Related Video and Audio

VIDEO 1 MINUTE 33 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 33 SECONDS1:33
Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBCበእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች
- BBC
Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 23 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 23 SECONDS1:23
Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBCሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ?
- BBC
Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBC
ጭምቅ ሃሳብ
- በአራት ቀናት ውስጥ ከ260 ሺህ በላይ ፍልስጥኤማውያን ከጋዛ ተፈናቅለዋል፡ የተባበሩት መንግሥታት
- ኢራን በእስራኤል ላይ ለተፈጸመው ጥቃት ድጋፏን ሰጥታ ይሆን?
- የፍልስጥኤማውያን የተቃውሞ ሰልፍ በዌስት ባንክ
- የቀጠለው የእስራኤል ጥቃት እና የአውሮፓ ኅብረት ትችት
- እስራኤል ከሶሪያ በኩል ለተሰነዘረ ጥቃት አጸፋውን መመለሷን ገለጸች
- የሳዑዲው ልዑል ሞሐመድ ቢን ሳልማን ለፍልስጥኤማውያን ድጋፋቸውን ገለጹ
- ውጊያው ሳይቆም በታጋቾች ጉዳይ ላይ አንደራደርም፡ ሐማስ
- በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት አጀማመር ምን ይመስላል?
- በጋዛ ከ123 ሺህ በላይ ፍልስጥኤማውያን ተፈናቀለዋል
- ኢራን፣ ሐማስ በፈጸመው ጥቃት ላይ ተሳትፎ የለኝም አለች
- እስራኤል በሊባኖስ ላይ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት ፈጸመች
ቀጥታ ዘገባ
- የታተመዉ 12:4512:45ዌስት ባንክ ውስጥ በተካሄደ ተቃውሞ ወቅት 11 ሰዎች ተገደሉ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየፍልስጥኤም የጤና ሚኒስቴር ዌስት ባንክ ውስጥ በተቃዋሚዎች እና በእስራኤል ወታደሮች መካከል በተከሰተ ግጭት 11 ሰዎች መገደላቸውን አስታወቀ።ዛሬ አርብ ከጋዛ ርቆ በሚገኘው የፍልስጥኤም ግዛት በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጥኤማውያን ጋዛ ውስጥ ወገኖቻቸው ከቤታቸው እንዲፈናቀሉ መገደዳቸውን በመቃወም ነው አደባባይ ወጥተው ተቃውሞ ያሰሙት።ሰዎቹ የተገደሉት ዌስት ባንክ ውስጥ በሚገኙት ራማላህ፣ ናብሉስ፣ ሄብሮን እና ቱልካራም ውስጥ በተካሄዱ ተቃውሞዎች ወቅት ከእስራኤል ወታደሮች ጋር በመጋጨታቸው ነው።ከተገደሉት ሰዎች በተጨማሪም ከአንድ መቶ የሚበልጡ ሌሎች ደግሞ የመቁሰል ጉዳት እደደረሰባቸው ተዘግቧል።በዌስት ባንክ እና በምሥራቅ ኢየሩሳሌም ውስጥ የሚገኙ ፍልስጥኤማውያን ከ1967 (እአአ) ጀምሮ በእስራኤል ወረራ ስር ነው የሚኖሩት።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ

- የታተመዉ 12:0612:06በትንሽ ቦታ ብዙ ሕዝብ ተጨናንቆ የሚኖርባት ጋዛ
BBCCopyright: BBCጋዛ ሰርጥ በዓለም ላይ ብዙ ሕዝብ በከፍተኛ ሁኔታ ተጠጋግቶ ከሚኖርባቸው አካባቢዎች አንዱ ነው። በዚህም 365 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሆን ስፋት ባለው ግዛቷ ውስጥ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ይኖራል።በእያንዳንዷ የጋዛ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ቦታ ላይ 5,700 ሰዎች ተጠጋግተው ይኖራሉ። ይህ የለንደን ሕዝብ ካለው የጥግግት መጠን ጋር ተመሳሳይ ነው።ከላይ የተቀመጠው ካርታ እንደሚያሳየው ደግሞ ከዋዲ ጋዛ በስተሰሜን ባለው የጋዛ ከተማ ውስጥ ከ9,000 ሰዎች በላይ በእያንዳንዱ ስኩዌር ኪሎ ሜትሮች ላይ ሰፍረው ይገኛሉ።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 11:1611:16ሐማስ በእስራኤል ላይ የሚፈጽመው የሮኬት ጥቃት መቀጠሉን አስታወቀ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesዛሬ አርብ ሰባተኛ ቀኑን በደፈነው ግጭት ፍልስጥኤማዊው ታጣቂ ቡድን ሐማስ ወደ እስራኤል ሮኬቶችን መተኮሱን ቀጥሏል።ቡድኑ እንዳለው ዛሬ አርብ ከሰዓት በኋላ በሰሜናዊ እስራኤል ውስጥ ወደምትገኘው ሳፊድ ከተማ ሚሳኤል አስወንጭፏል።የእስራኤል የጦር ኃይሎች ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ በኤክስ (ትዊተር) ላይ እንዳሰፈሩት ከጋዛ ወደ ሰሜናዊ እስራኤል ክልል የተተኮሱ ሮኬቶች እንዲከሽፉ ተደርገዋል ያሉ ሲሆን፣ ነገር ግን የተተኮሰባትን ከተማ ስም አልጠቀሱም።ሐማስ ወደ ባሕር ዳርቻ ከተማዋ ቴል አቪቭ ሮኬቶችን ካስወነጨፈ በኋላ በከተማዋ ውስጥ የአየር ጥቃት መስጠንቀቂያ ደወል ድምጽ ተሰምቷል።ታጣቂው ቡድን ባለፈው ቅዳሜ በፈጸመው ጥቃት 1,300 ሰዎችን ወደ ገደለባቸው የደቡብ እስራኤል ከተሞች ወደሆኑት አሽኬሎን፣ ስዴሮት እና ቤሪ ሮኬቶችን መተኮሱን ገልጿል።እስራኤል በጋዛ ላይ የአጸፋ ጥቃት እየፈጸመችበት ባለበት በአሁኑ ጊዜ ሐማስ በሺዎች የሚቆጠሩ ሮኬቶችን ሲቪሎች ወደ ሚኖሩባቸው የእስራኤል አካባቢዎች ተኩሷል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:568:56የሊባኖሱ ሄዝቦላህ ሐማስን በመደገፍ እንሚሰለፍ ገለጸ
EPACopyright: EPAየኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የሄዝቦላህ መሪ ቤይሩት ውስጥ በተወያዩበት ወቅትImage caption: የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የሄዝቦላህ መሪ ቤይሩት ውስጥ በተወያዩበት ወቅትየሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላህ ከእስራኤል ጋር ግጭት ውስጥ የገባው ፍልስጥኤማዊውን ሐማስን በመደገፍ እንደሚሰለፍ አስታወቀ።የሄዝቦላህ መሪ ሐሰን ናስራላህ ሊባኖስን በመጎብኘት ላይ ካሉት የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴይን አብዶላሃይን ጋር ተገናኝተው በተወያዩበት ጊዜ፣ ጋዛ ውስጥ የሚፈጸመውን “የጦር ወንጀል ለመቋቋም ያለጥርጥር የጋራ ምላሽን መነሳቱ አይቀርም” ሲሉ ተናግረዋል።በተመሳሳይ የሄዝቦላህ ምክትል መሪ ሐማስ ከእስራኤል ጋር በሚያደርገው ጦርነት ውስጥ “ጊዜው ሲደርስ” ቡድናቸው ለመሳተፍ “ሙሉ ለሙሉ ዝግጁ ነው” ሲሉ በቤይሩት ዳርቻ በተደረገ ሰልፍ ላይ ተናግረዋል።ሄዝቦላህ የፍልስጥኤም አጋሩን ሐማስን ለመደገፍ ወስኖ በጦርነቱ ከተሳተፈ እና እስራኤል ላይ ጥቃት ከከፈተ፣ አዲስ የጦርነት ግንባር ሊከፈት ይችላል የሚል ተጨባጭ ስጋት አለ።እንደ ፍልስጥኤሙ ሐማስ ሁሉ የሊባኖሱ ሄዝቦላህ በዩናይትድ ኪንግደም፣ በአሜሪካ እና በሌሎች ምዕራባውያን አገራት ሽብርተኛ ድርጅት ተብሎ ተፈርጇል።ሄዝቦላህ በሊባኖስ ውስጥ በፖለቲካ እና በወታደራዊ መስክ ኃያል ሚና ያለው ሲሆን፣ የምዕራባውያን ባላንጣ ከሆነችው ኢራን ጋር ወዳጅ ነው።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:158:15የእስራኤልን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ነዋሪዎች ከሰሜናዊ ጋዛ እየሸሹ ነው
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤልን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ በሰሜናዊ ጋዛ የሚገኙ በርካታ ነዋሪዎች ባገኙት የመጓጓዣ ዘዴ በመጠቀም አካባቢውን ለቀው እየወጡ ይገኛሉ።የእስራኤል ሠራዊት ከጋዛ ነዋሪ ግማሹ ከሚገኝበት አካባቢ ሕዝቡ ለቆ እንዲወጣ ያዘዘው በጋዛ ውስጥ ላሉት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሠራተኞች ነው።ሰሜናዊ ጋዛ 1.1 ሚሊዮን ነዋሪዎች በ24 ሰዓታት ውስጥ አካባቢውን ለቀው ወደ ደቡብ እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ከተሰጠ በኋላ ሴቶች እና ሕጻናትን ጨምሮ ፍልስጥኤማውያን መኖሪያቸውን እየለቀቁ በመውጣት ላይ ናቸው።እጅግ በተጨናነቀ ሁኔታ ከሚኖርባቸው የዓለማችን ክፍሎች መካከል አንዷ በሆነችው ጋዛ ውስጥ ካለው ነዋሪ ግማሽ የመሆኑት ከ18 ዓመት በታች ያሉ ናቸው።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 6:496:49ሰበርሐማስ በጋዛ 13 ታጋቾች በእስራኤል የአየር ጥቃት መገደላቸውን ገለጸ
ReutersCopyright: Reutersሐማስ በእገታ ከወሰዳቸው ውስጥ ቢያንስ 13 እስራኤላውያንን እና የውጭ አገራት ዜጎች እስራኤል በጋዛ ሰርጥ እያደረገችው ባለችው የአየር ጥቃቶች መገደላቸው አስታወቀ።ታጋቾቹ ባለፉት 24 ሰዓታት እስራኤል በምታደርገው የአየር ጥቃቶች መገዳላቸውንም ነው የሃማስ የጦር ክንፍ የገለጸው።”13 እስረኞች፣ የውጭ ዜጎችን ጨምሮ” የእስራኤል ተዋጊ ጄቶች ኢላማ ባደረጓቸው አምስት ስፍራዎች መገደላቸውን የኢዜዲን አል ቃሳብ ብርጌድ በመግለጫው አስፍሯል።ሐማስ ከቀናት በፊት በሰነዘረው ድንገተኛ ጥቃት ወደ 150 የሚጠጉ ታጋቾችን ወስዷል። እስራኤል ያለምንም ማስጠንቀቂያ የሰላማዊ ዜጎችን መኖሪያ ቤቶችን በቦምብ የምትደበድብ ከሆነ ታጋቾችን ለመግደልም ዝቷል።ታጋቾች ተገድለዋል መባሉን ተከትሎ የዩናይትድ ኪንግደም የመከላከያ ሚኒስትር ግራንት ሻፕስ መረጃውን በጥንቃቄ እንደሚያዩት ቢገልጹም ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረባቸው አይቲቪ ለተሰኘው ሚዲያ ተናግረዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 6:166:16ብሊንከን እና የፍልስጥኤሙ ፕሬዚዳንት በዮርዳኖስ ተገናኙ
ReutersCopyright: Reutersየአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን ከፍልስጥኤሙ ፕሬዚዳንት ማህሙድ አባስ ጋር ተገናኙ።ብሊንከን እና ፕሬዚዳንቱ የተገናኙት ዛሬ ጥቅምት 2/2016 ዓ.ም በዮርዳኖስ ነው።ዌስት ባንክን የሚመራው የማህሙድ አባሱ ፋታህ እና የጋዛ ሰርጥን የሚቆጣጠረው ታጣቂው ቡድን ሐማስ ተቀናቃኝ ናቸው።ብሊንከን ከዮርዳኖሱ ንጉስ አብዱላህ ጋር በአማን ይገናኛሉ ተብሏል።የውጭ ጉዳይ ኃላፊው ትናንት ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር ተገናኝተው የነበረ ሲሆን በሐማስ ተገደሉ የተባሉ የሞቱ ህጻናትን ምስሎችም እንዲያዩ መደረጋቸውም ተገልጿል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 6:036:03በጠና የታመሙ ፍልስጥኤማውያንን ከሰሜን ጋዛ ማስወጣት “የሞት ፍርድ ነው”_ የዓለም ጤና ድርጅት
AFPCopyright: AFPእስራኤል 1.1 ሚሊዮን ፍልስጥኤማያውን ከሰሜን ዋዲ ጋዛ ወጥተው ወደ ደቡባዊ ጋዛ እንዲሸሹ ትዕዛዝ መስጠቷን ተከትሎ በጠና የታመሙ ነዋሪዎችን ማስወጣት “የሞት ፍርድ ነው” ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።የዓለም ጤና ድርጅት በሆስፒታል ውስጥ ያሉ ህመምተኞችን በጭራሽ ማስወጣት እንደማይቻልም ነው የገለጸው።”በጠና የታመሙ እና የመዳን እድላቸው በድጋፍ ሰጪ ቬንትሌተሮች ብቻ የሆኑ በርካታ ፍልስጥኤማውያን በሆስፒታሎች አሉ” ሲሉም የዓለም ጤና ድርጅት ቃለ አቀባይ ታሪክ ጃሳሬቪች ተናግረዋል።”እነዚህን ህመምተኞች ማንቀሳቀስ ማለት የሞት ፍርድ ነው። የጤና ባለሙያዎች ይህንን ያድርጉ ማለት ከጭካኔ በላይ ነው” ሲሉም አስረድተዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 5:585:58እስራኤል በጋዛ ዒላማ አድርጌያቸዋለሁ ያለቻቸው የሐማስ ዋሻዎችሐማስ ያልተጠበቀ የተባለውን ጥቃት መሰንዘሩንተከትሎ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ የሚገኙ ዋሻዎችን ዒላማ ማድረጓን አስታውቃለች።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 4:074:07በእስራኤል- ሐማስ ግጭት የተከሰቱ ዋና ዋና ጉዳዮች
EPA-EFE/REX/ShutterstockCopyright: EPA-EFE/REX/Shutterstockእስራኤል ሐማስ ላደረሰው ጥቃት ምላሽ ነው በሚል በጋዛ ሰርጥ የምታደርጋቸው ተደጋጋሚ የአየር ጥቃቶች ቀጥለዋል።
- 1.1 ሚሊዮን ነዋሪዎች ያሉባት የሰሜን ዋዲ ጋዛ ነዋሪዎች ወደ ደቡብ እንዲሸሹ የእስራኤል ጦር የ24 ሰዓታት ትዕዛዝ መስጠቱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል።
- የእስራኤል ጦር የጋዛን ህዝብ “ለደህንነታቸው” ሲሉ አካካቢውን ለቀው እንዲወጡም መልዕክቱን አስተላልፏል።
- እስራኤል ሃማስን ለማጥፋት የምድር ላይ ዘመቻ ለማካሄድ እየተጠበቀችበት ባለበት ወቅት ነው ይህን ማስጠንቀቂያ የተሰማው
- የተባበሩት መንግሥታት ይህንን ያህል ህዝብ ማስወጣት የማይቻል ነው በሚል “አሰቃቂ ሰብዓዊ መዘዝ እንደሚያስከትል” በማስጠንቀቅ እስራኤል ውሳኔዋን እንድትቀለብስ ጠይቋል።
- እስራኤል በበኩሏ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ እየሞከረች መሆኗን ጠቅሳ የተመድን ምላሽ “አሳፋሪ ነው” ስትል ተችታለች።
- የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን ከፍልስጥኤም ፕሬዚዳንት ማህሙድ አባስ ጋር ዛሬ ይገናኛሉ ተብሏል።
- የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲንም እስራኤል ገብተዋል ተብሏል።
- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በእስራኤል እና በሐማስ ግጭት ላይ ለመምከር ዛሬ የዝግ ስብሰባ ያደርጋል ተብሏል።
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 3:343:34ሐማስ የእስራኤልን ከሰሜን ጋዛ ለቃችሁ ውጡ ማስጠንቀቂያ ህዝቡ እንዳይሰማ ተናገረ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesእስራኤል 1.1 ሚሊዮን ፍልስጥኤማውያን ከሰሜን ጋዛ ለቀው ወደ ደቡባዊ ጋዛ እንዲሸሹ ማስጠንቀቂያ መስጠቷን ተክትሎ ሐማስ ህዝቡ እንዳይሰማ ተናገረ።ሐማስ ማስጠንቀቂያውን “ሃሰተኛ ፕሮፓጋንዳ” እንደሆነ ገልጾ ዜጎች ችላ እንዲሉትም አሳስቧል። የተባበሩት መንግሥታት የጋዛን ህዝብ የማስወጣት እቅድ በመቃወም ሁኔታውን የከፋ ያደርገዋል ሲልም እስራኤል ውሳኔዋን እንድትቀለብስ አጥብቆ ተማጽኗል።”እንዲህ ያለ የህዝብ እንቅስቃሴ አስከፊ ሰብዓዊ መዘዞች ሳያስከትል መተግበር አይቻልም” ሲልም የተባበሩት መንግሥታት ባወጣው መግለጫ አስጠንቅቋል።ሐማስ ታጣቂዎቹን ለመጠበቅ ሲል ንጹሃን ዜጎችን አደጋ ውስጥ በመክተት እንደ ሽፋን ይጠቀምባቸዋል የሚሉ ትችቶች ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ይቀርብበታል።ሐማስ በጋዛ ሰርጥ በአውሮፓውያኑ 2006 የተካሄደውን የህግ አውጭ ምርጫ ካሸነፈ በኋላ አካባቢውን ማስተዳደር ጀምሯል። በቀጣዩ ዓመትም ተቀናቃኙን ፋታህን በማስወገድ በጋዛ ሰርጥ ስልጣኑን አጠናክሯል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:173:17ፈረንሳይ የፍልስጥኤም የድጋፍ ሰልፎችን ከለከለችየድጋፍ ሰልፎችን ሙሉ በሙሉ የከለለከችው ፈረንሳይ ይህንን ህግ ተላልፈው ለሰልፍ የሚወጡ የውጭ ሃገር ዜጎች ከአገሪቱ መባበረርን የመሰለ ጠበቅ ያለ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ጄራልድ ዳርሚን አስጠንቅቀዋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:420:42ሰበርእስራኤል 1.1 ሚሊዮን ፍልስጥኤማውያን ከጋዛ በ24 ሰዓታት ይውጡ አለች- ተመድ
AFPCopyright: AFPየእስራኤል ጦር 1.1 ሚሊዮን የጋዛ ነዋሪዎች በ24 ሰዓታት ውስጥ እንዲወጡ መጠየቋን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።ጦሩ በሰሜን ዋዲ ጋዛ የሚኖሩ ነዋሪዎች ወደ ደቡባዊ ጋዛ በ24 ሰዓታት ውስጥ መዛወር እንዳለባቸው ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መናገሩን የተመድ ቃለ አቀባይ ተናግረዋል።በዚህ አካባቢ የሚኖሩ ፍልስጥኤማውያን 1.1 ሚሊዮን አካባቢ ሲሆኑ ይህም ከጠቅላላው የጋዛ ሰርጥ ህዝብ ግማሽ ያህሉ እንደሆነም ነው ተመድ ያስታወቀው።ነዋሪዎች እንዲወጡ ከተጠየቁበትም ውስጥ በርካታ ህዝብ በተጨናነቀ ሁኔታ የሚኖርባት የጋዛ ከተማን ያጠቃልላል።ትዕዛዙ የተላለፈው በጋዛ እና እየሩሳሌም ሰዓት አቆጣጠር ትናንት ዕኩለ ሌሊት አካባቢም መሆኑ ተገልጿል። የእስራኤል ጦር መኮንኖች በጋዛ ተቀማጭነታቸውን ላደረጉ የተባበሩት መንግሥታት የቡድን አመራሮች ስለተላለፈው ትዕዛዘዝም ነግረዋቸዋል።ትዕዛዙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰራተኞችን ጨምሮ በተባበሩት መንግሥታት ተቋማት ትምህርት ቤቶች ፣ የጤና ማዕከላት እና ክሊኒኮች የተጠለሉ ፍልስጥኤማውያንንም ያጠቃልላል ተብሏል።የተባበሩት መንግሥታት የጋዛን ህዝብ የማስወጣት እቅድ በመቃወም ሁኔታውን የከፋ ያደርገዋል ሲልም እስራኤል ውሳኔዋን እንድትቀለብስ አጥብቆ ተማጽኗል።”እንዲህ ያለ የህዝብ እንቅስቃሴ አስከፊ ሰብዓዊ መዘዞች ሳያስከትል መተግበር አይቻልም” ሲልም የተባበሩት መንግሥታት ባወጣው መግለጫ አስጠንቅቋል።እስራኤል ምድር ላይ ልታደርገው ላቀደችው ወታደራዊ ዘመቻ በጋዛ ሰርጥ ድንበር በርካታ ወታደሮችን፣ ከባድ መሳሪያዎችን እያሰማራች ትገኛለች።ሐማስ ላደረገው ጥቃት ምላሽ ነው በሚል እስራኤል እረፍት የሌለው የአየር ጥቃት እየፈጸመች ትገኛለች።ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮም የእስራኤል አየር ኃይል በጋዛ ላይ እየፈጸመ ባለው የአየር ድብደባ ስድስት ሺህ የሚደርሱ ቦምቦችን በከተማዋ ላይ መጣሉም ተገልጿል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:400:40እስራኤል የምትመካበት የሚሳኤል እና የሮኬቶች ማምከኛ ‘አይረን ዶም’ ምንድን ነው?እስራኤል ከየትኛውም ወገን የሚሰነዘሩባትን የሚሳኤል እና የሮኬት ጥቃቶችን ለመከላከል “አይረን ዶም” የተባለውን የአየር ላይ ጥቃት ማምከኛ ሥርዓትን ትጠቀማለች።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 13:02 12 ጥቅምት 202313:02 12 ጥቅምት 2023ከቅዳሜ ጀምሮ ጋዛ በስድስት ሺህ ቦምቦች ድብደባ ተፈጽሞባታል፡ የእስራኤል ጦር
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesባለፈው ቅዳሜ ግጭቱ ከጀመረ አንስቶ የእስራኤል አየር ኃይል በጋዛ ላይ እየፈጸመ ባለው የአየር ድብደባ ስድስት ሺህ የሚደርሱ ቦምቦችን በከተማዋ ላይ መታሉ ተገለጸ።የእስራኤል መከላከያ ኃይሎች ቃል አቀባይ እንዳሉት ውጊያው ከተጀመረ በኋላ አስከ ሐሙስ ድረስ ቀን ከሌት በጋዛ ላይ በተፈጸመው የአየር ድብደባ ነው አየር ኃይሉ ጥቃቱን የፈጸመው።ቃል አቀባዩ ዳንኤል ሃጋሪ በጋዛ ላይ የተፈጸመው የቦንብ ውጅብኝ ስድስት ሺህ መሆኑን ያሳወቁት፣ አሁን ኤክስ በሚባለው የቀድሞው ትዊተር የማኅበራዊ ትስስር መድረክ ላይ በጭስ ተሸፍኖ በፍንዳታ የሚናወጥ አንድ ሕንጻን የሚያሳይ ቪዲዮን በማያያዝ ነው።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 11:15 12 ጥቅምት 202311:15 12 ጥቅምት 2023በእስራኤል ጥቃት ጋዛ ውስጥ ከተገደሉ 450 የሚደርሱ ሕጻናት ናቸው
ReutersCopyright: Reutersየሐማስ ጥቃትን ተከትሎ እስራኤል በጋዛ ላይ እያካሄደችው ባለው የአየር ድብደባ ከተገደሉት መካከል 447ቱ ሕጻነት፣ 248 ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።የእስራኤል የአየር ድብደባ በቀጠለበት በአሁኑ ጊዜ የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን፣ ከቅዳሜ ጀምሮ አስከ ዛሬ ሐመስ አመሻሽ ድረስ በአጠቃላይ 1,417 ሰዎች ጋዛ ውስጥ መገደላቸው ተገልጿል።የሐማስ ታጣቂዎች ወደ እስራኤል በሺዎች የሚቆጠሩ ሮኬቶችን በመተኮስ እና ወደ እስራኤል ሰርጎ በመግባት ቅዳሜ ዕለት በፈጸሙት ጥቃት ከ1300 በላይ እስራኤላውያን መገደላቸውም ተነግሯል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 9:41 12 ጥቅምት 20239:41 12 ጥቅምት 2023አሜሪካ በየትኛውም ጊዜ ከእስራኤል ጎን ትቆማለች፡ አንቶኒ ብሊንከን
us poolCopyright: us poolየአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁImage caption: የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁየአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን እስራኤል በሐማስ ለተፈጸመባት ጥቃት በጋዛ ላይ የአጸፋ እርምጃ እየወሰደች ባለበት ጊዜ አሜሪካ ለአስራኤል ያላትን አጋርነት ለመግለጽ በእስራኤል ጉብኝት እያደረጉ ነው።ብሊንከን ከእስራኤሉ ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል።ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በመሆን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫም፣ አሜሪካ በየትኛው ጊዜ ከአስራኤል ጎን እንደምትቆምና ድጋፏን እንደምትሰጥ ገልጸዋል።
- ለጉብኝት እስራኤል የገቡት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን አገራቸው “በየትኛው ጊዜ እስራኤልን ለመርዳት” ከጎኗ እንደምትቆም በመግለጽ፣ ለሰላማዊ ሰዎች ጥበቃ ማድረግ አስፈላጊ ነው አሉ።
- የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ሐማስ “አይሲስ ለአይሲስ በተስተናገደበት መንገድ ምላሽ ያገኛል” ብለዋል።
- የእስራኤል ሠራዊት ጋዛ ሰርጥ ውስጥ የማስጠንቀቂያ ወረቀቶችን በመበተን ነዋሪዎች ሐማስ የሚጠቀምባቸው ሕንጻዎችን ስለሚያጠቃ ነዋሪዎች ወደ መጠለያ እንዲሄዱ አሳስቧል።
- ስድስተኛ ቀኑን በያዘው እስራኤል በጋዛ ላይ በምትፈጽመው የአየር ጥቃት ቢያንስ 1,417 ሰዎች ሲገደሉ፣ 6,268 ሰዎች ላይ ደግሞ ጉዳት መድረሱን የጋዛ የጤና ባለሥልጣንት ገለጹ።
- በሌላ በኩል የሐማስ ታጣቂዎች የገደሏቸው እስራኤላውያን ቁጥርም 1,300 ደርሷል። ሌሎች በርካቶች ደግሞ የመቁሰል ጉዳት እንደደረሰባቸው የእስራኤል ባለሥልጣንት አስታውቀዋል።
- ብሪቲሽ ኤርዌይስ በእስራኤል ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ወደዚያው የሚያደርጋቸውን በራረቀዎች ለሚቀጥሉት ሦስት ሳምንታት እንዲቋረጡ ወሰነ።
- የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ከእስራኤል ለቀው ለመውጣት ለሚፈልጉ ዜጎቹ የአየር ጉዞዎችን ማመቻቸቱን አስታወቀ።
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 9:28 12 ጥቅምት 20239:28 12 ጥቅምት 2023እስራኤል በሶሪያ አየር ማረፊያዎች ላይ ጥቃት መፈጸሟ ተዘገበእስራኤል በዋና ከተማዋ ደማስቆ እና በሌላኛዋ ከተማ አሌፖ ውስጥ በሚገኙ አየር ማረፊያዎች ላይ ጥቃት መፈጸሟን የሶሪያ መንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።የሶሪያ ዜና አገልግሎት ሳና “የሚሳኤል ፍንዳታዎች” በአየር ማረፊያው የመንደርደሪያ ሜዳ ላይ ጉዳት በማድረስ ከአግልግሎት ውጪ አድርጓቸዋል።ጥቃቱ በተፈጸመበት ጊዜ የሶሪያ የአየር መከላከያ መሳሪያዎች ምላሽ ለመስጠት መተኮሳቸውን የሶሪያ መገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል።የሶሪያ ሰብአዊ መብቶች ክትትል የተባለው መቀመጫውን በዩናይትድ ኪንግደም ያደረገው የግጭት ተከታታይ ቡድንም በርካታ ፍንዳታዎች አሌፖ ውስጥ መከሰታቸውን አረጋግጧል።ይህ የአየር ጥቃት መፈጸሙን የሚያመለክተው ዘገባ የወጣው የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሶሪያን ይጎበኛሉ ከተባለበት አንድ ቀን ቀደም ብሎ ነው።ሶሪያ እና ኢራን ከእስራኤል ጋር በጠላትንት የሚፈላለጉ አገራት ሲሆኑ፣ ኢራን አሁን እስራኤል እያደነችው ያለው ሐማስ ቡድንን እንደምትደግፍ ይነገራል።እስራኤል ከዚህ በፊትም ሶሪያ ውስጥ ያሉ የኢራን ናቸው የተባሉ እና የሊባኖስ ታጣቂ ቡድን የሆነውን ሄዝቦላህን ኢላማዎች በተደጋጋሚ ብትደበድብም በይፋ አረጋግጣ አታውቅም።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 5:35 12 ጥቅምት 20235:35 12 ጥቅምት 2023የኢራን ፕሬዚደንት እስራኤልን ‘በዘር ማጥፋት’ ከሰሱ
ReutersCopyright: Reutersየኢራን ፕሬዚደንት እስራኤልን በዘር ማጥፋት ከሰሱ።ፕሬዚደንቱ ይህን ያሉት እስራኤል በጋዛ ላይ የምትፈፅመውን ጥቃት አጠናክራ በቀጠለችበት ወቅት ነው።ፕሬዚደንት ኢብራሒም ሬይሲ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የውሃ እና የነዳጅ አቅርቦት እንዲቋረጥ ተደርጎ በጋዛ ላይ የተደረገው ከበባ ሁሉንም ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የጣሰ ነው ሲሉ ኮንነውታል።ኢራን በጋዛ ያለውን ታጣቂ ቡድን ሐማስን በመደገፍና በማስታጠቅ ትታወቃለች።ሆኖም ማክሰኞ ዕለት የኢራን የበላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ አገራቸው ቅዳሜ ዕለት በእስራኤል ላይ ከተፈተው ጥቃት ጀርባ እንደሌለችበት ተናግረዋል።መሪው ይህን ይበሉ እንጂ ከጥቃቱ በኋላ በቴሌቪዥን በሰጡት በዚህ የመጀመሪያ መግለጫቸው፣በአይሁድ መንግሥት ላይ ጥቃቱን ለመፈፀም ያቀዱትን አድንቀናል ብለዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:39 12 ጥቅምት 20233:39 12 ጥቅምት 2023ሰበርታጋቾች እስኪለቀቁ ጋዛ መብራት፣ ውሃ እና ነዳጅ አታገኝም- እስራኤል
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesታጋቾች እስኪለቀቁ ድረስ የጋዛ ሙሉ ከበባ እንደሚቀጥል የእስራኤል ኢነርጂ ሚንስትር እስራኤል ካትዝ ገለጹ።”ታጋቾች” እስኪፈቱ ድረስ “መብራት አይኖርም፣ ውሃ አይለቀቀም እንዲሁም ምንም ዓይነት የነዳጅ መኪና አይገባም” ሲሉ እስራኤል ካትዝ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ጽፈዋል።የቅዳሜውን የሐማስን ጥቃት ተከትሎ ነው እስራኤል ወደ ጋዛ ሰርጥ የሚገቡ ምርቶችን ያገደችው። እስራኤል በሙሉ ከበባ ውስጥ ባስገባቻት ጋዛ ኤሌክትሪክ እና ውሃን ጨምሮ መሰረተ ልማቶች ተቋርጠዋል።መውጫ መግቢያ በታጣባት ጋዛ የተወሰነ እርዳታ እንዲገባ እና ነዋሪዎች እንዲወጡ ለማድረግ አሜሪካ ከእስራኤል፣ ከተባበሩት መንግሥታት እና ከግብጽ ጋር እየተነጋገረች መሆኗን ዋይት ሃውስ አስታውቋል።