Skip to content
ጭምቅ ሃሳብ
- በጋዛ 187 ሺህ ፍልስጥኤማውያን ተፈናቅለዋል
- በእስራኤል እና በጋዛ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሺህ በላይ ሆነ
- በጋዛ ከ123 ሺህ በላይ ፍልስጥኤማውያን ተፈናቀለዋል
- ኢራን፣ ሐማስ በፈጸመው ጥቃት ላይ ተሳትፎ የለኝም አለች
- እስራኤል በሊባኖስ ላይ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት ፈጸመች
- የእስራኤል ጦር በሃማስ ላይ ለሚሰነዘረው የአጸፋ ጥቃት በጋዛ ሰርጥ የሚኖሩ ነዋሪዎች ቤታቸውን ለቀው እንዲለቁ ጠየቀ
- ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ “ጥቁር ቀን” ብለው ለጠሩት ጥቃትም ምላሽ በፍልስጥኤም ታጣቂዎች ላይ “ከፍተኛ የበቀል እርምጃ” እንደሚወስዱ አስጠንቅቀዋል።
- በግብጽ ሁለት እስራኤላውያን ቱሪስቶች በተተኮሰባቸው ጥይት ተገደሉ
- የፍልስጥኤም ታጣቂ ቡድን ሃማስ ያልተጠበቀ የተባለውን ከሁለት ሺህ በላይ ሮኬቶችን በእስራኤል ላይ ተኩሰዋል።
- በጥቃቱ 250 ሰዎች ሲገደሉ በርካታ እስራኤል ታግተዋል ተብሏል።
- እስራኤል በምላሹ ተከታታይ የአየር ጥቃቶችን በጋዛ ላይ የፈጸመች ሲሆን በዚህም ከ230 ሰዎች በላይ ተገድለዋል።
- እስራኤል የጋዛን መሰረታዊ አገልግሎቶች ታቋርጣለች- ኔታንያሁ
- የሃማስ ታጣቂዎች በእስራኤል ውስጥ ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ነው አሉ
- 313 ፍልስጥኤማውያን እና 300 እስራኤላውያን መገደላቸው ተነገረ
- የታተመዉ 2:472:47የፍልስጥኤማውያን የተቃውሞ ሰልፍ በዌስት ባንክ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤልን ጥቃት በመቃወም ዌስት ባንክ ራማላህ ውስጥ ሰልፍ የወጡ ፍስጥኤማውያንImage caption: የእስራኤልን ጥቃት በመቃወም ዌስት ባንክ ራማላህ ውስጥ ሰልፍ የወጡ ፍስጥኤማውያንዛሬ ረቡዕ ማለዳ ጎህ ሲቀድ ከጋዛ ባሻገር በወረራ በተያዘችው ዌስት ባንክ ውስጥ ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጥኤማውያን እስራኤል በጋዛ ላይ እየፈጸመችው ያለውን የአውሮፕላን ድብደባ በመቃወም ሰልፍ አድርገዋል።የፍልስጥኤም ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ የፍልስጥኤምን ሰንደቅ ዓላማ እና በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎችን ፎቶፍራፎች ይዘው ነው አደባባይ የወጡት።Article share tools
- የታተመዉ 2:392:39ኢራን በእስራኤል ላይ ለተፈጸመው ጥቃት ድጋፏን ሰጥታ ይሆን?የሐማስ ታጣቂዎች ከፍተኛ ቅንጅት ታይቶበታል የተባለውን ጥቃት በእስራኤል ላይ መፈጸማቸውን ተከትሎ የኢራን ስም በተደጋጋሚ እየተነሳ ይገኛል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ኢራን በጥቃቱ ተሳትፎ ነበራት ወይ? የሚለው ጥያቄ ከተለያዩ ወገኖች እየተመላለሰ የሚነሳ ሆኗል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- የታተመዉ 1:271:27የቀጠለው የእስራኤል ጥቃት እና የአውሮፓ ኅብረት ትችት
Getty ImagesCopyright: Getty Images- ሌሊቱን የእስራኤል አየር ኃይል የጦር ጄቶች የሐማስ የሮኬት ጥቃቶች የሚወነጨፉበት ነው ባለው የጋዛው አል-ፉርቃን አካባቢ ያሉ ከ200 በላይ ኢላማዎች ላይ ድብደባ መፈጸሙን ገልጿል። ይህም ጥቃት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ የተፈጸመ ሦስተኛው ድብደባ ነው።
- እስራኤል ሌሊቱን ጋዛ ላይ በፈጸመችው የአየር ድብደባ ቢያንስ 30 ሰዎች መገደላቸውን የሐማስ ቃል አቀባይ አስታወቁ።
- የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሆኑት ጆሴፍ ቦሬል እስራኤል በጋዛ ላይ እየወሰደች ያለችው እርምጃ ዓለም አቀፍ ሕግን የጣሰ ነው ሲሉ ተቹ። “እስራኤል እራሷን የመከላከል መብት ቢኖራትም ይህንን ማድረግ ያለባት በዓለም አቀፍ ሕጎች መሠረት መሆን አለበት” ብለዋል።
- የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሐማስን ጥቃት አጥብቀው ያወገዙ ሲሆን አሜሪካ ለእስራኤል የምትሰጠውን ወታደራዊ ድጋፍ በማጠናከር የመጀመሪያው የጦር መሳሪያ ድጋፍ ማክሰኞ ደቡባዊ እስራኤል ደርሷል።
- የጋዛ ነዋሪዎች “ደኅንነቱ የተጠበቀ መተላለፊያ” እንዲያገኙ ከእስራኤል እና ከግብፅ ጋር እየተነጋገረች መሆኗን የአሜሪካ ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጃክ ሰሊቫን ገለጹ።
- አስካሁን ከፍልስጥኤም እና ከእስራኤል ወገን የሞቱት ሰዎች አሃዝ በአጠቃላይ ወደ 2,100 ሲደርስ፣ ከእስራኤል በኩል 1,200፣ ከፍልስጥኤም ወገን ደግሞ 900 ሰዎች ተገድለዋል።
- በጥቃቶቹ የደረሰው ጉዳት ታይቶ የማይታወቅ መሆኑን እስራኤላውያን እና ፍልስጥኤማውያን እየተናገሩ ነው። እስራኤላውያን “በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመ ጭፍጨፋ ነው” ሲሉ፣ ፍልስጥኤማውያን ደግሞ “ሕይወታችንን የምናድንበት ቦታ አጣን” እያሉ ነው።
Article share tools
- የታተመዉ 1:011:01እስራኤል ከሶሪያ በኩል ለተሰነዘረ ጥቃት አጸፋውን መመለሷን ገለጸችየእስራኤል ጦር ሠራዊት ከሶሪያ በኩል ወደ ጉላን ተራሮች ለተሰነዘረ የከባድ መሳሪያ ጥቃት በመድፍ ተኩስ ምላሽ መስጠቱን ገለጸ።የጎላን ተራሮች የ1967ቱን የአረብ እስራኤል ጦርነትን ተከትሎ እስራኤል አስካሁን ድረስ በወረራ የያዘቻቸው መሆኑ ይታወቃል።የእስራኤል ጦር ባወጣው መግለጫ ከሶሪያ በኩል የተሰነዘረውን የከባድ መሳሪያ ጥቃት ተከትሎ “ወታደሮቻችን መድፍ እና ሞርታር ጥቃቱ ወደ ተነሳበት ስፍራ በአጸፋው ተኩሰዋል” ብሏል።ጨምሮም ቀደም ሲልም በርካታ ጥቃቶች ከሶሪያ በኩል ወደ እስራኤል ግዛቶች መፈጸማቸውን ገልጿል።የእስራኤል ጦር ሠራዊት ቃል አቀባይ ለፈረንሳይ ዜና ወኪል ኤኤፍፒ ጥቃቶቹ በሞርታር እንደተፈጸሙ ገልጸዋል።ሐማስ ባለፈው ቅዳሜ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ግጭቱ ከተባባሰ በኋላ በእስራኤል እና በሶሪያ መካከል የከባድ መሳሪያ ተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ ይህ የመጀመሪያው ነው።Article share tools
- የታተመዉ 0:200:20በአራት ቀናት ውስጥ ከ260 ሺህ በላይ ፍልስጥኤማውያን ከጋዛ ተፈናቅለዋል፡ የተባበሩት መንግሥታት
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤል ጦር ሠራዊት የፍልስጥኤሟን ግዛት ጋዛን በጦር አውሮፕላኖች መደብደቡን በቀጠለበት በአሁኑ ጊዜ ከ260 ሺህ በላይ ሰዎች ከጋዛ መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታት አስታወቀ።ድርጅቱ እንዳለው ይህ በአራት ቀናት ያጋጠመው የነዋሪዎች መፈናቀል ከሰባት ዓመት በፊት ጋዛ ውስጥ ሁለት ወራት ለሚጠጋ ጊዜ ቆይቶ በነበረው ግጭት ከተፈናቀሉት የበለጠ ነው። የተፈናቃዮች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊጨምር እንደሚችል ይጠበቃል።ጋዛ ሰርጥ ውስጥ 2.3 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች የሚኖሩ ሲሆን፣ በጠባብ ስፍራ ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ተጠጋግተው ከሚኖሩባቸው ቦታዎች መካከል የሚጠቀስ ነው።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጨምሮ እንዳለው ለቀናት በቀጠለው የአየር ጥቃት ጋዛ ውስጥ ከአንድ ሺህ በላይ የመኖሪያ ቤቶች ወድመዋል።የእስራኤል የአየር ጥቃት በቀጠለበት ሁኔታ በጋዛ ውስጥ ለሚገኙ ነዋሪዎች መሠረታዊ አቅርቦቶችን ማሟላት “በጣም ፈታኝ” እየሆነ መምጣቱ ተገልጿል።ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በቀጠለው ግጭት እስካሁን በእስራኤል በኩል 1,200 እንዲሁም ከፍልስጥኤም ወገን ደግሞ ከ900 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።Article share tools
- የታተመዉ 12:31 10 ጥቅምት 202312:31 10 ጥቅምት 2023የዛሬ ዋና ዋና ክስተቶች በአጭሩ
BBCCopyright: BBCባለፈው ቅዳሜ የተቀሰቀሰው የእስራኤል እና የሐማስ ውጊያ ለአራተኛ ቀን ቀጥሎ እስራኤል ጋዛን በጦር ጀቶቿ ስትደበድብ፣ ሐማስ ደግሞ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል መተኮሱን ቀጥሏል።በዛሬው ዕለት የተከሰቱ ቁልፍ ነገሮችን አጭሩ እነሆ፡…- ·የሐማስ ታጣቂዎች እስራኤላውያን ነዋሪዎች አሽኬሎን ከተባለችው ከተማ ለቀው እንዲወጡ አሰጠንቅቀው አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ የሮኬት ተኩስ በከተማዋ ውስጥ ተሰምቷል።
- ·የሐማስን ጥቃት ተከትሎ የደረሱበት ያልታወቁ የአሜሪካ ዜጎች ዘመዶች በእስራኤሏ መዲና ቴል አቪቭ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እየጠበቋቸው ስላሉት የቤተሰቦቻቸው አሳዛኝ ታሪኮችን ተናግረዋል።
- ·ከቅዳሜ ጀምሮ በእስራኤል የአየር ድብደባዎች የተገደሉ ፍልስጥኤማውያን ቁጥር ወደ 830 ሲደርስ፣ በእስራኤላውያን በኩል የተመዘገበው ሞት ደግሞ ቢያነስ 1,008 መድረሱ ተዘግቧል።
- ·ሐማስ “ውጊያው አስኪቆም ድረስ” በእገታው ስር ስላሉ እስራኤላውያን ጉዳይ እንደማይነጋገር አሳውቋል። አስካሁን ባለ መረጃ ከ100 አስከ 150 የሚደርሱ እስራኤላውያን በሐማስ እገታ ውስጥ እንዳሉ ይታመናል።
- ·እስራኤል ጋዛ ላይ የምትፈጽመው የአየር ጥቃት ቀን ከሌት ሳይል የቀጠለ ሲሆን፣ ሐማስም ሮኬቶቹን ማስወንጨፉን ቀጥሏል።
Article share tools
- የታተመዉ 8:52 10 ጥቅምት 20238:52 10 ጥቅምት 2023የሳዑዲው ልዑል ሞሐመድ ቢን ሳልማን ለፍልስጥኤማውያን ድጋፋቸውን ገለጹ
ReutersCopyright: Reutersልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማንImage caption: ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማንየሳዑዲው ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን አገራቸው የፍልስጥኤማውያን መብት እንዲከበር ድጋፏን እንደምትቀጥል ተናገሩ።ሳዑዲ አረቢያ መሪ የሆኑት ቢን ሳልማን ይህንን ያሉት እስራኤል በሐማስ የተፈጸመባትን ጥቃት ተከትሎ ጋዛ ውስጥ ከባድ ጥቃት እያካሄደች ባለበት ጊዜ ከፍልስጥኤም ፕሬዝዳንት ማሐሙድ አባስ ጋር በስልክ በተወያዩበት ጊዜ ነው።ቢን ሳልማን “ፍልስጥኤማውያን ተገቢ መብቶቻቸው፣ የተረጋጋ ሕይወት፣ ፍትሃዊ እና ዘላቂ ሰላምን እንዲያገኙ ለማስቻል” አገራቸው ድጋፏን ትቀጥላለች ብለዋል።ጨምረውም ከዓለም አቀፍ እና ከአካባቢያው ማኅበረሰብ ጋር በመሆን ግጭቱ እንዳይስፋፋ እየሰሩ መሆናቸውን ለአባስ ገልጸውላቸዋል።ፍልስጥኤሙ ፕሬዝዳንት ማሐሙድ አባስ እና ጋዛን የተቆጣጠረው ሐማስ የፖለቲካ ተቀናቃኞች ናቸው። አባስ ሌላኛውን የፍልስጥኤም ግዛት ዌስት ባንክን የተቆጣጠረው የፋታህ ንቅናቄ እና የፍልስጥኤም ነጻነት ድርጅት (ፒኤልኦ) መሪ ናቸው።ሳዑዲ አረቢያ ለፍልስጥኤም ያላትን ድጋፍ የገለጸችው በአሜሪካ አማካይነት ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት ለመሻሻል ድርድር እየተደረገ ባለበት ጊዜ ነው።ተንታኞች የተቀሰቀሰው ግጭት ግንኙነታቸውን ለማሻሻል በእስራኤል እና በሳዑዲ መካከል በሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት ደቅኗል ብለዋል።ቅዳሜ ዕለት የተፈጸመውን የሐማስን ጥቃት ተከትሎ ሳዑዲ አረቢያ ባወጣችው መግለጫ ለግጭቱ መባባስ እስራኤልን ተጠያቂ አድርጋለች።Article share tools
- የታተመዉ 8:15 10 ጥቅምት 20238:15 10 ጥቅምት 2023ውጊያው ሳይቆም በታጋቾች ጉዳይ ላይ አንደራደርም፡ ሐማስ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesውጊያው እስኪያቆም ድረስ በቁጥጥሩ ስር ስላሉ ታጋቾች ሐማስ ከእስራኤል ጋር እንደማይደራደር የቡድኑ ፖለቲካ ቢሮ ኃላፊ ኢስማኤል ሃኒያህ ተናገሩ።“በቁጥጥራችን ስር ያሉ የጠላት አስረኞች ጉዳይ ጦርነቱ ከማብቃቱ በፊት እንደማይነሳ ጥያቄ ላቀረቡልን ወገኖች ሁሉ አሳውቀናቸዋል” ያሉት ሃኒያህ ቡድናቸው “ጉዳዩን የሚቀበለው የሚፈልገውን ምላሽ ሲያገኝ ብቻ ነው” ብለዋል።ሐማስ ባለፈው ቅዳሜ በእስራኤል ላይ ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ፣ ከደቡባዊ እስራኤል አካባቢዎች በ100 እና በ150 መካከል የሚገኙ ሰዎች በፍልስጥኤማዊው ቡድን ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ተዘግቧል።የኳታር እና የአሜሪካ አሸማጋዮች ሐማስ እና እስራኤል በእጃቸው ያሉ ሴቶች እና ሕጻናት እስረኞችን እንዲለዋወጡ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ሮይርስ ዘግቦ ነበር።የሐማስ ጥቃትን ተከትሎ ለቀናት የቆየ የአጸፋ ጥቃት እየፈጸሙ ያሉት የእስራኤል መከላከያ ኃይሎች ዛሬ ማክሰኞም የሐማስ ናቸው ያሏቸውን ኢላማዎች ማጥቃታቸውን ቀጥለዋል።ሰኞ ሌሊት የእስራኤል አየር ኃይል 200 ኢላማዎችን ጋዛ ውስጥ መደብደቡን ገልጸዋል።Article share tools
- የታተመዉ 6:49 10 ጥቅምት 20236:49 10 ጥቅምት 2023ሰበርበጋዛ የተገደሉ ፍልስጥኤማውያን ቁጥር 770 ደረሰ
ReutersCopyright: Reutersእስራኤል በጋዛ ሰርጥ እየፈጸመቻቸው ያሉ የአየር ጥቃቶችን ተከትሎ በጋዛ ሰርጥ የተገደሉ ፍልስጥኤማውያን ቁጥር 770 ደረሰ።በተጨማሪም 4 ሺህ 100 መቁሰላቸውን የእስራኤል ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ሙሉ ከበባ እንዲፈጸም ትዕዛዝ መስጠቷን ተከትሎ የዓለም የጤና ድርጅት ለሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት መተላለፊያ እንዲኖር ጥሪ አቅርቧል።እስራኤል በጋዛ የኤሌክትሪክ፣ ምግብ፣ ነዳጅ እና ውሃ አቅርቦት እንዲቋረጥም ማድረጓን ተከትሎ ነው የዓለም የጤና ድርጅት እና ዩኒሴፍ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲገባ እየጠየቁ ያሉት።የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኃላፊ ቮልከር ቱርክ የሃማስን ጥቃት አውግዘው የእስራኤል ከበባ በዓለም አቀፍ ህግ መሰረት ህገወጥ ነው ብለዋል።Article share tools
- የታተመዉ 6:49 10 ጥቅምት 20236:49 10 ጥቅምት 2023በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት አጀማመር ምን ይመስላል?ቅዳሜ ዕለት በጋዛ የሚገኙ የፍልስጥኤም ታጣቂዎች ጥቃት ፈጽመዋል። ጥቃቱ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ ነው ተብሏል። ለመሆኑ ለቀናት ቀጥሎ የበርካቶችን ሕይወት የቀጠፈው ግጭት አጀማመር እና ዋና ዋና ጉዳዮች ምን ይመስላሉ?ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- የታተመዉ 6:11 10 ጥቅምት 20236:11 10 ጥቅምት 2023በጋዛ 187 ሺህ ፍልስጥኤማውያን ተፈናቅለዋል- ተመድ
ReutersCopyright: Reutersእስራኤል ገና መጀመሩ እንደሆነ በገለጸችው የጋዛ የአየር ጥቃቶችን ተከትሎ 187 ሺህ ፍልስጥኤማውያን መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል።ቁጥሩ ከዚህ ሊልቅ እንደሚችልም ነው ተመድ ያሳሰበው።በጋዛ ባሉ 83 የተባበሩት መንግሥታት ትምህርት ቤቶች ውስጥ 137 ሺህ 500 ፍልስጥኤማውያን ተጠልለው ይገኛሉ ተብሏል።በጋዛ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የፍልስጥኤም ስደተኞች ኤጀንሲ ጽህፈት ቤት በአየር ጥቃቱ ጉዳት ደርሶበታል ተብሏል።በጋዛ የሚገኙ የምግብ ማከፋፈያ ማዕከላት በመዘጋታቸው ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ፍልስጥኤማውያን የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እርዳታ ማግኘት አልቻሉም ተብሏል።እስራኤል ጋዛ ሰርጥን ሙሉ በሙሉ በመዝጋት ከበባ እንዲደረግ አዛለች። በጋዛ ‘ኤሌክትሪክ፣ ምግብ፣ ነዳጅ አይኖርም ሲሉም የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት ትዕዛዝ ሰጥተዋል።ጋዛ ሰርጥ ወደ 2.3 ሚሊዮን የሚጠጉ ፍልስጥኤማውያን መኖሪያ ስትሆን ለ16 ዓመታት ያህል የቆየ ከበባ ውስጥ ትገኛለች።Article share tools
- የታተመዉ 5:18 10 ጥቅምት 20235:18 10 ጥቅምት 2023ሐማስ በእስራኤል ላይ ለፈጸመው ጥቃት ምክንያቱ ምንድን ነው?ፍልስጥኤማዊው ታታቂ ቡድን ሐማስ ቅዳሜ መስከረም26/2016 ዓ.ም. በእስራኤል ላይ የፈጸመው ጥቃት በመጠኑ እና ባደረሰው ጉዳት ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ነው። ክስተቱ በድነገት ያጋጠመ ቢሆንም ለአስርታት በፍልስጥኤማውያን እና በእስራኤል መካከል የዘለቀው ውጥረት ውጤት ነው። ሐማስ እንደሚለው ለዚህ ጥቃት በርካታ ምክንያቶች ኣሉት ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል አራቱን እንደመልከት።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- የታተመዉ 4:27 10 ጥቅምት 20234:27 10 ጥቅምት 2023በእስራኤል የሚገኙ ኤርትራውያን ተጎጂዎችን ለመርዳት አልባሳት እያሰባሰቡ ነውበእስራኤል የሚኖሩ ኤርትራውያን በአገሪቷ ደቡባዊ ክፍል የሚገኙ ተጎጂዎችን ለመርዳት አልባሳት፣ ውሃ እና አስፈላጊ ቁሳቁሶችን እያሰባሰቡ ነው።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- የታተመዉ 3:28 10 ጥቅምት 20233:28 10 ጥቅምት 2023የእስራኤል ጦር በጋዛ ድንበር 35 ክፍለ ጦር ማሰማራቱን አስታወቀ
EPACopyright: EPAየእስራኤል መከላከያ ኃይል በጋዛ ሰርጥ ድንበር 35 ክፍለ ጦር ማሰማራቱን አስታውቋል።እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ እየፈጸመቻቸው ካሉ የአየር ጥቃቶች በተጨማሪ በምድር ላይ ከፍተኛ ወታደራዊ ጥቃት በቅርቡ ትጀምራለች ተብሎ ይጠበቃል።“ለወደፊት ለሚደረገው ዘመቻ መንገድ እያመቻቹ መሆናቸውንም” የሰራዊቱ ቃለ አቀባይ ሪቻርድ ሄክት ተናግረዋል።አንድ ክፍለ ጦር በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ይዟል።የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በጋዛ ላይ እየተፈጸሙ ያሉ የአየር ጥቃቶች ገና እየጀመሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል።Article share tools
- የታተመዉ 3:16 10 ጥቅምት 20233:16 10 ጥቅምት 2023እስራኤል በጋዛ የስደተኞች ካምፕን በአየር ደበደበች
ReutersCopyright: Reutersእስራኤል በጋዛ ሰርጥ በስተሰሜን በሚገኘው የጃባሊያ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ላይ የአየር ጥቃት ፈጸመች።በዚህም የአየር ጥቃት ቢያንስ 15 ሰዎች መሞታቸውን የፍልስጥኤም ባለስልጣናት ተናግረዋል።እስራኤል ገና የመጀመሪያው ነው ባለችው ተከታታይ የአየር ጥቃቶች በርካታ ህንጻዎች መውደማቸውን ከአካባቢው የወጡ ምስሎች አሳይተዋል።የእስራኤል አየር ኃይል በአንድ ምሽት 200 የታጣቂ ኢላማዎችን መምታተቱን አስታውቋል።ከቅዳሜ ጀምሮ በቀጠለው የአየር ጥቃቶች ወደ 700 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
ReutersCopyright: Reuters
ReutersCopyright: Reuters
ReutersCopyright: ReutersArticle share tools
- የታተመዉ 3:01 10 ጥቅምት 20233:01 10 ጥቅምት 2023የእስራኤል ባለሥልጣናት ጋዛ ‘በቅርቡ የነዳጅ፣ መድኃኒት እና የምግብ አቅርቦት አይኖራትም’ አሉእስራኤል እና ሐማስ በገቡበት ግጭት ምክንያት የእስራኤል የእስራኤል ባለሥልጣናት ወደ ጋዛ የሚሄዱ የነዳጅ፣ የመድኃኒት እና የምግብ አቅርቦቶችን እንሚቋረጡ ተናገሩ። እነዚህ መሠረታዊ አቅርቦቶች የሚቋረጡ ከሆነ ወትሮም በችግር ውስጥ በምትገኘው ጋዛ ሰርጥ ያለው የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ቀውስ ክፉኛ ይባባሳል ተብሎ ተሰግቷል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- የታተመዉ 2:34 10 ጥቅምት 20232:34 10 ጥቅምት 2023የእስራኤል መከላከያ ፍልስጥኤማውያን ወደ ግብጽ እንዲሻገሩ መከረ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤል መከላከያ ፍልስጥኤማውያን ጋዛን ለቀው ወደ ግብጽ እንዲሻገሩ ምክሩን ሰጥቷል።የእስራኤል መከላከያ ይህንን መልዕክቱን ያስተላለፈው እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ እየፈጸመች ያለቸውን የአየር ጥቃቶች አጠናክራ በቀጠለችበት ወቅት ነው።”ወደ ግብጽ የሚያሻግረው የራፋህ ድንበር አሁንም ክፍት እንደሆነ አውቃለሁ” በማለት ኮሎኔል ሪቻርድ ሄችት ተናግረዋል።አክለውም “መውጣት የሚችል ማንኛውም ሰው እንዲወጣ እመክራለሁ” ብለዋል። የእስራኤል መከላከያ ከጋዛ ጋር ያለው ድንበር ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አስታውቋል።Article share tools
- የታተመዉ 1:28 10 ጥቅምት 20231:28 10 ጥቅምት 2023የአፍሪካ አገራት በእስራኤል እና ሐማስ ግጭት የተለያየ አቋም ይዘዋልየአፍሪካ መሪዎች የፍልስጥኤም ታጣቂ ቡድን ሐማስ በሰነዘረው ድንገተኛ ጥቃት ምክንያት የተቀሰቀሰውን ግጭት እንዲያቆሙ ሁሉንም ተፋላሚ ወገኖች ጠይቀዋል።የአገራቱ አቋም ግን ሙሉ ለሙሉ ተመሳሳይ አልነበረም።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- የታተመዉ 1:18 10 ጥቅምት 20231:18 10 ጥቅምት 2023የፍልስጥኤም ደጋፊዎች በተለያዩ አገራት የአደባባይ ተቃውሞ አደረጉ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesበአሜሪካዋ ማንሃተን የፍልስጥኤም ደጋፊዎች ነጻ ፍልስጥኤም የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋልImage caption: በአሜሪካዋ ማንሃተን የፍልስጥኤም ደጋፊዎች ነጻ ፍልስጥኤም የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋልፍልስጥኤምን የሚደግፉ ሰላማዊ ሰልፎች በተለያዩ አገሮች ተደረጉ። በነዚህ ሰልፎች ላይ ነጻ ፍልስጥኤም የሚሉ እና እስራኤል በጋዛ ላይ እያደረገችው ያለውን የአየር ጥቃት የሚቃወሙ መፈክሮች ታይተዋል።
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesበሺዎች የሚቆጠሩ የፍልስጥኤም ደጋፊዎች በለንደን በሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ አቅራቢያ ትናንት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። እስራኤል በፍልስጥኤማውያን ላይ የምታደርገውን ጭቆና እና የኃይል እርምጃ እንድታቆም ጠይቀዋልImage caption: በሺዎች የሚቆጠሩ የፍልስጥኤም ደጋፊዎች በለንደን በሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ አቅራቢያ ትናንት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። እስራኤል በፍልስጥኤማውያን ላይ የምታደርገውን ጭቆና እና የኃይል እርምጃ እንድታቆም ጠይቀዋል
EPACopyright: EPAበኒውዮርክ ለፍልስጥኤም የተደረገ ሰልፍImage caption: በኒውዮርክ ለፍልስጥኤም የተደረገ ሰልፍ
EPACopyright: EPAበለንደን የፍልስጥኤም ደጋፊዎች ያደረጉት የተቃውሞ ሰልፍImage caption: በለንደን የፍልስጥኤም ደጋፊዎች ያደረጉት የተቃውሞ ሰልፍArticle share tools
- የታተመዉ 0:58 10 ጥቅምት 20230:58 10 ጥቅምት 2023ምዕራባውያን ለእስራኤል ያላቸውን ድጋፍ ገለጹ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesበለንደን የሚገኘው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለእስራኤል ድጋፍ ለማሳየት በሰንደቅ አላማዋ ሰማያዊ እና ነጭ መብራቶች ሰኞ እለት ደምቆ ነበርImage caption: በለንደን የሚገኘው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለእስራኤል ድጋፍ ለማሳየት በሰንደቅ አላማዋ ሰማያዊ እና ነጭ መብራቶች ሰኞ እለት ደምቆ ነበር
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesዋይት ሃውስ በእስራኤል ሰንደቅ ዓላማImage caption: ዋይት ሃውስ በእስራኤል ሰንደቅ ዓላማ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየፓሪሱ አይፍል ታወርም ከእስራኤል ሰንደቅ ዓላማ በተጨማሪ የዳዊት ኮከብን በማሳየት ድጋፋቸውን ገልጸዋል።Image caption: የፓሪሱ አይፍል ታወርም ከእስራኤል ሰንደቅ ዓላማ በተጨማሪ የዳዊት ኮከብን በማሳየት ድጋፋቸውን ገልጸዋል።
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesፍልስጥኤማውያንን በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ የተደረገባት የሲድኒ ኦፔራ ሃውስ ለእስራኤልም ድጋፍ ለማሳየት ህንጻው በሰማያዊ እና በነጭ ሰንደቅ አላማ መብራት በርቶ ነበርImage caption: ፍልስጥኤማውያንን በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ የተደረገባት የሲድኒ ኦፔራ ሃውስ ለእስራኤልም ድጋፍ ለማሳየት ህንጻው በሰማያዊ እና በነጭ ሰንደቅ አላማ መብራት በርቶ ነበርArticle share tools