ስለአማራ ፋኖ ተጋድሎ
የአብን የበአዴን ታናሽ አገልጋይ መሆን የፈጠረው ክፍተት ይሞላ! ( መንግስቱ ሙሴ )
——————————————————–

( መንግስቱ ሙሴ )
የአማራ ፋኖ የአርበኝነት ትግል ትናንትም በሁለተኛው የጠላት ወረራ ሆነ ዛሬም በፋሽስት ጠባብ የኦሮሞ ብሔርተኝነት ያሳየው ትግል አንጸባራቂ ነው/ነበር። እንደአለድል ሆኖ ግን የአማራ ልሂቃን አሁንም ከመሸማቀቅ ያልወጣ ወይ ለመንግስት ያደረ ነው አለያም አንገቱን ደፍቶ የተቀመጠ ወይንም የፖለቲካ ትንተና በባዶ ሜዳ የሚያደርግ እና አሁንም መሐል ሰፋሪነትን የተላበሰ ሆኖ ይታያል።
ለምሳሌ አብን የተባለው ድርጅት ከአጥናፍ አጥናፍ በአማራ ሕዝብ ሲደገፍ ዋናው ምክንያት እንደፖለቲካ ድርጅት የአጭር እና የረጅም ግዜ ፕሮግራም አውጥቶ ግብ ያለው ፖለቲካ ይሰራል በሚል ነበር። በሚያሳዝን ይህ ድርጅት ግን ሕዝብ ክዶ ገሚሶቹ በመንግስት ስልጣን በፋሽስቱ መዋቅር ስር ለጠላት አገልጋይ ሆነው አረፉት ቀሪወች በሞተ ፓርላማ ተቀምጠው ጠላት አነጣጥሮ ልሳናቸውን ለመዝጋት አስቻለው። መደረግ የነበረበት አብን የለቀቁትን አራግፎ ከፓርላማም ያሉት ከፓርላማ ወጥተው ወደሜዳው በመግባት ከፋኖ ተጋድሎ ጎን ፖለቲካዊ መዋቅር ማጠናከር እና ስለፖለቲካ ግቡ መስራት ነበር። ያ ሳይሆን ጠላት ጠንካራ ያላቸውን ከበአዴንም ከአብንም ወደእስር ሲወረውር ቀሪወች አሁንም የፖለቲካ ለውጥ አርገው ከሕዝባቸው ጎን መቆም ሲገባ የት እንዳሉ የማይታወቅበት ሁኔታ ውስጥ መገኘት እጅግ አሳፋሪ ድርጊት ብለን እናልፈዋለን።
አሁንም ይህን የፋኖ ጠንካራ ተጋድሎ ከመሸሽ ይልቅ አብንን የመሰለ ድርጅት በተሎ በሜዳው ማደራጀት እና በአንድ እጅ ጠበንጃን ከተጋዳዩ የፋኖ ኃይሎች ጋር በሌላ በኩል የፖለቲካ አመራር ለመስጠት ቢዘገይም ሊሰሩት ይገባል።
ለማሳሰቢያ ያክል የዲያስፖራ የአማራ ማህበራትም ሆኑ የፋኖ ደጋፊወች የፖለቲካ ሰንሰለት ሊሰሩ እና የጋራ አቋም ተጋዳዩን ሊያሲዙ አይችሉም። ቢችሉም ተገቢ ቦታላይ ባለመሆናቸው የትግሉን የቀን ተቀንም ሆነ ሁለንተናዊ ሁኔታወችን ሊረዱ ስለማይችሉ ነው። በድጋሚ የኔ ዋና ማሳሰቢያ የፋኖ ተጋድሎ አብይንም ሆነ ማንነም ጸረ አማራ/ጸረ ኢትዮጵያ ኃይላት እንዳርበደበድ ሁሉ ይህን የጋራ የፖለቲካ እና ሳይንሳዊ መርህ የማስያዝ ጉዳይ በተገቢው ሰአት እንዲነሳ እና እንዲሰራ ያስፈልጋል።
በዝርዝር ወደፊት ልመለስበት የሚገባ ጥልቅ ትንታኔ የሚፈልግ ቢኦሆንም እንደአቅሚቲ ይህን ጉዳይ ለመዳሰስ እሞክራለሁ።
ለምን? አሁን የአማራ ፋኖ የተጋድሎ ትግል ከሚጠበቀው በላይ ግብ የደረሰ ሲሆን ጭንጋፉ ድርጅቱ “አብን” ይህን ተጋድሎ ፖለቲካዊ ቦታውን ሊሸፍን ሲገባው ባዶ በማድረጉ ዛሬ አሜሪካኖች እነ ማይክ ሐመር የፋኖን ወታደራዊ ቁመና አይቶ ለማናጋር ሲፈልጉ አንድም ከውጭ ያሉ ሰወችን ሰባስበው አልየም በማህብርነት የተደራጁትን ማግኘት ሆኖ መገኘቱ አሁን የአማራ ፋኖ እና የአማራ ሕዝብ ትግል ግቡን ሙሉ ለሙሉ እንዲመታ ከታሰበ ሐገር ውስጥ ልክ እንደፋኖ ወታደራዊ ቁመና ሁሉ አንድ የዚሁ ወታደራዊ ቁመናን ሊስተካከል እና አብሮ ከፋኖ ጋር የሚንቀሳቀስ የፖለቲካ ኃይል እንደሚፈልግ የግድ ያለ ሁኔታ እያየን ነው።
ለምን የፖለቲካ ድርጅት ፋኖን የተላበሰ አስፈለገ ሲባል አንዱ እና ዋነኛው አንድ አቋም፤ አንድ ፖለቲካዊ ዲስፕሊን እና የጋራ አይን እና ጆሮ ሆኖ ሊያገለግል የሚገባው መነሳት የግድ ይላል።
የፋኖ አደረጃጀቶች ውስጥ ያሉ ምሁራን ቁጥረ ብዙ እንደሆኑ እያየን በመሆኑም ወይ እነዚህ ምሁራን አንድ መሪ ድርጅት እንዲፈጥሩ የግድ እየሆነ ስለመጣ ይህን ወታደራዊ ቁመና ፖለቲካዊ መሐከላዊ አንድነት እና ጥንካሬ ሊሰጥ የሚገባው መሪ ፓርቲ ያስፈልጋል።
ለዚህ ተግባር እንዲሳካ ሁላችንም ማገዝ እና ትልቁን ወታደራዊ ቁመና በፖለቲካ አላማ ማጠናከር ይገባል።
ባጭሩ የወታደራዊ ድንቅ መሪወች እንደወጡ ሁሉ በዚህ ትግል ማህጸን የፖለቲካ መሪወች እንዲወለዱ ይገባል ለማለት ነው! ( መንግስቱ ሙሴ )
