October 9, 2023 

ብርሃኑ ነጋ ከገነት ዘውዴና ከሽፈራው ሽጉጤ በባሰ መልኩ የትምሕርት ስርዐቱን መግደሉን የተማሪዎች ውጤት በቂ ማሳያ ነው። አሳፋሪ እጅግም አስደንጋጭ ትውልድ ገዳይ ነው።

817.733 ተማሪዎች ከጥቅም ውጪ እንዲሆኑ በብርሃኑ ነጋ ተፈርዶባቸዋል። ይህ እጅግ አስደንጋጭና አሳፋሪ ሃላፊነት የጎደለው የትምሕርት ስርዐቱንም ከበፊቱ በባሰ መልኩ የገደለ ነው። ……. ሆን ተብሎ የተደረገና ትውልዱን ለማምከት ለማሳደድ የተወጠነ ሴራ ነው። ብርሃኑ ነጋ የሚባል ከይሲ ማሰብ የማይችል ግለሰብ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጥ አያፍርም። ከትምሕርት ስርዐቱን ከገነትና ከሽፈራው በባሰ መልኩ ገድሎታል። ይህ የተማሪዎች ውጤት በቂ ምስክር ነው። የትምሕርት ጥራት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑ ይህ አስደንጋጭ ውጤት ካለፈው አመት በባሰ መልኩ ሊወርድ የቻለው የትምሕርት ሚኒስቴር ደካማ አሰራርን ያሳየናል።

የትምሕርት ሚኒስቴር ማላጋጨ እንደሚያሳየው በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ከወሰዱ 845 ሺህ ገደማ ተማሪዎች መካከል፤ ወደ ዩኒቨርስቲ የማለፊያ ነጥብ ያመጡት ተፈታኞች ብዛት 27,267 ተማሪዎች አሊያም 3.2 በመቶዎቹ ብቻ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ካስፈተኑ 3,106 ትምህርት ቤቶች መካከል፤ 1,328ቱ አሊያም 42.8 በመቶ የሚሆኑት አንድም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ይፋ አድርጓል። አሳፋሪ እጅግም አስደንጋጭ ነው። 

#MinilikSalsawi