October 14, 2023 – Konjit Sitotaw

ወልቂጤ ከተማ ከትላንት ጀምሮ በተኩስ እየተናጠች ነው። የተኩሱ ምክንያት ቀቤና የሚባሉ ብሄረሰቦች “ወልቅጤ የእኛ ከተማ ነች፤ መቀመጫችን ወልቅጤ ናት” በሚል ወደ ወልቅጤ የሚያስገቡ መንገዶችን ዘግተዋል።

የቀቤና ፖሊስ ግምጃ ቤትን ዘርፈው በጉራጌ ህዝብ ላይ ተኩስ ከፍተዋል። በጥቃቱ የቀቤና ፖሊሶችም ተሳትፈዋል ተብሏል። ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ውጪ ታሳድራለች እንደሚባለው ቀበናዎች መሬት ጠቧቸው በጉራጌ ህዝብ ላይ ከፍተኛ ጥቃት እያደረሱ ነው። በርካታ የጉራጌ ቤቶች እየተለዩ እየነደዱ ነው። በርካቶች እየተሰው፤ እየቆሰሉ ነው።

ቀቤና ማለት የኦሮሞ ዘር አለን ብለው የሚያምኑ ኩሾች ሲሆኑ በቀደም አፃፃፍ ስልታቸውን ከሳባ ወደ ላቲን የቀየሩ ህዝቦች ናቸው። በተደጋጋሚ በETV እና አንዳንድ የመንግስት ሚዲያዎች “የገዳ ስርዓት በጉራጌ ዞን ከ100 አመት በፊት ይከበር እንደነበርና የአፃፃፍ ስልታቸውን ከሳባ ወደ ላቲንኛ እንደቀየሩ በስፋት ሲገለፅ ነበር።

በዚህ አካባቢ ኦነግ ሸኔ ለአመታት የዘለቀ ወረራ ፈፅሞ ከ10 በላይ ወረዳዎችን የቀማውም ይሄን ታሳቢ በማድረግ ነበር።