October 16, 2023

ጉዳዩን አትንካው አርፈህ ተቀመጥ ብሏል የኤርትራ መንግስት ፤ ፋኖ ሲያንጠባጥበው ሮጦ ቀይ ባሕር ለሄደው ሰውዬ ………..

የኤርትራ መንግስት የአብይን የቀይ ባሕር አጀንዳ አፈር ከዲሜ አስግጦታል። ከቀይ ባሕር በፊት እንደ ሃገር አስተዳዳሪ መንግስት የዜጎች ደሕንነትና የሃገር ሰላም በሚቀድምበት ወቅት ሌላ የማይፈለግ እና አጉል ማዘናጊያ አጀንዳ ያመጣውን አብይ የባህር በር ጉዳይ ላይ፤ ኤርትራ ለድርድር እንደማትቀመጥ አስረግጦ ነግሮታል። በቅርብ ጊዜ ስለ ውሃ እና ስለ ባህር በሮች እንዲሁም ተመሳሳይ ርዕሰ ጉዳዮች የተነገረው እና የተባለው ቁጥር የለውም በዚም ያልተገረመ ታዛቢ የለም” ብሏል፡፡

ፋኖ መግቢያ መውጫ ሲያሳጣው፤ መሄጃና መምጫውን ሲቆላልፍበት የማርያም መንገድ መጠየቅ ሲገባው የባሕር በር የጠየቀው አብይ በኤርትራ መንግስት ደግሞ እንዳያነሳው አድርጎ አስቀምጦለታል። በአየር መንገድ፣ በሕዳሴ ግድባ እና በቴሌ ቀይባሕርን ለውጬ እመጣለሁ ብሎ ሲያስብ በጦርነት ልቆጣጠረው እችላለው ብሎ ሲያልም ቀድመንሃል ተብሏል። ኤርትራ በተጠንቀቅ ላይ መሆኗን ደጋግመን ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኃላ የሰማነው ጉዳይ ነው። በኢትዮጵያ የሚኖሩ የኤርትራ ስደተኞችም መታፈሳቸውን የሰማነው ለጊዜው ጋብ ቢልም ሰሞኑን እንዳይቀጥል ስጋት ያሳደረውም ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኃላ ነው።

አብይ አሕመድ ለሕግ የበላይነት ለሃገር ሰላም እና ለዜጎች ደሕንነት ቅድሚያ የሚሰጥበትን ቀን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይናፍቃል። የሰላም እጦት፣ የኑሮ ውድነት፣ ከቦታ ቦታ ዞሮ መስራት አለመቻል። የዋጋ ግሽበት፣ስራት አልበኝነት፣ የመሳሰሉት በሰፈነበት አገር ውስጥ መጀመሪያ የሕግ የበላይነትና የዜጎች ደሕንነት ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል፤ ወደቡን እርሱት ። #MinilikSalsawi