October 14, 2023 – ምንሊክ ሳልሳዊ

እውነት ግን ጦርነት ወይስ የጀርባ ስምምነት ስለ ባሕር በር አብይ የሚጮኸው ? (ምንሊክ ሳልሳዊ)

ዜጎቹን አፍሶ በጦርነት ለመማገድ ስብሰባ የሚቀመጥ መንግስት እንዴት ስለ ሰላምና ደሕንነት የማውራት ሞራል ይኖረዋል ? በባሕር በር ፉጨት አብይንም ኢሳያስንም ማመን አያስፈልግም፤ የትግራዩ ጦርነት በሕወሓት ሽፋን አስጩኸውን ሚሊዮን ንፁሃን ረግፈዋል ………. የቀይ ባሕር ጉዳይ የአማራ ትግልን ለማስቀየስ ከሆነ መልፋት አያስፈልግም፤ ፋኖ ስራውን እየሰራ ነው። .

ፋኖ በተግባር እንጂ በአጀንዳ አይኖርም። ……….. ጦርነትም ላይኖር ይችላል ከጀርባ መስማማት ሌላው ጉዳይ ነው። ኢሳያስ አፍወርቂ የኢማራቱን ንጉስ እግር ተከትሎ ከሚዲያ እውቅና ውጪ አዲስ አበባ በመጣበት ወቅት የአሰብ ወደብ በባዶው ከሚያዛጋ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ 30% ወስደህ አሊያም ከአባይ ግድብ ኤሌክትሪክ ተቀብለህ ወደቡን አካፍለን የሚባለው የጀርባ ስምምነት እውን የመሆን መስመርም ሌላኛው የፖለቲካ ሰነድ ነው።

ከአለም የገንዘብ ድርጅት ጋር ስብሰባ ተቀምጠው የዋጋ ግሽበቱን በእጥፍ ለማድረግ ሲደራደሩ በገበያ ለመወሰን ሲስማሙ ለሕዝብ የኑሮ ውድነት ጥልቀት ውስጥ ሲከቱት ከባሕበር ጥያቄው ጋር የማያያዝበት ምክኛቱ ምን ይሆን ? …….. ከኤርትራ ጋር ለሚኖረው ቀጣይ ጦርነት ሕዝቡ ሊዋጋልኝ አይችልም በሚል ስጋት ወጣቱን አፍሶ ወደ ጦርነት ለመማገድ ማሰብ ሞኝነት ነው። ….. በብሄራዊ ውትድርና ወሰድከውም ካለፍላጎቱ አፈስከውም …………. የታፈሰው ወጣት ሳይተኩስ እጁን ለኤርትራ መንግስት እንደሚሰጥም ማሰብ ያስፈልጋል።

አሜሪካ ወደ ኤርትራ እንዲተኮስ ውክልና እንደማትሰጥ ፍንጭ አሳይታለች ፤ አሜሪካ ባለው የአብይ አገዛዝ ላይ እምነት እንዳሌላት በተደጋጋሚ አመላክታለች። የብልጽግና ሽለላና ፉከራ የሚዲያ ፕሮፓጋንዳ ሆኖ እንዳይቀር አደራ እንላለን። ……. በኤርትራ ላይ የሚከፈት ጦርነት አብይን ለኪሳራ ኢሳያስን ለትርፍ የሚሰጥ ሲሆን አብይ ወደ ኢሳያስ የሚተኩሰውን የመጀመሪያ ጥይት ለመስማት ዝግጁ ሆነን እየጠበቅን ነው።

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ግን ከጀርባ ያለውን ነገር መጠርጠር ያስፈልጋል። አብይ ከጀርባው ምናልባት የኢሳያስን ውክልና ተሸክሞ የሚያወራ ከሆነም የኢትዮጵያ ጠንካራ ተቋማት ለኤርትራ እና ለውጪ ሃይሎች የተወሰነ ድርሻ ሊሸጡ መሆኑን አመላካች ነው። ……. ሕወሃት ላይ አብይ ይተኩሳል ብለን ስንጠብቅ ድንገት ሬድዋን ሁሴን ለሕወሓት ነግሮ ሰሜን እዝ ላይ እንዳስተኮሰው እንዳይሆን ስንፈራ ኤርትራ ላይ ጦርነት መክፈት የአብይን አገዛዝ መገላገያ ካርድ ነው ብለን እናምናለን። እውነት ግን ጦርነት ወይስ የጀርባ ስምምነት ስለ ባሕር በር አብይ የሚጮኸው ? #MinilikSalsawi