Skip to content
ጭምቅ ሃሳብ
- በእስራኤል እና በጋዛ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሺህ በላይ ሆነ
- በጋዛ ከ123 ሺህ በላይ ፍልስጥኤማውያን ተፈናቀለዋል
- ኢራን፣ ሐማስ በፈጸመው ጥቃት ላይ ተሳትፎ የለኝም አለች
- እስራኤል በሊባኖስ ላይ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት ፈጸመች
- የእስራኤል ጦር በሃማስ ላይ ለሚሰነዘረው የአጸፋ ጥቃት በጋዛ ሰርጥ የሚኖሩ ነዋሪዎች ቤታቸውን ለቀው እንዲለቁ ጠየቀ
- ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ “ጥቁር ቀን” ብለው ለጠሩት ጥቃትም ምላሽ በፍልስጥኤም ታጣቂዎች ላይ “ከፍተኛ የበቀል እርምጃ” እንደሚወስዱ አስጠንቅቀዋል።
- በግብጽ ሁለት እስራኤላውያን ቱሪስቶች በተተኮሰባቸው ጥይት ተገደሉ
- የፍልስጥኤም ታጣቂ ቡድን ሃማስ ያልተጠበቀ የተባለውን ከሁለት ሺህ በላይ ሮኬቶችን በእስራኤል ላይ ተኩሰዋል።
- በጥቃቱ 250 ሰዎች ሲገደሉ በርካታ እስራኤል ታግተዋል ተብሏል።
- እስራኤል በምላሹ ተከታታይ የአየር ጥቃቶችን በጋዛ ላይ የፈጸመች ሲሆን በዚህም ከ230 ሰዎች በላይ ተገድለዋል።
- እስራኤል የጋዛን መሰረታዊ አገልግሎቶች ታቋርጣለች- ኔታንያሁ
- የሃማስ ታጣቂዎች በእስራኤል ውስጥ ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ነው አሉ
- 313 ፍልስጥኤማውያን እና 300 እስራኤላውያን መገደላቸው ተነገረ
- የታተመዉ 13:4913:49ሐማስ ላይ የምንወስደው እርምጃ ገና መጀመሩ ነው፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ
ReutersCopyright: Reutersየእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ የሐማስን ጥቃት ተከትሎ የእስራኤል ሠራዊት እየወሰደ ያለው የአጸፋ እርምጃ “ገና መጀመሩ ነው” ሲሉ ተናገሩ።በእስራኤል ግዛት በአስርት ዓመታት ውስጥ አጋጥሞ የማያውቅ ነው በተባለው የሐማስ ጥቃት በእጅጉ የተቆጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአገራቸው ምላሽ ቀጣይ መሆኑን ገልጸዋል።ኔታኒያሁ ይህንን የተናገሩት የሐማስ ጥቃት ዋነኛ ኢላማ ከሆነችው ደቡባዊ እስራኤል ከመጡ ባለሥልጣናት ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት ነው።ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ሐማስ የሚገጥመው ፈተና ከባድ እና አስከፊ” ነው ማለታቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ (ኤኤፍፒ) ዘግቧል።አክለውም “አሁን ያለው ሁኔታ ገና የመጀመሪያው ነው… ሁላችንም አብረናችሁ ነን፤ በከባድ ኃይል እናሸንፋቸዋለን” ብለዋል።ሐማስ ወደ እስራኤል ዘልቆ በመግባት ጥቃቱን ከጀመረ አንስቶ ከ700 በላይ ሰዎች እስራኤል ውስጥ ሲገደሉ፣ እስራኤል በከፈተችው የአየር ጥቃት ደግሞ ቢያንስ 560 ሰዎች ጋዛ ውስጥ ተገድለዋል።Article share tools
- የታተመዉ 10:2010:20ኳታር ከሐማስ ባለሥልጣናት ጋር ሽምግልና መጀመሯ ተነገረየኳታር አሸማጋዮች በሐማስ ታጣቂዎች ተይዘው ወደ ጋዛ ስርጥ የተወሰዱ እስራኤላውያን ሴቶች እና ሕጻናትን ለማስለቀቅ ጥረት እያደረጉ መሆናቸው ተሰማ።ሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው ኳታራውያን አደራዳሪዎች በሐማስ የተያዙትን እስራኤላውያን ለማስለቀቅ ከቡድኑ ባለሥልጣናት ጋር ግንኙነት እያደረጉ ነው።እየተደረገ ስላለው ንግግር መረጃ ያላቸው ምንጮች ለሮይተርስ እንደተናገሩት ኳታራውያኑ አደራዳሪዎች በሐማስ የተያዙትን፣ እስራኤል ውስጥ በእስር ላይ በሚገኙ 36 ፍልስጥኤማውያን ሴቶች እና ሕጻናት በመለዋወጥ እንዲለቀቁ ሃሳብ አቅርበዋል።ምንጮች እንዳሉት በኳታር አማካይነት የተካሄደው ንግግር ከአሜሪካ ጋር በመተባበር ነው።ነገር ግን አስካሁን ስለዚህ ጉዳይ እስራኤልም ሆነች ሐማስ በቀጥታ አስተያየታቸውን አልሰጡም።Article share tools
- የታተመዉ 8:598:59ብሪታኒያ እና አሜሪካ ዜጎቻቸው እስራኤል ውስጥ መሞታቸው ወይም መጥፋታቸውን አስታወቁ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesሐማስ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ብሪታኒያ እና አሜሪካ እስራኤል ውስጥ የሚገኙ ዜጎቻቸው መሞታቸውን እና የደረሱበት አለመታወቁን ገለጹ።ብሪታኒያ እስራኤልው ውስጥ ከሚገኙ ዜጎቿ መካከል አስካሁን ከ10 በላይ የሚሆኑት ሞተው ወይም ጠፍተው ሊሆኑ እንደሚችል ስጋቷን ገለጸች።የእራኤል ዋነኛዋ ወዳጅ አሜሪካ ደግሞ ዘጠኝ ዜጎቿ አስራኤል ውስጥ መሞታቸውን የአሜሪካ መንግሥት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።ቢቢሲ ከይፋዊ የዩናይትድ ኪንግደም ምንጮች እንደተረዳው “ከ10 የሚበልጡ” የብሪታኒያ ዜጎች የሮኬት ጥቃቶቹን ተከትሎ ሞተዋል ወይም የደረሱበት አልታወቀም ተብሎ ተሰግቷል።የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ዋይት ሐውስ ባወጣው መግለጫ ላይ ዘጠኝ አሜሪካውያን መሞታቸውን አረጋግጦ ጥልቅ ሐዘኑን በመግለጽ፣ ጉዳት የደረሰባቸውም በቶሎ እንዲያገግሙ መልካሙን ተመኝቷል።ጨምሮም በእስራኤል ውስጥ የተከሰተውን ሁኔታ የአሜሪካ መንግሥት በቅርበት እንደሚከታተለው እና ከእስራኤል መንግሥት በተለይም ከአካባቢ ባለሥልጣናት ጋር ግንኙነቱን እንደሚቀጥል አመልክቷል።አሜሪካ በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ ግዙፍ የጦር መርከቧን ወደ እስራኤል አንቀሳቅሳለች።Article share tools
- የታተመዉ 6:506:50ከጋዛ የተወነጨፉ ሮኬቶች በማዕከላዊ እስራኤል ጉዳት አደረሱ
ReutersCopyright: Reutersከጋዛ ሮኬቶች መወንጨፋቸውን ቀጥሏል።ከጋዛ ሰርጥ በስተሜን በምትገኘው አሽኬሎን በተወነጨፉ ሮኬቶች አራት ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል።ከነዚህም መካከል አንደኛው በጠና ቆስሎ ለህክምና ወደ ሆስፒታል መወሰዱን የእስራኤል የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት አስታውቋል።በአቅራቢያው በሚገኘው አሽዶድ አንዲት ሴት የከፋ ጉዳት ደርሶባት ወደ ሆስፒታል ተወስዳለች።Article share tools
- የታተመዉ 5:495:49ሰበርእስራኤል በጋዛ ላይ ‘ሙሉ ከበባ’ እንዲደረግ አዘዘች
EPACopyright: EPAአስራኤል ጋዛ ሰርጥን ሙሉ በሙሉ በመዝጋት ከበባ እንዲደረግ አዘዘች።በጋዛ ‘ኤሌክትሪክ፣ ምግብ፣ ነዳጅ አይኖርም ሲሉም የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት ትዕዛዝ ሰጥተዋል።ጋዛ ሰርጥ ወደ 2.3 ሚሊዮን የሚጠጉ ፍልስጥኤማውያን መኖሪያ ስትሆን ለ16 ዓመታት ያህል የቆየ ከበባ ውስጥ ትገኛለች።እስራኤል በጋዛ እና በአካባቢው የአየር፣ የመሬት እና የባሕር እገዳ የጣለች ሲሆን፣ በድንበሮች በኩል የሚገቡ ሸቀጦችንም ሆነ ዕቃዎች በተመለከተ የእስራኤል መንግሥት ሊፈቅድ ይገባል።በተመሳሳይ ግብፅ በራሷ ወሰን በኩል ወደ ጋዛ የሚገቡ እና የሚወጡትን ትቆጣጠራለች።በተያያዘ ዜና የእስራኤል መከላከያ በጋዛ ሰርጥ አቅራቢያ ያሉ ማኅበረሰቦችን ሙሉ በቁጥጥሩ ስር ማድረግ መቻሉን አስታውቋል።ሆኖም በአካባቢው ከፍልስጥኤም ታጣቂዎች ጋር ያለው ውጊያ መቀጠሉም ተነግሯል። እስራኤል በግዛቶቿ ውስጥ ባሉ ሰባት እና ስምንት ቦታዎች ውጊያዎች እየተካሄደ መሆኑንም አስታውቃለች።ከጋዛ ወደ እስራኤል የሚወነጨፉ ሮኬቶች አሁንም እየተተኮሱ ሲሆን፣ በእየሩሳሌም ቢያንስ ሦስት ፍንዳዎት ተሰምተዋል ተብሏል።እነዚህ ሮኬቶች ኢላማዎችን ይምቱ ወይም በእስራኤል የሚሳኤል መቃወሚያ እየከሸፉ ስለመሆኑ ግልጽ አይደለም።
BBCCopyright: BBCArticle share tools
- የታተመዉ 5:005:00ሰበርበጋዛ ሰርጥ የሚገኝ የተመድ ትምህርት ቤት በእስራኤል የአየር ጥቃት ተመታ
UNRWACopyright: UNRWAበጋዛ ሰርጥ የሚገኝ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ትምህርት ቤት በእስራኤል አየር ጥቃት መመታቱን የፍልስጥኤም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።ትምህርት ቤቱ ህጻናትን እና አረጋውያንን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች መጠለያ ሲሆን ሚኒስቴሩ ጥቃቱን “ጭካኔ የተሞላበት” ሲል ገልጿል።የተባባሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ጥቃቱ መፈጸሙን ያረጋገጠ ሲሆን ትምህርት ቤቱ “በከፋ ደረጃ ጉዳት ደርሶበታል” ብሏል። ሆኖም ህይወት አለመጥፋቱን አክሎ ገልጿል።እስራኤል በጋዛ ሰርጥ በምታደርገው ተደጋጋሚ የአየር ጥቃቶች ወደ 500 የሚጠጉ ሰዎችመገደላቸውን የፍልስጥኤም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።የቆሰሉ ሰዎች ቁጥርም ወደ 2 ሺህ 751 ከፍ ማለቱም ተገልጿል።Article share tools
- የታተመዉ 4:594:59ሐማስ ማነው? በጋዛ ሰርጥስ ምን ተፈጠረ? ሊያውቋቸው የሚገቡ ወሳኝ ጥያቄዎችየፍልስጥኤሙ ታጣቂ ቡድን ሐማስ ታይቶ የማይታወቅ የተባለለትን የተቀናጀ ጥቃት እስራኤል ላይ ሰንዝሯል። ተዋጊዎቹም በጋዛ ሰርጥ አቅራቢያ የሚገኙ ነዋሪዎችን ገድለዋል፣ አግተዋል። ስለተሳታፊዎቹ እና ስለጥቃቱ ቦታዎች ማወቅ ያለብዎት ነገር ወሳኝ መረጃዎችን እንደሚከተለው አጠናቅረናል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- የታተመዉ 3:443:44እስራኤል በጋዛ ከ500 በላይ ኢላማዎችን በአንድ ሌሊት መምታቷን አስታወቀች
ReutersCopyright: Reutersበጋዛ ሰርጥ በአንድ ሌሊት ከ500 በላይ ኢላማዎች በአየር መመታታቸውን የእስራኤል አየር ኃይል አስታወቀ።ኢላማ የተደረጉት የሐማስ እናየፍልስጥኤም ኢስላሚክ ጂሃድ ተቋማት መሆኑንም የአየር ኃይሉ አክሎ ገልጿል።እስራኤል በጋዛ ሰርጥ እየፈጸመቻቸው ባሉ የአየር ጥቃቶች መስጊድን ጨምሮ በርካታ ህንጻዎች እና መኖሪያዎች ወድመዋልየእስራኤል ኃይል በበኩሉ ተዋጊ ጄቶች፣ የጦር ሄሊኮፕተሮች እና ተወንጫፊ የጦር መሳሪያዎች ኢላማዎቹን መትተዋል ተብሏል።ሰባት የሐማስ ማዘዣ ማዕከላት እንዲሁም የፍልስጥኤም ኢስላሚክ ጂሃድ ማዕከል መመታታቸውን አክሎ ገልጿል።የአየር ጥቃቶቹንም ተከትሎ 413 ፍልስጥኤማውያን መገደላቸውን የፍልስጥኤም ባለስልጣናት ተናግረዋል።