October 11, 2023 – Konjit Sitotaw 

ነበልባሉ ፋኖ መለቀቅ ያለባቸውን ምርኮኞች በመፍታት ለቤተሰባቸው እንዲበቁ ማድረጉን ዘ-አምሃራ ዘግቧል። እንደ ጋዜጠኛ አዲሱ ደረበ ዘገባ በጎጃም ጦር ግንባር ብቻ ከተማረከው ከ10ሺህ በላይ የጠላት ምርኮኛ ውስጥ አንዳችም ወንጀል ያልፈጸሙ የአማራን ሴት ያልደፈሩ ንብረት ያልዘረፉና ንጹሃንን ያልገደሉ ብቻ ተመርጠው የተሓድሶ ስልጠና ከተሰጣቸው በኋላ 1650 የጠላት ወታደር ሆነው የተማረኩ የደቡብ ተወላጆችን ፋኖ አሰናብቶ ለቤተሰባቸው ማብቃት መቻሉን ነው የገለጸው።

የአማራን ሴት በመድፈር ንጹሃንን በመግደልና የአማራን ሀብትና ንብረት በመዝረፍ ተግባር ላይ የተገኙ ምርኮኞች ግን የማይለቀቁ በመሆናቸው በፋኖ ቁጥጥር ስር እንዳሉ ገልጿጵ። ከ350 በላይ የሚሆኑት ደግሞ በጦርነቱ ተመተው በመቁሰል የተማረኩ በአሁኑ ሰዓት በፋኖ ቁጥጥር ስር ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑ ገልጾ ከ6000 በላይ የሆኑ የስርዓቱ አገልጋይ ምርኮኞች ግን በዓላማና በአቌም የፋኖ ትግል ዓላማን አውቀውና መርጠው በራሳቸው ፈቃፍ ከፋኖ ጋር ተቀላቅለው ለመዋጋት በመረጡት መሰረት የሚያስፈልገውን የተሀድሶን ስልጠና ከጨረሱ በኋላ ፋኖን በመቀላቀል ፋሺስታዊውን ስርዓት በመዋጋት ላይ ይገኛሉ።

ይህ በአንድ የጎጃም ጦር ግንባር ላይ ብቻ ከተማረከው ከአስርሺህ በላይ የጠላት መንጋ ውስጥ ለሕግ የሚቀርበውን ወንጀለኛ መርጦ በመለየት ወደ ቤተሰቤ እሄደለሁ ያለውንም ለብቻ ለይቶ ወደ ቤተሰቡ እንዲገባ በማድረግና የለም ይህንን ፋሺስት ስርዓት ከፋኖ ጋር ሆኜ እታገላለሁ ብሎ በፈቃዱ የመረጠውን ምርኮኛ ለብቻ በመለየት የተፈጸመ ስራ ሲሆን በጎንደር በወሎና በሸዋ ግንባሮችም በአስር ሺህ የሚቆጠር የጠላት መንጋ በምርኮኝነት ተይዞ እንዳለ ይታወቃል።