ጥቃት ፈጽሞ እስራኤል ጋዛ ላይ የአየር ድብደባ ከጀመረች አንድ ሳምንት ሆነ
Related Video and Audio

VIDEO 1 MINUTE 33 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 33 SECONDS1:33
Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBCበእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች
- BBC
Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 23 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 23 SECONDS1:23
Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBCሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ?
- BBC
Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBC
ጭምቅ ሃሳብ
- በአራት ቀናት ውስጥ ከ260 ሺህ በላይ ፍልስጥኤማውያን ከጋዛ ተፈናቅለዋል፡ የተባበሩት መንግሥታት
- ኢራን በእስራኤል ላይ ለተፈጸመው ጥቃት ድጋፏን ሰጥታ ይሆን?
- የፍልስጥኤማውያን የተቃውሞ ሰልፍ በዌስት ባንክ
- የቀጠለው የእስራኤል ጥቃት እና የአውሮፓ ኅብረት ትችት
- እስራኤል ከሶሪያ በኩል ለተሰነዘረ ጥቃት አጸፋውን መመለሷን ገለጸች
- የሳዑዲው ልዑል ሞሐመድ ቢን ሳልማን ለፍልስጥኤማውያን ድጋፋቸውን ገለጹ
- ውጊያው ሳይቆም በታጋቾች ጉዳይ ላይ አንደራደርም፡ ሐማስ
- በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት አጀማመር ምን ይመስላል?
- በጋዛ ከ123 ሺህ በላይ ፍልስጥኤማውያን ተፈናቀለዋል
- ኢራን፣ ሐማስ በፈጸመው ጥቃት ላይ ተሳትፎ የለኝም አለች
- እስራኤል በሊባኖስ ላይ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት ፈጸመች
ቀጥታ ዘገባ
- የታተመዉ 8:028:02የሩሲያው ባለሥልጣን የሐማስ ተወካዮችን ለማናገር አቅደዋል
ReutersCopyright: Reutersየሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚኻይል ቦግዳኖቭImage caption: የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚኻይል ቦግዳኖቭየሩሲያው ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የታገቱ እስራኤላውያን መለቀቅን በተመለከተ ኳታር ውስጥ ከሐማስ ተወካዮች ጋር ለመገናኘት ማቀዳቸውን የሩሲያ መንግሥታዊ የዜና ወኪል ሪያ-ኖቮስቲ ዘገበ።ከሐማስ እና ታጣቂ ቡድኑን ትደግፋለች ተብላ ስሟ ከሚነሳው ኢራን ጋር ግንኙነት እንዳላት የሚነገረው ሩሲያ፣ በሐማስ እና በእስራኤል መካከል አሸማጋይ ሆና ለመቅረብ ጥረት እያደረገች ነው።ዛሬ ቅዳሜ በመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በተካሄደ ስብሰባ ላይ እርዳታ ለማቅረብ እንዲቻል ተኩስ እንዲቆም የሚጠይቅ ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ አቅርባለች።የሩሲያው ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚኻይል ቦግዳኖቭ ለሪያ-ኖቮስቲ ዜና ወኪል እንደተናገሩት፣ ወደ ኳታር በሚያደርጉት ጉዞ የሐማስ ተወካዮች “ፈቃደኛ ከሆኑ አግኝተው ለመነጋገር ፈቃደኛ” መሆናቸውን ገልጸዋል።“በተለይም አሁን ከላው ሁኔታ አንጻር፣ ይህ ውይይት ታጋቾችን የማስለቀቅ ጉዳይን ጭምሮ ተጨባጭ እርምጃ የሚፈልጉ ችግሮችን ለመፍታት ጠቃሚ ነው” ብለዋል ምክትል ሚኒስትሩ።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ

- የታተመዉ 7:347:34የእስራኤል ጦር ያለፈው ሳምንቱን ጥቃት ከመሩት ውስጥ አንዱን ገደልኩ አለባለፈው ሳምንት ድንበር ተሻግሮ በእስራኤል ሰፋሪዎች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት መርቷል የተባለውን የሐማስ አዛዥ አሊ ቃዲን መግደሉን የእስራኤል አየር ኃይል አስታወቀ።የእስራኤል የአገር ውስጥ ደኅንነት መሥሪያ ቤት ሺን ቤት እና የሠራዊቱ ወታደራዊ ደኅንነት ተቋም በሰጡት መረጃ መሠረት ነው የሐማሱ አዛዥ በድሮን ጥቃት የተገደለው ተብሏል።አሊ ቃዲ የሐማስ ዋነኛ ኮማንዶ ኃይል “ኑኽባ” የተባለው ቡድን አዛዥ ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት በተፈጸመው ድንበር ዘለል ጥቃት ውስጥ ተሳታፊ እንደነበር ተነግሯል።የ37 ዓመቱ አሊ አንድ ከእስራኤል የአገር ውስጥ ደኅንነት መሥሪያ ቤት ጋር ይሠራል የተባለን ሰው ጠልፎ ገድሏል ተብሎ በእስራኤል አስር ቤት ውስጥ ለዓመታት ታስሮ የነበረ መሆኑም ተገልጿል።ከእስር ሊወጣ የቻለውም በሐማስ ተይዞ የነበረን የእስራኤል ወታደር፣ ጊላድ ሻሊትን በልውውጥ ለማስለቀቅ በ2011 (እአአ) በተደረሰ ስምምነት መሠረት እስራኤል ከእስር ከፈታቻቸው የቡድኑ አባላት መካከል አንዱ በመሆን ነበር ተብሏል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 5:375:37ሰበርጋዛ ውስጥ አስካሁን ከ2,200 በላይ ሲገደሉ 8,700 ጉዳት ደርሶባቸዋል
BBCCopyright: BBCአንድ ሳምንት በሞላው የእስራኤል የአየር ድብደባ ጋዛ ውስጥ አስከ ቅዳሜ እኩለ ቀን ድረስ ቢያንስ 2,215 ሰዎች ሲገደሉ፣ 8,714 ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲል የፍልስጥኤም ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።በሌላው የፍልስጥኤም ክፍል ዌስት ባንክ ውስጥ ደግሞ 54 ሰዎች ተገድለው፣ 1,100 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል ተብሏል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 5:295:29ሩሲያ በጋዛ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ለፀጥታው ምክር ቤት የውሳኔ ሃሳብ አቀረበች
AFPCopyright: AFPሩሲያ ጋዛ ውስጥ ሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ የሚያስችል የተኩስ አቁም እንዲደረግ የሚጠይቅ ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ የፀጥታው ምክር ቤት ባደረገው ዝግ ስብሰባ ወቅት አቀረበች።ባለአንድ ገጹ የውሳኔ ሃሳብ አስቸኳይ፣ ዘላቂ እና ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ የሚሆን ተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ ሁሉም ታጋቾች ደኅንነታቸው ተጠብቆ እንዲለቀቁ እንዲሁም እርዳታ እንዲቀርብ እና ለመውጣት የሚፈልጉ ሲቪሎች ያለችግር እንዲወጡ የሚጠይቅ ነው።በመንግሥታቱ ድርጅት የሩሲያ አምባሳደር የሆኑት ቫዚሊ ኔቤንዚያ ከስብሰባው በኋላ ስለውሳኔ ሃሳቡ ለጋዜጠኞች መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።የምክር ቤቱ አባላት በውሳኔ ሃሳቡ ላይ ተቃውሞ ማንሳት እና ድርድር ማድረግ የሚችሉ ሲሆን፣ ነገር ግን ረቂቁ ወደ መደበኛ ድምጽ አሰጣጥ ይሄድ እንደሆነ ግልጽ አይደለም።አንድ ምዕራባዊ ዲፕሎማት ግን በጉዳዩ ላይ ሩሲያ የምሯን መሆኑን እንደሚጠራጠሩ ተናግረዋል። ጨምረውም ሞስኮ ሃሳቡን ስታዘጋጅ ሌሎች የምክር ቤቱን አባላት ካለማማከሯ በተጨማሪ ሐማስን ሳትጠቅስ አልፋዋለች በማለት ተችተዋል።በመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የሚወጣ የውሳኔ ሃሳብ ከአባላቱ መካከል ዘጠኝ ድጋፍ የሚያስፍልገው ሲሆን፣ ቋሚ አባላት ከሆኑት ከአሜሪካ፣ ከዩናይትድ ኪንግድም፣ ከፈረንሳይ፣ ከሩሲያ እና ከቻይና ግን ድጋፍ አያስፈለገውም።አሜሪካ በፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ውስጥ ወዳጇ የሆነችውን አስራኤልን የሚተች ማንኛውንም ሃሳብ ድምጽን በድምጽ የመሻር ሥልጣኗን በመጠቀም በተዳጋጋሚ ውድቅ ስታደርግ ቆይታለች።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 5:095:09በእስራኤል የአየር ድብደባ ጋዛ ውስጥ ከ1,300 በላይ ሕንጻዎች ወደሙ
ReutersCopyright: Reutersእስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ ለአንድ ሳምንት ባካሄደችው የአየር ድብደባ ከ1,300 በላይ ሕንጻዎች መውደማቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።የድርጅቱ የሰብአዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (ኦቻ) እንዳለው በወደሙት ሕንጻዎች ላይ የነበሩ “5,540 ቤቶች” ሲወድሙ 3,750 የሚደርሱ ሌሎች ቤቶች ደግሞ ለመኖሪያ በማይሆኑ ሁኔታ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 4:594:59በሞት ጥላ ስር ሆነው እስራኤልን እንቅልፍ የነሷት የሐማስ መሪዎች እነማን ናቸው?ሐማስ “የአል-አቅሳ ጎርፍ” ብሎ በሰየመው ዘመቻ ድንገተኛውን እና ታይቶ የማይታወቀውን የተቀናጀ ጥቃት ቅዳሜ መስከረም 26/2016 ዓ.ም. በእስራኤል ላይ ከፈጸመ ለኋላ በርካቶች የቡድኑ መሪዎች እነማን ናቸው? የሚል ጥያቄን እያነሱ ነው። ታጣቂው ቡድን የፈጸመውን ጥቃት በማቀድ እና በማደራጀት በአሁኑ ወቅት ጉልህ ሚና አላቸው ተብለው የሚታመኑት የሐማስ የፖለቲካ እና ወታደራዊ ክንፍ ቁልፍ ሰዎችን ማንነት እነሆ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:183:18በጭንቅ ውስጥ የሚገኙት የሰሜን ጋዛ ነዋሪዎች
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesከሰሜናዊ ጋዛ እየለቀቁ በመውጣት ላይ ያሉ ፍልስጥኤማውያንImage caption: ከሰሜናዊ ጋዛ እየለቀቁ በመውጣት ላይ ያሉ ፍልስጥኤማውያንበሰሜን ጋዛ ያሉ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ በእስራኤል የተቀመጠው ገደብ ዛሬ ይጠናቀቃል። የተባበሩት መንግሥታት እንደገመተው አስር ሺዎች ለቀው ወጥተዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ በጋዛ ላይ የሚፈጸመው የአየር ድብደባ መጀመሩን በመግለጽ የከፋው ሁኔታ ገና እንሚመጣ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።በተጨናነቀ ሁኔታ ሕዝብ በሰፈረበት የሰሜን ጋዛ ያለው ነዋሪ አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ የሚያስጠነቅቅ ጽሁፍ አስራኤል ከበተነች በኋላ ነዋሪው ሽብር ውስጥ ይገኛል።በርካቶች መኖሪያቸውን ለቀው ለመውጣት በመኪና እና በእግር በረጅም ሰልፍ ጉዞ ሲጀምሩ፣ በርካቶች ደግሞ ከመኖሪያቸው ላለመውጣት የቆረጡ እንዲሁም ገና እንቅስቃሴ ያልጀመሩ ናቸው።የተባበሩት መንግሥታት እና ሌሎችም ድርጅቶች ይህን ያህል ሕዝብ ከአካባቢው የሚፈናቀል ከሆነ አደጋን እንደሚያስከትል በማስጠንቀቅ፣ እስራኤል በጋዛ ላይ የጣለችውን ከበባ በማንሳት ሰብአዊ እርዳታ እንዲደርስ እንድትፈቅድ እየጠየቁ ነው።እስራኤል በጋዛ ላይ እየፈጸመች ያለችው የአየር ጥቃት ሐማስን ለማጥፋት ያለመ መሆኑን ስትገልጽ፣ ሐማስ በበኩሉ አስከ መጨረሻዋ የደም ጠብታ እንደሚዋጋ ዝቷል።እስራኤል ወደ ጋዛ እግረኛ ሠራዊቷን ለማሰማራት ዝግጅት በማድረግ ቀዳሚ ወታደራዊ እርምጃዎችን እየወሰደች እንደሆነ እየተነገረ ነው።ባለፉት ቀናትም ሮኬቶች የሚተኮሱባቸው ስፍራዎችን ኢላማ በማድረግ ወታደሮቿ በተወሰኑ የጋዛ አካባቢዎች ላይ አሰሳ በማካሄድ ስለታገቱ ዜጎቻቸው መረጃዎችን እየሰበሰቡ ነው።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:481:48ሐማስ ጥቃት ፈጽሞ እስራኤል ጋዛ ላይ የአየር ድብደባ ከጀመረች አንድ ሳምንት ሆነ
EPACopyright: EPAልክ የዛሬ ሳምንት ቅዳሜ መስከረም 26/2016 ዓ.ም. ማለዳ ሐማስ በእስራኤል ላይ በፈጸመው የተቀናጀ ጥቃት የተጀመረው ግጭት ተባብሶ ቀጥሏል።ባለፉት ሰባት ቀናት እስራኤል በጋዛ ላይ ቀን አና ሌሊት ያለተቋረጠ የአየር ድብደባ አየፈጸመቸ ሲሆን፣ ሐማስም ወደ እስራኤል ሮኬቶቸን ሲተኩሰ ቆይቷል።በዚህም ባለፉት ቀናት ከሦስት ሺህ በላይ ሰዎች ከሁለቱም ወገን ሲገደሉ፣ ከፍልስጥኤም በኩል ከ300 ሺህ በላይ ለመፈናቀል መዳረጋቸውን የተባበሩት መንግሥታት አስታውቋል።ባለፈው አንድ ሳምንት የተከሰቱ ዋና ዋና ነገሮች ምንድን ናቸው።
- የሐማስ ታጣቂዎቸ የዛሬ ሳምንት በአስራኤል ላይ ጥቃት ፈጽመው 1,300 ሰዎችን ሲገድሉ፣ 150 ሰዎችን ደግሞ አግተው ወደ ጋዛ ወስደዋል።
- እስራኤል ላለፉት ቀናት በጋዛ ላይ በወሰደችው የአጸፋ የአየር ድብደባ 1,900 ያህል ሰዎች መገደላቸወን የአካባቢው ባለሥልጣናት አስውቀዋል።
- ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ፍልስጥኤማውያን የእስራኤል ሠራዊት የምድር ላይ ጥቃት ከመክፈቱ በፊት አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል።
- በሰሜናዊ ጋዛ ያሉ ነዋሪዎች እስእራኤል አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ የ24 ሰዓት የጊዜ ገደብ ካስቀመጠች በኋላ በመኪና፣ በጋሪ እና በእግር ከቀያቸው እየሸሹ ነው።
- የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የእስራኤልን ውሳኔ አሰቃቂ ያለው ሲሆን፣ አሜሪካ ደግሞ አስራኤል ሰላማዊ ሰዎች እንዳይገደሉ ጥንቃቄ እድታደርግ ጠይቃለች።
- የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንክን ጋዛ ውስጥ “ከጥቃት የተከለለ አካባቢ” እንዲለይ ከእስራኤል ጋር እየተነጋገሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
- እስራኤል ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በሚኖርባት የሐማስ መቀመጫ በሆነችው ጋዛ ላይ ከምትፈጽመው የአየር ጥቃት በተጨማሪ ወደ ግዛቱ ምንም አይነት ነገር እንዳይገባ እና እንዳይወጣ አግዳለች። በዚህም ምክንያት ጋዛ ውስጥ ያለው ነዳጅ፣ ምግብ እና ውሃ እየተሟጠጠ ነው።
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 12:45 13 ጥቅምት 202312:45 13 ጥቅምት 2023ዌስት ባንክ ውስጥ በተካሄደ ተቃውሞ ወቅት 11 ሰዎች ተገደሉ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየፍልስጥኤም የጤና ሚኒስቴር ዌስት ባንክ ውስጥ በተቃዋሚዎች እና በእስራኤል ወታደሮች መካከል በተከሰተ ግጭት 11 ሰዎች መገደላቸውን አስታወቀ።ዛሬ አርብ ከጋዛ ርቆ በሚገኘው የፍልስጥኤም ግዛት በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጥኤማውያን ጋዛ ውስጥ ወገኖቻቸው ከቤታቸው እንዲፈናቀሉ መገደዳቸውን በመቃወም ነው አደባባይ ወጥተው ተቃውሞ ያሰሙት።ሰዎቹ የተገደሉት ዌስት ባንክ ውስጥ በሚገኙት ራማላህ፣ ናብሉስ፣ ሄብሮን እና ቱልካራም ውስጥ በተካሄዱ ተቃውሞዎች ወቅት ከእስራኤል ወታደሮች ጋር በመጋጨታቸው ነው።ከተገደሉት ሰዎች በተጨማሪም ከአንድ መቶ የሚበልጡ ሌሎች ደግሞ የመቁሰል ጉዳት እደደረሰባቸው ተዘግቧል።በዌስት ባንክ እና በምሥራቅ ኢየሩሳሌም ውስጥ የሚገኙ ፍልስጥኤማውያን ከ1967 (እአአ) ጀምሮ በእስራኤል ወረራ ስር ነው የሚኖሩት።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 12:06 13 ጥቅምት 202312:06 13 ጥቅምት 2023በትንሽ ቦታ ብዙ ሕዝብ ተጨናንቆ የሚኖርባት ጋዛ
BBCCopyright: BBCጋዛ ሰርጥ በዓለም ላይ ብዙ ሕዝብ በከፍተኛ ሁኔታ ተጠጋግቶ ከሚኖርባቸው አካባቢዎች አንዱ ነው። በዚህም 365 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሆን ስፋት ባለው ግዛቷ ውስጥ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ይኖራል።በእያንዳንዷ የጋዛ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ቦታ ላይ 5,700 ሰዎች ተጠጋግተው ይኖራሉ። ይህ የለንደን ሕዝብ ካለው የጥግግት መጠን ጋር ተመሳሳይ ነው።ከላይ የተቀመጠው ካርታ እንደሚያሳየው ደግሞ ከዋዲ ጋዛ በስተሰሜን ባለው የጋዛ ከተማ ውስጥ ከ9,000 ሰዎች በላይ በእያንዳንዱ ስኩዌር ኪሎ ሜትሮች ላይ ሰፍረው ይገኛሉ።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 11:16 13 ጥቅምት 202311:16 13 ጥቅምት 2023ሐማስ በእስራኤል ላይ የሚፈጽመው የሮኬት ጥቃት መቀጠሉን አስታወቀ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesዛሬ አርብ ሰባተኛ ቀኑን በደፈነው ግጭት ፍልስጥኤማዊው ታጣቂ ቡድን ሐማስ ወደ እስራኤል ሮኬቶችን መተኮሱን ቀጥሏል።ቡድኑ እንዳለው ዛሬ አርብ ከሰዓት በኋላ በሰሜናዊ እስራኤል ውስጥ ወደምትገኘው ሳፊድ ከተማ ሚሳኤል አስወንጭፏል።የእስራኤል የጦር ኃይሎች ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ በኤክስ (ትዊተር) ላይ እንዳሰፈሩት ከጋዛ ወደ ሰሜናዊ እስራኤል ክልል የተተኮሱ ሮኬቶች እንዲከሽፉ ተደርገዋል ያሉ ሲሆን፣ ነገር ግን የተተኮሰባትን ከተማ ስም አልጠቀሱም።ሐማስ ወደ ባሕር ዳርቻ ከተማዋ ቴል አቪቭ ሮኬቶችን ካስወነጨፈ በኋላ በከተማዋ ውስጥ የአየር ጥቃት መስጠንቀቂያ ደወል ድምጽ ተሰምቷል።ታጣቂው ቡድን ባለፈው ቅዳሜ በፈጸመው ጥቃት 1,300 ሰዎችን ወደ ገደለባቸው የደቡብ እስራኤል ከተሞች ወደሆኑት አሽኬሎን፣ ስዴሮት እና ቤሪ ሮኬቶችን መተኮሱን ገልጿል።እስራኤል በጋዛ ላይ የአጸፋ ጥቃት እየፈጸመችበት ባለበት በአሁኑ ጊዜ ሐማስ በሺዎች የሚቆጠሩ ሮኬቶችን ሲቪሎች ወደ ሚኖሩባቸው የእስራኤል አካባቢዎች ተኩሷል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:56 13 ጥቅምት 20238:56 13 ጥቅምት 2023የሊባኖሱ ሄዝቦላህ ሐማስን በመደገፍ እንሚሰለፍ ገለጸ
EPACopyright: EPAየኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የሄዝቦላህ መሪ ቤይሩት ውስጥ በተወያዩበት ወቅትImage caption: የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የሄዝቦላህ መሪ ቤይሩት ውስጥ በተወያዩበት ወቅትየሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላህ ከእስራኤል ጋር ግጭት ውስጥ የገባው ፍልስጥኤማዊውን ሐማስን በመደገፍ እንደሚሰለፍ አስታወቀ።የሄዝቦላህ መሪ ሐሰን ናስራላህ ሊባኖስን በመጎብኘት ላይ ካሉት የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴይን አብዶላሃይን ጋር ተገናኝተው በተወያዩበት ጊዜ፣ ጋዛ ውስጥ የሚፈጸመውን “የጦር ወንጀል ለመቋቋም ያለጥርጥር የጋራ ምላሽን መነሳቱ አይቀርም” ሲሉ ተናግረዋል።በተመሳሳይ የሄዝቦላህ ምክትል መሪ ሐማስ ከእስራኤል ጋር በሚያደርገው ጦርነት ውስጥ “ጊዜው ሲደርስ” ቡድናቸው ለመሳተፍ “ሙሉ ለሙሉ ዝግጁ ነው” ሲሉ በቤይሩት ዳርቻ በተደረገ ሰልፍ ላይ ተናግረዋል።ሄዝቦላህ የፍልስጥኤም አጋሩን ሐማስን ለመደገፍ ወስኖ በጦርነቱ ከተሳተፈ እና እስራኤል ላይ ጥቃት ከከፈተ፣ አዲስ የጦርነት ግንባር ሊከፈት ይችላል የሚል ተጨባጭ ስጋት አለ።እንደ ፍልስጥኤሙ ሐማስ ሁሉ የሊባኖሱ ሄዝቦላህ በዩናይትድ ኪንግደም፣ በአሜሪካ እና በሌሎች ምዕራባውያን አገራት ሽብርተኛ ድርጅት ተብሎ ተፈርጇል።ሄዝቦላህ በሊባኖስ ውስጥ በፖለቲካ እና በወታደራዊ መስክ ኃያል ሚና ያለው ሲሆን፣ የምዕራባውያን ባላንጣ ከሆነችው ኢራን ጋር ወዳጅ ነው።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:15 13 ጥቅምት 20238:15 13 ጥቅምት 2023የእስራኤልን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ነዋሪዎች ከሰሜናዊ ጋዛ እየሸሹ ነው
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤልን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ በሰሜናዊ ጋዛ የሚገኙ በርካታ ነዋሪዎች ባገኙት የመጓጓዣ ዘዴ በመጠቀም አካባቢውን ለቀው እየወጡ ይገኛሉ።የእስራኤል ሠራዊት ከጋዛ ነዋሪ ግማሹ ከሚገኝበት አካባቢ ሕዝቡ ለቆ እንዲወጣ ያዘዘው በጋዛ ውስጥ ላሉት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሠራተኞች ነው።ሰሜናዊ ጋዛ 1.1 ሚሊዮን ነዋሪዎች በ24 ሰዓታት ውስጥ አካባቢውን ለቀው ወደ ደቡብ እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ከተሰጠ በኋላ ሴቶች እና ሕጻናትን ጨምሮ ፍልስጥኤማውያን መኖሪያቸውን እየለቀቁ በመውጣት ላይ ናቸው።እጅግ በተጨናነቀ ሁኔታ ከሚኖርባቸው የዓለማችን ክፍሎች መካከል አንዷ በሆነችው ጋዛ ውስጥ ካለው ነዋሪ ግማሽ የመሆኑት ከ18 ዓመት በታች ያሉ ናቸው።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 6:49 13 ጥቅምት 20236:49 13 ጥቅምት 2023ሰበርሐማስ በጋዛ 13 ታጋቾች በእስራኤል የአየር ጥቃት መገደላቸውን ገለጸ
ReutersCopyright: Reutersሐማስ በእገታ ከወሰዳቸው ውስጥ ቢያንስ 13 እስራኤላውያንን እና የውጭ አገራት ዜጎች እስራኤል በጋዛ ሰርጥ እያደረገችው ባለችው የአየር ጥቃቶች መገደላቸው አስታወቀ።ታጋቾቹ ባለፉት 24 ሰዓታት እስራኤል በምታደርገው የአየር ጥቃቶች መገዳላቸውንም ነው የሃማስ የጦር ክንፍ የገለጸው።”13 እስረኞች፣ የውጭ ዜጎችን ጨምሮ” የእስራኤል ተዋጊ ጄቶች ኢላማ ባደረጓቸው አምስት ስፍራዎች መገደላቸውን የኢዜዲን አል ቃሳብ ብርጌድ በመግለጫው አስፍሯል።ሐማስ ከቀናት በፊት በሰነዘረው ድንገተኛ ጥቃት ወደ 150 የሚጠጉ ታጋቾችን ወስዷል። እስራኤል ያለምንም ማስጠንቀቂያ የሰላማዊ ዜጎችን መኖሪያ ቤቶችን በቦምብ የምትደበድብ ከሆነ ታጋቾችን ለመግደልም ዝቷል።ታጋቾች ተገድለዋል መባሉን ተከትሎ የዩናይትድ ኪንግደም የመከላከያ ሚኒስትር ግራንት ሻፕስ መረጃውን በጥንቃቄ እንደሚያዩት ቢገልጹም ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረባቸው አይቲቪ ለተሰኘው ሚዲያ ተናግረዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 6:16 13 ጥቅምት 20236:16 13 ጥቅምት 2023ብሊንከን እና የፍልስጥኤሙ ፕሬዚዳንት በዮርዳኖስ ተገናኙ
ReutersCopyright: Reutersየአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን ከፍልስጥኤሙ ፕሬዚዳንት ማህሙድ አባስ ጋር ተገናኙ።ብሊንከን እና ፕሬዚዳንቱ የተገናኙት ዛሬ ጥቅምት 2/2016 ዓ.ም በዮርዳኖስ ነው።ዌስት ባንክን የሚመራው የማህሙድ አባሱ ፋታህ እና የጋዛ ሰርጥን የሚቆጣጠረው ታጣቂው ቡድን ሐማስ ተቀናቃኝ ናቸው።ብሊንከን ከዮርዳኖሱ ንጉስ አብዱላህ ጋር በአማን ይገናኛሉ ተብሏል።የውጭ ጉዳይ ኃላፊው ትናንት ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር ተገናኝተው የነበረ ሲሆን በሐማስ ተገደሉ የተባሉ የሞቱ ህጻናትን ምስሎችም እንዲያዩ መደረጋቸውም ተገልጿል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 6:03 13 ጥቅምት 20236:03 13 ጥቅምት 2023በጠና የታመሙ ፍልስጥኤማውያንን ከሰሜን ጋዛ ማስወጣት “የሞት ፍርድ ነው”_ የዓለም ጤና ድርጅት
AFPCopyright: AFPእስራኤል 1.1 ሚሊዮን ፍልስጥኤማያውን ከሰሜን ዋዲ ጋዛ ወጥተው ወደ ደቡባዊ ጋዛ እንዲሸሹ ትዕዛዝ መስጠቷን ተከትሎ በጠና የታመሙ ነዋሪዎችን ማስወጣት “የሞት ፍርድ ነው” ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።የዓለም ጤና ድርጅት በሆስፒታል ውስጥ ያሉ ህመምተኞችን በጭራሽ ማስወጣት እንደማይቻልም ነው የገለጸው።”በጠና የታመሙ እና የመዳን እድላቸው በድጋፍ ሰጪ ቬንትሌተሮች ብቻ የሆኑ በርካታ ፍልስጥኤማውያን በሆስፒታሎች አሉ” ሲሉም የዓለም ጤና ድርጅት ቃለ አቀባይ ታሪክ ጃሳሬቪች ተናግረዋል።”እነዚህን ህመምተኞች ማንቀሳቀስ ማለት የሞት ፍርድ ነው። የጤና ባለሙያዎች ይህንን ያድርጉ ማለት ከጭካኔ በላይ ነው” ሲሉም አስረድተዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 5:58 13 ጥቅምት 20235:58 13 ጥቅምት 2023እስራኤል በጋዛ ዒላማ አድርጌያቸዋለሁ ያለቻቸው የሐማስ ዋሻዎችሐማስ ያልተጠበቀ የተባለውን ጥቃት መሰንዘሩንተከትሎ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ የሚገኙ ዋሻዎችን ዒላማ ማድረጓን አስታውቃለች።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 4:07 13 ጥቅምት 20234:07 13 ጥቅምት 2023በእስራኤል- ሐማስ ግጭት የተከሰቱ ዋና ዋና ጉዳዮች
EPA-EFE/REX/ShutterstockCopyright: EPA-EFE/REX/Shutterstockእስራኤል ሐማስ ላደረሰው ጥቃት ምላሽ ነው በሚል በጋዛ ሰርጥ የምታደርጋቸው ተደጋጋሚ የአየር ጥቃቶች ቀጥለዋል።
- 1.1 ሚሊዮን ነዋሪዎች ያሉባት የሰሜን ዋዲ ጋዛ ነዋሪዎች ወደ ደቡብ እንዲሸሹ የእስራኤል ጦር የ24 ሰዓታት ትዕዛዝ መስጠቱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል።
- የእስራኤል ጦር የጋዛን ህዝብ “ለደህንነታቸው” ሲሉ አካካቢውን ለቀው እንዲወጡም መልዕክቱን አስተላልፏል።
- እስራኤል ሃማስን ለማጥፋት የምድር ላይ ዘመቻ ለማካሄድ እየተጠበቀችበት ባለበት ወቅት ነው ይህን ማስጠንቀቂያ የተሰማው
- የተባበሩት መንግሥታት ይህንን ያህል ህዝብ ማስወጣት የማይቻል ነው በሚል “አሰቃቂ ሰብዓዊ መዘዝ እንደሚያስከትል” በማስጠንቀቅ እስራኤል ውሳኔዋን እንድትቀለብስ ጠይቋል።
- እስራኤል በበኩሏ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ እየሞከረች መሆኗን ጠቅሳ የተመድን ምላሽ “አሳፋሪ ነው” ስትል ተችታለች።
- የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን ከፍልስጥኤም ፕሬዚዳንት ማህሙድ አባስ ጋር ዛሬ ይገናኛሉ ተብሏል።
- የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲንም እስራኤል ገብተዋል ተብሏል።
- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በእስራኤል እና በሐማስ ግጭት ላይ ለመምከር ዛሬ የዝግ ስብሰባ ያደርጋል ተብሏል።
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 3:34 13 ጥቅምት 20233:34 13 ጥቅምት 2023ሐማስ የእስራኤልን ከሰሜን ጋዛ ለቃችሁ ውጡ ማስጠንቀቂያ ህዝቡ እንዳይሰማ ተናገረ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesእስራኤል 1.1 ሚሊዮን ፍልስጥኤማውያን ከሰሜን ጋዛ ለቀው ወደ ደቡባዊ ጋዛ እንዲሸሹ ማስጠንቀቂያ መስጠቷን ተክትሎ ሐማስ ህዝቡ እንዳይሰማ ተናገረ።ሐማስ ማስጠንቀቂያውን “ሃሰተኛ ፕሮፓጋንዳ” እንደሆነ ገልጾ ዜጎች ችላ እንዲሉትም አሳስቧል። የተባበሩት መንግሥታት የጋዛን ህዝብ የማስወጣት እቅድ በመቃወም ሁኔታውን የከፋ ያደርገዋል ሲልም እስራኤል ውሳኔዋን እንድትቀለብስ አጥብቆ ተማጽኗል።”እንዲህ ያለ የህዝብ እንቅስቃሴ አስከፊ ሰብዓዊ መዘዞች ሳያስከትል መተግበር አይቻልም” ሲልም የተባበሩት መንግሥታት ባወጣው መግለጫ አስጠንቅቋል።ሐማስ ታጣቂዎቹን ለመጠበቅ ሲል ንጹሃን ዜጎችን አደጋ ውስጥ በመክተት እንደ ሽፋን ይጠቀምባቸዋል የሚሉ ትችቶች ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ይቀርብበታል።ሐማስ በጋዛ ሰርጥ በአውሮፓውያኑ 2006 የተካሄደውን የህግ አውጭ ምርጫ ካሸነፈ በኋላ አካባቢውን ማስተዳደር ጀምሯል። በቀጣዩ ዓመትም ተቀናቃኙን ፋታህን በማስወገድ በጋዛ ሰርጥ ስልጣኑን አጠናክሯል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:17 13 ጥቅምት 20233:17 13 ጥቅምት 2023ፈረንሳይ የፍልስጥኤም የድጋፍ ሰልፎችን ከለከለችየድጋፍ ሰልፎችን ሙሉ በሙሉ የከለለከችው ፈረንሳይ ይህንን ህግ ተላልፈው ለሰልፍ የሚወጡ የውጭ ሃገር ዜጎች ከአገሪቱ መባበረርን የመሰለ ጠበቅ ያለ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ጄራልድ ዳርሚን አስጠንቅቀዋል።ተጨማሪ ያንብቡ