Related Video and Audio

VIDEO 1 MINUTE 33 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 33 SECONDS1:33
Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBCበእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች
- BBC
Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 23 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 23 SECONDS1:23
Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBCሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ?
- BBC
Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBC
ጭምቅ ሃሳብ
- በአራት ቀናት ውስጥ ከ260 ሺህ በላይ ፍልስጥኤማውያን ከጋዛ ተፈናቅለዋል፡ የተባበሩት መንግሥታት
- ኢራን በእስራኤል ላይ ለተፈጸመው ጥቃት ድጋፏን ሰጥታ ይሆን?
- የፍልስጥኤማውያን የተቃውሞ ሰልፍ በዌስት ባንክ
- የቀጠለው የእስራኤል ጥቃት እና የአውሮፓ ኅብረት ትችት
- እስራኤል ከሶሪያ በኩል ለተሰነዘረ ጥቃት አጸፋውን መመለሷን ገለጸች
- የሳዑዲው ልዑል ሞሐመድ ቢን ሳልማን ለፍልስጥኤማውያን ድጋፋቸውን ገለጹ
- ውጊያው ሳይቆም በታጋቾች ጉዳይ ላይ አንደራደርም፡ ሐማስ
- በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት አጀማመር ምን ይመስላል?
- በጋዛ ከ123 ሺህ በላይ ፍልስጥኤማውያን ተፈናቀለዋል
- ኢራን፣ ሐማስ በፈጸመው ጥቃት ላይ ተሳትፎ የለኝም አለች
- እስራኤል በሊባኖስ ላይ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት ፈጸመች
ቀጥታ ዘገባ
- የታተመዉ 5:355:35የኢራን ፕሬዚደንት እስራኤልን ‘በዘር ማጥፋት’ ከሰሱ
ReutersCopyright: Reutersየኢራን ፕሬዚደንት እስራኤልን በዘር ማጥፋት ከሰሱ።ፕሬዚደንቱ ይህን ያሉት እስራኤል በጋዛ ላይ የምትፈፅመውን ጥቃት አጠናክራ በቀጠለችበት ወቅት ነው።ፕሬዚደንት ኢብራሒም ሬይሲ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የውሃ እና የነዳጅ አቅርቦት እንዲቋረጥ ተደርጎ በጋዛ ላይ የተደረገው ከበባ ሁሉንም ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የጣሰ ነው ሲሉ ኮንነውታል።ኢራን በጋዛ ያለውን ታጣቂ ቡድን ሐማስን በመደገፍና በማስታጠቅ ትታወቃለች።ሆኖም ማክሰኞ ዕለት የኢራን የበላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ አገራቸው ቅዳሜ ዕለት በእስራኤል ላይ ከተፈተው ጥቃት ጀርባ እንደሌለችበት ተናግረዋል።መሪው ይህን ይበሉ እንጂ ከጥቃቱ በኋላ በቴሌቪዥን በሰጡት በዚህ የመጀመሪያ መግለጫቸው፣ጥቃቱን ለመፈፀም ያቀዱትን አድንቀናል ብለዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ

- የታተመዉ 3:393:39ሰበርታጋቾች እስኪለቀቁ ጋዛ መብራት፣ ውሃ እና ነዳጅ አታገኝም- እስራኤል
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesታጋቾች እስኪለቀቁ ድረስ የጋዛ ሙሉ ከበባ እንደሚቀጥል የእስራኤል ኢነርጂ ሚንስትር እስራኤል ካትዝ ገለጹ።”ታጋቾች” እስኪፈቱ ድረስ “መብራት አይኖርም፣ ውሃ አይለቀቀም እንዲሁም ምንም ዓይነት የነዳጅ መኪና አይገባም” ሲሉ እስራኤል ካትዝ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ጽፈዋል።የቅዳሜውን የሐማስን ጥቃት ተከትሎ ነው እስራኤል ወደ ጋዛ ሰርጥ የሚገቡ ምርቶችን ያገደችው። እስራኤል በሙሉ ከበባ ውስጥ ባስገባቻት ጋዛ ኤሌክትሪክ እና ውሃን ጨምሮ መሰረተ ልማቶች ተቋርጠዋል።መውጫ መግቢያ በታጣባት ጋዛ የተወሰነ እርዳታ እንዲገባ እና ነዋሪዎች እንዲወጡ ለማድረግ አሜሪካ ከእስራኤል፣ ከተባበሩት መንግሥታት እና ከግብጽ ጋር እየተነጋገረች መሆኗን ዋይት ሃውስ አስታውቋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:103:10ከጋዛ የተገኙ የቅርብ ጊዜ መረጃዎች
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesእስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ በምታደርገው የአየር ጥቃት የሞቱ ፍልስጥኤማውያን ቁጥር ከ1 ሺህ 200 ሰዎች በላይ መድረሱን የጤና ሚኒስቴሯ አስታውቋል።በተጨማሪም 5 ሺህ 339 ፍልስጥኤማውያን ቆስለዋል።እስራኤል ሃማስ ለሰነዘረብኝ ጥቃት አጸፋዊ ምላሽ ነው በሚልም ተደጋጋሚ የአየር ጥቃቶች በጋዛ ሰርጥ ላይ እየፈጸመች ትገኛለች።ሃማስ ባደረገው የተቀናጀ ጥቃት እና እስራኤል እየፈጸመችው ባሉ የአየር ጥቃቶች የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 500 ደርሷል።ተደጋጋሚ የአየር ጥቃቶቹንም ተከትሎ ከ338 ሺህ በላይ ፍልስጥኤማውያን መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታት የፍልስጥኤም ስደተኞች ኤጀንሲ አስታውቋል።አብዛኛዎቹም በሆስፒታሎች እና በተባበሩት መንግሥታት ትምህርት ቤቶች ተጠልለው ይገኛሉ።እስራኤል በሙሉ ከበባ ውስጥ ባስገባቻት ጋዛ ኤሌክትሪክ እና ውሃን ጨምሮ መሰረተ ልማቶች ተቋርጠዋል።መውጫ መግቢያ በታጣባት ጋዛ የተወሰነ እርዳታ እንዲገባ እና ነዋሪዎች እንዲወጡ ለማድረግ አሜሪካ ከእስራኤል፣ ከተባበሩት መንግሥታት እና ከግብጽ ጋር እየተነጋገረች መሆኗን ዋይት ሃውስ አስታውቋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:472:47የተባበሩት መንግሥታት በእስራኤል እና በጋዛ ጉዳይ ነገ ስብሰባ ሊያካሂድ ነው
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በእስራኤል እና ጋዛ መካከል ያለው ግጭት ላይ ለመወያየት ነገ ስብሰባ ሊያካሂድ ነው።በጋዛ ሰርጥ ስላለው ሁኔታ ለመነጋገር ስብሰባውን የጠራችው የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታውን ምክር ቤት በሰብሳቢነት የተረከበችው ብራዚል መሆኗን የአገሪቷ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።የብራዚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማውሮ ቬራ በኒውዮርክ በሚካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ወደ እስያ የሚያደርጉትን ጉዞ አቋርጠዋል።የጸጥታው ምክር ቤት አባላት እሑድ ዕለት ባካሄዱት ስብሰባ እስራኤል እና ፍልስጥኤምን በሚመለከተው ፖሊሲ ላይ ተከፋፍለዋል።የብራዚል ፕሬዚደንት ሊዩዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ ረቡዕ ዕለት “በየትኛውም ዓለም ሕጻናት በፍጹም መታገት የለባቸውም” ሲሉ በኤክስ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።ፕሬዚደንቱ ጨምረውም ሐማስ ከቤተሰቦቻቸው ነጥቆ ያገታቸውን ሕጻናት መልቀቅ አለበት ብለዋል።ፕሬዚደንቱ እስራኤል በፍልስጥኤማዊ ሕጻናት እና እናቶቻቸው ላይ የምታዘንበውን ቦምብ እንድታቆም ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ ይህም በግብጽ በኩል ከጋዛ እንዲወጡ እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል።“በጦርነት እብደት ውስጥም ቢሆን ትንሽ ሰብዓዊነት ሊኖር ይገባል” ሲሉም አክለዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:382:38ብሊንከን እና የፍልስጥኤሙ ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ ሊወያዩ ነው
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየፍልስጥኤም ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ እና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን በመጪው አርብ ተገናኝተው ሊነጋገሩ መሆኑን የፍልስጥኤም ነጻነት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ሁሴን አል-ሼክ ገለጹ።የፍልስጥኤም የፖለቲካ መሪዎች ዌስት ባንክን በሚመራው በማህሙድ አባሱ ፋታህ ፓርቲ እና ጋዛ ሰርጥን በሚቆጣጠረው ታጣቂ ቡድን ሐማስ ተከፋፍለዋል።ብሊንከን ከሰዓታት በኋላ እስራኤል እንደሚገቡ ይጠበቃል።በቆይታቸውም የሐማሳን ጥቃት ተከትሎ ለእስራኤል እና ለህዝቦቿ ያላቸውን ድጋፍ ያሳያሉ ተብሏል።የፍልስጥኤም ባለስልጣናት በኤክስ ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት ፕሬዝዳንት አባስ ከዮርዳኖሱ ንጉስ አበዱላህ ጋር ዛሬ አማን ውስጥ ይገኛሉ።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:292:29እያንዳንዱ የሐማስ አባል በሞት ጥላ ሥር መሆኑን ኔታንያሁ ተናገሩየእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ እያንዳንዱ የሐማስ አባል በሞት ጥላ ሥር መሆኑን ተናገሩ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:292:29በእስራኤል-ሐማስ ዙሪያ ሐሰተኛ መረጃዎች ላይ እርምጃ እንዲወስድ የአውሮፓ ህብረት ሜታን ጠየቀሐማስ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ “ሐሰተኛ መረጃዎች” በሜታ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመስፋፋቱ የአውሮፓ ሕብረት ማርክ ዙከርበርግን አስጠነቀቀ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:292:29ሐማስ ጥቃት ከመፈጸሙ ከቀናት በፊት ግብፅ እስራኤልን አስጠንቅቃ ነበር – አሜሪካሐማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት ከመክፈቱ ሦስት ቀናት ቀደም ብሎ ግብፅ እስራኤልን አስጠንቅቃ እንደነበር የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር ተናገሩ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:170:17ሐማስ የእስራኤልን መከላከያ ለማለፍ የተጠቀመው የ2ኛው የዓለም ጦርነት መሣሪያየእስራኤል እና የሐማስ ግጭት ከተጀመረ ቀናት ተቆጥረዋል። ቅዳሜ ዕለት ሐማስ የፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ የተጀመረው ግጭት ዓለምን እያነጋገረ ነው። አገራትንም ጎራ አስለይቷል።ለመሆኑ ሐማስ የእስራኤልን መከላከያ ለማለፍ ስለተጠቀመው የሁለተኛው የዓለም ጦርነት መሣሪያ ምን እናውቃለን?ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 23:49 11 ጥቅምት 202323:49 11 ጥቅምት 2023የሐማስ ጥቃት እና በሕዝቡ ዘንድ የፈጠረው ድንጋጤ በቤተ እስራኤላዊው ዐይንባለፈው ቅዳሜ ሐማስ ወደ እስራኤል ግዛቶች በመግባት የፈጸመው ጥቃት የቀሰቀሰው ግጭት ቀናት የተቆጠሩ ሲሆን፣ በቀላሉ የሚቋጭ አይመስልም። ከሁለቱም ወገን በሰው ላይ የሚደርሰው ጉዳት ከዕለት ዕለት እየጨመረ ነው። ስለጥቃቱ ዕለት እና ጥቃቱን ተከትሎ በሕዝቡ ውስጥ የተፈጠረውን ስሜት ከጋዛ አቅራቢያ ከምትገኘው አሽኬሎን ከተማ ነዋሪ የሆኑ ቤተ እስራኤላዊ ነግረውናል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 13:58 11 ጥቅምት 202313:58 11 ጥቅምት 2023‘የት እንሂድ?’ የጋዛ ነዋሪዎችን መሸሸጊያ አልባ ያደረገው የተጠናከረው የእስራኤል ጥቃትየእስራኤል ጥቃት በርካታ የመኖሪያ ሕንፃዎችን አውድሟል። የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያ ቢሮዎች እና የጋዛ እስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ሕንጻም ክፉኛ ተጎድተዋል። ሰኞ ዕለት አስፈሪ ፍንዳታዎች አካባቢውን ሲንጡ አመሹ። ልጆች ያለቅሳሉ፤ ለደቂቃዎች ማሸለብ የቻለም የለም።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 10:58 11 ጥቅምት 202310:58 11 ጥቅምት 2023ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ የአስቸኳይ ጊዜ መንግሥት እና የጦርነት ካቢኔ አቋቋሙ
OREN ROSENFELDCopyright: OREN ROSENFELDበስምምነቱ ከሐማስ ጋር የሚካሄደውን ጦርነት የሚመራ ካቢኔ ተቋቁሟልImage caption: በስምምነቱ ከሐማስ ጋር የሚካሄደውን ጦርነት የሚመራ ካቢኔ ተቋቁሟልየእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ እና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ቤኒ ጋንትዝ የአስቸኳይ ጊዜ መንግሥት ለማቋቋም ተስማሙ።ሁለቱ ፖለቲከኞች እዚህ ስምምነት ላይ የደረሱት ሐማስ ድንገተኛ ጥቃት ከፈጸመ በኋላ እስራኤል መጠነ ሰፊ የአጸፋ እርምጃ በጋዛ ላይ እያካሄደች ባለበት አምስተኛ ቀን ላይ ነው።ይህንን ስምምነት ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ፣ ጋንትዝ እና የአገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር ያሉበት “የጦርነት ካቢኔ” ያቋቁማሉ ተብሏል።በስምምነቱ መሠረት ጦርነቱ በሚካሄድበት ጊዜ “የጦርነቱን ሂደት ከሚመለከቱ ጉዳዮች በስተቀር ማንኛውም አይነት ሕግም ሆነ የመንግሥት ሃሳብ ለውሳኔ አይቀርብም።”በተጨማሪም ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የመንግሥት ሥልጣንን እንዲይዙ የተሾሙ ሰዎች የኃላፊነት ጊዜ በጦርነቱ ወቅት ሁሉ የሚቀጥል ይሆናል።ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ እና የናሽናል ዩኒቲ ፓርቲ ሊቀ መንበር ጋንትዝ የአስቸኳይ ጊዜ መንግሥት ለማቋቋም የተስማሙት ላለፉት ቀናት ንግግር ካደረጉ በኋላ ነው።ከስምምነቱ በኋላ ከሁለቱም ወገን በጋራ በወጣ መግለጫ ላይ “የአስቸኳይ ጊዜ መንግሥት ለመመሥረት እና ጦርነቱን የሚመራ ካቢኔ ለማቋቋም ተስማምተዋል።“ጦርነቱን የሚመራው ካቢኔም ጠቅላይ ሚኒስትሩን፣ የመከላከያ ሚኒስትሩን እና የተቃዋሚ ፓርቲውን መሪ በአባልነት ይዞ ይመሠረታል” ተብሏል።ከሦስቱ ባለሥልጣናት በተጨማሪ የጦርነቱ መሪ ካቢኔን በታዛቢነት የሚያገለግሉ ሁለት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ይካተቱበታል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:59 11 ጥቅምት 20238:59 11 ጥቅምት 2023ረቡዕ የተከሰቱ ዋና ዋና ጉዳዮች
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየጋዛ ዋነኛ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ማዕከልImage caption: የጋዛ ዋነኛ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ማዕከልእስራኤል በሐማስ ለተፈጸመባት ጥቃት አጸፋ ጋዛ ላይ ከበባ በመጣል ለአምስተኛ ቀን ተከታታይ የአየር ጥቃት እየፈጸመች ሲሆን፣ ሐማስም የሮኬት ጥቃቱን ቀጥሏል።በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የጋዛ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል።መሠረታዊ አቅርቦቶች በከተማዋ ውስጥ እየተሟጠጡ መሆናቸው እየተዘገበ ነው።ዛሬ ረቡዕ እስካሁን የተከሰቱ ዋና ዋና ጉዳዮች ምንድን ናቸው?
- እስራኤል በጋዛ ላይ በጣለችው ጥብቅ ገደብ የነዳጅ ዕጥረት በመከሰቱ የከተማዋ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ማዕከል ሥራ ማቆሙን ባለሥልጣናት ተናግረዋል።
- ሰኞ ዕለት እስራኤል ወደ ጋዛ የሚገቡ የኤሌክትሪክ እና የውሃ መስመሮች እንዲሁም የነዳጅ አቅርቦትን እንደምታቋርጥ አስታውቃ ነበር።
- የእስራኤል የአየር ጥቃት በጋዛ ላይ ተጠናክሮ በቀጠለበት በአሁኑ ጊዜ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ከጥቃት ለመሸሽ ወደ ሆስፒታሎች እና ትምህርት ቤቶች እየገቡ ነው።
- በእስራኤል ሰሜን እና ደቡብ ግዛቶች ውስጥ የሮኬት ጥቃት ማስጠንቀቂያ ደወሎች የተሰሙ ሲሆን፣ ከጋዛ በተተኮሱ ሮኬቶች የቆሰሉ ሰዎች እንዳሉ ተዘግቧል።
- የእስራኤል ጦር 300 ሺህ ተጠባባቂዎችን ጨምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮችን በጋዛ ድንበር ላይ አሰባስቧል።
- እስራኤል በድንበር በምትጎራበታት ሊባኖስ ውስጥ የሚገኙ የሄዝቦላህ ታጣቂዎች የፈጸሙባትን ጥቃት ተከትሎም ሊባኖስ ግዛት ውስጥ የአጸፋ ጥቃት ፈጽማለች።
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 6:51 11 ጥቅምት 20236:51 11 ጥቅምት 2023በእስራኤል-ፍልስጥኤም ግጭት የአፍሪካ አገራት ምን አቋም ያዙ?
BBCCopyright: BBCባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ የተቀሰቀሰውን ግጭት በተመለከተ የዓለም አገራት የተለያየ አቋማቸውን እያንጸባረቁ ነው።በዚህም በግልጽ ከእስራኤል ወይም ከፍልስጥኤም ጎን መሠለፋቸውን ያሳወቁ አገራት የመኖራቸውን ያህል፣ ከየትኛውም ወገን ሳይቆሙ ገለልተኛ አቋም ያንጸባረቁም አሉ።ከ54ቱ የአፍሪካ አገራት መካከልም ከፍልስጥኤም ጎን የተሰለፉ፣ እስራኤልን የደገፉ፣ ገለልተኛ አቋም የያዙ እና ለጊዜው ዝምታን የመረጡ አገራት አሉ።በዚህ ዝርዝር አስካሁን በይፋ አቋማቸውን ያንጸባረቁ የአፍሪካ አገራት ተካተዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 6:29 11 ጥቅምት 20236:29 11 ጥቅምት 2023ጋዛ ውስጥ በእስራኤል ጥቃት የተገደሉት ፍልስጥኤማውያን ቁጥር 1,055 ደረሰ
EPACopyright: EPAእስራኤል ጋዛ ላይ እያካሄደችው ባለው የአየር ጥቃት ምክንያት የተገደሉ እና ጉዳት የደረሰባቸው ፍልስጥኤማውያን ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው።የፍልስጥኤም የጤና ሚኒስቴር ረቡዕ እኩለ ቀን ላይ ባወጣው መረጃ የተገደሉ ሰዎች አሃዝ 1,055 ሲደርስ፣ ከ5,100 በላይ ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጨምሮ እንዳለው፣ በጥቃቱ ከተጎዱት ሰዎች መካከል 60 በመቶዎቹ ሴቶች እና ሕጻናት ናቸው።ሐማስ ቅዳሜ ዕለት በፈጸመው ጥቃት የተገደሉ እስራኤላውያን 1,200 ሲሆኑ ከ2,700 በላይ የሚሆኑ ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 5:49 11 ጥቅምት 20235:49 11 ጥቅምት 2023እስራኤል በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን ወደ ጋዛ እያስጠጋች ነው
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤል አየር ኃይል ጋዛ ውስጥ የሐማስ ናቸው ያላቸውን ኢላማዎች ለአራተኛ ቀን እየደበደበ ባለበት በዛሬው ዕለት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የእስራኤል ወታደሮች ከጋዛ አቅራቢያ ሰፍረዋል።የሐማስ ጠንካራ ይዞታ በሆነችው ጋዛ ላይ እየተፈጸመ ባለው የአየር ጥቃት ምክንያት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የጋዛ ነዋሪዎች መፈናቀላቸው የተዘገበ ሲሆን፣ በነዳጅ ችግር ምክንያት በከተማዋ በሰዓታት ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ይቋረጣል።የሐማስ ተዋጊዎችን ለማደን እና የታገቱ ዜጎቿን ለማስለቀቅ እስራኤል እግረኛ ሠራዊቷን ወደ ጋዛ ታሰማራ እንደሆነ አስካሁን የታወቀ ነገር ባይኖርም፣ አስፈላጊውን ሁሉ እርምጃ እንደምትወስድ አስታውቃለች።የእስራኤል ጦር ሠራዊት ዛሬ ረቡዕ እንዳሳወቀው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቹ “የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለመፈጸም ዝግጁ ሆነው” ከጋዛ አቅራቢያ ይገኛሉ ብሏል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:47 11 ጥቅምት 20232:47 11 ጥቅምት 2023የፍልስጥኤማውያን የተቃውሞ ሰልፍ በዌስት ባንክ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤልን ጥቃት በመቃወም ዌስት ባንክ ራማላህ ውስጥ ሰልፍ የወጡ ፍስጥኤማውያንImage caption: የእስራኤልን ጥቃት በመቃወም ዌስት ባንክ ራማላህ ውስጥ ሰልፍ የወጡ ፍስጥኤማውያንዛሬ ረቡዕ ማለዳ ጎህ ሲቀድ ከጋዛ ባሻገር በወረራ በተያዘችው ዌስት ባንክ ውስጥ ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጥኤማውያን እስራኤል በጋዛ ላይ እየፈጸመችው ያለውን የአውሮፕላን ድብደባ በመቃወም ሰልፍ አድርገዋል።የፍልስጥኤም ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ የፍልስጥኤምን ሰንደቅ ዓላማ እና በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎችን ፎቶፍራፎች ይዘው ነው አደባባይ የወጡት።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:39 11 ጥቅምት 20232:39 11 ጥቅምት 2023ኢራን በእስራኤል ላይ ለተፈጸመው ጥቃት ድጋፏን ሰጥታ ይሆን?የሐማስ ታጣቂዎች ከፍተኛ ቅንጅት ታይቶበታል የተባለውን ጥቃት በእስራኤል ላይ መፈጸማቸውን ተከትሎ የኢራን ስም በተደጋጋሚ እየተነሳ ይገኛል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ኢራን በጥቃቱ ተሳትፎ ነበራት ወይ? የሚለው ጥያቄ ከተለያዩ ወገኖች እየተመላለሰ የሚነሳ ሆኗል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:27 11 ጥቅምት 20231:27 11 ጥቅምት 2023የቀጠለው የእስራኤል ጥቃት እና የአውሮፓ ኅብረት ትችት
Getty ImagesCopyright: Getty Images
- ሌሊቱን የእስራኤል አየር ኃይል የጦር ጄቶች የሐማስ የሮኬት ጥቃቶች የሚወነጨፉበት ነው ባለው የጋዛው አል-ፉርቃን አካባቢ ያሉ ከ200 በላይ ኢላማዎች ላይ ድብደባ መፈጸሙን ገልጿል። ይህም ጥቃት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ የተፈጸመ ሦስተኛው ድብደባ ነው።
- እስራኤል ሌሊቱን ጋዛ ላይ በፈጸመችው የአየር ድብደባ ቢያንስ 30 ሰዎች መገደላቸውን የሐማስ ቃል አቀባይ አስታወቁ።
- የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሆኑት ጆሴፍ ቦሬል እስራኤል በጋዛ ላይ እየወሰደች ያለችው እርምጃ ዓለም አቀፍ ሕግን የጣሰ ነው ሲሉ ተቹ። “እስራኤል እራሷን የመከላከል መብት ቢኖራትም ይህንን ማድረግ ያለባት በዓለም አቀፍ ሕጎች መሠረት መሆን አለበት” ብለዋል።
- የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሐማስን ጥቃት አጥብቀው ያወገዙ ሲሆን አሜሪካ ለእስራኤል የምትሰጠውን ወታደራዊ ድጋፍ በማጠናከር የመጀመሪያው የጦር መሳሪያ ድጋፍ ማክሰኞ ደቡባዊ እስራኤል ደርሷል።
- የጋዛ ነዋሪዎች “ደኅንነቱ የተጠበቀ መተላለፊያ” እንዲያገኙ ከእስራኤል እና ከግብፅ ጋር እየተነጋገረች መሆኗን የአሜሪካ ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጃክ ሰሊቫን ገለጹ።
- አስካሁን ከፍልስጥኤም እና ከእስራኤል ወገን የሞቱት ሰዎች አሃዝ በአጠቃላይ ወደ 2,100 ሲደርስ፣ ከእስራኤል በኩል 1,200፣ ከፍልስጥኤም ወገን ደግሞ 900 ሰዎች ተገድለዋል።
- በጥቃቶቹ የደረሰው ጉዳት ታይቶ የማይታወቅ መሆኑን እስራኤላውያን እና ፍልስጥኤማውያን እየተናገሩ ነው። እስራኤላውያን “በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመ ጭፍጨፋ ነው” ሲሉ፣ ፍልስጥኤማውያን ደግሞ “ሕይወታችንን የምናድንበት ቦታ አጣን” እያሉ ነው።
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 1:01 11 ጥቅምት 20231:01 11 ጥቅምት 2023እስራኤል ከሶሪያ በኩል ለተሰነዘረ ጥቃት አጸፋውን መመለሷን ገለጸችየእስራኤል ጦር ሠራዊት ከሶሪያ በኩል ወደ ጉላን ተራሮች ለተሰነዘረ የከባድ መሳሪያ ጥቃት በመድፍ ተኩስ ምላሽ መስጠቱን ገለጸ።የጎላን ተራሮች የ1967ቱን የአረብ እስራኤል ጦርነትን ተከትሎ እስራኤል አስካሁን ድረስ በወረራ የያዘቻቸው መሆኑ ይታወቃል።የእስራኤል ጦር ባወጣው መግለጫ ከሶሪያ በኩል የተሰነዘረውን የከባድ መሳሪያ ጥቃት ተከትሎ “ወታደሮቻችን መድፍ እና ሞርታር ጥቃቱ ወደ ተነሳበት ስፍራ በአጸፋው ተኩሰዋል” ብሏል።ጨምሮም ቀደም ሲልም በርካታ ጥቃቶች ከሶሪያ በኩል ወደ እስራኤል ግዛቶች መፈጸማቸውን ገልጿል።የእስራኤል ጦር ሠራዊት ቃል አቀባይ ለፈረንሳይ ዜና ወኪል ኤኤፍፒ ጥቃቶቹ በሞርታር እንደተፈጸሙ ገልጸዋል።ሐማስ ባለፈው ቅዳሜ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ግጭቱ ከተባባሰ በኋላ በእስራኤል እና በሶሪያ መካከል የከባድ መሳሪያ ተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ ይህ የመጀመሪያው ነው።