Godana Yacob

  · 

ሄደን ሄደን ጥቁር ወተት ላይ ደረስን አለ ወንድሜ ከወተት ውጪ የሚጠጣ ነገር ሳያውቅ አድጎ ኮካ ኮላ ጠጣ ብለው ሲሰጡት!!!

የኦህዴድ ብልፅግና ዘመን የሚጠሉት ሚኒሊክንም አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ገፈው…አዋርደው…አቃጥለው…መሬት ላይ ረግጠው ይህን ባንዲራቸው አለበሱት አይደል መቼም ተዓምር አያልቅ!!!

የኦህዴድ ዘመን እንዲህ ያለን አይን ያወጣ ተረኛነት አሳየን!!!

ስርዐት ከተባለ ገዳ…..! ሸምጋይ ከተባለ አባ ገዳ….! ቋንቋ ከተባለ ኦሮምኛ…..! በድምቀትና በመንግስ ወጪ የሚከበር ክብረ በአል ከተባለ ኢሬቻ….! ክፍለ ከተማ ከተባለ ለሚ ኩራ….!

ከዛ ደግሞ እኩልነት….! ህብረ ብሔራዊነት እያሉ ያደነቁሩናል የሚያምናቸው ያለ ይመስል!!!!

መቼም ሞኝ ይረታል…ምን ብሎ ሲባል እምቢ ብሎ እንዲሉ ነው የሆነው!!!

እነሱን በአንድ ስሙ አላማ ብለው የያዙትን አንድ…ሁለት…ሶስት ብለው ቆጥረው እየፈፀሙና እያስፈፀሙ ነው!!!

የኛ ያልናቸው ጉምቱ ፓለቲከኞች አሉ አይደል እንዴ አጉል ሚዛናዊ ለመባልና ርካሽ ተወዳጅነትን ለማትረፍ ወይም ደግሞ መላ ቅጡ ጠፍቶባቸውና ተጃጅለው “የኦሮሞ መንግስት አትበሉ….! ስለ ተረኛነት አታውሩ….!

ይህን መንግስት የኦሮሞ….ሰራዊቱም የኦህዴድ ነው!” አትበሉ እያሉ ምክር አይሉት ተግሳፅ ሊሰፍሩልን ይጣጣራሉ!!!

ዛሬ ላይ የኦሮሞ ብሔርተኞች/ልሂቃን ፋኖ መጥቶ በእጃችን የገባውን ስልጣን….ያነበርነውን ተረኛነት ሊቀማን ነውና በአንድነት ከአብይ አህመድ ጋር እንቁም….! ልዩነታችንን አጥብበን በእጃችን የገባውን ስልጣን እናስጠብቅ….! እያሉ ተረኛነታቸውን በአደባባይ እና ያለምንም መሳቀቅ እያወጁ….የኛዎቹ የሚናገሩትን አያውቁምና ይቅር በሏቸው ይሉናል!!!

ተረኛ ነን ያሉት ተሳስተው ነውና አትስሟቸው ይሉናል!!!

“ብልፅግና የኦሮሞ…ከኦሮሞ…ለኦሮሞ ነው” ያሉትን የብልፅግና መስራቿች አትመኗቸው እያሉ ያደርቁናል!!!

“በመጀመሪያ እነሱ ነበሩ…ከዛ ትግሬ መጣ…አሁን ደግሞ የኦሮሞ ተራ ነው ማለት ከሆነ ተረኛነት አሪፍ ነገር እኮ ነው” የሚል ሰው ኢታማዦር ሹም ሆኖና…በ150 አመታት ውስጥ ያልተገኘ የሚለው አብይ የሀገሪቱ የጦር ጠቅላይ አዛዥ የሆነበትን ሰራዊት የኦህዴድ አይደለም ብለው ቅቤ ላይወጣቸው እየተናጡ ይዘበዝቡናል!!!

“ለመጀመሪያ ጊዜ ዲሞክራሲ ባሕሉ ከሆነው ከኦሮሞ የተገኘ መሪ” እያለ ሌንጫ ለታ የሚያሞካሸውን የአብይ አህመድን አገዛዝ “እንኳን ኦሮሞን ቀርቶ የኦሮሞ ልሂቃንን አይወክልም” እያሉ ይነዘንዙናል!!!

እንደ ጠንቋይ እኔ አውቅላቿለሁን አይን አውጥቶ የሚታየውን ተረኛነትም አትመኑ….! ተረኛ ነን…ጊዜው የኛ ነው እያሉ ሳይደብቁ በአደባባይ ደጋግመው የሚናገሩትንም አትስሙ….! አትመኑም…! ይሉናል መቼም ተዓምር አያልቅ!!!!

እኔ ከሞኝ አጥፊ….ከየዋህ መካሪ በአንድ ፊቱ ተንኮለኛና አውቆ አጥፊ ይሻለኛል!!! ከሁሉ በላይ ግንርካሽ ተወድጅነት ለማትረፍ እጅና እግር አውጥቶ በገሀድ የሚታይን ነገር ሊያስክደን የሚጋጋጥ አንደበተኛን ነብሴ አምርራ ትፀየፈዋለች!!!

የሆነ ሆኖ በኢሬቻ ሰበብ መላ አዲስ አበባን የኦሮሚያ ባንዲራን የማልበስ ሂደት አዲስ አበባን ፊንፊኔ የማድረግ ሂደት አንድ ምዕራፍ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል!!!

https://www.facebook.com/watch/?v=1265047631558704&tn=F