Related Video and Audio

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48
Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች
- BBC
Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 23 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 23 SECONDS1:23
Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBCሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ?
- BBC
Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBC

VIDEO 1 MINUTE 33 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 33 SECONDS1:33
Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBCበእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች
- BBC
Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBC
ጭምቅ ሃሳብ
- የጋዛ ሆስፒታሎች መጠባበቂያ ነዳጃቸው በ24 ሰዓታት ተሟጦ ያልቃል- ተመድ
- የእስራኤል ጦር በጋዛ በአየር፣ በባህር እና በመሬት ላይ የተቀናጀ ጥቃት ለመፈጸም ወታደራዊ ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ
- እስራኤል በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን በጋዛ ድንበር ያሰማራች ሲሆን እግረኛ ጦሯም ወደ ጋዛ ዘልቆ እንደሚገባም እየተጠበቀ ነው
- የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ግንባር ላሉ ወታደሮቻቸው “ቀጣዩ ሂደት እየመጣ ነው” ብለዋል
- እስራኤል በሰሜን ጋዛ የሚኖሩ 1.1 ሚሊዮን ፍልስጥኤማውያን ወደ ደቡባዊ ጋዛ እንዲወጡ ማስጠንቀቋን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ በተሽከርካሪዎች እና በእግራቸው እየሸሹ ይገኛሉ
- የዓለም ጤና ድርጅት የእስራኤልን ውጡ ማስጠንቀቂያ በሆስፒታል ያሉ ህሙማንን አስገድዶ ማስወጣት “የሞት ፍርድ ነው” ሲል አውግዞታል
- ከሰሜን ጋዛ እየሸሹ የነበሩ ነዋሪዎችን አሳፍሮ በነበሩ ተሽከርካሪዎች ላይ በእስራኤል በተፈጸመ ጥቃት ሴቶች እና ህጻናት መገደላቸውን ቢቢሲ አረጋግጧል
- እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ እየፈጸመችው ባለው የአየር ጥቃቶች ከ2 ሺህ 200 በላይ ሰዎች ተገድለዋል
- በእስራኤል ባለፈው ሳምንት ሐማስ በፈጸመው የተቀናጀ ጥቃት 1 ሺህ 300 በላይ ሰዎች ተገድለዋል
ቀጥታ ዘገባ
- የታተመዉ 4:194:19የእስራኤል ጦር የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ አለመደረሱን ገለጸ
ReutersCopyright: Reutersየእስራኤል ጦር በደቡባዊ ጋዛ ምንም አይነት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ አለመደረሱን ገለጸ። በግብጽ እና ጋዛ ያለው የድንበር ማቋረጫ መከፈቱ ጋር በተያያዘ የተኩስ አቁም ስምምነት እንደሚኖር የግብጽ የደህንነት ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ሮይተርስ መዘገቡን ተከትሎም ነው ጦሩ ይህንን አስተያየት የሰጠው።”እኔ የማውቀው ምንም አይነት የተኩስ አቁም ስምምነት የለም። የሚወጡ ዘገባዎችን እያየሁ ነው። ምንም የማረጋግጠው ነገር የለም” ሲሉም የእስራኤል መከላከያ ኃይል ቃለ አቀባይ ኮሎኔል ሪቻርድ ሄክት ተናግረዋል።የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤትም እንዲሁም የተኩስ አቁም ስምምነት መደረሱን በተመለከተ የወጣውን ዘገባ ውድቅ አድርጓል።”በአሁኑ ወቅት ከጋዛ የውጭ አገር ዜጎችን በግብጽ ድንበር በኩል ለማስወጣት የተደረገ የተኩስ አቁም እንዲሁም የሰብዓዊ እርዳታ ስምምነት የለም” ሲልም የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጽህፈት ቤት በመግለጫው አትቷል።የሐማስ ሚዲያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በደቡባዊ ጋዛ ተደረሰ ስለተባለው የተኩስ አቁም ስምምነት ምንም ዓይነት መረጃ እንደሌላቸው መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።ሳላማ ማሩፍ በጋዛ እና ግብጽ መካከል ያለው የድንበር ማቋረጫን መከፈቱን በተመለከተ ከግብጽ በኩል ምንም ማረጋገጫ እንዳላገኙ ለዜና ወኪሉ ተናግረዋል።ሮይተርስ አሜሪካ፣ እስራኤል እና ግብጽ በደቡባዊ ጋዛ በኩል የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ሁለት የግብጽ የደህንነት ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘግቦ ነበር።ስምምነቱ የሚደረገው በጋዛ እና ግብጽ መካከል ያለው የራፋህ ድንበር ማቋረጫ መከፈት ጋር በተያያዘም እንደሆነ አስነብቧል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ

- የታተመዉ 3:233:23ለጋዛ የሚሆን እርዳታ በግብጽ ድንበር በኩል ሊገባ ይችላል ተባለ
ReutersCopyright: Reutersበጋዛ ሰርጥ እና ግብጽ መካከል ያለው የድንበር ማቋረጫ ለአጭር ጊዜ ሊከፈት እንደሚችል የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን እሁድ ዕለት ከግብጽ ባለስልጣናት ጋር ከተነጋገሩ በኋላ በግብጽ ቁጥጥር ስር ያለው ድንበር ወደ ጋዛ ዕርዳታ ለማድረስ እንደሚከፈት ተናግረዋል። ሆኖም መቼ እንደሚከፈት ዝርዝር መረጃ አልሰጡም።የእስራኤልን ሰሜናዊ ጋዛ ለቃችሁ ውጡ ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ ፍልስጥኤማውያን ወደ ደቡብ መሰደዳቸውን የመከላከያ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።ቢቢሲ ይህንን አኃዝ ማረጋገጥ አይችልም።በሙሉ ከበባ ውስጥ ባለችው ጋዛ ሁኔታዎች እየከፉ ነው። ውሃ፣ ምግብ፣ ኃይል እና መድኃኒቶች አቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ እየተመናመነ ነው።በጋዛ ሆስፒታሎች ያለው መጠባበቂያ ነዳጅ በ24 ሰዓታት ውስጥ ተሟጦ ሊያልቅ እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስጠንቅቆ በሺዎች የሚቆጠሩ ህሙማንንም ህይወት አደጋ ላይ እንደሚወድቅም አሳስቧል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:053:05ኻን ዩኒስ፡ ከድጡ ወደ ማጡ የሆነባት የጋዛ ከተማየሰው ማዕበል ወደ ጋዛዋ ኻን ዩኒስ ከተማ ጎርፏል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጥኤማውያን የእስራኤልን ውጡ ማስጠንቀቂያ ተከትለው መያዝ የሚችሉትን ሸክፈው ከሰሜናዊ ወደ ደቡባዊ ጋዛ ተሰደዋል። ነዳጅ ያገኙ በመኪና፤ ከተገኘ ደግሞ በፈረስ ጋሪ አማራጭ ያጡ ደግሞ በእግራቸው ኳትነዋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:372:37የ6 ዓመቱ ታዳጊ በጸረ ሙስሊም ጥቃት መገደሉን የአሜሪካ ፖሊስ አስታወቀበአሜሪካ ሙስሊም በመሆናቸው የስድስት አመት ታዳጊ እና እናቱን በስለት የወጋው የቤት አከራይ በነፍስ ግድያ እና በጥላቻ ወንጀል ተከሰሰ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:530:53የጋዛ ሆስፒታሎች መጠባበቂያ ነዳጃቸው በ24 ሰዓታት ተሟጦ ያልቃል- ተመድ
ReutersCopyright: Reutersበጋዛ ሆስፒታሎች ያለው መጠባበቂያ ነዳጅ በ24 ሰዓታት ውስጥ ተሟጦ ሊያልቅ እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስጠነቀቀ።“የመጠባባቂያ ጄነሬተሮችን ማቋረጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ህሙማንን ህይወት አደጋ ላይ ይጥላል” ሲል የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ በድረገጹ አስፍሯል።በሙሉ ከበባ ላይ ባለችው ጋዛ ውሃ፣ ምግብ፣ ሃይል እና መድኃኒት አቅርቦት እየተመናመነ የሚገኝ ሲሆን የተለያዩ የረድዔት ድርጅቶችም ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ መዳረሻዎች እንዲከፈቱ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።በጋዛ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን የህክምና ባለሙያ ዶክተር አቡ ሲታ በሆስፒታላቸው ውስጥ ያሉ የጤና ባለሙያዎች ህሙማንን ለመርዳት በቂ መሳሪያ እንደሌላቸው አስጠንቅቀዋል።የድንገተኛ ህሙማን ቁጥር በማሻቀቡም “በየቀኑ ለአንድ ወር ወይም ከአንድ ወር ተኩል በላይ ሊያገለግሉ የሚችሉ የሚችሉ የህክምና ቁሳቁሶችን እየተጠቀምን እንገኛለን” ብለዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:340:34እስራኤል በጋዛ ላይ በምታካሂደው የእግረኛ ጦር ዘመቻ ምን ማድረግ ትፈልጋለች?የእስራኤል መሪዎች ሐማስን ከጋዛ ጠራርገው ለማጥፋት ዝተዋል፣ በዚህም ሳቢያ ጋዛ ከዚህ በፊት የነበራት ገጽታ ባለበት የሚቀጥል አይመስልም።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 7:30 15 ጥቅምት 20237:30 15 ጥቅምት 2023የዩኬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለሰላማዊ ሰዎች ስቃይ ተጠያቂው ሐማስ ነው አሉ
BBCCopyright: BBCየዩናይትድ ኪንግደም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጀምስ ክሌቨርሊይ ሰላማዊ ሰዎች ለስቃይ ለመዳረጋቸው ተጠያቂው ሐማስ ነው አሉ።ሚኒስትሩ ይህ ያሉት ዛሬ ጠዋት ዩኬ የእስራኤል መንግሥት ጥቃቱን እንዲቀጥል ደግፋ እንደሆነ በተጠየቁበት ወቅት ነው።ሚኒስትሩም ሲመልሱ “ለፍልስጥኤማውያን ስቃይ ተጠያቂው ሐማስ ነው” ብለዋል።ሆኖም በተለይ እስራኤል የምድር ጥቃት ከመጀመሯ ቀደም ብሎ በጋዛ እየደረሰ ያለው ሞት እንዳሳሰባቸው ሚኒስትሩ ተናግረዋል።እስራኤል በጋዛ ላይ እየወሰደችው ባለው የቦምብ ዘመቻ ከ2 ሺህ 300 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የፍልጥኤም ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።ክሌቨርሊይ “ እስራኤል በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት የመቀነስ ግዴታ አለባት።በዚህ ጉዳይ ላይም ከእስራኤል መንግሥት ጋር በነበረኝ ውይይት ይህንኑ አንስቻለሁ” ብለዋል።የኖርዌይ የስደተኞች ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ሰላማዊ ሰዎች ከሰሜናዊ ጋዛ ወደ ደቡብ እንዲሄዱ መገደዳቸው እንደ ጦር ወንጀል ይቆጠራል ማለታቸውን ተከትሎም ዩኬ በእስራኤል ላይ የጦር ወንጀል ክስ አንስታ እንደሆነም ሚኒስትሩ ተጠይቀው ነበር።“የዩኬ መንግሥት ለዓለም አቀፍ ሕግ መከበር ቁርጠኛ አቋም ነው ያለው” ሲሉ የእንግሊዝ መንግሥት እስራኤል የምትፈፅመውን ጥሰትም ዝም ብሎ እንደማያልፍ ተናግረዋል።ሚኒስትሩ በመጨረሻም የዩኬ መንግሥት በግብፅ እና በጋዛ ሰርጥ መካከል ያለውን የራፋህ መሻገሪያን ለመክፈት ከግብፅ እና ከእስራኤል ጋር እየተነጋገረ መሆኑን፤ ነገር ግን እስካሁን አለመሳካቱን ተናግረዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 6:58 15 ጥቅምት 20236:58 15 ጥቅምት 2023የእስራኤል መከላከያ ኃይል የኪቡትዝን ጥቃት የመራውን የሐማስ አዛዥ ገድያለሁ አለ
EPACopyright: EPAየእስራኤል ጦር በደቡባዊ የጋዛ ከተማ ካን ዮኒስ የሚገኙ የሐማስ ኃይሎች አዛዥ የሆነውን ቢላል አል ከድራን መግደሉን አስታወቀ።ጦሩ ይህን ያለው እስራኤል በጋዛ የምታደርገውን የአየር ድብደባ በቀጠለችበት ወቅት ነው።እስራኤላውያን ባለፈው ቅዳሜ የሐማስ ታጣቂዎች የእስራኤልን ድንበር ጥሰው በመግባት ድንገተኛ ጥቃት ከከፈቱ በኋላ በደቡብ እስራኤል ኪቡትዝ ኒሪም ለተፈፀመው የጅምላ ግድያ ቢላል አል ከድራ ተጠያቂ ነው ብለዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 5:51 15 ጥቅምት 20235:51 15 ጥቅምት 2023126 እስራኤላውያን በጋዛ ታግተው እንዳሉ ጦሩ አስታወቀ
EPA-EFE/REX/ShutterstockCopyright: EPA-EFE/REX/Shutterstockሐማስ በከፈተው ድንገተኛ ጥቃት 279 ወታደሮቿ መገደላቸውን ያስታወቀው የእስራኤል ጦር 126 ታጋቾች ተወስደዋል ብሏል።በጥቃቱ ከ1 ሺህ 300 በላይ ሰዎች ሞተዋል።እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ ተደጋጋሚ የአየር ጥቃቶች እየፈጸመች ሲሆን በነዚህ ጥቃቶች 13 እስራኤላውያን ታጋቾች መገደላቸውን ሐማስ ከዚህ ቀደም አስታውቋል።እስራኤል በዚህ ላይ የሰጠችው አስተያየት የለም።ቀደም ሲል ወደ 150 የሚጠጉ ሰዎች ታግተው እንደነበር አስታውቃ የነበረ ሲሆን በዛሬው ዕለት የእስራኤል መከላከያ ኃይል የታጋቾች ቁጥር 126 መሆኑን ገልጿል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 5:18 15 ጥቅምት 20235:18 15 ጥቅምት 2023በሰሜን እስራኤል ከሊባኖስ በተተኮሰ ሚሳኤል አንድ ሰው ተገደለ
EPACopyright: EPAየእስራኤል ጦር በሊባኖስ ድንበርImage caption: የእስራኤል ጦር በሊባኖስ ድንበርበሰሜን እስራኤል ከሊባኖስ በተወነጨፈ ሚሳኤል አንድ ሰው ሲገደል ሁለት ሰዎች መቁሰላቸውን የእስራኤል የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት አስታውቋል።በሊባኖስ እና በእሰራኤል ድንበር ላይ ያለው ውጥረት እየተባባሰ መምጣቱም ተነግሯል። እስራኤል የተገደለው እንዲሁም የቆሰሉት ሰላማዊ ዜጎች መሆናቸውን አስታውቃለች።የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሂዝቦላህ ሽቱላ በተሰኝው የድንበር ከተማ ላይ ሚሳኤሎችን ማስወንጨፉን አስታውቋል።የእስራኤል ጦር በበኩሉ በከባድ መሳሪያ የታገዘ የጥቃት ምላሽ እንደሰጠም አስታውቋል። ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ እስራኤል እና ሄዝቦላህ የሮኬቶች እና የከባድ መሳሪያ ልውውጥ አድርገዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:27 15 ጥቅምት 20233:27 15 ጥቅምት 2023ሰበርእስራኤል ከሰሜን ጋዛ ለሚሸሹ አንደኛውን መንገድ ለሶስት ሰዓታት ከኢላማ ውጭ እንደምታደርገው አስታወቀች
EPACopyright: EPAእስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ የምታደርገውን የምድር ላይ ጥቃት ከመጀመሯ በፊት በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጥኤማውያን ከሰሜን ጋዛ እየሸሹ ይገኛሉ።በሰሜን ጋዛ ያሉ ሰላማዊ ሰዎች በአገሬው ሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ አንድ ሰዓት እስከ አራት ሰዓት ድረስ ወጥተው ወደ ደቡባዊ ጋዛ ማምራት እንዳለባቸው የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ አዲስ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።ነዋሪዎች ከቤይት ሃኑን ወደ ክሃን ዩንስ የሚወስደውን መስመር ብቻ መጠቀም እንዳለባቸው ጠቅሶ በእነዚያ ሰዓታት ውስጥ መንገዱ ከኢላማ ውጭም እንደሚሆንም አስፍሯል።እስራኤል በሰሜን ጋዛ ለሚኖሩ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች በ24 ሰዓታት ውስጥ ወደ ደቡባዊ ጋዛ እንዲሄዱ ማስጠንቀቂያ ሰጥታ የነበረ ሲሆን በዚህ ወቅትም ሁለት መንገዶችን መጠቀም አለባቸው ብላ ነበር።በሰሜን ጋዛ ያሉ ሆስፒታሎችም አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ተነግሯቸዋል። የዓለም ጤና ድርጅት የእስራኤልን ውጡ ማስጠንቀቂያ በሆስፒታል ያሉ ህሙማንን አስገድዶ ማስወጣት “የሞት ፍርድ ነው” ሲል አውግዞታልArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:19 15 ጥቅምት 20233:19 15 ጥቅምት 2023ጋዛን ለቀው እየወጡ በነበሩ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ስለተፈፀመው ጥቃት የምናውቀውአርብ ምሽት ላይ ሰላማዊ ሰዎችን አሳፍረው ወደ ደቡባዊ ጋዛ እየተጓዙ በነበሩ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት መፈፀሙን የሚያሳዩ ዘገባዎች ወጥተዋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:13 15 ጥቅምት 20232:13 15 ጥቅምት 2023በጋዛ የተገደሉ ሰዎች ከ2 ሺህ 300 በላይ ሆነ
EPACopyright: EPAእስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ እየፈጸመችው ባለችው የአየር ጥቃቶች የተገደሉ ሰዎች ከ2 ሺህ 300 በላይ መሆኑን የፍልስጥኤም ጤና ኃላፊዎች ተናግረዋል።በአየር ጥቃቶች 2 ሺህ 329 ፍልስኤማውያን ሲገደሉ 9 ሺህ 714 ሰዎች ደግሞ እንደቆሰሉ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። ሐማስ በሰነዘረው ጥቃት ስምንት ቀናትን አስቆጥሯል።በዚህ ጥቃት 1 ሺህ 300 እስራኤላውያን ተገድለዋል። እስራኤል የአጸፋ ምላሽ ነው በሚል በጋዛ ሰርጥ የማያባራ የአየር ጥቃት እየፈጸመች ትገኛለች።እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ እየፈጸመችው ካለችው የአየር ጥቃት በተጨማሪ እግረኛ ጦሯን ለማስገባት ዝግጅት ላይ መሆኗን ገልጻለች።የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ግንባር ላሉ ወታደሮቻቸው “ቀጣዩ ሂደት እየመጣ ነው” ብለዋል።የእስራኤል ጦር ጋዛ ሰርጥን በሙሉ ከበባ ውስጥ እንድትገባ በማድረግም ውሃ፣ ምግብ፣ መብራት እና ሌሎች መሰረተ ልማቶች መቋረጡንም ከቀናት በፊት አስታውቋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:58 15 ጥቅምት 20231:58 15 ጥቅምት 2023በእስራኤል- ጋዛ የተከሰቱ ዋና ዋና ጉዳዮች
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤል እና የሐማስ ግጭት ከተከሰተ ስምንተኛ ቀኑን ይዟል። በሳምንቱ የተከሰቱ ዋና ዋና ጉዳዮችን እንቃኝ
- የእስራኤል ጦር በጋዛ በአየር፣ በባህር እና በመሬት ላይ የተቀናጀ ጥቃት ለመፈጸም ወታደራዊ ዝግጅት ማድረጉን የገለጸ ሲሆን እግረኛ ጦሩም ወደ ጋዛ ዘልቆ እንደሚገባም እየተጠበቀ ነው።
- እስራኤል በሰሜን ጋዛ የሚኖሩ 1.1 ሚሊዮን ፍልስጥኤማውያን ወደ ደቡባዊ ጋዛ እንዲወጡ ማስጠንቀቋን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በተሽከርካሪዎች እና በእግራቸው እየሸሹ ይገኛሉ።
- በሰሜን ጋዛ ያሉ ሆስፒታሎችም አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ተነግሯቸዋል።የዓለም ጤና ድርጅት የእስራኤልን ውጡ ማስጠንቀቂያ በሆስፒታል ያሉ ህሙማንን አስገድዶ ማስወጣት “የሞት ፍርድ ነው” ሲል አውግዞታል
- የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እንዲሁም የፍልስጥኤም መሪ ማህሙድ አባስን በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ አነጋግረዋል።
- ሐማስ ከሳምንት በፊት በከፈተው ጥቃት 1 ሺህ 300 ሰዎች ተገድለዋል፤ 150 ሰዎች ታግተዋል።
- እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ እያካሄደችው ባለው ተደጋጋሚ የአየር ጥቃቶች ከ2 ሺህ 200 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የፍልስጥኤም ባለስልጣናት ተናግረዋል።
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 1:47 15 ጥቅምት 20231:47 15 ጥቅምት 2023በዩኬ ለፍልስጥኤም ድጋፋቸውን ለመግለጽ በሺዎች የሚቆጠሩ አደባባይ ወጡለንደን እና ማንቸስተርን ጨምሮ በበርካታ የዩኬ ከተሞች ፍልስጥኤምን የሚደግፉ ሰልፎች ተካሄዱ።የፍልስጥኤምን ሰንደቅ አላማ የያዙ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችም “ነጻ ፍልስጥኤም” ሲሉም ተደምጠዋል። በለንደን የተደረገው የአደባባይ ሰልፍ የተጀመረው በፖርትላንድ ፕላስ በሚገኘው የቢቢሲ ዋና መስሪያ ቤት ነው።ተጨማሪ ያንብቡ