October 10, 2023 

የአብይ ወራሪ ሰራዊት ገዳይ ቡድን ዛሬ በ29/1/2016 ዓ.ም  ከሞጣ ወደ አዴት መስመር አቅጣጫ በእግረኛ ጦር መልኩ ከጠዋቱ 1:48 ሰዓት ጀምሮ እየተጓዘ ይገኛሉ።ልዬ ቦታዉ ሙገር አለፍ ብለዉ ከጠዋቱ 2:30 አካባቢ መድረሳቸዉን በተጨባጭ መረጃ ለማረጋገጥ ተቸሏል።

በሌላ በኩል ትናንት በ28/1/2016 ዓ.ም  መነሻዉ ከአዴት ያደረገ የጠላት ኃይል ወደ ደጋ ዳሞት፣ቋሪት፣ሰከላ እና ሌሎች ቦታዎች ወደሚያዋስን መስመር በመሄድ ልዬ ቦታዉ ጎሽዬ ያመሸዉ መንጋ ከባድ መሳሪያ አስወጭፏል። በጎሽዬ አካባቢ በመኖሪያ ቤት ለቤት በመግባት መሳሪያ አምጡ  እያሉ እንዳመሹ የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል ዛሬም በ29/1/2016 ዓ.ም በዚህ ቦታ ሰፍረዉ ይገኛሉ።በሌላ በኩል ትናንት በ28/1/2016 ዓ.ም  ከሰዓት 10:00 ሰዓት ገደማ ሁለት ሄሌኮፍተር ብርሸለቆ የጠላት ኃይል ተራግፏል በመጣበት መንገድ በነበልባሉ ፋኖ ዋጋዉን ያገኛል ተብሏል።

ትናንት በደቡብ ወሎ ዞን ሳይንት ዴንሳ ከተማ የፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የፋኖ አባላት ላይ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት እያደረጉ ባለበት ሰዓት ድንገተኛ ጥቃት ተፈፅሞ የወረዳው የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊ፣ የፖሊስ አስተባባሪ እና የሚሊሻ አስተባባሪው ህይወታቸው አልፏል። ጥቃቱ የተፈፀመው በፖሊስ ጣቢያው ተሰብስበው ስምሪት እየወሰዱ ባለበት ሰዓት ከቀኑ 8:30 ገደማ ነው ተብሏል

ትናንት ገንጅ ምድር በተአምር ተርፎ የወጣው 12 መኪና የጠላት ጦር ባህር ዳር ድንበር ሰባታሚት ነበር ከትናንት ምሽት ጀምሮ ያረፈው። ዛሬ የተወሰነ ሰአታት በወሰደ ውጊያ የአካባቢው ህዝብ እና በኢንጅነሩ ፋኖ የሚመራው የጎጃም ፋኖ ዕዝ  የባህር ዳር ፋኖ ጠንካራ ዱላ አሳርፈውበት የጠላት ጦር ከሰባታሚት ወደ መኮድ የእውር ድንብሩን እየፈረጠጠ ነው። ፋኖ እግር በእግር እያሳደደው ይገኛል።

ዛሬ አዴት ከተማ የገባው የጥላት ኃይል በከተማዋ በሁሉም አቅጣጫዎች ተከቦ እየተወቀጠ ነው። ውጊያ ሐይስኩል ትምህርት ቤቱ አካባቢ (መሽጎበት ከነበረው ቦታ) ላይ ተጀምሯል።