Related Video and Audio

VIDEO 7 MINUTES 59 SECONDSVIDEO 7 MINUTES 59 SECONDS7:59

Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBCከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ

Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBC

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 23 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 23 SECONDS1:23

Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBCሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ?

Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBC

VIDEO 1 MINUTE 33 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 33 SECONDS1:33

Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBCበእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች

Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBC

ጭምቅ ሃሳብ

  1. ኢራን ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ሰጠች
  2. ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እስራኤልን ሊጎበኙ ነው
  3. የጋዛ ሆስፒታሎች መጠባበቂያ ነዳጃቸው በ24 ሰዓታት ተሟጦ ያልቃል- ተመድ
  4. የእስራኤል ጦር በጋዛ በአየር፣ በባህር እና በመሬት ላይ የተቀናጀ ጥቃት ለመፈጸም ወታደራዊ ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ
  5. እስራኤል በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን በጋዛ ድንበር ያሰማራች ሲሆን እግረኛ ጦሯም ወደ ጋዛ ዘልቆ እንደሚገባም እየተጠበቀ ነው
  6. የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ግንባር ላሉ ወታደሮቻቸው “ቀጣዩ ሂደት እየመጣ ነው” ብለዋል
  7. እስራኤል በሰሜን ጋዛ የሚኖሩ 1.1 ሚሊዮን ፍልስጥኤማውያን ወደ ደቡባዊ ጋዛ እንዲወጡ ማስጠንቀቋን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ በተሽከርካሪዎች እና በእግራቸው እየሸሹ ይገኛሉ
  8. የዓለም ጤና ድርጅት የእስራኤልን ውጡ ማስጠንቀቂያ በሆስፒታል ያሉ ህሙማንን አስገድዶ ማስወጣት “የሞት ፍርድ ነው” ሲል አውግዞታል
  9. ከሰሜን ጋዛ እየሸሹ የነበሩ ነዋሪዎችን አሳፍሮ በነበሩ ተሽከርካሪዎች ላይ በእስራኤል በተፈጸመ ጥቃት ሴቶች እና ህጻናት መገደላቸውን ቢቢሲ አረጋግጧል
  10. እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ እየፈጸመችው ባለው የአየር ጥቃቶች ከ2 ሺህ 200 በላይ ሰዎች ተገድለዋል
  11. በእስራኤል ባለፈው ሳምንት ሐማስ በፈጸመው የተቀናጀ ጥቃት 1 ሺህ 300 በላይ ሰዎች ተገድለዋል

ቀጥታ ዘገባ

  1. የታተመዉ 11:5411:54እስካሁን ጋዛ ውስጥ 3,000 ሰዎች ሲገደሉ ከ12,000 በላይ ተጎድተዋልየፍንዳታ ጭስ በጋዛEPACopyright: EPAጋዛImage caption: ጋዛየፍልስጥኤም ጤና ሚኒስቴር አዲስ ያወጣው መረጃ ባለፉት ዘጠኝ ቀናት 3,000 የሚደርሱ ሰዎች ጋዛ ሰርጥ ውስጥ በተፈጸሙ የአየር ጥቃቶች ምክንያት መገደላቸውን አመለከተ።መስከረም 26/2016 ዓ.ም. ሐማስ ድንበር ተሻግሮ በእስራኤል ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ፣ በጋዛ ላይ የእስራኤል አየር ኃይል ያለማቋረጥ በፈጸመው የአየር ድብደባ ነው ሰዎቹ የተገደሉት።ከተገደሉት ፍልስጥኤማውያን በተጨማሪ 12,500 የሚሆኑት ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል።በሌላ በኩል ደግሞ ከጋዛ በስተምሥራቅ ተነጥሎ በሚገኘው የፍልስጥኤም ግዛት ዌስት ባንክ ውስጥ 61 ፍልስጥኤማውያን የተገደሉ ሲሆን፣ ከ1,250 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል።በጋዛ ላይ የእስራኤል ጦር ኃይል ሙሉ ከበባ በመጣሉ የመሠረታዊ አቅርቦቶች ችግር የተፈጠረ ሲሆን፤ የውሃ፣ የኤሌክትሪክ እና የነዳጅ አቅርቦት በመቋረጡ በነዋሪው ላይ የበለጠ ችግር ይፈጠራል ተብሎ ተሰግቷል።የፍልስጥኤም የጤና ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እንዳሉት፣ ጋዛ ውስጥ ኤሌክትሪክ በመቋረጡ እና የነዳጅ እጥረት በመፈጠሩ ሆስፒታሎች “ሥራቸውን ወደማቆም ተቃርበዋል።”Article share tools
  2. የታተመዉ 10:1910:19የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሐማስ መሪ ጋር ተወያዩየሐማሱ መሪ ኢስማኤል ሃኒያህ እና የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶርAFP/REUTERSCopyright: AFP/REUTERSየሐማሱ መሪ ኢስማኤል ሃኒያህ እና የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶርImage caption: የሐማሱ መሪ ኢስማኤል ሃኒያህ እና የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶርየደቡብ አፍሪካዋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሐማስ መሪ ጋር “ወደ ፍልስጥኤም ግዛቶች ሰብአዊ እርዳታ በሚቀርብበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን” ጽህፈት ቤታቸው አስታወቀ።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ናሌዲ ፓንዶር የደቡብ አፍሪካ መንግሥትን በመወከል ከሐማሱ መሪ ኢስማኤል ሃኒያህ ጋር መወያየታቸውን ዛሬ ማክሰኞ አረጋግጠዋል።ነገር ግን ውይይቱ የተደረገው በደቡብ አፍሪካ መንግሥት ጥያቄ ሳይሆን በሐማስ ፍላጎት መሆኑም ተነግሯል።በስልክ በተደረገው ውይይት ወቅት “ሚኒስትር ፓንዶር ደቡብ አፍሪካ ለፍልስጥኤም ሕዝብ ያላትን ድጋፍ በመግለጽ፣ በፍልስጥኤም እና በእስራኤል ሰላማዊ ዜጎች ላይ በደረሰው የሕይወት መጥፋት ማዘናቸውን ተናግረዋል” ብሏል የወጣው መግለጫ።በተጨማሪም “ሚኒስትሯ እና የሐማሱ መሪ አስፈላጊ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ወደ ጋዛ እና ወደ ሌሎች የፍልስጥኤም ግዛቶች እንዴት ሊደረስ እንደሚችል” መወያየታቸው ተገልጿል።ከሳምንት በፊት ሐማስ በእስራኤል ላይ ከባድ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የእስራኤል ሠራዊት በጋዛ ላይ ከበባ በመጣሉ ሐማስ በሚያስተዳድራት በጋዛ ውስጥ የመሠረታዊ አቅርቦት ቀውስ ተፈጥሯል።የሚኒስትሯ ጽህፈት ቤት በአንድ የአገሪቱ የመገናኛ ብዙኃን ሐማስ በእስራኤል ላይ ለፈጸመውን ጥቃት ሚኒስትሯ ድጋፋቸውን ገልጸዋል መባሉን አስተባብሏል።በሐማስ እና በእስራኤል መካከል ግጭቱ ከተጀመረ በኋላ ከታጣቂ ቡድኑ ጋር መወያየታቸውን በይፋ ከተናገሩ ጥቂት አገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ አንዷ ናት።Article share tools
  3. የታተመዉ 8:448:44ጋዛ ውስጥ ያሉ 11 ሺህ ቁስለኞችን ለመርዳት እንድገባ ይፈቀድልኝ፡ የዓለም ጤና ድርጅትራፋህ ውስጥ በእስራኤል ጥቃት ጉዳት የደረሰበትን ሰው የተሸከሙ ሰዎችReutersCopyright: Reutersራፋህ ውስጥ በእስራኤል ጥቃት ጉዳት የደረሰበትን ሰው የተሸከሙ ሰዎችImage caption: ራፋህ ውስጥ በእስራኤል ጥቃት ጉዳት የደረሰበትን ሰው የተሸከሙ ሰዎችየዓለም ጤና ድርጅት አስራ አንድ ሺህ ሰዎች የመቁሰል ጉዳት ወደደረሰባቸው ጋዛ እርዳታ እና የሕክምና አቅርቦት ለማድረስ አስቸኳይ ፈቃድ እንዲሰጠው ጠየቀ።ድርጅቱ ጨምሮም ጋዛ ውስጥ አሁን ያለው ሁኔታ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ሰብአዊ ቀውስጥ ሊከሰት ይችላል በማለት አስጠንቅቋል።የሐማስን ጥቃት ተከትሎ እስራኤል በጋዛ ላይ የአጸፋ የአየር ድብደባ መፈጸም ከጀመረች ሳምንት ያለፋት ሲሆን፣ ወደ ሦስት ሺህ የሚጠጉ ፍልስጥኤማውያን አስካሁን ተገድለዋል።የዓለም ጤና ድርጅትን ጠቅሶ ሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገባው ጋዛ ውስጥ ከተገደሉት 2,800 ሰዎች መካከል ግማሽ የሚሆኑት ሴቶች እና ሕጻናት ናቸው። በተጨማሪም አስካሁን 11,000 ሺህ ሰዎች በጥቃቱ የመቁሰል ጉዳት ደርሶባቸዋል።ድርጅቱ ምንም አይነት ነገር ለማስገባት እና ለማስወጣት ወደማይቻልባት ጋዛ አስፈላጊው የሕክምና እና የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ለማድረስ የሚያስችል በር በአስቸኳይ እንዲከፈት ለማስቻል “ከውሳኔ ሰጪ አካላት” ጋር እየተነጋገረ መሆኑን ገልጿል።ባለሥልጣናት ጨምረውም በጋዛ ውስጥ ባሉ በ115 የጤና አገልግሎት ተቋማት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፣ አብዛኞቹ የጋዛ ሆስፒታሎች የውሃ እና የኤሌክትሪክ አቅርቦት ችግር ስላለባቸው ሥራቸውን እያከናወኑ አይደለም።የውሃ እና የንጽህን አቅርቦቶች በመቋረጣቸው “የተቅማጥ እና የውሃ ወለድ በሽታዎች ስጋት ከፍተኛ ነው” የመንግሥታቱ ድርጅት የፍልስጥኤም ስደተኞች ተቋም “ካለውሃ ሰዎች መሞት ይጀምራሉ” በማለት ስጋቱን ገልጿል።Article share tools
  4. የታተመዉ 8:238:23የተባበሩት መንግሥታት ጋዛ ውስጥ የጦር ወንጀል ሊፈጸም ይችላል ሲል አስጠነቀቀከጋዛ የሚወጡ ፍልስጥኤማውያንReutersCopyright: Reutersየእስራኤልን ጥቃት በመፍራት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጥኤማውያን ከሰሜን ጋዛ እየወጡ ነውImage caption: የእስራኤልን ጥቃት በመፍራት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጥኤማውያን ከሰሜን ጋዛ እየወጡ ነውየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የእርዳታ ድርጅቶች ወደ ጋዛ መግባት እንዲፈቀድላቸው በድጋሚ በመጠየቅ፣ ጋዛ ውስጥ የጦር ወንጀሎች ሊፈጸሙ ይችላል ሲል አስጠነቀቀ።የድርጅቱ የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ራቪና ሳምዳሳኒ እንዳሉት፣ የእስራኤል ሠራዊት በሰሜን ጋዛ ያሉ ፍልስጥኤማውያን ወደ ደቡብ እንዲወጡ ማዘዙ “ዓለም አቀፍ ሕግን በመጣስ ሲቪሎችን በኃይል ከመኖሪያቸው ማስወጣት ነው” በማለት ሁኔታው የተባበሩት መንግሥታት “እንዳሳሰበው” ገልጸዋል።አንድ አገር በግጭት ወቅት የጦር ወንጀል ፈጽሟል ተብሎ ከታመነ ጉዳዩ በዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ሊታይ ይችላል። ፍልስጥኤም የፍርድ ቤቱ አባል ስትሆን እስራኤል ግን አይደለችም።ቃል አቀባይዋ በሰጡት መግለጫ ከሰሜናዊ ጋዛ ለመውጣት በሚሞክሩ ሲቪል ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች በገለልተኛ ወገን መመርመር አለባቸውም ብለዋል።በተጨማሪም ቁጥራቸው ወደ 199 የደረሰው በሐማስ የታገቱ እስራኤላውያን “ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ” እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።Article share tools
  5. የታተመዉ 6:416:41የራፋህ የድንበር ማቋረጫ ምንድን ነው? እንዴትስ የጋዛ ነዋሪዎች ተስፋ ለመሆን በቃ?ከሚጠበቀው የእስራኤል የእግረኛ ጦር ዘመቻ በፊት ፍልስጥኤማውያን ከአካባቢው ለመልቀቅ በማሰብ ከደቡባዊ የጋዛ ሰርጥ ወደ ግብፅ በሚያሻግረው የራፋህ የድንበር ማቋረጫ ላይ እየተሰባሰቡ ነው። የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን በዚህ ጊዜ ባይሉም የድንበር ማቋረጫው ጥምር ዜግነት ያላቸውን ለማስወጣት እና ሰብዓዊ እርዳታ ለማስገባት እንደሚከፍት ዘግበዋል። ሆኖም ድንበር ማቋረጫው እስካሁን ድረስ እንደተዘጋ ነው። የራፋህ የድንበር ማቋረጫ ምንድን ነው?ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  6. የታተመዉ 5:535:53በደቡባዊ ጋዛ አየር ጥቃት የተገደሉት በርካቶቹ በእስራኤል ትዕዛዝ ከሰሜን የተፈናቀሉ ናቸውበአየር ጥቃቶቹ የተጎዱ ሰዎችReutersCopyright: Reutersእስራኤል በደቡባዊ ጋዛ በፈጸመችው የአየር ጥቃት የተገደሉት በርካቶች በእስራኤል አስገዳጅ ትዕዛዝ ከሰሜን የተፈናቀሉ ናቸው።እስራኤል 1.1 ሚሊዮን የሚሆኑ የደቡባዊ ጋዛ ነዋሪዎች ወደ ሰሜን እንዲሄዱ 24 ሰዓታት ሰጥታቸዋለች።የቢቢሲ ዘጋቢ በርካታ ተፈናቃዮችን እያስተናገደች ባለችው ኻን ዩኒስ ይገኛል። ቀያቸውን ለቀው ወደ ደቡባዊ ጋዛ ለተሰደዱ በርካቶች የሆነው ነገር አሳሳቢ ነው።እስራኤል በምሽቱ በፈጸመቻቸው ሶስት የአየር ጥቃቶች ከ100 በላይ ሰዎችን እንደገደለች የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል።አብዛኛዎቹም በእስራኤል ትዕዛዝ ከሰሜን የተፈናቀሉ ናቸው። በርካታ የተፈናቀሉ ፍልስጥኤማውያንን እቃቸውን ሸክፈው ወደ ቤታቸው ለመመለስ እንዳሰቡ በጋዛ ለሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ ተናግረዋል።ለባለፉት ቀናት ጎዳና ለማደር እንደተገደደ የሚናገረው አንድ ግለስብም በውሃ ጥም ከመሞት በክብር መሞትን እንደሚመርጥም ተናግሯል።ቀድሞም በከፍተኛ ህዝብ ተጨናንቃ በነበረችው ኻን ዩኒስ ሁኔታዎች በከፍተኛ ሁኔታ አሳሳቢ ሆኗል። በአሁኑ ወቅት ከሰሜን ጋዛ የተፈናቀሉ 600 ሺህ የሚገመቱ ተጨማሪ ፍልስጥኤማውያንን ማስተናገድ ይጠበቅባታል።እስራኤል ጋዛ ሰርጥን ሙሉ በሙሉ በመዝጋት ከበባ እንዲደረግ ያዘዘች ሲሆን፣ በጋዛ ‘ኤሌክትሪክ፣ ምግብ፣ ነዳጅ አይኖርም ሲሉም የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት ባለፈው ሳምንት ትዕዛዝ መስጠታቸው ይታወሳል።Article share tools
  7. የታተመዉ 4:364:36ኢራን ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ሰጠችየእስራኤል መድፍ በድንበር ላይReutersCopyright: Reutersእስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ እየፈጸመችው ያለውን ጥቃት ዝም ብላ እንደማትመለከት ኢራን አስታወቀች።እስራኤል በጋዛ ባሉ “ፍልስጥኤማውያንን ላይ እየፈጸመችው ያለችውን የጦር ወንጀሎች” ካላቆመች ኢራን የመከላከል እርምጃም እንደምትወስድም በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል አስታውቃለች።እስራኤል ለሐማስ ጥቃት ምላሽ ነው በሚል እየፈጸመችው ያለውን የአየር ጥቃት ተከትሎ በእስራኤል እና በሊባኖስ ድንበር ላይ ውጥረት ነግሷል።በኢራን የሚደገፈው ሄዝቦላህ በጦርነቱ ተሳታፊ ሊሆን ይችላል የሚልም ስጋት አጭሯል። አሜሪካ ኢራን ግጭቱን ከማባባስ እንድትቆጠብ ማስጠንቀቂያ የሰጠች ሲሆን እስራኤል በበኩሏ ሄዝቦላህ ተሳታፊ ከሆነ የከፋ ምላሽ እሰጣለሁ ብላለች።ባለፈው ሳምንት ሄዝቦላህ እና የእስራኤል ጦር በድንበር አካባቢ የተኩስ ልውውጥ ቢያደርጉም ከቁጥጥር ስር የወጣ አይደለም ተብሏል።የእስራኤል ጦር ትናንት ምሽት ከሄዝቦላህ ጋር የተገናኙ መሰረተ ልማቶችን ዒላማ ማድረጉን ገልጿል። በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ስለመድረሱ ምንም አይነት መረጃ የለም።Article share tools
  8. የታተመዉ 3:273:27በጋዛ- እስራኤል የተከሰቱ ዋና ዋና ጉዳዮችየጋዛ ህጻናትReutersCopyright: Reutersአስር ቀናት ባስቆጠረው የሐማስ እስራኤል ግጭት የተከሰቱ ዋና ዋና ጉዳዮችን እንቃኝ
    • የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ረቡዕ ወደ እስራኤል ያቀናሉ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን እንደተናገሩት ፕሬዚዳንቱ የሚያደርጉት ጉብኝት ለእስራኤል፣ ለአካባቢው እና ለመላው ዓለም ወሳኝ በሆነ ወቅት ላይ ነው።
    • የእስራኤልን ከሰሜናዊ ጋዛ ውጡ ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ቤታቸውን ለቀው የተፈናቀሉ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ስደተኞች አስቸኳይ ምግብ፣ ውሃ እና ነዳጅ እንደሚያስፈልጋቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስጠንቅቋል።
    • ሩሲያ ለተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ለጋዛ ሰብዓዊ መፍትሄ እንዲበጅ ያቀረበችው ረቂቅ አሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ ምዕራባውያን አገራት ሐማስን ማውገዝ ባለመቻሉ ውድቅ አድርገውታል።
    • አሜሪካ ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ጋዛ እንዲደርስ ለማድረግ ከእስራኤል ዋስትና እንዳገኘች የተናገሩት ብሊንከን መቼ እና እንዴት እንደሆነ ዝርዝር ጉዳዮችን አልሰጡም።
    • በግብጽ እና በጋዛ መካከል ያለው ራፋህ የተሰኘው የድንበር ማቋረጫንም ለማስከፈት የተጀመሩ ዲፕሎማሲያዊ ንግግሮች አሁንም ቀጥለዋል።
    • የአሜሪካ ከፍተኛ ጄነራል ሚካኤል ኩሪላ በይፋ ባይነገርም በአሁኑ ወቅት በእስራኤል ይገኛሉ። ጄነራሉ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ኃይሎችን እንዲሁም የጦሩ ማዕከላዊ እዝ መሪ ናቸው።
    • የእስራኤል አየር ኃይል በኢራን የሚደገፈውን የሊባኖሱን ሄዝቦላህ ታጣቂ ቡድንን ኢላማዎችን መምታቱን አስታውቋል።
    • ሐማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት በሰነዘረበት ወቅት ካገታቸው ሰዎች መካከል አንዷን የሚያሳይ ቪዲዮ ለቋል። የ21 ዓመቷ ግለሰብ ስሟ ማያ ሼም መሆኑንም በዕብራይስጥ ቋንቋ ስትናገር ይሰማል።
    • ባለፉት አስር ቀናት ውስጥ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ እስራኤላውያን እንደተፈናቀሉ ጦሩ አስታውቋል።
    Article share tools
  9. የታተመዉ 3:233:23ታዋቂው ካርቱኒስት ኔታንያሁን በጋዛ ላይ በሚያሳየው ካርቱን ምክንያት ከሥራው ተባረረስመ ጥሩ የጋርዲያን ጋዜጣ ካርቱኒስት ስቲቭ ቤል በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ዙሪያ በሳለው ካርቱን ምክንያት በተፈጠረ አለመግባባት ከሥራው ተባረረ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  10. የታተመዉ 1:211:21በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጋዛ-ግብፅ የድንበር ማቋረጫ በኩል ለመውጣት እየተጠባበቁ ነውበሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ራፋህ በተሰኘው የጋዛ-ግብፅ የድንበር ማቋረጫ በኩል ለመውጣት በተስፋ እየተጠባበቁ ነው።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  11. የታተመዉ 1:131:13ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ለእስራኤል ያላቸውን ጥልቅ አጋርነት በድጋሚ አረጋገጡውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን አገራቸው አሜሪካ ለእስራኤል ያላት አጋርነት ጥብቅና ጥልቅ እንደሆነ አረጋገጡ። ብሊንከን በጥቂት ቀናት ውስጥ ለ2ኛ ጊዜ ቴል አቪቭ ለጉብኝት ከገቡ በኋላ እንዳሉት ‘’እስራኤል ራሷን የመከላከል እርምጃዋን አሜሪካ በጥብቅ ትደግፋለች።’’ ሐማስ በእስራኤል ላይ መብረቃዊ ጥቃት ከፈጸመ ወዲህ ብሊንከን ወደ ቴል አቪቭ አቅንተው ቤንያሚን ናታኒያሁን ሲያገኙ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  12. የታተመዉ 0:360:36ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ‘ክፍቱ እስር ቤት’ በመባል የምትጠራው ጋዛ በትንሽ ቦታ ላይ በርካታ ሰዎች ከሚኖሩባቸው የዓለማችን ቦታዎች አንዷ ናት ናት። የሐማስን ጥቃት ተከትሎ በእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች ቀን ከሌት የምትደበደበው ጋዛ ነዋሪዎቿ በከባድ ችግር ውስጥ ይገኛሉ። ለመሆኑ ጋዛ ለነዋሪዎቿ ምን ትመስላለች? ለምን ይህች አነስተኛ የተጎሳቆለች ግዛት የዓለምን ቀልብ በድጋሚ ለመሳብ በቃች?ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  13. የታተመዉ 12:22 16 ጥቅምት 202312:22 16 ጥቅምት 2023ግጭቱ ወደ ሌሎች ግንባሮች እየተስፋፋ ነው ስትል ኢራን አስጠነቀቀችየእስራኤል ወታደሮች ከሊባኖስ ድንበር አቅራቢያEPACopyright: EPAየእስራኤል ታንኮች ከሊባኖስ ድንበር አቅራቢያImage caption: የእስራኤል ታንኮች ከሊባኖስ ድንበር አቅራቢያየኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴይን አሚራብዶላሃይም በሐማስ እና በእስራኤል መካከል የሚካሄደው ግጭት ወደ ሌሎች ግንባሮች እየተስፋፋ ነው ሲሉ አስጠነቀቁ።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ግጭቱ ወደ ሌሎች ግንባሮች በመስፋፋት “ለማስቆም ከማይቻልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው” ብለዋል።በኤክስ (ትዊተር) የማኅበራዊ ትስስር መድረክ ላይ በተሰራጨው መግለጫ ላይ ሚኒስትሩ ለተፈጠረው ችግር “ፖለቲካዊ መፍትሄ ለማግኘት የሚቻልበት ጊዜ እያለፈ ነው” በማለት እስራኤልን ጋዛ ውስጥ “ወንጀል እና ግድያ” እየፈጸመች ነው ሲሉ ከሰዋል።ጨምረውም “ከማሌዢያ፣ ከፓኪስታን እና ከቱኒዚያ አቻዎቼ ጋር ተወያይቻለሁ። በአስቸኳይ ጽዮናውያን ጋዛ ውስጥ የሚፈጽሟቸው ወንጀሎች እና ግድያዎች እንዲቆሙ እንዲሁም ሰብአቂ እርዳታ እንዲገባ አጽንኦት ሰጥተናል” በማለት አስፍረዋል።“ፖለቲካዊ መፍትሄ ለማግኘት ጊዜው እያበቃ መሆኑን አበክሬ ተናግሪያለሁ፣ ጦርነቱ ወደ ሌሎች ግንባሮች የመዛመቱ ዕድል ለማስቀረት ከማይቻልበት ደረጃ ላይ ደርሷል” ብለዋል የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር።ኢራን እስራኤል ቀዳሚ ባላንጣዎቼ ከምትላቸው አገራት መካከል ቀዳሚዋ ስትሆን፣ ሐማስን ጨምሮ በአካባቢው አሉ የሚባሉ ታጣቂ ቡድኖችን በማስታጠቅና በመደገፍ ትታወቃለች።Article share tools
  14. የታተመዉ 9:21 16 ጥቅምት 20239:21 16 ጥቅምት 2023ጋዛ ውስጥ ከ1,000 በላይ ሰዎች በፍርስራሾች ውስጥ ተቀብረዋል፡ ባለሥልጣናትፍልስጥኤማውያን በኻን ዩኑስ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ካለ ፍርስራሽ ሰዎችን ሲፈልጉEPACopyright: EPAፍልስጥኤማውያን በኻን ዩኑስ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ካለ ፍርስራሽ ሰዎችን ሲፈልጉImage caption: ፍልስጥኤማውያን በኻን ዩኑስ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ካለ ፍርስራሽ ሰዎችን ሲፈልጉእስራኤል በጋዛ ላይ ባለፉት ቀናት በፈጸመችው የአየር ድብደባ ምክንያት በፈራረሱ ሕንጻዎች እና ቤቶች ስር ተቀብረው ያልተገኙ ሰዎች ከአንድ ሺህ በላይ መሆናቸውን የፍልስጥኤም የአደጋ ጊዜ ነፍስ አድን ተቋም አስታወቀ።በጋዛ ውስጥ ያለው በሐማስ የሚመራው የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ አያድ አል-ቦዞም፣ ያልተገኙት ሰዎችን በተመለከተ የተጠቀሰው ቁጥሩ ትክክል እንደሆነ አረጋግጠዋል።ከአንድ ሳምንት በፊት ቅዳሜ መስከረም 26/2016 ዓ.ም. የተፈጸመውን የሐማስ ጥቃትን ተከትሎ እስራኤል በጋዛ ላይ እያካሄደች ባለው የአየር ድብደባ ምክንያት ቢያንስ 2,750 ፍልስጥኤማውያን ሲገደሉ፣ 9,700 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በተጨማሪም ሌላኛው የፍልስጥኤም ክፍል በሆነው ዌስት ባንክ ውስጥ አስካሁን 58 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ1,250 በላይ የሚሆኑት ደግሞ መጎዳታቸውን ሚኒስቴሩ አመልክቷል።Article share tools
  15. የታተመዉ 9:02 16 ጥቅምት 20239:02 16 ጥቅምት 2023የእስራኤል የአየር ድብደባ እና የሚያደርሰው ጉዳትእስራኤል በጋዛ ላይ የምትፈጽመውን የአየር ድብደባን ቀጥላለች። የአገሪቱ የመገናኛ ብዙኃን እንዳሉት ባለፉት 24 ሰዓታት ከ100 በላይ ወታደራዊ ናቸው የተባሉ የተለያዩ ኢላማዎች ላይ ድብደባ ተፈጽሟል።ከአንድ ሳምንት በላይ በዘለቀው ጥቃት በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ያሉ ሕንጻዎች፣ መሠረተ ልማቶች እና የመኖሪያ አካባቢዎች ላይ ከባድ ውድመት ደርሷል። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም ለሞት እና ለጉዳት ተዳርገዋል።ኻን ዩኒስ ውስጥ በእስራኤል የአየር ጥቃት ከወደመ ሕንጻ አቅራቢያ የተሰበሰቡ ሰዎችReutersCopyright: Reutersኻን ዩኒስ ውስጥ በእስራኤል የአየር ጥቃት ከወደመ ሕንጻ አቅራቢያ የተሰበሰቡ ሰዎችImage caption: ኻን ዩኒስ ውስጥ በእስራኤል የአየር ጥቃት ከወደመ ሕንጻ አቅራቢያ የተሰበሰቡ ሰዎችኻን ዩኒስ ውስጥ በእስራኤል የአየር ጥቃት ከወደመ ሕንጻ ፍርስራሽ ውስጥ የተጎዱ ሰዎችን ሲፈልጉReutersCopyright: Reutersኻን ዩኒስ ውስጥ በእስራኤል የአየር ጥቃት ከወደመ ሕንጻ ፍርስራሽ ውስጥ የተጎዱ ሰዎችን ሲፈልጉImage caption: ኻን ዩኒስ ውስጥ በእስራኤል የአየር ጥቃት ከወደመ ሕንጻ ፍርስራሽ ውስጥ የተጎዱ ሰዎችን ሲፈልጉጋዛ ውስጥ መሠረታዊ አቅርቦቶች እየተሟጠጡ በመሆናቸው ሰብአዊ ቀውስ ይከሰታል በማለት የእርዳታ ድርጅቶች እያስጠነቀቁ ነውReutersCopyright: Reutersጋዛ ውስጥ መሠረታዊ አቅርቦቶች እየተሟጠጡ በመሆናቸው ሰብአዊ ቀውስ ይከሰታል በማለት የእርዳታ ድርጅቶች እያስጠነቀቁ ነውImage caption: ጋዛ ውስጥ መሠረታዊ አቅርቦቶች እየተሟጠጡ በመሆናቸው ሰብአዊ ቀውስ ይከሰታል በማለት የእርዳታ ድርጅቶች እያስጠነቀቁ ነውArticle share tools
  16. የታተመዉ 6:25 16 ጥቅምት 20236:25 16 ጥቅምት 2023ብሊንከን ወደ እስራኤል ተመለሱየአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከንReutersCopyright: Reutersከአራት ቀናት በፊት እስራኤልን ጎብኝተው የነበሩት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን በዛሬው ዕለት ተመልሰው መጥተዋል።ብሊንከን በጋዛ ላይ ስላለው ግጭት ከእስራኤል አመራሮች ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩም ይጠበቃል።ብሊንከን አሜሪካ ለእስራኤል ያላትን ድጋፍ ለማሳየት ባለፈው ሳምንት ሐሙስ እለት ወደ ቴልአቪቭ አቅንተው የነበረ ሲሆን በመቀጠልም ወደ ስድስት የአረብ አገራት በማቅናት ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶችን አድርገዋል።ፕሬዚዳንት ባይደንም ከእስራኤል በቀረበላቸው ግብዣ መሰረት በሚቀጥሉት ቀናት አገሪቱን ይጎበኛሉ የሚል ግምት አለ።Article share tools
  17. የታተመዉ 6:23 16 ጥቅምት 20236:23 16 ጥቅምት 2023500 ኪሎ ሜትር የሚረዝሙት እና ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት የሐማስ ዋሻዎችእስራኤል በጋዛ ላይ ለመፈጸም እየተዘጋጀችበት ላለው የእግረኛ ጦር ወረራ ከመሬት በታች ያሉ ዋሻዎችን ማፈራረስ ዋነኛ ኢላማዋ አድርጋለች። ነገር ግን የዋሻዎቹ መግቢያዎች ጋዛ ውስጥ በሚገኙ የመኖሪያ ሕንጻዎች ውስጥ በመሆናቸው እና በቅርቡ ሐማስ ያገታቸውን ሰዎች በዋሻዎቹ ውስጥ ደብቋል ተብሎ ስለሚታመን ዘመቻው ውስብስብ ሊሆን ይችላል ተብሎ ተሰግቷል። ለመሆኑ ዋሻዎቹ ምን ይመስላሉ?ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  18. የታተመዉ 4:19 16 ጥቅምት 20234:19 16 ጥቅምት 2023የእስራኤል ጦር የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ አለመደረሱን ገለጸግብጽ እና ጋዛ ያለው የድንበር ማቋረጫReutersCopyright: Reutersየእስራኤል ጦር በደቡባዊ ጋዛ ምንም አይነት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ አለመደረሱን ገለጸ። በግብጽ እና ጋዛ ያለው የድንበር ማቋረጫ መከፈቱ ጋር በተያያዘ የተኩስ አቁም ስምምነት እንደሚኖር የግብጽ የደህንነት ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ሮይተርስ መዘገቡን ተከትሎም ነው ጦሩ ይህንን አስተያየት የሰጠው።”እኔ የማውቀው ምንም አይነት የተኩስ አቁም ስምምነት የለም። የሚወጡ ዘገባዎችን እያየሁ ነው። ምንም የማረጋግጠው ነገር የለም” ሲሉም የእስራኤል መከላከያ ኃይል ቃለ አቀባይ ኮሎኔል ሪቻርድ ሄክት ተናግረዋል።የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤትም እንዲሁም የተኩስ አቁም ስምምነት መደረሱን በተመለከተ የወጣውን ዘገባ ውድቅ አድርጓል።”በአሁኑ ወቅት ከጋዛ የውጭ አገር ዜጎችን በግብጽ ድንበር በኩል ለማስወጣት የተደረገ የተኩስ አቁም እንዲሁም የሰብዓዊ እርዳታ ስምምነት የለም” ሲልም የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጽህፈት ቤት በመግለጫው አትቷል።የሐማስ ሚዲያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በደቡባዊ ጋዛ ተደረሰ ስለተባለው የተኩስ አቁም ስምምነት ምንም ዓይነት መረጃ እንደሌላቸው መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።ሳላማ ማሩፍ በጋዛ እና ግብጽ መካከል ያለው የድንበር ማቋረጫን መከፈቱን በተመለከተ ከግብጽ በኩል ምንም ማረጋገጫ እንዳላገኙ ለዜና ወኪሉ ተናግረዋል።ሮይተርስ አሜሪካ፣ እስራኤል እና ግብጽ በደቡባዊ ጋዛ በኩል የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ሁለት የግብጽ የደህንነት ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘግቦ ነበር።ስምምነቱ የሚደረገው በጋዛ እና ግብጽ መካከል ያለው የራፋህ ድንበር ማቋረጫ መከፈት ጋር በተያያዘም እንደሆነ አስነብቧል።Article share tools
  19. የታተመዉ 3:23 16 ጥቅምት 20233:23 16 ጥቅምት 2023ለጋዛ የሚሆን እርዳታ በግብጽ ድንበር በኩል ሊገባ ይችላል ተባለበድንበር ያሉ ፍልስጥኤማውያንReutersCopyright: Reutersበጋዛ ሰርጥ እና ግብጽ መካከል ያለው የድንበር ማቋረጫ ለአጭር ጊዜ ሊከፈት እንደሚችል የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን እሁድ ዕለት ከግብጽ ባለስልጣናት ጋር ከተነጋገሩ በኋላ በግብጽ ቁጥጥር ስር ያለው ድንበር ወደ ጋዛ ዕርዳታ ለማድረስ እንደሚከፈት ተናግረዋል። ሆኖም መቼ እንደሚከፈት ዝርዝር መረጃ አልሰጡም።የእስራኤልን ሰሜናዊ ጋዛ ለቃችሁ ውጡ ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ ፍልስጥኤማውያን ወደ ደቡብ መሰደዳቸውን የመከላከያ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።ቢቢሲ ይህንን አኃዝ ማረጋገጥ አይችልም።በሙሉ ከበባ ውስጥ ባለችው ጋዛ ሁኔታዎች እየከፉ ነው። ውሃ፣ ምግብ፣ ኃይል እና መድኃኒቶች አቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ እየተመናመነ ነው።በጋዛ ሆስፒታሎች ያለው መጠባበቂያ ነዳጅ በ24 ሰዓታት ውስጥ ተሟጦ ሊያልቅ እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስጠንቅቆ በሺዎች የሚቆጠሩ ህሙማንንም ህይወት አደጋ ላይ እንደሚወድቅም አሳስቧል።Article share tools
  20. የታተመዉ 3:05 16 ጥቅምት 20233:05 16 ጥቅምት 2023ኻን ዩኒስ፡ ከድጡ ወደ ማጡ የሆነባት የጋዛ ከተማየሰው ማዕበል ወደ ጋዛዋ ኻን ዩኒስ ከተማ ጎርፏል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጥኤማውያን የእስራኤልን ውጡ ማስጠንቀቂያ ተከትለው መያዝ የሚችሉትን ሸክፈው ከሰሜናዊ ወደ ደቡባዊ ጋዛ ተሰደዋል። ነዳጅ ያገኙ በመኪና፤ ከተገኘ ደግሞ በፈረስ ጋሪ አማራጭ ያጡ ደግሞ በእግራቸው ኳትነዋል።ተጨማሪ ያንብቡ