https://www.bbc.com/amharic/live/67042690
ጭምቅ ሃሳብ
- በጋዛ 187 ሺህ ፍልስጥኤማውያን ተፈናቅለዋል
- በእስራኤል እና በጋዛ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሺህ በላይ ሆነ
- በጋዛ ከ123 ሺህ በላይ ፍልስጥኤማውያን ተፈናቀለዋል
- ኢራን፣ ሐማስ በፈጸመው ጥቃት ላይ ተሳትፎ የለኝም አለች
- እስራኤል በሊባኖስ ላይ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት ፈጸመች
- የእስራኤል ጦር በሃማስ ላይ ለሚሰነዘረው የአጸፋ ጥቃት በጋዛ ሰርጥ የሚኖሩ ነዋሪዎች ቤታቸውን ለቀው እንዲለቁ ጠየቀ
- ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ “ጥቁር ቀን” ብለው ለጠሩት ጥቃትም ምላሽ በፍልስጥኤም ታጣቂዎች ላይ “ከፍተኛ የበቀል እርምጃ” እንደሚወስዱ አስጠንቅቀዋል።
- በግብጽ ሁለት እስራኤላውያን ቱሪስቶች በተተኮሰባቸው ጥይት ተገደሉ
- የፍልስጥኤም ታጣቂ ቡድን ሃማስ ያልተጠበቀ የተባለውን ከሁለት ሺህ በላይ ሮኬቶችን በእስራኤል ላይ ተኩሰዋል።
- በጥቃቱ 250 ሰዎች ሲገደሉ በርካታ እስራኤል ታግተዋል ተብሏል።
- እስራኤል በምላሹ ተከታታይ የአየር ጥቃቶችን በጋዛ ላይ የፈጸመች ሲሆን በዚህም ከ230 ሰዎች በላይ ተገድለዋል።
- እስራኤል የጋዛን መሰረታዊ አገልግሎቶች ታቋርጣለች- ኔታንያሁ
- የሃማስ ታጣቂዎች በእስራኤል ውስጥ ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ነው አሉ
- 313 ፍልስጥኤማውያን እና 300 እስራኤላውያን መገደላቸው ተነገረ
ቀጥታ ዘገባ
- የታተመዉ 12:3112:31የዛሬ ዋና ዋና ክስተቶች በአጭሩ
BBCCopyright: BBCባለፈው ቅዳሜ የተቀሰቀሰው የእስራኤል እና የሐማስ ውጊያ ለአራተኛ ቀን ቀጥሎ እስራኤል ጋዛን በጦር ጀቶቿ ስትደበድብ፣ ሐማስ ደግሞ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል መተኮሱን ቀጥሏል።በዛሬው ዕለት የተከሰቱ ቁልፍ ነገሮችን አጭሩ እነሆ፡…
- ·የሐማስ ታጣቂዎች እስራኤላውያን ነዋሪዎች አሽኬሎን ከተባለችው ከተማ ለቀው እንዲወጡ አሰጠንቅቀው አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ የሮኬት ተኩስ በከተማዋ ውስጥ ተሰምቷል።
- ·የሐማስን ጥቃት ተከትሎ የደረሱበት ያልታወቁ የአሜሪካ ዜጎች ዘመዶች በእስራኤሏ መዲና ቴል አቪቭ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እየጠበቋቸው ስላሉት የቤተሰቦቻቸው አሳዛኝ ታሪኮችን ተናግረዋል።
- ·ከቅዳሜ ጀምሮ በእስራኤል የአየር ድብደባዎች የተገደሉ ፍልስጥኤማውያን ቁጥር ወደ 830 ሲደርስ፣ በእስራኤላውያን በኩል የተመዘገበው ሞት ደግሞ ቢያነስ 1,008 መድረሱ ተዘግቧል።
- ·ሐማስ “ውጊያው አስኪቆም ድረስ” በእገታው ስር ስላሉ እስራኤላውያን ጉዳይ እንደማይነጋገር አሳውቋል። አስካሁን ባለ መረጃ ከ100 አስከ 150 የሚደርሱ እስራኤላውያን በሐማስ እገታ ውስጥ እንዳሉ ይታመናል።
- ·እስራኤል ጋዛ ላይ የምትፈጽመው የአየር ጥቃት ቀን ከሌት ሳይል የቀጠለ ሲሆን፣ ሐማስም ሮኬቶቹን ማስወንጨፉን ቀጥሏል።
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 8:528:52የሳዑዲው ልዑል ሞሐመድ ቢን ሳልማን ለፍልስጥኤማውያን ድጋፋቸውን ገለጹ
ReutersCopyright: Reutersልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማንImage caption: ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማንየሳዑዲው ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን አገራቸው የፍልስጥኤማውያን መብት እንዲከበር ድጋፏን እንደምትቀጥል ተናገሩ።ሳዑዲ አረቢያ መሪ የሆኑት ቢን ሳልማን ይህንን ያሉት እስራኤል በሐማስ የተፈጸመባትን ጥቃት ተከትሎ ጋዛ ውስጥ ከባድ ጥቃት እያካሄደች ባለበት ጊዜ ከፍልስጥኤም ፕሬዝዳንት ማሐሙድ አባስ ጋር በስልክ በተወያዩበት ጊዜ ነው።ቢን ሳልማን “ፍልስጥኤማውያን ተገቢ መብቶቻቸው፣ የተረጋጋ ሕይወት፣ ፍትሃዊ እና ዘላቂ ሰላምን እንዲያገኙ ለማስቻል” አገራቸው ድጋፏን ትቀጥላለች ብለዋል።ጨምረውም ከዓለም አቀፍ እና ከአካባቢያው ማኅበረሰብ ጋር በመሆን ግጭቱ እንዳይስፋፋ እየሰሩ መሆናቸውን ለአባስ ገልጸውላቸዋል።ፍልስጥኤሙ ፕሬዝዳንት ማሐሙድ አባስ እና ጋዛን የተቆጣጠረው ሐማስ የፖለቲካ ተቀናቃኞች ናቸው። አባስ ሌላኛውን የፍልስጥኤም ግዛት ዌስት ባንክን የተቆጣጠረው የፋታህ ንቅናቄ እና የፍልስጥኤም ነጻነት ድርጅት (ፒኤልኦ) መሪ ናቸው።ሳዑዲ አረቢያ ለፍልስጥኤም ያላትን ድጋፍ የገለጸችው በአሜሪካ አማካይነት ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት ለመሻሻል ድርድር እየተደረገ ባለበት ጊዜ ነው።ተንታኞች የተቀሰቀሰው ግጭት ግንኙነታቸውን ለማሻሻል በእስራኤል እና በሳዑዲ መካከል በሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት ደቅኗል ብለዋል።ቅዳሜ ዕለት የተፈጸመውን የሐማስን ጥቃት ተከትሎ ሳዑዲ አረቢያ ባወጣችው መግለጫ ለግጭቱ መባባስ እስራኤልን ተጠያቂ አድርጋለች።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:158:15ውጊያው ሳይቆም በታጋቾች ጉዳይ ላይ አንደራደርም፡ ሐማስ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesውጊያው እስኪያቆም ድረስ በቁጥጥሩ ስር ስላሉ ታጋቾች ሐማስ ከእስራኤል ጋር እንደማይደራደር የቡድኑ ፖለቲካ ቢሮ ኃላፊ ኢስማኤል ሃኒያህ ተናገሩ።“በቁጥጥራችን ስር ያሉ የጠላት አስረኞች ጉዳይ ጦርነቱ ከማብቃቱ በፊት እንደማይነሳ ጥያቄ ላቀረቡልን ወገኖች ሁሉ አሳውቀናቸዋል” ያሉት ሃኒያህ ቡድናቸው “ጉዳዩን የሚቀበለው የሚፈልገውን ምላሽ ሲያገኝ ብቻ ነው” ብለዋል።ሐማስ ባለፈው ቅዳሜ በእስራኤል ላይ ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ፣ ከደቡባዊ እስራኤል አካባቢዎች በ100 እና በ150 መካከል የሚገኙ ሰዎች በፍልስጥኤማዊው ቡድን ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ተዘግቧል።የኳታር እና የአሜሪካ አሸማጋዮች ሐማስ እና እስራኤል በእጃቸው ያሉ ሴቶች እና ሕጻናት እስረኞችን እንዲለዋወጡ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ሮይርስ ዘግቦ ነበር።የሐማስ ጥቃትን ተከትሎ ለቀናት የቆየ የአጸፋ ጥቃት እየፈጸሙ ያሉት የእስራኤል መከላከያ ኃይሎች ዛሬ ማክሰኞም የሐማስ ናቸው ያሏቸውን ኢላማዎች ማጥቃታቸውን ቀጥለዋል።ሰኞ ሌሊት የእስራኤል አየር ኃይል 200 ኢላማዎችን ጋዛ ውስጥ መደብደቡን ገልጸዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 6:496:49ሰበርበጋዛ የተገደሉ ፍልስጥኤማውያን ቁጥር 770 ደረሰ
ReutersCopyright: Reutersእስራኤል በጋዛ ሰርጥ እየፈጸመቻቸው ያሉ የአየር ጥቃቶችን ተከትሎ በጋዛ ሰርጥ የተገደሉ ፍልስጥኤማውያን ቁጥር 770 ደረሰ።በተጨማሪም 4 ሺህ 100 መቁሰላቸውን የእስራኤል ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ሙሉ ከበባ እንዲፈጸም ትዕዛዝ መስጠቷን ተከትሎ የዓለም የጤና ድርጅት ለሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት መተላለፊያ እንዲኖር ጥሪ አቅርቧል።እስራኤል በጋዛ የኤሌክትሪክ፣ ምግብ፣ ነዳጅ እና ውሃ አቅርቦት እንዲቋረጥም ማድረጓን ተከትሎ ነው የዓለም የጤና ድርጅት እና ዩኒሴፍ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲገባ እየጠየቁ ያሉት።የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኃላፊ ቮልከር ቱርክ የሃማስን ጥቃት አውግዘው የእስራኤል ከበባ በዓለም አቀፍ ህግ መሰረት ህገወጥ ነው ብለዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 6:496:49በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት አጀማመር ምን ይመስላል?ቅዳሜ ዕለት በጋዛ የሚገኙ የፍልስጥኤም ታጣቂዎች ጥቃት ፈጽመዋል። ጥቃቱ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ ነው ተብሏል። ለመሆኑ ለቀናት ቀጥሎ የበርካቶችን ሕይወት የቀጠፈው ግጭት አጀማመር እና ዋና ዋና ጉዳዮች ምን ይመስላሉ?ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 6:116:11በጋዛ 187 ሺህ ፍልስጥኤማውያን ተፈናቅለዋል- ተመድ
ReutersCopyright: Reutersእስራኤል ገና መጀመሩ እንደሆነ በገለጸችው የጋዛ የአየር ጥቃቶችን ተከትሎ 187 ሺህ ፍልስጥኤማውያን መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል።ቁጥሩ ከዚህ ሊልቅ እንደሚችልም ነው ተመድ ያሳሰበው።በጋዛ ባሉ 83 የተባበሩት መንግሥታት ትምህርት ቤቶች ውስጥ 137 ሺህ 500 ፍልስጥኤማውያን ተጠልለው ይገኛሉ ተብሏል።በጋዛ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የፍልስጥኤም ስደተኞች ኤጀንሲ ጽህፈት ቤት በአየር ጥቃቱ ጉዳት ደርሶበታል ተብሏል።በጋዛ የሚገኙ የምግብ ማከፋፈያ ማዕከላት በመዘጋታቸው ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ፍልስጥኤማውያን የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እርዳታ ማግኘት አልቻሉም ተብሏል።እስራኤል ጋዛ ሰርጥን ሙሉ በሙሉ በመዝጋት ከበባ እንዲደረግ አዛለች። በጋዛ ‘ኤሌክትሪክ፣ ምግብ፣ ነዳጅ አይኖርም ሲሉም የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት ትዕዛዝ ሰጥተዋል።ጋዛ ሰርጥ ወደ 2.3 ሚሊዮን የሚጠጉ ፍልስጥኤማውያን መኖሪያ ስትሆን ለ16 ዓመታት ያህል የቆየ ከበባ ውስጥ ትገኛለች።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 5:185:18ሐማስ በእስራኤል ላይ ለፈጸመው ጥቃት ምክንያቱ ምንድን ነው?ፍልስጥኤማዊው ታታቂ ቡድን ሐማስ ቅዳሜ መስከረም26/2016 ዓ.ም. በእስራኤል ላይ የፈጸመው ጥቃት በመጠኑ እና ባደረሰው ጉዳት ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ነው። ክስተቱ በድነገት ያጋጠመ ቢሆንም ለአስርታት በፍልስጥኤማውያን እና በእስራኤል መካከል የዘለቀው ውጥረት ውጤት ነው። ሐማስ እንደሚለው ለዚህ ጥቃት በርካታ ምክንያቶች ኣሉት ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል አራቱን እንደመልከት።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 4:274:27በእስራኤል የሚገኙ ኤርትራውያን ተጎጂዎችን ለመርዳት አልባሳት እያሰባሰቡ ነውበእስራኤል የሚኖሩ ኤርትራውያን በአገሪቷ ደቡባዊ ክፍል የሚገኙ ተጎጂዎችን ለመርዳት አልባሳት፣ ውሃ እና አስፈላጊ ቁሳቁሶችን እያሰባሰቡ ነው።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:283:28የእስራኤል ጦር በጋዛ ድንበር 35 ክፍለ ጦር ማሰማራቱን አስታወቀ
EPACopyright: EPAየእስራኤል መከላከያ ኃይል በጋዛ ሰርጥ ድንበር 35 ክፍለ ጦር ማሰማራቱን አስታውቋል።እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ እየፈጸመቻቸው ካሉ የአየር ጥቃቶች በተጨማሪ በምድር ላይ ከፍተኛ ወታደራዊ ጥቃት በቅርቡ ትጀምራለች ተብሎ ይጠበቃል።“ለወደፊት ለሚደረገው ዘመቻ መንገድ እያመቻቹ መሆናቸውንም” የሰራዊቱ ቃለ አቀባይ ሪቻርድ ሄክት ተናግረዋል።አንድ ክፍለ ጦር በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ይዟል።የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በጋዛ ላይ እየተፈጸሙ ያሉ የአየር ጥቃቶች ገና እየጀመሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:163:16እስራኤል በጋዛ የስደተኞች ካምፕን በአየር ደበደበች
ReutersCopyright: Reutersእስራኤል በጋዛ ሰርጥ በስተሰሜን በሚገኘው የጃባሊያ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ላይ የአየር ጥቃት ፈጸመች።በዚህም የአየር ጥቃት ቢያንስ 15 ሰዎች መሞታቸውን የፍልስጥኤም ባለስልጣናት ተናግረዋል።እስራኤል ገና የመጀመሪያው ነው ባለችው ተከታታይ የአየር ጥቃቶች በርካታ ህንጻዎች መውደማቸውን ከአካባቢው የወጡ ምስሎች አሳይተዋል።የእስራኤል አየር ኃይል በአንድ ምሽት 200 የታጣቂ ኢላማዎችን መምታተቱን አስታውቋል።ከቅዳሜ ጀምሮ በቀጠለው የአየር ጥቃቶች ወደ 700 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
ReutersCopyright: Reuters
ReutersCopyright: Reuters
ReutersCopyright: ReutersArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:013:01የእስራኤል ባለሥልጣናት ጋዛ ‘በቅርቡ የነዳጅ፣ መድኃኒት እና የምግብ አቅርቦት አይኖራትም’ አሉእስራኤል እና ሐማስ በገቡበት ግጭት ምክንያት የእስራኤል የእስራኤል ባለሥልጣናት ወደ ጋዛ የሚሄዱ የነዳጅ፣ የመድኃኒት እና የምግብ አቅርቦቶችን እንሚቋረጡ ተናገሩ። እነዚህ መሠረታዊ አቅርቦቶች የሚቋረጡ ከሆነ ወትሮም በችግር ውስጥ በምትገኘው ጋዛ ሰርጥ ያለው የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ቀውስ ክፉኛ ይባባሳል ተብሎ ተሰግቷል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:342:34የእስራኤል መከላከያ ፍልስጥኤማውያን ወደ ግብጽ እንዲሻገሩ መከረ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤል መከላከያ ፍልስጥኤማውያን ጋዛን ለቀው ወደ ግብጽ እንዲሻገሩ ምክሩን ሰጥቷል።የእስራኤል መከላከያ ይህንን መልዕክቱን ያስተላለፈው እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ እየፈጸመች ያለቸውን የአየር ጥቃቶች አጠናክራ በቀጠለችበት ወቅት ነው።”ወደ ግብጽ የሚያሻግረው የራፋህ ድንበር አሁንም ክፍት እንደሆነ አውቃለሁ” በማለት ኮሎኔል ሪቻርድ ሄችት ተናግረዋል።አክለውም “መውጣት የሚችል ማንኛውም ሰው እንዲወጣ እመክራለሁ” ብለዋል። የእስራኤል መከላከያ ከጋዛ ጋር ያለው ድንበር ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አስታውቋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:281:28የአፍሪካ አገራት በእስራኤል እና ሐማስ ግጭት የተለያየ አቋም ይዘዋልየአፍሪካ መሪዎች የፍልስጥኤም ታጣቂ ቡድን ሐማስ በሰነዘረው ድንገተኛ ጥቃት ምክንያት የተቀሰቀሰውን ግጭት እንዲያቆሙ ሁሉንም ተፋላሚ ወገኖች ጠይቀዋል።የአገራቱ አቋም ግን ሙሉ ለሙሉ ተመሳሳይ አልነበረም።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:181:18የፍልስጥኤም ደጋፊዎች በተለያዩ አገራት የአደባባይ ተቃውሞ አደረጉ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesበአሜሪካዋ ማንሃተን የፍልስጥኤም ደጋፊዎች ነጻ ፍልስጥኤም የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋልImage caption: በአሜሪካዋ ማንሃተን የፍልስጥኤም ደጋፊዎች ነጻ ፍልስጥኤም የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋልፍልስጥኤምን የሚደግፉ ሰላማዊ ሰልፎች በተለያዩ አገሮች ተደረጉ። በነዚህ ሰልፎች ላይ ነጻ ፍልስጥኤም የሚሉ እና እስራኤል በጋዛ ላይ እያደረገችው ያለውን የአየር ጥቃት የሚቃወሙ መፈክሮች ታይተዋል።
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesበሺዎች የሚቆጠሩ የፍልስጥኤም ደጋፊዎች በለንደን በሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ አቅራቢያ ትናንት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። እስራኤል በፍልስጥኤማውያን ላይ የምታደርገውን ጭቆና እና የኃይል እርምጃ እንድታቆም ጠይቀዋልImage caption: በሺዎች የሚቆጠሩ የፍልስጥኤም ደጋፊዎች በለንደን በሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ አቅራቢያ ትናንት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። እስራኤል በፍልስጥኤማውያን ላይ የምታደርገውን ጭቆና እና የኃይል እርምጃ እንድታቆም ጠይቀዋል
EPACopyright: EPAበኒውዮርክ ለፍልስጥኤም የተደረገ ሰልፍImage caption: በኒውዮርክ ለፍልስጥኤም የተደረገ ሰልፍ
EPACopyright: EPAበለንደን የፍልስጥኤም ደጋፊዎች ያደረጉት የተቃውሞ ሰልፍImage caption: በለንደን የፍልስጥኤም ደጋፊዎች ያደረጉት የተቃውሞ ሰልፍArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:580:58ምዕራባውያን ለእስራኤል ያላቸውን ድጋፍ ገለጹ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesበለንደን የሚገኘው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለእስራኤል ድጋፍ ለማሳየት በሰንደቅ አላማዋ ሰማያዊ እና ነጭ መብራቶች ሰኞ እለት ደምቆ ነበርImage caption: በለንደን የሚገኘው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለእስራኤል ድጋፍ ለማሳየት በሰንደቅ አላማዋ ሰማያዊ እና ነጭ መብራቶች ሰኞ እለት ደምቆ ነበር
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesዋይት ሃውስ በእስራኤል ሰንደቅ ዓላማImage caption: ዋይት ሃውስ በእስራኤል ሰንደቅ ዓላማ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየፓሪሱ አይፍል ታወርም ከእስራኤል ሰንደቅ ዓላማ በተጨማሪ የዳዊት ኮከብን በማሳየት ድጋፋቸውን ገልጸዋል።Image caption: የፓሪሱ አይፍል ታወርም ከእስራኤል ሰንደቅ ዓላማ በተጨማሪ የዳዊት ኮከብን በማሳየት ድጋፋቸውን ገልጸዋል።
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesፍልስጥኤማውያንን በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ የተደረገባት የሲድኒ ኦፔራ ሃውስ ለእስራኤልም ድጋፍ ለማሳየት ህንጻው በሰማያዊ እና በነጭ ሰንደቅ አላማ መብራት በርቶ ነበርImage caption: ፍልስጥኤማውያንን በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ የተደረገባት የሲድኒ ኦፔራ ሃውስ ለእስራኤልም ድጋፍ ለማሳየት ህንጻው በሰማያዊ እና በነጭ ሰንደቅ አላማ መብራት በርቶ ነበርArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:150:15እስራኤልን ባስደነገጠው የሐማስ ጥቃት የተቀሰቀሰው ቀውስ ወዴት ያመራ ይሆን?ከ50 ዓመታት በፊት ግብፅ እና ሶሪያ በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት በፈጸሙበት ተመሳሳይ ዕለት ሐማስም ያልተጠበቀ ከባድ ጥቃት ፈጽሞ ጦርነት ተቀስቅሷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአካባቢው ውጥረት እየጨመረ ቢመጣም ከዚህ በፊት እንደታየው ጋዛን የሚያስተዳድረው ሐማስም ሆነ እስራኤል ግጭት እንዲፈጠር አይፈልግጉም ተብሎ ሲታመን ቆይቷል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 13:49 9 ጥቅምት 202313:49 9 ጥቅምት 2023ሐማስ ላይ የምንወስደው እርምጃ ገና መጀመሩ ነው፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ
ReutersCopyright: Reutersየእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ የሐማስን ጥቃት ተከትሎ የእስራኤል ሠራዊት እየወሰደ ያለው የአጸፋ እርምጃ “ገና መጀመሩ ነው” ሲሉ ተናገሩ።በእስራኤል ግዛት በአስርት ዓመታት ውስጥ አጋጥሞ የማያውቅ ነው በተባለው የሐማስ ጥቃት በእጅጉ የተቆጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአገራቸው ምላሽ ቀጣይ መሆኑን ገልጸዋል።ኔታኒያሁ ይህንን የተናገሩት የሐማስ ጥቃት ዋነኛ ኢላማ ከሆነችው ደቡባዊ እስራኤል ከመጡ ባለሥልጣናት ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት ነው።ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ሐማስ የሚገጥመው ፈተና ከባድ እና አስከፊ” ነው ማለታቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ (ኤኤፍፒ) ዘግቧል።አክለውም “አሁን ያለው ሁኔታ ገና የመጀመሪያው ነው… ሁላችንም አብረናችሁ ነን፤ በከባድ ኃይል እናሸንፋቸዋለን” ብለዋል።ሐማስ ወደ እስራኤል ዘልቆ በመግባት ጥቃቱን ከጀመረ አንስቶ ከ700 በላይ ሰዎች እስራኤል ውስጥ ሲገደሉ፣ እስራኤል በከፈተችው የአየር ጥቃት ደግሞ ቢያንስ 560 ሰዎች ጋዛ ውስጥ ተገድለዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 10:20 9 ጥቅምት 202310:20 9 ጥቅምት 2023ኳታር ከሐማስ ባለሥልጣናት ጋር ሽምግልና መጀመሯ ተነገረየኳታር አሸማጋዮች በሐማስ ታጣቂዎች ተይዘው ወደ ጋዛ ስርጥ የተወሰዱ እስራኤላውያን ሴቶች እና ሕጻናትን ለማስለቀቅ ጥረት እያደረጉ መሆናቸው ተሰማ።ሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው ኳታራውያን አደራዳሪዎች በሐማስ የተያዙትን እስራኤላውያን ለማስለቀቅ ከቡድኑ ባለሥልጣናት ጋር ግንኙነት እያደረጉ ነው።እየተደረገ ስላለው ንግግር መረጃ ያላቸው ምንጮች ለሮይተርስ እንደተናገሩት ኳታራውያኑ አደራዳሪዎች በሐማስ የተያዙትን፣ እስራኤል ውስጥ በእስር ላይ በሚገኙ 36 ፍልስጥኤማውያን ሴቶች እና ሕጻናት በመለዋወጥ እንዲለቀቁ ሃሳብ አቅርበዋል።ምንጮች እንዳሉት በኳታር አማካይነት የተካሄደው ንግግር ከአሜሪካ ጋር በመተባበር ነው።ነገር ግን አስካሁን ስለዚህ ጉዳይ እስራኤልም ሆነች ሐማስ በቀጥታ አስተያየታቸውን አልሰጡም።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:59 9 ጥቅምት 20238:59 9 ጥቅምት 2023ብሪታኒያ እና አሜሪካ ዜጎቻቸው እስራኤል ውስጥ መሞታቸው ወይም መጥፋታቸውን አስታወቁ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesሐማስ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ብሪታኒያ እና አሜሪካ እስራኤል ውስጥ የሚገኙ ዜጎቻቸው መሞታቸውን እና የደረሱበት አለመታወቁን ገለጹ።ብሪታኒያ እስራኤልው ውስጥ ከሚገኙ ዜጎቿ መካከል አስካሁን ከ10 በላይ የሚሆኑት ሞተው ወይም ጠፍተው ሊሆኑ እንደሚችል ስጋቷን ገለጸች።የእራኤል ዋነኛዋ ወዳጅ አሜሪካ ደግሞ ዘጠኝ ዜጎቿ አስራኤል ውስጥ መሞታቸውን የአሜሪካ መንግሥት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።ቢቢሲ ከይፋዊ የዩናይትድ ኪንግደም ምንጮች እንደተረዳው “ከ10 የሚበልጡ” የብሪታኒያ ዜጎች የሮኬት ጥቃቶቹን ተከትሎ ሞተዋል ወይም የደረሱበት አልታወቀም ተብሎ ተሰግቷል።የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ዋይት ሐውስ ባወጣው መግለጫ ላይ ዘጠኝ አሜሪካውያን መሞታቸውን አረጋግጦ ጥልቅ ሐዘኑን በመግለጽ፣ ጉዳት የደረሰባቸውም በቶሎ እንዲያገግሙ መልካሙን ተመኝቷል።ጨምሮም በእስራኤል ውስጥ የተከሰተውን ሁኔታ የአሜሪካ መንግሥት በቅርበት እንደሚከታተለው እና ከእስራኤል መንግሥት በተለይም ከአካባቢ ባለሥልጣናት ጋር ግንኙነቱን እንደሚቀጥል አመልክቷል።አሜሪካ በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ ግዙፍ የጦር መርከቧን ወደ እስራኤል አንቀሳቅሳለች።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 6:50 9 ጥቅምት 20236:50 9 ጥቅምት 2023ከጋዛ የተወነጨፉ ሮኬቶች በማዕከላዊ እስራኤል ጉዳት አደረሱ
ReutersCopyright: Reutersከጋዛ ሮኬቶች መወንጨፋቸውን ቀጥሏል።ከጋዛ ሰርጥ በስተሜን በምትገኘው አሽኬሎን በተወነጨፉ ሮኬቶች አራት ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል።ከነዚህም መካከል አንደኛው በጠና ቆስሎ ለህክምና ወደ ሆስፒታል መወሰዱን የእስራኤል የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት አስታውቋል።በአቅራቢያው በሚገኘው አሽዶድ አንዲት ሴት የከፋ ጉዳት ደርሶባት ወደ ሆስፒታል ተወስዳለች።