October 10, 2023 

ባንዳዎች ተመስገን ጥሩነህ እና አበባው ታደሰም የውጭ እድል አጥተው እንጂ መኮብለል ይፈልጋሉ ተብሏል ::

አቶ አሰማኸኝ አስረስ ከሀገር መዉጣታቸው ተሰማ::

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና የቋሚ ኮሚቴዉ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አሰማኸኝ አስረስ ከሀገር መዉጣታቸዉን አስታወቁ።

የአማራ ክልል ኮምኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ ሆነዉ ያገለገሉት አቶ አሰማኸኝ አስረስ  በአማራ ክልል ከተፈጠረዉ ክስተት ጋር ተያይዞ  የወጣዉ የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት  በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በሚፀድቅበት ጊዜ አለመገኘታቸዉን የገለፁ ሲሆን በአሁኑ ሰዐትም ክልሉ ካለበት ነባራዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ  መንግስት ጥቃት ወይም እስር ሊያደርስባቸዉ እንደሆነ በመስጋት እና እኔም ያገለገልኩት ስርዐት ሀገር እያፈረሰ ነዉ ብለዉ በማመናቸው ምክንያት ከሀገር ለመሰደድ መገደዳቸዉን ለበይነ መረብ ሚዲያዎች በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

አመራሩ በአማራ ክልል በአሁን ሰዐት መንግስት የለም ያሉ ሲሆን ዝቡም የኔትወርክን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን በማያገኝበት ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረዋል።”
ሮሃ ሚዲያ