መከላከያው በሰሜን ጎንደር ከፋኖና ከገበሬው ጋር በገጠመው ጦርነት ከባድ ጉዳት ማስተናገዱ ተገለፀ::
በሰሜን ጎንደር ዞን አጅሬ ጃኖራና ጃናሞራ አካባቢ በመከላከያውና በፋኖ መካከል የተጀመረው ውግያ መከላከያው ገበሬውን ትጥቅ አስፈታለሁ ብሎ በመንቀሳቀሱ እንደሆነ የፋኖ የህዝብ ግንኙነት መናገራቸው ተዘግቧል።
የህዝብ ግንኙነቱ እንዳሉት ከዳባት ጀምሮ ያለው ገበሬ በጥሩምባ ተጠራርቶ መከላከያውን ውግያ እንደገጠመና የፋኖ አባላትም እንደተሳተፉበት ተናግረዋል።
በዚህም በመከላከያው ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ገልፀዋል።
በተመሳሳይ የመከላከያ ሰራዊቱ በባህርዳር ሳባታሚት አካባቢ የሚገኘውን የፈለገ ግዮን ስፔዣላይድ ሆስፒታል ካምፕ እንዳደረገው ተሰምቷል።
መከላከያው ይህን ያደረገው በሆስፒታሉ ላይ ተኩስ ከፍቶ ከገባና በውስጡ የነበሩ ታካሚዎችን ከፊሎቹን ፋኖ ናችሁ በሚል ከረሸነ የተቀሩትን ደግሞ ካሰረና ካባረረ በኋላ ነው።
በተመሳሳይ በትናንትናው እለት ከማለዳው ጀምሮ
በእንጅባራ ከተማ የመከላከያና አድማ አባላት ከፋኖ ጋር ከባድ ውግያ ማድረጋቸው ታውቋል።
ፋኖዎች በተለምዶ እንጦጦ ወይም የአድማ ብተና ካምፕ በሚባለው የእንጅባራ መውጫ በር፣በባህርዳርና በአዲስ አበባ መውጫ በሮች ውግያዎችና ከበባዎች መፈፀማቸው ታውቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ መከላከያው ከምንጃር አረርቲ ወደ በረኸት በመንቀሳቀስ ከመስከረም 30 ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከፋኖ ጋር ውግያ እያደረገ ነው።
በዚህም በከሰም ፣ በቆስጤ ገብርኤል እና ምንታምር አካባቢ በከባድ መሳሪያ የታገዘው ውግያ አለቆመም።
በጦርነቱም የአፋር ታጣቂዎች ከፋኖ ጋር አብረው ወደ ውግያው መግባታቸው ተነግሯል።
አሻራ ሚዲያ
