታጣቂ ቡድን ሃማስ ያልተጠበቀ የተባለውን ከሁለት ሺህ በላይ ሮኬቶችን በእስራኤል ላይ ተኩሰዋል።
- በጥቃቱ 250 ሰዎች ሲገደሉ በርካታ እስራኤል ታግተዋል ተብሏል።
- እስራኤል በምላሹ ተከታታይ የአየር ጥቃቶችን በጋዛ ላይ የፈጸመች ሲሆን በዚህም ከ230 ሰዎች በላይ ተገድለዋል።
- እስራኤል የጋዛን መሰረታዊ አገልግሎቶች ታቋርጣለች- ኔታንያሁ
- የሃማስ ታጣቂዎች በእስራኤል ውስጥ ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ነው አሉ
- 313 ፍልስጥኤማውያን እና 300 እስራኤላውያን መገደላቸው ተነገረ
ቀጥታ ዘገባ
- የታተመዉ 8:158:15ሰበርየተገደሉ እስራኤላውያን ቁጥር ከ500 በላይ መድረሱ ተነገረ
ReutersCopyright: Reutersየሃማስ ታጣቂዎች ቅዳሜ ዕለት በከፈቱት ጥቃት የሞቱ እስራኤላውያን ቁጥር ከ500 በላይ መድረሱን የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።ዘገባዎቹ አክለውም 2 ሺህ ሰዎች መቁሰላቸውን ሪፖርት አድርገዋል።
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 6:566:56በእስራኤል ጦር እና በሐማስ ታጣቂዎች መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች እንደቀጠሉ ነው
AFPCopyright: AFPእስራኤል ጦር እና በሐማስ ታጣቂዎች መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች በደቡባዊ እስራኤል መቀጠላቸውን የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።የእስራኤል ጦር በርካታ የደቡባዊ አካባቢዎችን መልሶ መቆጣጠሩን ሃሬትዝ የተሰኘው ሚዲያ የእስራኤልን ጦር ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።ነገር ግን ቤይሪ እና ስዴሮት የተባሉ ግዛቶችን ጨምሮ በጋዛ ድንበር አቅራቢያ ባሉ አካባቢዎች ውጊያዎች ቀጥለዋል ብሏል።በደቡባዊ እስራኤል እና በጋዛ ሰርጥ ከ400 በላይ የፍልስጥኤም ታጣቂዎች መገደላቸውን እንዲሁም በርካቶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የእስራኤል መከላከያ ኃይል ቃለ አቀባይን ዋቢ አድርጎ ታይምስ ኦፍ እስራኤል ዘግቧል።የእስራኤል ባለስልጣናት ሃገሪቱ “አሁንም በጦርነት ላይ ነች። የእስራኤልን ግዛት እና ማህበረሰቦችን ከሃማስ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የምታደርገውን ጥረት በማጠናቀቅ ላይ ናት” ብለዋል።
BBCCopyright: BBCዩናይትድ ኪንግደም ጄክ ማርሎዌ የተሰኘ ዜጋዋ መጥፋቱን እስራኤል በሚገኘው ኤምባሲዋ በኩል አስታውቃለች።በጋዛ ድንበር አቅራቢያ በነበረ የዳንስ ፌስቲቫል ላይ ጥቃት በተፈጸመበት ወቅት የደህንነት ስራ እየሰራ ነበር ተብሏል።እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ በፈጸመችው ተከታታይ የአየር ጥቃቶች ቢያንስ 313 መገደላቸውን የፍልስጥኤም ባለስልጣናት ተናግረዋል።እስካሁን ቢያንስ 300 እስራኤላውያን መገደላቸውን እንዲሁም በርካቶች መታገታቸውን የእስራኤልን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዋቢ አድርጎ በቱርክ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ ገልጿል።
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 6:146:14ሰበርበግብጽ ሁለት እስራኤላውያን ቱሪስቶች በተተኮሰባቸው ጥይት ተገደሉ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesበግብጽ አሌክሳንድሪያ ከተማ ሁለት እስራኤላውያን ቱሪስቶች እና ግብጻዊ አስጎብኛቸው በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸውን የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።አንድ ፖሊስ በከተማዋ በነበሩ የእስራኤል ቱሪስቶች ላይ ተኩስ ከፍቷል ተብሏል። ፖሊሱ በእስር ላይ እንደሚገኝም ዘገባዎች ጠቁመዋል።በዚህ ጥቃት አንድ ግለሰብ እንደቆሰለም ኤክስትራ ኒውስ የተሰኘው የቴሌቪዥን ጣቢያ ማንነታቸው ያልተገለጸ የደህንነት ኃላፊዎችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።በግብፅ በእስራኤላውያን ላይ እንዲህ አይነት ጥቃት ሲከፈት ከአስር ዓመታት በኋላ የመጀመሪያው እንደሆነም ተነግሯል።
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 4:534:53በቀጣይ ምን ሊፈጠር ይችላል?
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesሃማስ “እስራኤል በወረራ ከያዘቻቸው ግዛቶች ለመጠራረግ” ፍልስጥኤማውያን እንዲሁም ሌሎች አረቦች ትግሉን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል።ትልቅ ጥያቄ የሚሆነው በእስራኤል በወረራ በተያዘችው ዌስት ባንክ፣ ምስራቅ ኢየሩሳሌም ወይም በሌሎች አካባቢዎች ያሉ ፍልስጥኤማውያን ጥሪውን ይቀበሉታል የሚለው ነው።እስራኤል ያለ ጥርጥር በበርካታ ግንባሮች ሊከፈት የሚችል ጦርነት ሊኖር እንደሚችል ነው እየታያት ኣለው። ምናልባትም ጦርነቱ የከፋ የሚሆነው ከፍተኛ ኃይል ያለውን የሊባኖሱን ታጣቂ ቡድን ሂዝቦላ መሳብ ከቻለ ነው።ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስራኤል ጦር ከፍተኛ በሆነ ሁኔታ ወታደሮቹን ማሰማራት ይዟል። በተጨማሪም በጋዛ ላይ ተከታታይ የከፉ የአየር ጥቃቶችን ከማድረግ በተጨማሪ የምድር ላይ ዘመቻ ለማድረግ ማቀዱን አመልክቷል።
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 4:054:05ሰበር313 ፍልስጥኤማውያን እና 300 እስራኤላውያን መገደላቸው ተነገረ
ReutersCopyright: Reutersእስራኤል በጋዛ እየፈጸመችው ባለው አጸፋዊ የአየር ጥቃቶች 313 ፍልስጥኤማውያን መገደላቸውን የፍልስጥኤም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።ሚኒስቴሩ 2 ሺህ ሰው መቁሰላቸውንም አክሎ ገልጿል።ከእስራኤል በኩል ደግሞ ቢያንስ 300 እስራኤል መገደላቸውን በቱርክ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ አስታውቋል።ኤምባሲው የእስራኤልን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርን ዋቢ አድርጎ ባወጣው መረጃ በርካቶች ታግተዋል ብሏል።በተጨማሪም ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ቆስለው በሆስፒታሎች ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን መግለጫው ጠቅሶ ከእነዚህም ውስጥ 19ቱ በአስጊ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ብሏል።አኃዙን በተመለከተ የእስራኤል መንግሥት በይፋ አላረጋገጠም።
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 3:273:27የሃማስ ታጣቂዎች በእስራኤል ውስጥ ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ነው አሉ
AHMED ZAKOT/ REUTERSCopyright: AHMED ZAKOT/ REUTERSየእስራኤል ጦር በስምንት ስፍራዎች ላይ የሃማስ ታጣቂዎች መኖራቸውን ገልጾ ቦታዎቹን “ከአሸባሪዎች ለማጽዳት” ጥረት እያደረግኩ ነው ብሏል።እስራኤል ጦሯ ከሃማስ ታጣቂዎች ጋር ውጊያ እንዳለ ባትገልጽም ሃማስ በበኩሉ በእስራኤል ውስጥ “ከባድ ውጊያ” እያደረጉ እንደሆነ ተናግሯል።እስራኤል በጠቀሰቻቸው ስምንት ቦታዎች ላይ እየተከናወኑ ያሉ ሁኔታዎች በትክክል አይታወቅም።እስራኤል የሃማስ ታጣቂዎች አሉባቸው ያለቻቸው ስፍራዎች ስዴሮት፣ ያኪኒ፣ ክፋር አዛ፣ ሱፋ፣ ቤአሪ፣ ኪቡትዝ፣ ኪሱፊም፣ ‘ሆም ፍሮንት ኮማንድ’ የተሰኙ ናቸው።
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 3:003:00ሰበርእስራኤል ግዛቴን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር እየሞከርኩ ነው አለች
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesእስራኤል በሃማስ የደረሰውን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ የፍልስጥኤም ታጣቂዎች ሰርገው የገቡባቸው ስምንት አካባቢዎች ነጻ ለማድረግ እየሞከርኩ ነው አለች።በዛሬው ዕለት የእስራኤል መከላከያ ኃይል ቃለ አቀባይ ኤልት ኮል ሪቻርድ ሄክት መግለጫ የሰጡ ሲሆን። ከመግለጫቸው ያገኘናቸው አንኳር ነጥቦች እነሆ፦
- በሃማስ ታጣቂዎች ተይዘው ነበር የተባሉ 22 ስፍራዎችን የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት መልሶ በቁጥጥር ስር አውሏል።በአሁኑ ወቅትም በስምንት አካባቢዎች ባሉ ስፍራዎች ታጣቂዎች ያሉ ሲሆን በዋናነትም “በእነዚያ ማህበረሰቦች ውስጥ ያሉ አሸባሪዎችን ለማጽዳት” እየሰራን ነው ብለዋል።የእስራኤል ባለስልጣናት በጋዛ ሰርጥ እና አካባቢው ያሉትን ነዋሪዎች “ቀስ በቀስ ማስወጣት መጀመራችውን” ተናግረዋል። ሆኖም ምን ያህል ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል ለሚለው ምላሽ አልሰጡም።እስራኤል ከሊባኖስ ለሚደርስባት ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን ተናግረው ነገር ግን በመሬት ላይ ሊካሄድ ስለሚችል ወረራን በተመለከተ ምንም አይነት አስተያየት አልሰጡም።እስራኤል “አሁንም በጦርነት ላይ ነች። የእስራኤልን ግዛት እና ማህበረሰቦችን ከሃማስ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የምታደርገውን ጥረት በማጠናቀቅ ላይ ናት”ይህንን ማስፈንጠ
- የታተመዉ 2:352:35በሐማስ ታግተው ስለተወሰዱ እስራኤላውያን እስካሁን የምናውቀውበጋዛ ሰርጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው እስራኤላዊ ሰላማዊ ሰዎች እና ወታደሮች በፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ሐማስ ታግተው እንደሚገኙ የእስራኤል ጦር አስታውቋል።ተጨማሪ ያንብቡ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 2:262:26እስራኤል የጋዛን መሰረታዊ አገልግሎቶች ታቋርጣለች- ኔታንያሁ
ReutersCopyright: Reutersጋዛ የኤሌክትሪከ፣ የነዳጅ እና የሸቀጥ ፍጆታዎች አቅርቦቶች እንደሚቋረጥባት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጽህፈት ቤት መግለጫን ጠቅሰው የአገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል።የጋዛን የኤሌክትሪክ ኃይል የእስራኤል ባለስልጣናት ትናንት መቁረጣቸውን ተከትሎ ግዛቲቷ በጨለማ ውስጥ እንደገባች ተነግሯል። የጋዛ ሰርጥ ላይ ለ16 ዓመታት ያህል የቆየ ከበባ ውስጥ ትገኛለች።እስራኤል ከግብጽ ጋር በመሆን ከአውሮፓውያኑ 2007 ጀምሮ የጋዛን ሰርጥ ለደህንነት ሲባል ከበባ ውስጥ አስገብታታለች።እስራኤል በጋዛ እና በአካባቢው የአየር፣ የመሬት እና የባህር እገዳ የጣለች ሲሆን በድንበሮች በኩል የሚገቡ ሸቀጦችንም ሆነ ዕቃዎች በተመለከተ የእስራኤል መንግሥት ሊፈቅድ ይገባል።በተመሳሳይ ግብጽ በራሷ ወሰን በጋዛ ድንበር በኩል የሚገቡትን እና የሚወጡትን ትቆጣጠራለች።
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 2:022:02ሰበርእስራኤል በሊባኖስ ላይ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት ፈጸመች
EPACopyright: EPAየእስራኤል መከላከያ ኃይል በሊባኖስ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት መጀመሩን አስታውቋል።ኃይሉ በእስራኤል ግዛት ለተፈጸመ የተኩስ ምላሸ ነው ብሏል።ተኩሱ የመጣው እስራኤል፣ ሊባኖስ እና ሶሪያ በሚወዛገቡበት ግዛት እና ሶስቱንም ሃገራት በሚያገናቸው የዶቭ ተራራ አካባቢ እንደሆነም የእስራኤል መከላከያ ኃይል ቃለ አቀባይ ተናግረዋል።እስራኤል የሊባኖስ ታጣቂ ሂዝቦላህ በውጊያው ውስጥ ጣልቃ እንዳይገባ አስጠንቅቃለች።ሂዝቦላህ በሊባኖስ ውስጥ መሰረቱን ያደረገ የሺአ እስላማዊ፣ የፖለቲካ፣ ወታደራዊ ድርጅት ነው።እንደ ሃማስ ሁሉ ሊባኖስ በእስራኤል ጠላት ኢራን ይደገፋል።በአውሮፓውያኑ 2006ም ከእስራኤል ጋር ለአንድ ወር የዘለቀ ጦርነት አካሂዷል።ከጥቂት ወራት በፊት ከሊባኖስ የጸረ ታንክ ሚሳኤል መተኮሱን ተከትሎ እስራኤል በከባድ መሳሪያ አጸፋዊ ምላሽ ሰጥታለች።
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 1:331:33የቅርብ ጊዜ ክስተቶች ምንድን ናቸው?
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesሃማስ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ድንገተኛ የሮኬቶች ጥቃት ተከትሎ እስራኤል ተከታታይ የአየር ጥቃቶችን እየፈጸመች ትገኛለች።በሮኬቶች እንዲሁም በአየር ጥቃቶቹ በእስራኤል እና በጋዛ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተገድለዋል።
- በሃማስ ጥቃት ከ250 እስራኤላውያን ሞተዋል የተባለ ሲሆን እስራኤል “ረዥም እና አስቸጋሪ ጦርነት” ውስጥ መግባቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ተናግረዋል።ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ በርካታ እስራኤላውያን በጋዛ እንደታገቱ የእስራኤል ጦር አስታውቋል።እስራኤል አጸፋዊ ጥቃቶች እንደምታካሂድ በማስጠንቀቅም ጋዛውያን ቤታቸውን ለቀው እንዲሸሹ እና መጠለያ እንዲፈልጉም ተናግራለች።እስራኤል ባደረሰችው ጥቃት ከ230 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል።በደቡባዊ እስራኤል በሃማስ ታጣቂዎች እና በእስራኤል መከላከያ ኃይል የሚደረገው ውጊያ እንደቀጠለ ነውእስራኤል በጋዛ ሌሊቱን ሙሉ የቀጠለ የአየር ድበደባዎች እንደፈጸመች የተዘገበ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በከበባ ላይ ባለችው ጋዛ የኤሌክትሪክ እና ሌሎች አቅርቦቶችን እንደምታቋርጥ ተናግረዋል።ሃማስ ያደረሰው ጥቃት በርካታ ምዕራባውያን ያወገዙት ሲሆን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይን አሜሪካ ለእስራኤል ያላት ድጋፍ “ጠንካራ እና የማይናወጥ” እንደሆነም ተናግረዋል።ሃማስ በበኩሉ ኢራን ጥቃቱን እንደደገፈች ለቢቢሲ ተናግሯል። ሳዑዲ አረቢያ በበኩሏ “በወረራ የተያዙ ግዛቶች” ስለሚያስከትላቸው አደጋዎች ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ እንደሰጠችና ሁኔታው በአስቸኳይ እንዲረግብም ጠይቃለች።ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 1:011:01ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ?የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ሐማስ ከዚህ በፊት ታይታ በማይታወቅ ሁኔታ በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃትን ከፍቶ ውጥረት በማይለየው የመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ጦርነት ተቀስቅሷል። ሐማስ ጥቃቱን በከፈተበት በአጭር ጊዜ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሮኬቶችን ከጋዛ ከተማ በመተኮስ በርካታ የእስራኤል ከተሞችን የመታ ሲሆን፣ ታጣቂዎቹም ወደ እስራኤል ግዛት ዘልቀው መግባታቸው ተዘግቧል። እስራኤልም በአጸፋው በጋዛ ላይ የአየር ጥቃት የከፈተች ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁም አገራቸው “ጦርነት ውስጥ” መሆኗን ተናግረዋል። ይህ ግጭት እንዴት ጀመረ?ተጨማሪ ያንብቡ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 0:550:55የእስራኤል የስለላ ተቋማት መጠነ ሰፊውን የሐማስ ጥቃት እንዴት ሳይደርሱበት ቀሩ?እስራኤል ካላት ወታደራዊ እና የመረጃ አቅም አንጻር ቅዳሜ ማለዳ በሐማስ ስለተፈጸመባት የተቀናጀ ጥቃት ምንም አይነት ፍንጭ ሳይኖራት በድንገት መፈጸሙ አስደንጋጭ ሆኖባታል። የእስራኤል ባለሥልጣናትም ከዚህ በፊት ካጋጠሙት በእጅጉ የተለየ ስለሆነው የሐማስ ጥቃት ሲጠየቁ “እንዴት ሊፈጸም እንደቻለ ምንም አናውቅም” የሚል ነው ምላሻቸው።ተጨማሪ ያንብቡ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 0:540:54በጋዛ ምን እየተከናወነ ነው?
EPACopyright: EPAየሐማስ ድንገተኛ ጥቃትን ተከትሎ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ ተከታታይ የአየር ጥቃቶችን ፈጽማለች።እስካሁን ድረስ ከ230 በላይ የጋዛ ነዋሪዎች እንደተገደሉ እና ከአንድ ሺህ በላይም እንደቆሰሉ ባለስልጣናቱ ተናግረዋል።የእስራኤል ጦር ለረጅም ጊዜ ተከባ ባለችው ጋዛ ውስጥ የሚኖሩ ሰባት የተለያዩ አካባቢዎች ነዋሪዎች ቤታቸውን ለቀው ወደ መሃል ከተማ እንዲሄዱ ወይም በመጠለያ ውስጥ እንዲጠለሉ አሳስቧል።በርካታ ፍልስጥኤማውያን ቤተሰቦች ከቤታቸው ወጥተው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሚተዳደሩ ትምህርት ቤቶች ተጠልለው እንደሚገኙ የዓይን እማኞች ገልጸዋል።የጋዛ ነዋሪዎች እስራኤል እየፈጸመች ያለችውን የአየር ጥቃት ቀጣይ እና ከፍተኛ ሲሉም ገልጸውታል።
EPACopyright: EPA
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 0:520:52ሐማስ ከ2 ሺህ በላይ ሮኬቶችን ከተኮሰ በኋላ አስራኤል ጦርነት እንደተከፈተባት አስታወቀች
ReutersCopyright: Reutersየፍልስጤማዊው ቡድን ሐማስ ከሁለት ሺህ በላይ ሮኬቶችን በእስራኤል ላይ ከተኮሰ በኋላ፣ ታጣቂዎቹ ወደ ደቡባዊ የእስራኤል ክፍል ዘልቀው መግባታቸውን ተከትሎ አስራኤል ጦርነት ውስጥ መግባቷን አስታወቀች።ይህንን ከባድ ጥቃት ተከትሎ የእስራኤል ወታደራዊ ባለሥልጣናት በሐማስ ላይ ስለሚወሰደው እርምጃ አስቸኳይ ምክክር አድርገዋል፤ የጦር ሠራዊቱም ለአባላቱ “ለጦርነት ዝግጁ” እንዲሆኑ ትዕዛዝ በማስተላለፍ፣ ለአገሪቱ ተጠባባቂ ጦር አባላት ጥሪ አቅርቧል።ፍልስጤማዊው ታጣቂ ቡድን ሐማስ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በእስራኤል ላይ ጥቃት ከፍቶ ተዋጊዎቹ ወደ እስራኤል ግዛት ሰርገው ከገቡ በኋላ ጦርነት እንደተከፈተባት እስራኤል ገልጻለች።ድንገተኛውን ጥቃት ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ “ጦርነት ውስጥ ነን” በማለት አገራቸው ላይ በሐማስ ታጣቂዎች ጦርነት እንደተከፈተ ተናግረዋል።ቅዳሜ ማለዳ ላይ የሐማስ ታጣቂዎች ከጋዛ ሰርጥ ከፍተኛ መጠን ያለው የሮኬት ውርጅብኝ በእስራኤል ላይ በሚያዘንቡበት ጊዜ፣ ተዋጊዎቻቸው የድንበር አጥር በመሻገር ነው ወደ እስራኤል መግባታቸው የተነገረው።