
በደቡብ ጎንደር በተደረገ የደፈጣ ውጊያ አራት ከፍተኛ የአማራ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ 15 ጠባቂ የአድማ ብተና ቡድን መገደላቸው ተሰማ
በደቡብ ጎንደር አለም በር አቅራቢያ ወደ ደብረታቦር እየተጓዘ የነበረየአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናትንና የፀጥታ አካላትን የያዘ ቡድን እርምጃ እንደተወሰደትና በጥቃቱም አራት የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናትና 15 ጠባቂ የአድማ በተና ሃይሎቸ መገደላቸውን አንከር ሚዲያ የደፈጣ ውጊያውን ከመራው ኮማንደር ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ለማወቅ ተቾሏል። ፋኖ በወሰደው እርምጃም የክልሉ አፈጉባኤ አመራር፥ የደቡብ ጎንደር አድማ ብተና አዛዥ እና ሌሎቸ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች መገደላቸውን ለማወቅ ተችሏል።
ፋኖ ንፁሃንን ሳይገድሉ ከነመሳሪያቸው እጃቸውን የሚሠጡ የሥርዓቱ ወታደሮችን በሰላም ወደቤተሰቦቻቸው እየሸኘ መሆኑን አስታውቋል።
በጎጃም አማራ ቀጠና ብቻ ከተያዙት ውስጥ 1640 ያህል ወታደሮች ደቡብ ኢትዮጵያ ከሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ጋር በሰላም መቀላቀላቸውን፤ 300 ያህል ቆስለው በህክምና ላይ እንደሚገኙና ሌሎች 6000 ያህል ወታደሮች ደግሞ ሕዝባዊ ኃይሉን ተቀላቅለው ሥርዓቱን እየተዋጉ እንደሚገኙ ተገልጿል። ከዚህ ቀደም ተማርከው የተለቀቁና ለ2ኛ ጊዜ የተማረኩ፣ ንፁሃንን ሲገድሉ የተያዙ እና በመድፈር የተሳተፉ ወታደሮች ብቻ በእጃቸው እንደሚገኙ የቀጠናው ፋኖ ቃል- አቀባይ ገልፆልናል። በሌሎች ግምባሮችም እየተጣራ ተመሳሳይ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል።
ፋሽስቱ መከላከያ ሠራዊት ውስጥ ልጆቻችሁን የላካችሁ ቤተሰቦች ልጆቻችሁን በዓይነ-ስጋ ማየት ከፈለጋችሁ እየደወላችሁ እጅ እንዲሰጡ አድርጉ። የዐቢይ አህመድ ዙፋን እግሩ ተሰብሯል፤ በድሀ ልጆች ደም ሊጠገን ከማይችልበት ደረጃ ደርሷል። ሞት ሳይቀድማችሁ ቅደሙት!!
