October 13, 2023 – Zemedkun Bekele
“…ሰላም ላንተ ይሁን ዘመዴ…! ጠፋን አይደል… ፋኖ እያሯሯጠን ምን እረፍት አለ ብለህ ነው። ወደ ገደለው ስንገባ ቀጣዩን መልእክት እንደተለመደው ለፋኖና ለዐማራ ሕዝብ አድርስልን።
1~ በጀነራል ጌታቸው ጉዲና አማካኝንት በግንባር ለሚገኙ የጦር አዛዦች የወረደ መልእክት ተላልፏል። ውጊያው በምንፈልገው መልኩ ስላልሄደልን፣ ከዚህ በላይ ከሄድን የባሰ ውርደት ስለሚመጣ ጉዳዩ በእርቅ ያልቅ ዘንድ ጠቅላዩን አሳምነነዋል። ስለዚህ እናንተ “ከፋኖ ጋር የምታደርጉትን ውጊያ ለጊዜው ኃይል ቀንሱ” በማለት ለዚሁም ሽማግሌዎች ተሰይመው ማለቃቸውን መልክት አስተላልፏል። አንድ ትልቅ ጀነራልም ጉዳዩን ይመራዋል። እርቁ የሚያልቀው ለብልፅግና በሚያደላ መንገድ አቅጣጫ ተቀምጦለት ነው። ስለዚህ ፋኖዎቹ ካልመጡባችሁ በቀር ሄዳችሁባቸው ሠራዊቱን አታስመቱ የሚል መመሪያ ነው ያወረደው ጌታቸው ጉዲና። ስለዚህ ፋኖን እርቅ ብሎ ነገር የለም። ልክ እንደ ቡልጋው፣ እንደ አዴት፣ እንደ ደቡብ ጎንደሩ ያለበት ድረስ ሄዳችሁ በትኑት በልልን ብለዋል። የህዳሴውንም ግድብ የሚጠብቅ የነበረው ጦር ወደ ዐማራ ክልል ታዝዞ ገብቷል። አልፎ ወደ ኤርትራ ድንበር ይሄደላም እየተባለ ነው። ነገር ግን ሠራዊቱ አልቋል።
2~ የተወሰኑቱ የኦሮሞ ጄነራሎች እና አቢይ አሕመድ የፍልስጤሙ ሃማስ በእስራኤል ላይ ያደረሰውን ጥቃት ቀደም ብለው መረጃ ሳይኖራቸው አይቀርም እየተባለ እየተወራ ነው። እነ ሬድዋን ሁሴን እና የኦሮሞ ጀነራሎቹ በደንብ ያውቁታል፣ የድጋፍ እጃቸው ይኑርበት አይኑርበት እስከአሁን የታወቀ ነገር የለም እንጂ አሳምረው ሳያውቁ አይቀርም። “ኦሮሞም እንደ ፍልስጤም በኢምፓየሪቷ ኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ስር ያለ ሕዝብ ነው። የዐማራን መስፋፋት ኦነግ መጥቶ ባያስቆምልን ኖሮ እኛም ዕጣፈንታችን እንደፍልስጤም ነበር የምንሆነው፣ በድፍረት ለፍልስጤም እስከመዝመት ድረስ ዝግጁ ነን የሚሉም አሉ። በየመስጊዱ የፍልስጤም ባንዲራ ተይዞ የሚፎከረውም ለዚህ ነው። እናም አሁን የቀይ ባህር አጀንዳ የመጣው ከዚህ ጭንቀት ለማገገም ነው የሚሉም አሉ። እስራኤላውያኑ ከደረሱበት ግን እንጃልን…ብለዋል ጀነራሎቹ።
3~ ሌላው የመከላከያ ጀነራሎች ሦስት ዓይነት ታርጋ እየተጠቀሙ ነው። ግቢ እያሉ የመከላከያ ታርጋ፣ ከግቢ ሲወጡ ከድ 2 እና ኮድ 3፣ ከከተማ ሲወጡ ደግሞ የዕርዳታ ድርጅት ታርጋ ነው የሚጠቀሙት። ስለዚህ ፋኖ እንዳይዘነጋ ንገርልን። የሚገርመው ነገር ደግሞ ምን እንደሰሙ ባይታወቅም ለኦሮሞ ጀነራሎችና መኮንኖች ብቻ “አከማችታችሁ ቀለብ ያዙ” ተብለው አንድ ኩንታል ጤፍ፣ ሩዝ እና መካሮኒ ከዘይት ጋር ያዙ ተብለው እየታደላቸው ነው። ምን እንደሰሙ ፈጣሪ ይወቅ።
4~ ብርሃኑ ጁላና አቢይ ሳይኮራረፉ አልቀረም። አበባውም እንደዚያው አያናግረውም የሚሉ አሉ። ጁላን አዋረድከኝ ነው የሚለው። ከቁም እስረኝነት አውጥቼ ያስወገድኩህን አባ ገዳዎች ናቸው ኦሮሞ ነው ለምን ታዋርደዋለህ፣ ሹመት ስጠው ብለው ” ፊልድ ማርሻል” የሚል ፈጥሬ ሰጥቼ እርባና ለሌለው ሰው ሹመጥ ሰጥቼ የተዋረድኩት ብሎ እያበደበት ነው ይሉናል ቤተሰብ የሆኑ ወዳጆቻችን። እስከ መስከረም 30 ብሎ ብሬም ሳይቦተረፍ አይቀርም። ወፍ የለም ሲሆንበት ነው አብይ ያበደበት ተብሏል ነው የሚሉት።
5~ ፋኖ በቅርቡ የጀመረው የዞንና የወረዳ የብአዴን አመራሮችን፣ የፖሊስ አዛዦችን እና የሚኒሻ ሃላፊዎችን ማጽዳቱ እንዴት ያለ ክፍተት በመዋቅሩ ውስጥ እንደሚከፍት ልንነግርህ አንችልም። የክልል ፕሬዘዳንት ከመግደል ይልቅ የዞንና የወረዳ የካቢኔ አባላት ላይ የሚወሰድ እርምጃ አገዛዙን በቶሎ ያፍረከርከዋል። ቡልጋ ላይ ፋኖ አስቀድሞ የብልፅግና አመራሮችን ከምንገድላቸው በማለት ለቃቅሞ ማሰሩ መከላከያው እውር እንዲሆን ነው ያደረገው። ያ ሁሉ ጦር የተደመሰሰው ብልፅግናዎች በፋኖ በመታሰራቸው ነው። ስለዚህ እዚህ ላይ ይሠራበት። ይገርምሃል አንዳንድ ቦታ እኛ ገብተን አዲስ መዋቅር ለመሥራት ሕዝቡን አወያይተን አዲስ ሰው እንምረጥ ስንል እሺ ብሎ የሚሾም ሰው አላገኘንም። ልጆቼን ላሳድግበት የሚለን ነው የበዛው። ደመቀ መኮንን ቤተ መንግሥት ተቀምጦ የሚያዘው ከጠፋ ያው መሸነፉም አይደል? ስለዚህ ወረዳ፣ ከተማ ላይ የዞንና የወረዳ ሰዎችን መኮርኮም ድሉን ያፋጥነዋል በልልን።
“…መጪው ጊዜ ስለእውነት ከባድ ነው። ጥቅምት ህዳር የእህል ነገር እንጃ፣ ምን እንደሚሻል አናውቅም። ከመከላከያ ወደ ፋኖ የሚኮበልለውም በዝቷል። እርስ በእርስም በኦሮሞ እና በሌላው የሠራዊቱ አዛዦች መሃል ልዩነቱ በዝቷል። በተለይ የአውራ ጎዳናን በግልጽ ከዐማራ ላይ ወስደው ለኦሮሞ ሲያደርጉ ሰራዊቱ ዝም እንዲል ብቻ ሳይሆን ተባባሪ መሆኑ ሲታይ ሁሉም ደብሮታል። ለፋኖ ስትልልን ወደ ፋኖ ኮብልሎ የሚመጣውን ሁሉ በጥንቃቄ መቀበሉን አትዘንጉ። ላሊበላ አካባቢ በፋኖ ላይ የደረሰው ጉዳት መረጃው የመጣው ከዚያው ከመሃላቸው ነው። እናም ጥብቅ ዲሲፒሊን ይውሰዱ።
“…በትግራይ በኩል ጦርነት ይመጣል የሚል ግምገማ በእኛ በኩል የለም። ኖረም አልኖረም ግን ፋኖም የዐማራ ሕዝብም ሁልጊዜ ዝግጁ መሆናችሁን አትዘንጉ። ዝግጁ ሁኑ በልልን። በመጨረሻም ሰሞኑን በቡልጋ፣ ምንጃር የተፈጸመው ዓይነት የፋኖ ስህተት እንዳይደገም በልልን። ሰራዊቱን የደመሰሱበት ታክቲክ ልዩ እንደነበር ሰምተናል። ነገር ግን የማረካችሁትን ዙ23 መሣሪያ ስለተቆለፈ ብቻ አልከፈት ብሎናል ብላችሁ ማቃጠላችሁ ትክክል አይደለም በልልን። ስንትናስንት ባለሙያ የሆነ ዐማራ እያለ ይሄን የመሰለ ጮማ የሆነ መሳሪያ በእሳት ማቃጠል አግባብ አይደለም በልልን ብለዋል ጀነራሎቹ።
• አድርሻለሁ…!
