October 16, 2023 

( መንግስቱ ሙሴ )

ጽናቱን ሁሉ ለናንተ ያርገው ያለጧሪ ያለ ቀባሪ ለቀራችሁ የትግራይ እናቶች!

ለአማራ እናቶች!

ለአፋር እናቶች

ለኢትዮጵያ እናቶች ሁሉ።

ገዳይ እና አስገዳዮች አሁንም በስልጣን ያሉት ከስልጣን የወረዱትም ሁሉም ሐዘን እነሱቤት የለም። ሐዘኑም የጋራችን አይደለም እምነታቸውም አንድ ነው እኛ ነና እነሱ በሚል ፉክክር እና ዘረኝነት ተውጠው የኢትዮጵያውያንን የእርስ በእርስ መተላለቅ እንደፖለቲካ ግብ የሚቆጥሩት ገዥወች አሁንም ሐዘን እነሱቤት አልገባም የጥጋብ እና የዘረኝነት ልካቸው ያልበረደው ለ 31 አመታት ያስቀጠሉት ስርአት እስካልተወገደ የሕዝባችን መከራ እና የድሀ ልጆች ሞት ቀጣይ ነው።

የነሱ ልጆች ትናንትም ዛሬም ለምናልባት ችግር እንዳይገጥማቸው፤ ትምህርታቸው እንዳይጓደል፤ የአካል ጉዳት ቀርቶ የሰው አይን እንዳያርፍባቸው፤ በውጭ ሐገራት በየግል ትምህርትቤቶች ይኖራሉ ትምህርታቸውንም በሰላም እና በተረጋጋ ይከታተላሉ።

ይህ ቀን በዚያ ጀኖሳይዳል ጦርነት ላለቁትም ሆነ አሁንም በሚካሄደው ጀኖሳይዳል ጦርነት ብሔራዊ የሐዘን ቀን ሊኖረው በተገባ ሆኖም የሚጫወቱት ፖለቲካ የደሐ ወላጆችን ሐዘን እና ስቃይ ፖለቲካዊ ስለአደረጉት የፈጠሯትም ሐገር የባእዳን ስብስብ ብለው ስለሚያምኑ እና ለቀጣይ የርስ በእርስ ጦርነት ስለሚዘጋጁ የአንዱ ክልል፤ ስደት እና መከራ ለሌላው ምኑም አይደለም ብለው ያምናሉ።

እናም እነዚህ በግራ እና ቀኝ ያሉት በትግራይም ሆነ በኦሮሚያ ወይንም የነሱ ጭራ የሆኑት በሁሉም ክልል የተኮለኮሉት እና ስርአታቸው እስካልተወገደ የሕዝባችን ሞት፤ ስደት እና መከራ ቀጣይ ነው። በጥቅሉ መጽኔውን ለኢትዮጵያ እናት እና አባት። መጽኔ እየፈረሰች ላለችው ሐገራችን። ( መንግስቱ ሙሴ )