
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ጄ. ብሊንከን እና የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአፍሪካ ቀንድ የጸጥታ ችግሮች እና የአንድነት፣ ሰላማዊ እና የበለፀገች ኢትዮጵያ የጋራ ግብ ላይ ዛሬ ተወያይተዋል።
ጸሃፊ ብሊንከን በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ያለው ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው ገልፀው በፖለቲካዊ ውይይት እና ሰብአዊ መብቶችን በማስከበር በሰላማዊ መንገድ መፍታት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።
ፀሃፊው እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ የምግብ ዕርዳታውን እንደገና ለማስጀመር በተሻሻለው የሰብአዊ ቁጥጥር ላይም ተወያይተዋል። ጸሃፊ ብሊንከን እውነተኛ፣ ተአማኒ እና ሁሉን ያካተተ የሽግግር የፍትህ ሂደት ለመመስረት እየተካሄደ ያለውን ስራ በደስታ ተቀብለዋል።
The following is attributable to Spokesperson Matt Miller:
Secretary of State Antony J. Blinken and Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed today discussed security challenges in the Horn of Africa and the shared goal of a unified, peaceful, and prosperous Ethiopia. Secretary Blinken expressed concern about the situations in the Amhara and Oromia Regions and underscored the need to promote peaceful resolution through political dialogue and protection of human rights. The Secretary and Prime Minister also discussed improved humanitarian oversight to allow for the resumption of food assistance. Secretary Blinken welcomed ongoing work to establish a genuine, credible, and inclusive transitional justice process.
