ቀጥታ

እስራኤል 1.1 ሚሊዮን ፍልስጥኤማውያን ከጋዛ በ24 ሰዓታት ይውጡ አለች- ተመድ

Related Video and Audio

VIDEO 1 MINUTE 33 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 33 SECONDS1:33

Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBCበእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች

Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 23 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 23 SECONDS1:23

Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBCሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ?

Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBC

ጭምቅ ሃሳብ

  1. በአራት ቀናት ውስጥ ከ260 ሺህ በላይ ፍልስጥኤማውያን ከጋዛ ተፈናቅለዋል፡ የተባበሩት መንግሥታት
  2. ኢራን በእስራኤል ላይ ለተፈጸመው ጥቃት ድጋፏን ሰጥታ ይሆን?
  3. የፍልስጥኤማውያን የተቃውሞ ሰልፍ በዌስት ባንክ
  4. የቀጠለው የእስራኤል ጥቃት እና የአውሮፓ ኅብረት ትችት
  5. እስራኤል ከሶሪያ በኩል ለተሰነዘረ ጥቃት አጸፋውን መመለሷን ገለጸች
  6. የሳዑዲው ልዑል ሞሐመድ ቢን ሳልማን ለፍልስጥኤማውያን ድጋፋቸውን ገለጹ
  7. ውጊያው ሳይቆም በታጋቾች ጉዳይ ላይ አንደራደርም፡ ሐማስ
  8. በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት አጀማመር ምን ይመስላል?
  9. በጋዛ ከ123 ሺህ በላይ ፍልስጥኤማውያን ተፈናቀለዋል
  10. ኢራን፣ ሐማስ በፈጸመው ጥቃት ላይ ተሳትፎ የለኝም አለች
  11. እስራኤል በሊባኖስ ላይ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት ፈጸመች

ቀጥታ ዘገባ

  1. የታተመዉ 4:074:07በእስራኤል- ሐማስ ግጭት የተከሰቱ ዋና ዋና ጉዳዮችየጋዛ የአየር ጥቃትEPA-EFE/REX/ShutterstockCopyright: EPA-EFE/REX/Shutterstockእስራኤል ሐማስ ላደረሰው ጥቃት ምላሽ ነው በሚል በጋዛ ሰርጥ የምታደርጋቸው ተደጋጋሚ የአየር ጥቃቶች ቀጥለዋል።
    • 1.1 ሚሊዮን ነዋሪዎች ያሉባት የሰሜን ዋዲ ጋዛ ነዋሪዎች ወደ ደቡብ እንዲሸሹ የእስራኤል ጦር የ24 ሰዓታት ትዕዛዝ መስጠቱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል።
    • የእስራኤል ጦር የጋዛን ህዝብ “ለደህንነታቸው” ሲሉ አካካቢውን ለቀው እንዲወጡም መልዕክቱን አስተላልፏል።
    • እስራኤል ሃማስን ለማጥፋት የምድር ላይ ዘመቻ ለማካሄድ እየተጠበቀችበት ባለበት ወቅት ነው ይህን ማስጠንቀቂያ የተሰማው
    • የተባበሩት መንግሥታት ይህንን ያህል ህዝብ ማስወጣት የማይቻል ነው በሚል “አሰቃቂ ሰብዓዊ መዘዝ እንደሚያስከትል” በማስጠንቀቅ እስራኤል ውሳኔዋን እንድትቀለብስ ጠይቋል።
    • እስራኤል በበኩሏ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ እየሞከረች መሆኗን ጠቅሳ የተመድን ምላሽ “አሳፋሪ ነው” ስትል ተችታለች።
    • የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን ከፍልስጥኤም ፕሬዚዳንት ማህሙድ አባስ ጋር ዛሬ ይገናኛሉ ተብሏል።
    • የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲንም እስራኤል ገብተዋል ተብሏል።
    • የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በእስራኤል እና በሐማስ ግጭት ላይ ለመምከር ዛሬ የዝግ ስብሰባ ያደርጋል ተብሏል።
    Article share tools
  2. የታተመዉ 3:343:34ሐማስ የእስራኤልን ከሰሜን ጋዛ ለቃችሁ ውጡ ማስጠንቀቂያ ህዝቡ እንዳይሰማ ተናገረየጋዛ የአየር ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesእስራኤል 1.1 ሚሊዮን ፍልስጥኤማውያን ከሰሜን ጋዛ ለቀው ወደ ደቡባዊ ጋዛ እንዲሸሹ ማስጠንቀቂያ መስጠቷን ተክትሎ ሐማስ ህዝቡ እንዳይሰማ ተናገረ።ሐማስ ማስጠንቀቂያውን “ሃሰተኛ ፕሮፓጋንዳ” እንደሆነ ገልጾ ዜጎች ችላ እንዲሉትም አሳስቧል። የተባበሩት መንግሥታት የጋዛን ህዝብ የማስወጣት እቅድ በመቃወም ሁኔታውን የከፋ ያደርገዋል ሲልም እስራኤል ውሳኔዋን እንድትቀለብስ አጥብቆ ተማጽኗል።”እንዲህ ያለ የህዝብ እንቅስቃሴ አስከፊ ሰብዓዊ መዘዞች ሳያስከትል መተግበር አይቻልም” ሲልም የተባበሩት መንግሥታት ባወጣው መግለጫ አስጠንቅቋል።ሐማስ ታጣቂዎቹን ለመጠበቅ ሲል ንጹሃን ዜጎችን አደጋ ውስጥ በመክተት እንደ ሽፋን ይጠቀምባቸዋል የሚሉ ትችቶች ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ይቀርብበታል።ሐማስ በጋዛ ሰርጥ በአውሮፓውያኑ 2006 የተካሄደውን የህግ አውጭ ምርጫ ካሸነፈ በኋላ አካባቢውን ማስተዳደር ጀምሯል። በቀጣዩ ዓመትም ተቀናቃኙን ፋታህን በማስወገድ በጋዛ ሰርጥ ስልጣኑን አጠናክሯል።Article share tools
  3. የታተመዉ 3:173:17ፈረንሳይ የፍልስጥኤም የድጋፍ ሰልፎችን ከለከለችየድጋፍ ሰልፎችን ሙሉ በሙሉ የከለለከችው ፈረንሳይ ይህንን ህግ ተላልፈው ለሰልፍ የሚወጡ የውጭ ሃገር ዜጎች ከአገሪቱ መባበረርን የመሰለ ጠበቅ ያለ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ጄራልድ ዳርሚን አስጠንቅቀዋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  4. የታተመዉ 0:420:42ሰበርእስራኤል 1.1 ሚሊዮን ፍልስጥኤማውያን ከጋዛ በ24 ሰዓታት ይውጡ አለች- ተመድየአየር ጥቃት በጋዛAFPCopyright: AFPየእስራኤል ጦር 1.1 ሚሊዮን የጋዛ ነዋሪዎች በ24 ሰዓታት ውስጥ እንዲወጡ መጠየቋን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።ጦሩ በሰሜን ዋዲ ጋዛ የሚኖሩ ነዋሪዎች ወደ ደቡባዊ ጋዛ በ24 ሰዓታት ውስጥ መዛወር እንዳለባቸው ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መናገሩን የተመድ ቃለ አቀባይ ተናግረዋል።በዚህ አካባቢ የሚኖሩ ፍልስጥኤማውያን 1.1 ሚሊዮን አካባቢ ሲሆኑ ይህም ከጠቅላላው የጋዛ ሰርጥ ህዝብ ግማሽ ያህሉ እንደሆነም ነው ተመድ ያስታወቀው።ነዋሪዎች እንዲወጡ ከተጠየቁበትም ውስጥ በርካታ ህዝብ በተጨናነቀ ሁኔታ የሚኖርባት የጋዛ ከተማን ያጠቃልላል።ትዕዛዙ የተላለፈው በጋዛ እና እየሩሳሌም ሰዓት አቆጣጠር ትናንት ዕኩለ ሌሊት አካባቢም መሆኑ ተገልጿል። የእስራኤል ጦር መኮንኖች በጋዛ ተቀማጭነታቸውን ላደረጉ የተባበሩት መንግሥታት የቡድን አመራሮች ስለተላለፈው ትዕዛዘዝም ነግረዋቸዋል።ትዕዛዙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰራተኞችን ጨምሮ በተባበሩት መንግሥታት ተቋማት ትምህርት ቤቶች ፣ የጤና ማዕከላት እና ክሊኒኮች የተጠለሉ ፍልስጥኤማውያንንም ያጠቃልላል ተብሏል።የተባበሩት መንግሥታት የጋዛን ህዝብ የማስወጣት እቅድ በመቃወም ሁኔታውን የከፋ ያደርገዋል ሲልም እስራኤል ውሳኔዋን እንድትቀለብስ አጥብቆ ተማጽኗል።”እንዲህ ያለ የህዝብ እንቅስቃሴ አስከፊ ሰብዓዊ መዘዞች ሳያስከትል መተግበር አይቻልም” ሲልም የተባበሩት መንግሥታት ባወጣው መግለጫ አስጠንቅቋል።እስራኤል ምድር ላይ ልታደርገው ላቀደችው ወታደራዊ ዘመቻ በጋዛ ሰርጥ ድንበር በርካታ ወታደሮችን፣ ከባድ መሳሪያዎችን እያሰማራች ትገኛለች።ሐማስ ላደረገው ጥቃት ምላሽ ነው በሚል እስራኤል እረፍት የሌለው የአየር ጥቃት እየፈጸመች ትገኛለች።ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮም የእስራኤል አየር ኃይል በጋዛ ላይ እየፈጸመ ባለው የአየር ድብደባ ስድስት ሺህ የሚደርሱ ቦምቦችን በከተማዋ ላይ መጣሉም ተገልጿል።Article share tools
  5. የታተመዉ 0:400:40እስራኤል የምትመካበት የሚሳኤል እና የሮኬቶች ማምከኛ ‘አይረን ዶም’ ምንድን ነው?እስራኤል ከየትኛውም ወገን የሚሰነዘሩባትን የሚሳኤል እና የሮኬት ጥቃቶችን ለመከላከል “አይረን ዶም” የተባለውን የአየር ላይ ጥቃት ማምከኛ ሥርዓትን ትጠቀማለች።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  6. የታተመዉ 13:02 12 ጥቅምት 202313:02 12 ጥቅምት 2023ከቅዳሜ ጀምሮ ጋዛ በስድስት ሺህ ቦምቦች ድብደባ ተፈጽሞባታል፡ የእስራኤል ጦርጋዛGetty ImagesCopyright: Getty Imagesባለፈው ቅዳሜ ግጭቱ ከጀመረ አንስቶ የእስራኤል አየር ኃይል በጋዛ ላይ እየፈጸመ ባለው የአየር ድብደባ ስድስት ሺህ የሚደርሱ ቦምቦችን በከተማዋ ላይ መታሉ ተገለጸ።የእስራኤል መከላከያ ኃይሎች ቃል አቀባይ እንዳሉት ውጊያው ከተጀመረ በኋላ አስከ ሐሙስ ድረስ ቀን ከሌት በጋዛ ላይ በተፈጸመው የአየር ድብደባ ነው አየር ኃይሉ ጥቃቱን የፈጸመው።ቃል አቀባዩ ዳንኤል ሃጋሪ በጋዛ ላይ የተፈጸመው የቦንብ ውጅብኝ ስድስት ሺህ መሆኑን ያሳወቁት፣ አሁን ኤክስ በሚባለው የቀድሞው ትዊተር የማኅበራዊ ትስስር መድረክ ላይ በጭስ ተሸፍኖ በፍንዳታ የሚናወጥ አንድ ሕንጻን የሚያሳይ ቪዲዮን በማያያዝ ነው።Article share tools
  7. የታተመዉ 11:15 12 ጥቅምት 202311:15 12 ጥቅምት 2023በእስራኤል ጥቃት ጋዛ ውስጥ ከተገደሉ 450 የሚደርሱ ሕጻናት ናቸውፍልስጥኤማዊት ሕጻንReutersCopyright: Reutersየሐማስ ጥቃትን ተከትሎ እስራኤል በጋዛ ላይ እያካሄደችው ባለው የአየር ድብደባ ከተገደሉት መካከል 447ቱ ሕጻነት፣ 248 ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።የእስራኤል የአየር ድብደባ በቀጠለበት በአሁኑ ጊዜ የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን፣ ከቅዳሜ ጀምሮ አስከ ዛሬ ሐመስ አመሻሽ ድረስ በአጠቃላይ 1,417 ሰዎች ጋዛ ውስጥ መገደላቸው ተገልጿል።የሐማስ ታጣቂዎች ወደ እስራኤል በሺዎች የሚቆጠሩ ሮኬቶችን በመተኮስ እና ወደ እስራኤል ሰርጎ በመግባት ቅዳሜ ዕለት በፈጸሙት ጥቃት ከ1300 በላይ እስራኤላውያን መገደላቸውም ተነግሯል።Article share tools
  8. የታተመዉ 9:41 12 ጥቅምት 20239:41 12 ጥቅምት 2023አሜሪካ በየትኛውም ጊዜ ከእስራኤል ጎን ትቆማለች፡ አንቶኒ ብሊንከንየአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁus poolCopyright: us poolየአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁImage caption: የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁየአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን እስራኤል በሐማስ ለተፈጸመባት ጥቃት በጋዛ ላይ የአጸፋ እርምጃ እየወሰደች ባለበት ጊዜ አሜሪካ ለአስራኤል ያላትን አጋርነት ለመግለጽ በእስራኤል ጉብኝት እያደረጉ ነው።ብሊንከን ከእስራኤሉ ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል።ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በመሆን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫም፣ አሜሪካ በየትኛው ጊዜ ከአስራኤል ጎን እንደምትቆምና ድጋፏን እንደምትሰጥ ገልጸዋል።
    • ለጉብኝት እስራኤል የገቡት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን አገራቸው “በየትኛው ጊዜ እስራኤልን ለመርዳት” ከጎኗ እንደምትቆም በመግለጽ፣ ለሰላማዊ ሰዎች ጥበቃ ማድረግ አስፈላጊ ነው አሉ።
    • የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ሐማስ “አይሲስ ለአይሲስ በተስተናገደበት መንገድ ምላሽ ያገኛል” ብለዋል።
    • የእስራኤል ሠራዊት ጋዛ ሰርጥ ውስጥ የማስጠንቀቂያ ወረቀቶችን በመበተን ነዋሪዎች ሐማስ የሚጠቀምባቸው ሕንጻዎችን ስለሚያጠቃ ነዋሪዎች ወደ መጠለያ እንዲሄዱ አሳስቧል።
    • ስድስተኛ ቀኑን በያዘው እስራኤል በጋዛ ላይ በምትፈጽመው የአየር ጥቃት ቢያንስ 1,417 ሰዎች ሲገደሉ፣ 6,268 ሰዎች ላይ ደግሞ ጉዳት መድረሱን የጋዛ የጤና ባለሥልጣንት ገለጹ።
    • በሌላ በኩል የሐማስ ታጣቂዎች የገደሏቸው እስራኤላውያን ቁጥርም 1,300 ደርሷል። ሌሎች በርካቶች ደግሞ የመቁሰል ጉዳት እንደደረሰባቸው የእስራኤል ባለሥልጣንት አስታውቀዋል።
    • ብሪቲሽ ኤርዌይስ በእስራኤል ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ወደዚያው የሚያደርጋቸውን በራረቀዎች ለሚቀጥሉት ሦስት ሳምንታት እንዲቋረጡ ወሰነ።
    • የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ከእስራኤል ለቀው ለመውጣት ለሚፈልጉ ዜጎቹ የአየር ጉዞዎችን ማመቻቸቱን አስታወቀ።
    Article share tools
  9. የታተመዉ 9:28 12 ጥቅምት 20239:28 12 ጥቅምት 2023እስራኤል በሶሪያ አየር ማረፊያዎች ላይ ጥቃት መፈጸሟ ተዘገበእስራኤል በዋና ከተማዋ ደማስቆ እና በሌላኛዋ ከተማ አሌፖ ውስጥ በሚገኙ አየር ማረፊያዎች ላይ ጥቃት መፈጸሟን የሶሪያ መንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።የሶሪያ ዜና አገልግሎት ሳና “የሚሳኤል ፍንዳታዎች” በአየር ማረፊያው የመንደርደሪያ ሜዳ ላይ ጉዳት በማድረስ ከአግልግሎት ውጪ አድርጓቸዋል።ጥቃቱ በተፈጸመበት ጊዜ የሶሪያ የአየር መከላከያ መሳሪያዎች ምላሽ ለመስጠት መተኮሳቸውን የሶሪያ መገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል።የሶሪያ ሰብአዊ መብቶች ክትትል የተባለው መቀመጫውን በዩናይትድ ኪንግደም ያደረገው የግጭት ተከታታይ ቡድንም በርካታ ፍንዳታዎች አሌፖ ውስጥ መከሰታቸውን አረጋግጧል።ይህ የአየር ጥቃት መፈጸሙን የሚያመለክተው ዘገባ የወጣው የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሶሪያን ይጎበኛሉ ከተባለበት አንድ ቀን ቀደም ብሎ ነው።ሶሪያ እና ኢራን ከእስራኤል ጋር በጠላትንት የሚፈላለጉ አገራት ሲሆኑ፣ ኢራን አሁን እስራኤል እያደነችው ያለው ሐማስ ቡድንን እንደምትደግፍ ይነገራል።እስራኤል ከዚህ በፊትም ሶሪያ ውስጥ ያሉ የኢራን ናቸው የተባሉ እና የሊባኖስ ታጣቂ ቡድን የሆነውን ሄዝቦላህን ኢላማዎች በተደጋጋሚ ብትደበድብም በይፋ አረጋግጣ አታውቅም።Article share tools
  10. የታተመዉ 5:35 12 ጥቅምት 20235:35 12 ጥቅምት 2023የኢራን ፕሬዚደንት እስራኤልን ‘በዘር ማጥፋት’ ከሰሱየኢራን ፕሬዚደንት ኢብራሒም ሬይሲReutersCopyright: Reutersየኢራን ፕሬዚደንት እስራኤልን በዘር ማጥፋት ከሰሱ።ፕሬዚደንቱ ይህን ያሉት እስራኤል በጋዛ ላይ የምትፈፅመውን ጥቃት አጠናክራ በቀጠለችበት ወቅት ነው።ፕሬዚደንት ኢብራሒም ሬይሲ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የውሃ እና የነዳጅ አቅርቦት እንዲቋረጥ ተደርጎ በጋዛ ላይ የተደረገው ከበባ ሁሉንም ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የጣሰ ነው ሲሉ ኮንነውታል።ኢራን በጋዛ ያለውን ታጣቂ ቡድን ሐማስን በመደገፍና በማስታጠቅ ትታወቃለች።ሆኖም ማክሰኞ ዕለት የኢራን የበላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ አገራቸው ቅዳሜ ዕለት በእስራኤል ላይ ከተፈተው ጥቃት ጀርባ እንደሌለችበት ተናግረዋል።መሪው ይህን ይበሉ እንጂ ከጥቃቱ በኋላ በቴሌቪዥን በሰጡት በዚህ የመጀመሪያ መግለጫቸው፣በአይሁድ መንግሥት ላይ ጥቃቱን ለመፈፀም ያቀዱትን አድንቀናል ብለዋል።Article share tools
  11. የታተመዉ 3:39 12 ጥቅምት 20233:39 12 ጥቅምት 2023ሰበርታጋቾች እስኪለቀቁ ጋዛ መብራት፣ ውሃ እና ነዳጅ አታገኝም- እስራኤልጋዛGetty ImagesCopyright: Getty Imagesታጋቾች እስኪለቀቁ ድረስ የጋዛ ሙሉ ከበባ እንደሚቀጥል የእስራኤል ኢነርጂ ሚንስትር እስራኤል ካትዝ ገለጹ።”ታጋቾች” እስኪፈቱ ድረስ “መብራት አይኖርም፣ ውሃ አይለቀቀም እንዲሁም ምንም ዓይነት የነዳጅ መኪና አይገባም” ሲሉ እስራኤል ካትዝ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ጽፈዋል።የቅዳሜውን የሐማስን ጥቃት ተከትሎ ነው እስራኤል ወደ ጋዛ ሰርጥ የሚገቡ ምርቶችን ያገደችው። እስራኤል በሙሉ ከበባ ውስጥ ባስገባቻት ጋዛ ኤሌክትሪክ እና ውሃን ጨምሮ መሰረተ ልማቶች ተቋርጠዋል።መውጫ መግቢያ በታጣባት ጋዛ የተወሰነ እርዳታ እንዲገባ እና ነዋሪዎች እንዲወጡ ለማድረግ አሜሪካ ከእስራኤል፣ ከተባበሩት መንግሥታት እና ከግብጽ ጋር እየተነጋገረች መሆኗን ዋይት ሃውስ አስታውቋል።Article share tools
  12. የታተመዉ 3:10 12 ጥቅምት 20233:10 12 ጥቅምት 2023ከጋዛ የተገኙ የቅርብ ጊዜ መረጃዎችየተፈናቀሉ ፍልስጥኤማውያንGetty ImagesCopyright: Getty Imagesእስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ በምታደርገው የአየር ጥቃት የሞቱ ፍልስጥኤማውያን ቁጥር ከ1 ሺህ 200 ሰዎች በላይ መድረሱን የጤና ሚኒስቴሯ አስታውቋል።በተጨማሪም 5 ሺህ 339 ፍልስጥኤማውያን ቆስለዋል።እስራኤል ሃማስ ለሰነዘረብኝ ጥቃት አጸፋዊ ምላሽ ነው በሚልም ተደጋጋሚ የአየር ጥቃቶች በጋዛ ሰርጥ ላይ እየፈጸመች ትገኛለች።ሃማስ ባደረገው የተቀናጀ ጥቃት እና እስራኤል እየፈጸመችው ባሉ የአየር ጥቃቶች የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 500 ደርሷል።ተደጋጋሚ የአየር ጥቃቶቹንም ተከትሎ ከ338 ሺህ በላይ ፍልስጥኤማውያን መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታት የፍልስጥኤም ስደተኞች ኤጀንሲ አስታውቋል።አብዛኛዎቹም በሆስፒታሎች እና በተባበሩት መንግሥታት ትምህርት ቤቶች ተጠልለው ይገኛሉ።እስራኤል በሙሉ ከበባ ውስጥ ባስገባቻት ጋዛ ኤሌክትሪክ እና ውሃን ጨምሮ መሰረተ ልማቶች ተቋርጠዋል።መውጫ መግቢያ በታጣባት ጋዛ የተወሰነ እርዳታ እንዲገባ እና ነዋሪዎች እንዲወጡ ለማድረግ አሜሪካ ከእስራኤል፣ ከተባበሩት መንግሥታት እና ከግብጽ ጋር እየተነጋገረች መሆኗን ዋይት ሃውስ አስታውቋል።Article share tools
  13. የታተመዉ 2:47 12 ጥቅምት 20232:47 12 ጥቅምት 2023የተባበሩት መንግሥታት በእስራኤል እና በጋዛ ጉዳይ ነገ ስብሰባ ሊያካሂድ ነውየተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በእስራኤል እና ጋዛ መካከል ያለው ግጭት ላይ ለመወያየት ነገ ስብሰባ ሊያካሂድ ነው።በጋዛ ሰርጥ ስላለው ሁኔታ ለመነጋገር ስብሰባውን የጠራችው የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታውን ምክር ቤት በሊቀመንበርነት የተረከበችው ብራዚል መሆኗን የአገሪቷ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።የብራዚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማውሮ ቬራ በኒውዮርክ በሚካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ወደ እስያ የሚያደርጉትን ጉዞ አቋርጠዋል።የጸጥታው ምክር ቤት አባላት እሑድ ዕለት ባካሄዱት ስብሰባ እስራኤል እና ፍልስጥኤምን በሚመለከተው ፖሊሲ ላይ ወደ አንድ ሃሳብ መምጣት አልቻሉም ነበር።የብራዚል ፕሬዚደንት ሊዩዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ ረቡዕ ዕለት “በየትኛውም ዓለም ሕጻናት በፍጹም መታገት የለባቸውም” ሲሉ በኤክስ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።ፕሬዚደንቱ ጨምረውም ሐማስ ከቤተሰቦቻቸው ነጥቆ ያገታቸውን ሕጻናት መልቀቅ አለበት ብለዋል።ፕሬዚደንቱ እስራኤል በፍልስጥኤማዊ ሕጻናት እና እናቶቻቸው ላይ የምታዘንበውን ቦምብ እንድታቆም ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ ይህም በግብጽ በኩል ከጋዛ እንዲወጡ እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል።“በጦርነት እብደት ውስጥም ቢሆን ትንሽ ሰብዓዊነት ሊኖር ይገባል” ሲሉም አክለዋል።Article share tools
  14. የታተመዉ 2:38 12 ጥቅምት 20232:38 12 ጥቅምት 2023ብሊንከን እና የፍልስጥኤሙ ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ ሊወያዩ ነውአንቶኒ ብሊንከንGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየፍልስጥኤም ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ እና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን በመጪው አርብ ተገናኝተው ሊነጋገሩ መሆኑን የፍልስጥኤም ነጻነት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ሁሴን አል-ሼክ ገለጹ።የፍልስጥኤም የፖለቲካ መሪዎች ዌስት ባንክን በሚመራው በማህሙድ አባሱ ፋታህ ፓርቲ እና ጋዛ ሰርጥን በሚቆጣጠረው ታጣቂ ቡድን ሐማስ ተከፋፍለዋል።ብሊንከን ከሰዓታት በኋላ እስራኤል እንደሚገቡ ይጠበቃል።በቆይታቸውም የሐማሳን ጥቃት ተከትሎ ለእስራኤል እና ለህዝቦቿ ያላቸውን ድጋፍ ያሳያሉ ተብሏል።የፍልስጥኤም ባለስልጣናት በኤክስ ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት ፕሬዝዳንት አባስ ከዮርዳኖሱ ንጉስ አበዱላህ ጋር ዛሬ አማን ውስጥ ይገኛሉ።Article share tools
  15. የታተመዉ 2:29 12 ጥቅምት 20232:29 12 ጥቅምት 2023እያንዳንዱ የሐማስ አባል በሞት ጥላ ሥር መሆኑን ኔታንያሁ ተናገሩየእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ እያንዳንዱ የሐማስ አባል በሞት ጥላ ሥር መሆኑን ተናገሩ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  16. የታተመዉ 2:29 12 ጥቅምት 20232:29 12 ጥቅምት 2023በእስራኤል-ሐማስ ዙሪያ ሐሰተኛ መረጃዎች ላይ እርምጃ እንዲወስድ የአውሮፓ ህብረት ሜታን ጠየቀሐማስ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ “ሐሰተኛ መረጃዎች” በሜታ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመስፋፋቱ የአውሮፓ ሕብረት ማርክ ዙከርበርግን አስጠነቀቀ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  17. የታተመዉ 2:29 12 ጥቅምት 20232:29 12 ጥቅምት 2023ሐማስ ጥቃት ከመፈጸሙ ከቀናት በፊት ግብፅ እስራኤልን አስጠንቅቃ ነበር – አሜሪካሐማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት ከመክፈቱ ሦስት ቀናት ቀደም ብሎ ግብፅ እስራኤልን አስጠንቅቃ እንደነበር የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር ተናገሩ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  18. የታተመዉ 0:17 12 ጥቅምት 20230:17 12 ጥቅምት 2023ሐማስ የእስራኤልን መከላከያ ለማለፍ የተጠቀመው የ2ኛው የዓለም ጦርነት መሣሪያየእስራኤል እና የሐማስ ግጭት ከተጀመረ ቀናት ተቆጥረዋል። ቅዳሜ ዕለት ሐማስ የፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ የተጀመረው ግጭት ዓለምን እያነጋገረ ነው። አገራትንም ጎራ አስለይቷል።ለመሆኑ ሐማስ የእስራኤልን መከላከያ ለማለፍ ስለተጠቀመው የሁለተኛው የዓለም ጦርነት መሣሪያ ምን እናውቃለን?ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  19. የታተመዉ 23:49 11 ጥቅምት 202323:49 11 ጥቅምት 2023የሐማስ ጥቃት እና በሕዝቡ ዘንድ የፈጠረው ድንጋጤ በቤተ እስራኤላዊው ዐይንባለፈው ቅዳሜ ሐማስ ወደ እስራኤል ግዛቶች በመግባት የፈጸመው ጥቃት የቀሰቀሰው ግጭት ቀናት የተቆጠሩ ሲሆን፣ በቀላሉ የሚቋጭ አይመስልም። ከሁለቱም ወገን በሰው ላይ የሚደርሰው ጉዳት ከዕለት ዕለት እየጨመረ ነው። ስለጥቃቱ ዕለት እና ጥቃቱን ተከትሎ በሕዝቡ ውስጥ የተፈጠረውን ስሜት ከጋዛ አቅራቢያ ከምትገኘው አሽኬሎን ከተማ ነዋሪ የሆኑ ቤተ እስራኤላዊ ነግረውናል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  20. የታተመዉ 13:58 11 ጥቅምት 202313:58 11 ጥቅምት 2023‘የት እንሂድ?’ የጋዛ ነዋሪዎችን መሸሸጊያ አልባ ያደረገው የተጠናከረው የእስራኤል ጥቃትየእስራኤል ጥቃት በርካታ የመኖሪያ ሕንፃዎችን አውድሟል። የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያ ቢሮዎች እና የጋዛ እስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ሕንጻም ክፉኛ ተጎድተዋል። ሰኞ ዕለት አስፈሪ ፍንዳታዎች አካባቢውን ሲንጡ አመሹ። ልጆች ያለቅሳሉ፤ ለደቂቃዎች ማሸለብ የቻለም የለም።
  21. ተጨማሪ ያንብቡ