ቀጥታ

በእስራኤል ጥቃት ጋዛ ውስጥ ከተገደሉት መካከል 450 የሚደርሱት ሕጻናት ናቸው

Related Video and Audio

VIDEO 1 MINUTE 33 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 33 SECONDS1:33

Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBCበእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች

Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 23 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 23 SECONDS1:23

Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBCሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ?

Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBC

ጭምቅ ሃሳብ

  1. በአራት ቀናት ውስጥ ከ260 ሺህ በላይ ፍልስጥኤማውያን ከጋዛ ተፈናቅለዋል፡ የተባበሩት መንግሥታት
  2. ኢራን በእስራኤል ላይ ለተፈጸመው ጥቃት ድጋፏን ሰጥታ ይሆን?
  3. የፍልስጥኤማውያን የተቃውሞ ሰልፍ በዌስት ባንክ
  4. የቀጠለው የእስራኤል ጥቃት እና የአውሮፓ ኅብረት ትችት
  5. እስራኤል ከሶሪያ በኩል ለተሰነዘረ ጥቃት አጸፋውን መመለሷን ገለጸች
  6. የሳዑዲው ልዑል ሞሐመድ ቢን ሳልማን ለፍልስጥኤማውያን ድጋፋቸውን ገለጹ
  7. ውጊያው ሳይቆም በታጋቾች ጉዳይ ላይ አንደራደርም፡ ሐማስ
  8. በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት አጀማመር ምን ይመስላል?
  9. በጋዛ ከ123 ሺህ በላይ ፍልስጥኤማውያን ተፈናቀለዋል
  10. ኢራን፣ ሐማስ በፈጸመው ጥቃት ላይ ተሳትፎ የለኝም አለች
  11. እስራኤል በሊባኖስ ላይ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት ፈጸመች

ቀጥታ ዘገባ

  1. የታተመዉ 13:0213:02ከቅዳሜ ጀምሮ ጋዛ በስድስት ሺህ ቦምቦች ድብደባ ተፈጽሞባታል፡ የእስራኤል ጦርጋዛGetty ImagesCopyright: Getty Imagesባለፈው ቅዳሜ ግጭቱ ከጀመረ አንስቶ የእስራኤል አየር ኃይል በጋዛ ላይ እየፈጸመ ባለው የአየር ድብደባ ስድስት ሺህ የሚደርሱ ቦምቦችን በከተማዋ ላይ መታሉ ተገለጸ።የእስራኤል መከላከያ ኃይሎች ቃል አቀባይ እንዳሉት ውጊያው ከተጀመረ በኋላ አስከ ሐሙስ ድረስ ቀን ከሌት በጋዛ ላይ በተፈጸመው የአየር ድብደባ ነው አየር ኃይሉ ጥቃቱን የፈጸመው።ቃል አቀባዩ ዳንኤል ሃጋሪ በጋዛ ላይ የተፈጸመው የቦንብ ውጅብኝ ስድስት ሺህ መሆኑን ያሳወቁት፣ አሁን ኤክስ በሚባለው የቀድሞው ትዊተር የማኅበራዊ ትስስር መድረክ ላይ በጭስ ተሸፍኖ በፍንዳታ የሚናወጥ አንድ ሕንጻን የሚያሳይ ቪዲዮን በማያያዝ ነው።Article share tools
  2. የታተመዉ 11:1511:15በእስራኤል ጥቃት ጋዛ ውስጥ ከተገደሉ 450 የሚደርሱ ሕጻናት ናቸውፍልስጥኤማዊት ሕጻንReutersCopyright: Reutersየሐማስ ጥቃትን ተከትሎ እስራኤል በጋዛ ላይ እያካሄደችው ባለው የአየር ድብደባ ከተገደሉት መካከል 447ቱ ሕጻነት፣ 248 ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።የእስራኤል የአየር ድብደባ በቀጠለበት በአሁኑ ጊዜ የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን፣ ከቅዳሜ ጀምሮ አስከ ዛሬ ሐመስ አመሻሽ ድረስ በአጠቃላይ 1,417 ሰዎች ጋዛ ውስጥ መገደላቸው ተገልጿል።የሐማስ ታጣቂዎች ወደ እስራኤል በሺዎች የሚቆጠሩ ሮኬቶችን በመተኮስ እና ወደ እስራኤል ሰርጎ በመግባት ቅዳሜ ዕለት በፈጸሙት ጥቃት ከ1300 በላይ እስራኤላውያን መገደላቸውም ተነግሯል።Article share tools
  3. የታተመዉ 9:419:41አሜሪካ በየትኛውም ጊዜ ከእስራኤል ጎን ትቆማለች፡ አንቶኒ ብሊንከንየአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁus poolCopyright: us poolየአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁImage caption: የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁየአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን እስራኤል በሐማስ ለተፈጸመባት ጥቃት በጋዛ ላይ የአጸፋ እርምጃ እየወሰደች ባለበት ጊዜ አሜሪካ ለአስራኤል ያላትን አጋርነት ለመግለጽ በእስራኤል ጉብኝት እያደረጉ ነው።ብሊንከን ከእስራኤሉ ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል።ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በመሆን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫም፣ አሜሪካ በየትኛው ጊዜ ከአስራኤል ጎን እንደምትቆምና ድጋፏን እንደምትሰጥ ገልጸዋል።
    • ለጉብኝት እስራኤል የገቡት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን አገራቸው “በየትኛው ጊዜ እስራኤልን ለመርዳት” ከጎኗ እንደምትቆም በመግለጽ፣ ለሰላማዊ ሰዎች ጥበቃ ማድረግ አስፈላጊ ነው አሉ።
    • የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ሐማስ “አይሲስ ለአይሲስ በተስተናገደበት መንገድ ምላሽ ያገኛል” ብለዋል።
    • የእስራኤል ሠራዊት ጋዛ ሰርጥ ውስጥ የማስጠንቀቂያ ወረቀቶችን በመበተን ነዋሪዎች ሐማስ የሚጠቀምባቸው ሕንጻዎችን ስለሚያጠቃ ነዋሪዎች ወደ መጠለያ እንዲሄዱ አሳስቧል።
    • ስድስተኛ ቀኑን በያዘው እስራኤል በጋዛ ላይ በምትፈጽመው የአየር ጥቃት ቢያንስ 1,417 ሰዎች ሲገደሉ፣ 6,268 ሰዎች ላይ ደግሞ ጉዳት መድረሱን የጋዛ የጤና ባለሥልጣንት ገለጹ።
    • በሌላ በኩል የሐማስ ታጣቂዎች የገደሏቸው እስራኤላውያን ቁጥርም 1,300 ደርሷል። ሌሎች በርካቶች ደግሞ የመቁሰል ጉዳት እንደደረሰባቸው የእስራኤል ባለሥልጣንት አስታውቀዋል።
    • ብሪቲሽ ኤርዌይስ በእስራኤል ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ወደዚያው የሚያደርጋቸውን በራረቀዎች ለሚቀጥሉት ሦስት ሳምንታት እንዲቋረጡ ወሰነ።
    • የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ከእስራኤል ለቀው ለመውጣት ለሚፈልጉ ዜጎቹ የአየር ጉዞዎችን ማመቻቸቱን አስታወቀ።
    Article share tools
  4. የታተመዉ 9:289:28እስራኤል በሶሪያ አየር ማረፊያዎች ላይ ጥቃት መፈጸሟ ተዘገበእስራኤል በዋና ከተማዋ ደማስቆ እና በሌላኛዋ ከተማ አሌፖ ውስጥ በሚገኙ አየር ማረፊያዎች ላይ ጥቃት መፈጸሟን የሶሪያ መንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።የሶሪያ ዜና አገልግሎት ሳና “የሚሳኤል ፍንዳታዎች” በአየር ማረፊያው የመንደርደሪያ ሜዳ ላይ ጉዳት በማድረስ ከአግልግሎት ውጪ አድርጓቸዋል።ጥቃቱ በተፈጸመበት ጊዜ የሶሪያ የአየር መከላከያ መሳሪያዎች ምላሽ ለመስጠት መተኮሳቸውን የሶሪያ መገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል።የሶሪያ ሰብአዊ መብቶች ክትትል የተባለው መቀመጫውን በዩናይትድ ኪንግደም ያደረገው የግጭት ተከታታይ ቡድንም በርካታ ፍንዳታዎች አሌፖ ውስጥ መከሰታቸውን አረጋግጧል።ይህ የአየር ጥቃት መፈጸሙን የሚያመለክተው ዘገባ የወጣው የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሶሪያን ይጎበኛሉ ከተባለበት አንድ ቀን ቀደም ብሎ ነው።ሶሪያ እና ኢራን ከእስራኤል ጋር በጠላትንት የሚፈላለጉ አገራት ሲሆኑ፣ ኢራን አሁን እስራኤል እያደነችው ያለው ሐማስ ቡድንን እንደምትደግፍ ይነገራል።እስራኤል ከዚህ በፊትም ሶሪያ ውስጥ ያሉ የኢራን ናቸው የተባሉ እና የሊባኖስ ታጣቂ ቡድን የሆነውን ሄዝቦላህን ኢላማዎች በተደጋጋሚ ብትደበድብም በይፋ አረጋግጣ አታውቅም።Article share tools
  5. የታተመዉ 5:355:35የኢራን ፕሬዚደንት እስራኤልን ‘በዘር ማጥፋት’ ከሰሱየኢራን ፕሬዚደንት ኢብራሒም ሬይሲReutersCopyright: Reutersየኢራን ፕሬዚደንት እስራኤልን በዘር ማጥፋት ከሰሱ።ፕሬዚደንቱ ይህን ያሉት እስራኤል በጋዛ ላይ የምትፈፅመውን ጥቃት አጠናክራ በቀጠለችበት ወቅት ነው።ፕሬዚደንት ኢብራሒም ሬይሲ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የውሃ እና የነዳጅ አቅርቦት እንዲቋረጥ ተደርጎ በጋዛ ላይ የተደረገው ከበባ ሁሉንም ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የጣሰ ነው ሲሉ ኮንነውታል።ኢራን በጋዛ ያለውን ታጣቂ ቡድን ሐማስን በመደገፍና በማስታጠቅ ትታወቃለች።ሆኖም ማክሰኞ ዕለት የኢራን የበላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ አገራቸው ቅዳሜ ዕለት በእስራኤል ላይ ከተፈተው ጥቃት ጀርባ እንደሌለችበት ተናግረዋል።መሪው ይህን ይበሉ እንጂ ከጥቃቱ በኋላ በቴሌቪዥን በሰጡት በዚህ የመጀመሪያ መግለጫቸው፣በአይሁድ መንግሥት ላይ ጥቃቱን ለመፈፀም ያቀዱትን አድንቀናል ብለዋል።Article share tools
  6. የታተመዉ 3:393:39ሰበርታጋቾች እስኪለቀቁ ጋዛ መብራት፣ ውሃ እና ነዳጅ አታገኝም- እስራኤልጋዛGetty ImagesCopyright: Getty Imagesታጋቾች እስኪለቀቁ ድረስ የጋዛ ሙሉ ከበባ እንደሚቀጥል የእስራኤል ኢነርጂ ሚንስትር እስራኤል ካትዝ ገለጹ።”ታጋቾች” እስኪፈቱ ድረስ “መብራት አይኖርም፣ ውሃ አይለቀቀም እንዲሁም ምንም ዓይነት የነዳጅ መኪና አይገባም” ሲሉ እስራኤል ካትዝ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ጽፈዋል።የቅዳሜውን የሐማስን ጥቃት ተከትሎ ነው እስራኤል ወደ ጋዛ ሰርጥ የሚገቡ ምርቶችን ያገደችው። እስራኤል በሙሉ ከበባ ውስጥ ባስገባቻት ጋዛ ኤሌክትሪክ እና ውሃን ጨምሮ መሰረተ ልማቶች ተቋርጠዋል።መውጫ መግቢያ በታጣባት ጋዛ የተወሰነ እርዳታ እንዲገባ እና ነዋሪዎች እንዲወጡ ለማድረግ አሜሪካ ከእስራኤል፣ ከተባበሩት መንግሥታት እና ከግብጽ ጋር እየተነጋገረች መሆኗን ዋይት ሃውስ አስታውቋል።Article share tools
  7. የታተመዉ 3:103:10ከጋዛ የተገኙ የቅርብ ጊዜ መረጃዎችየተፈናቀሉ ፍልስጥኤማውያንGetty ImagesCopyright: Getty Imagesእስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ በምታደርገው የአየር ጥቃት የሞቱ ፍልስጥኤማውያን ቁጥር ከ1 ሺህ 200 ሰዎች በላይ መድረሱን የጤና ሚኒስቴሯ አስታውቋል።በተጨማሪም 5 ሺህ 339 ፍልስጥኤማውያን ቆስለዋል።እስራኤል ሃማስ ለሰነዘረብኝ ጥቃት አጸፋዊ ምላሽ ነው በሚልም ተደጋጋሚ የአየር ጥቃቶች በጋዛ ሰርጥ ላይ እየፈጸመች ትገኛለች።ሃማስ ባደረገው የተቀናጀ ጥቃት እና እስራኤል እየፈጸመችው ባሉ የአየር ጥቃቶች የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 500 ደርሷል።ተደጋጋሚ የአየር ጥቃቶቹንም ተከትሎ ከ338 ሺህ በላይ ፍልስጥኤማውያን መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታት የፍልስጥኤም ስደተኞች ኤጀንሲ አስታውቋል።አብዛኛዎቹም በሆስፒታሎች እና በተባበሩት መንግሥታት ትምህርት ቤቶች ተጠልለው ይገኛሉ።እስራኤል በሙሉ ከበባ ውስጥ ባስገባቻት ጋዛ ኤሌክትሪክ እና ውሃን ጨምሮ መሰረተ ልማቶች ተቋርጠዋል።መውጫ መግቢያ በታጣባት ጋዛ የተወሰነ እርዳታ እንዲገባ እና ነዋሪዎች እንዲወጡ ለማድረግ አሜሪካ ከእስራኤል፣ ከተባበሩት መንግሥታት እና ከግብጽ ጋር እየተነጋገረች መሆኗን ዋይት ሃውስ አስታውቋል።Article share tools
  8. የታተመዉ 2:472:47የተባበሩት መንግሥታት በእስራኤል እና በጋዛ ጉዳይ ነገ ስብሰባ ሊያካሂድ ነውየተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በእስራኤል እና ጋዛ መካከል ያለው ግጭት ላይ ለመወያየት ነገ ስብሰባ ሊያካሂድ ነው።በጋዛ ሰርጥ ስላለው ሁኔታ ለመነጋገር ስብሰባውን የጠራችው የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታውን ምክር ቤት በሊቀመንበርነት የተረከበችው ብራዚል መሆኗን የአገሪቷ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።የብራዚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማውሮ ቬራ በኒውዮርክ በሚካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ወደ እስያ የሚያደርጉትን ጉዞ አቋርጠዋል።የጸጥታው ምክር ቤት አባላት እሑድ ዕለት ባካሄዱት ስብሰባ እስራኤል እና ፍልስጥኤምን በሚመለከተው ፖሊሲ ላይ ወደ አንድ ሃሳብ መምጣት አልቻሉም ነበር።የብራዚል ፕሬዚደንት ሊዩዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ ረቡዕ ዕለት “በየትኛውም ዓለም ሕጻናት በፍጹም መታገት የለባቸውም” ሲሉ በኤክስ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።ፕሬዚደንቱ ጨምረውም ሐማስ ከቤተሰቦቻቸው ነጥቆ ያገታቸውን ሕጻናት መልቀቅ አለበት ብለዋል።ፕሬዚደንቱ እስራኤል በፍልስጥኤማዊ ሕጻናት እና እናቶቻቸው ላይ የምታዘንበውን ቦምብ እንድታቆም ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ ይህም በግብጽ በኩል ከጋዛ እንዲወጡ እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል።“በጦርነት እብደት ውስጥም ቢሆን ትንሽ ሰብዓዊነት ሊኖር ይገባል” ሲሉም አክለዋል።Article share tools
  9. የታተመዉ 2:382:38ብሊንከን እና የፍልስጥኤሙ ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ ሊወያዩ ነውአንቶኒ ብሊንከንGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየፍልስጥኤም ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ እና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን በመጪው አርብ ተገናኝተው ሊነጋገሩ መሆኑን የፍልስጥኤም ነጻነት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ሁሴን አል-ሼክ ገለጹ።የፍልስጥኤም የፖለቲካ መሪዎች ዌስት ባንክን በሚመራው በማህሙድ አባሱ ፋታህ ፓርቲ እና ጋዛ ሰርጥን በሚቆጣጠረው ታጣቂ ቡድን ሐማስ ተከፋፍለዋል።ብሊንከን ከሰዓታት በኋላ እስራኤል እንደሚገቡ ይጠበቃል።በቆይታቸውም የሐማሳን ጥቃት ተከትሎ ለእስራኤል እና ለህዝቦቿ ያላቸውን ድጋፍ ያሳያሉ ተብሏል።የፍልስጥኤም ባለስልጣናት በኤክስ ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት ፕሬዝዳንት አባስ ከዮርዳኖሱ ንጉስ አበዱላህ ጋር ዛሬ አማን ውስጥ ይገኛሉ።Article share tools
  10. የታተመዉ 2:292:29እያንዳንዱ የሐማስ አባል በሞት ጥላ ሥር መሆኑን ኔታንያሁ ተናገሩየእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ እያንዳንዱ የሐማስ አባል በሞት ጥላ ሥር መሆኑን ተናገሩ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  11. የታተመዉ 2:292:29በእስራኤል-ሐማስ ዙሪያ ሐሰተኛ መረጃዎች ላይ እርምጃ እንዲወስድ የአውሮፓ ህብረት ሜታን ጠየቀሐማስ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ “ሐሰተኛ መረጃዎች” በሜታ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመስፋፋቱ የአውሮፓ ሕብረት ማርክ ዙከርበርግን አስጠነቀቀ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  12. የታተመዉ 2:292:29ሐማስ ጥቃት ከመፈጸሙ ከቀናት በፊት ግብፅ እስራኤልን አስጠንቅቃ ነበር – አሜሪካሐማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት ከመክፈቱ ሦስት ቀናት ቀደም ብሎ ግብፅ እስራኤልን አስጠንቅቃ እንደነበር የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር ተናገሩ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  13. የታተመዉ 0:170:17ሐማስ የእስራኤልን መከላከያ ለማለፍ የተጠቀመው የ2ኛው የዓለም ጦርነት መሣሪያየእስራኤል እና የሐማስ ግጭት ከተጀመረ ቀናት ተቆጥረዋል። ቅዳሜ ዕለት ሐማስ የፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ የተጀመረው ግጭት ዓለምን እያነጋገረ ነው። አገራትንም ጎራ አስለይቷል።ለመሆኑ ሐማስ የእስራኤልን መከላከያ ለማለፍ ስለተጠቀመው የሁለተኛው የዓለም ጦርነት መሣሪያ ምን እናውቃለን?ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  14. የታተመዉ 23:49 11 ጥቅምት 202323:49 11 ጥቅምት 2023የሐማስ ጥቃት እና በሕዝቡ ዘንድ የፈጠረው ድንጋጤ በቤተ እስራኤላዊው ዐይንባለፈው ቅዳሜ ሐማስ ወደ እስራኤል ግዛቶች በመግባት የፈጸመው ጥቃት የቀሰቀሰው ግጭት ቀናት የተቆጠሩ ሲሆን፣ በቀላሉ የሚቋጭ አይመስልም። ከሁለቱም ወገን በሰው ላይ የሚደርሰው ጉዳት ከዕለት ዕለት እየጨመረ ነው። ስለጥቃቱ ዕለት እና ጥቃቱን ተከትሎ በሕዝቡ ውስጥ የተፈጠረውን ስሜት ከጋዛ አቅራቢያ ከምትገኘው አሽኬሎን ከተማ ነዋሪ የሆኑ ቤተ እስራኤላዊ ነግረውናል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  15. የታተመዉ 13:58 11 ጥቅምት 202313:58 11 ጥቅምት 2023‘የት እንሂድ?’ የጋዛ ነዋሪዎችን መሸሸጊያ አልባ ያደረገው የተጠናከረው የእስራኤል ጥቃትየእስራኤል ጥቃት በርካታ የመኖሪያ ሕንፃዎችን አውድሟል። የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያ ቢሮዎች እና የጋዛ እስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ሕንጻም ክፉኛ ተጎድተዋል። ሰኞ ዕለት አስፈሪ ፍንዳታዎች አካባቢውን ሲንጡ አመሹ። ልጆች ያለቅሳሉ፤ ለደቂቃዎች ማሸለብ የቻለም የለም።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  16. የታተመዉ 10:58 11 ጥቅምት 202310:58 11 ጥቅምት 2023ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ የአስቸኳይ ጊዜ መንግሥት እና የጦርነት ካቢኔ አቋቋሙየእስራኤል ወታደሮች በታንክ ላይOREN ROSENFELDCopyright: OREN ROSENFELDበስምምነቱ ከሐማስ ጋር የሚካሄደውን ጦርነት የሚመራ ካቢኔ ተቋቁሟልImage caption: በስምምነቱ ከሐማስ ጋር የሚካሄደውን ጦርነት የሚመራ ካቢኔ ተቋቁሟልየእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ እና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ቤኒ ጋንትዝ የአስቸኳይ ጊዜ መንግሥት ለማቋቋም ተስማሙ።ሁለቱ ፖለቲከኞች እዚህ ስምምነት ላይ የደረሱት ሐማስ ድንገተኛ ጥቃት ከፈጸመ በኋላ እስራኤል መጠነ ሰፊ የአጸፋ እርምጃ በጋዛ ላይ እያካሄደች ባለበት አምስተኛ ቀን ላይ ነው።ይህንን ስምምነት ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ፣ ጋንትዝ እና የአገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር ያሉበት “የጦርነት ካቢኔ” ያቋቁማሉ ተብሏል።በስምምነቱ መሠረት ጦርነቱ በሚካሄድበት ጊዜ “የጦርነቱን ሂደት ከሚመለከቱ ጉዳዮች በስተቀር ማንኛውም አይነት ሕግም ሆነ የመንግሥት ሃሳብ ለውሳኔ አይቀርብም።”በተጨማሪም ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የመንግሥት ሥልጣንን እንዲይዙ የተሾሙ ሰዎች የኃላፊነት ጊዜ በጦርነቱ ወቅት ሁሉ የሚቀጥል ይሆናል።ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ እና የናሽናል ዩኒቲ ፓርቲ ሊቀ መንበር ጋንትዝ የአስቸኳይ ጊዜ መንግሥት ለማቋቋም የተስማሙት ላለፉት ቀናት ንግግር ካደረጉ በኋላ ነው።ከስምምነቱ በኋላ ከሁለቱም ወገን በጋራ በወጣ መግለጫ ላይ “የአስቸኳይ ጊዜ መንግሥት ለመመሥረት እና ጦርነቱን የሚመራ ካቢኔ ለማቋቋም ተስማምተዋል።“ጦርነቱን የሚመራው ካቢኔም ጠቅላይ ሚኒስትሩን፣ የመከላከያ ሚኒስትሩን እና የተቃዋሚ ፓርቲውን መሪ በአባልነት ይዞ ይመሠረታል” ተብሏል።ከሦስቱ ባለሥልጣናት በተጨማሪ የጦርነቱ መሪ ካቢኔን በታዛቢነት የሚያገለግሉ ሁለት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ይካተቱበታል።Article share tools
  17. የታተመዉ 8:59 11 ጥቅምት 20238:59 11 ጥቅምት 2023ረቡዕ የተከሰቱ ዋና ዋና ጉዳዮችየጋዛ ዋነኛ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ማዕከልGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየጋዛ ዋነኛ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ማዕከልImage caption: የጋዛ ዋነኛ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ማዕከልእስራኤል በሐማስ ለተፈጸመባት ጥቃት አጸፋ ጋዛ ላይ ከበባ በመጣል ለአምስተኛ ቀን ተከታታይ የአየር ጥቃት እየፈጸመች ሲሆን፣ ሐማስም የሮኬት ጥቃቱን ቀጥሏል።በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የጋዛ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል።መሠረታዊ አቅርቦቶች በከተማዋ ውስጥ እየተሟጠጡ መሆናቸው እየተዘገበ ነው።ዛሬ ረቡዕ እስካሁን የተከሰቱ ዋና ዋና ጉዳዮች ምንድን ናቸው?
    • እስራኤል በጋዛ ላይ በጣለችው ጥብቅ ገደብ የነዳጅ ዕጥረት በመከሰቱ የከተማዋ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ማዕከል ሥራ ማቆሙን ባለሥልጣናት ተናግረዋል።
    • ሰኞ ዕለት እስራኤል ወደ ጋዛ የሚገቡ የኤሌክትሪክ እና የውሃ መስመሮች እንዲሁም የነዳጅ አቅርቦትን እንደምታቋርጥ አስታውቃ ነበር።
    • የእስራኤል የአየር ጥቃት በጋዛ ላይ ተጠናክሮ በቀጠለበት በአሁኑ ጊዜ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ከጥቃት ለመሸሽ ወደ ሆስፒታሎች እና ትምህርት ቤቶች እየገቡ ነው።
    • በእስራኤል ሰሜን እና ደቡብ ግዛቶች ውስጥ የሮኬት ጥቃት ማስጠንቀቂያ ደወሎች የተሰሙ ሲሆን፣ ከጋዛ በተተኮሱ ሮኬቶች የቆሰሉ ሰዎች እንዳሉ ተዘግቧል።
    • የእስራኤል ጦር 300 ሺህ ተጠባባቂዎችን ጨምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮችን በጋዛ ድንበር ላይ አሰባስቧል።
    • እስራኤል በድንበር በምትጎራበታት ሊባኖስ ውስጥ የሚገኙ የሄዝቦላህ ታጣቂዎች የፈጸሙባትን ጥቃት ተከትሎም ሊባኖስ ግዛት ውስጥ የአጸፋ ጥቃት ፈጽማለች።
    Article share tools
  18. የታተመዉ 6:51 11 ጥቅምት 20236:51 11 ጥቅምት 2023በእስራኤል-ፍልስጥኤም ግጭት የአፍሪካ አገራት ምን አቋም ያዙ?ግራፊክስBBCCopyright: BBCባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ የተቀሰቀሰውን ግጭት በተመለከተ የዓለም አገራት የተለያየ አቋማቸውን እያንጸባረቁ ነው።በዚህም በግልጽ ከእስራኤል ወይም ከፍልስጥኤም ጎን መሠለፋቸውን ያሳወቁ አገራት የመኖራቸውን ያህል፣ ከየትኛውም ወገን ሳይቆሙ ገለልተኛ አቋም ያንጸባረቁም አሉ።ከ54ቱ የአፍሪካ አገራት መካከልም ከፍልስጥኤም ጎን የተሰለፉ፣ እስራኤልን የደገፉ፣ ገለልተኛ አቋም የያዙ እና ለጊዜው ዝምታን የመረጡ አገራት አሉ።በዚህ ዝርዝር አስካሁን በይፋ አቋማቸውን ያንጸባረቁ የአፍሪካ አገራት ተካተዋል።Article share tools
  19. የታተመዉ 6:29 11 ጥቅምት 20236:29 11 ጥቅምት 2023ጋዛ ውስጥ በእስራኤል ጥቃት የተገደሉት ፍልስጥኤማውያን ቁጥር 1,055 ደረሰጋዛ ውስጥ በእስራኤል ጥቃት የተገደሉት ፍልስጥኤማውያን ቁጥር 1,055 ደረሰEPACopyright: EPAእስራኤል ጋዛ ላይ እያካሄደችው ባለው የአየር ጥቃት ምክንያት የተገደሉ እና ጉዳት የደረሰባቸው ፍልስጥኤማውያን ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው።የፍልስጥኤም የጤና ሚኒስቴር ረቡዕ እኩለ ቀን ላይ ባወጣው መረጃ የተገደሉ ሰዎች አሃዝ 1,055 ሲደርስ፣ ከ5,100 በላይ ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጨምሮ እንዳለው፣ በጥቃቱ ከተጎዱት ሰዎች መካከል 60 በመቶዎቹ ሴቶች እና ሕጻናት ናቸው።ሐማስ ቅዳሜ ዕለት በፈጸመው ጥቃት የተገደሉ እስራኤላውያን 1,200 ሲሆኑ ከ2,700 በላይ የሚሆኑ ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።Article share tools
  20. የታተመዉ 5:49 11 ጥቅምት 20235:49 11 ጥቅምት 2023እስራኤል በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን ወደ ጋዛ እያስጠጋች ነውየእስራኤል ወታደሮችGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤል አየር ኃይል ጋዛ ውስጥ የሐማስ ናቸው ያላቸውን ኢላማዎች ለአራተኛ ቀን እየደበደበ ባለበት በዛሬው ዕለት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የእስራኤል ወታደሮች ከጋዛ አቅራቢያ ሰፍረዋል።የሐማስ ጠንካራ ይዞታ በሆነችው ጋዛ ላይ እየተፈጸመ ባለው የአየር ጥቃት ምክንያት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የጋዛ ነዋሪዎች መፈናቀላቸው የተዘገበ ሲሆን፣ በነዳጅ ችግር ምክንያት በከተማዋ በሰዓታት ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ይቋረጣል።የሐማስ ተዋጊዎችን ለማደን እና የታገቱ ዜጎቿን ለማስለቀቅ እስራኤል እግረኛ ሠራዊቷን ወደ ጋዛ ታሰማራ እንደሆነ አስካሁን የታወቀ ነገር ባይኖርም፣ አስፈላጊውን ሁሉ እርምጃ እንደምትወስድ አስታውቃለች።የእስራኤል ጦር ሠራዊት ዛሬ ረቡዕ እንዳሳወቀው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቹ “የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለመፈጸም ዝግጁ ሆነው” ከጋዛ አቅራቢያ ይገኛሉ ብሏል።