· Getachew Shiferaw

 · ውሸታቸውን ነው!

ቀይ ባሕርን ለኢትዮጵያ አያስቡትም። ውሸታቸውን ነው። አንድ አገር ቀዳሚ ህልውናው የሚረጋገጠው ጠንካራ ተቋም ሲኖር እንጅ ውሃ ዳር ስላለው ብቻ አይደለም። ተቋም እያፈረሱ በባሕር አገር አይፀናም። ውሸታቸውን ነው።

ለምሳሌ!

ቴሌ በአማራ ተያዘ ብለው ዘመቱ። የሀሰት መረጃ የሚሰጡ እነ አብይ። ዘማች ኦ ኤም ኤንና የኦነግ ፌስቡከኛ።የ

አፋር ጨው በአማራ ባለሀብት ተያዘ ብለው ዘመቱ። የሀሰት መረጃ የሚሰጡት ከብሔር ወጥተን በቀጠና እናስብ የሚሉት እነ አብይ ዘጋቢያቸው ኦ ኤም ኤን።

አሁን ስለ ቀይ ባሕር እያወሩ በልማት ባንክ ዘመቱ። የአማራ ባለሐብት ነው ገንዘቡን የሚወስደው ብለው በሀሰት አስዘመቱ። ኃላፊ ቀየሩ።

አሁን የተቀየረው ሰው የኦሮሚያ የኢኮኖሚ አብዮት የሚል ቡድን አባል ነው። ከዛ ኬኛ አክሲዮን ኃላፊ፣ ቀጥለው ወደ ስንቄ ባንክ አመጡት። ብሔራዊ ባንክ “መስፈርት አያሟላም” አለ። አብይ አህመድ በቀጥታ ደውል “ፍቀዱ” አለ። በግድ ኃላፊ ሆነ። ከዛም ወደ ልማት ባንክ አመጡት። ከበርካታ የሀሰት ዘመቻ በኋላ።

ብርሃነ መስቀል አበበ ሰኚ የሚባለው በራሱ የሚዘባስቅ የሚመስለው ካለ ተሳስቷል። እነ አብይ አጀንዳ አስይዝ እያሉት ነው። በአንድ በኩል በጎሳው ተቋም እየወረረ፣ እያፈረሰ በሌላ በኩል ወደ ወረዳ አንመልከት ይላል። ይህ ቀበሌያም ሁላ።

ንግድ ባንክን በአቤ ሳኖ፣ ገቢዎችን በአዳነች አቤቤ ቀያየሩት። ስለእነዚህ ተቋማት አያወሩም። ዘመድ አዝማድ አጠራቅመውታል። አፍርሰዋቸዋል።

ለአገር መሰረቱ ተቋም ነው። ተቋም እያፈረሰ ባሕር አፋልጉኝ ይላል። ለኢትዮጵያ ባሕር እንደማትፈልጉ የታወቀ ነው። እኛ ኢሬቻ አናከብርም። ለኢሬቻ ቤርሙዳ ትሪያንግልም ካሳሳችሁ ሄዶ ማክበር መብታችሁ ነው።

የባሕር በር የምንፈልገው ለኢትዮጵያ አስበን ነው ግን አትበሉን። ቅጥፈት ነው። ምፅዋን ተጠቀሙ ስትባሉ “አማራ ይጠቀምበታል” ብላችሁ አልተዋችሁትም?