
ከ 1 ሰአት በፊት
ኬንያ በቅርቡ በወደብ ከተማዋ ላሙ ከተፈጸሙ ጥቃቶች ጀርባ እጃቸው አሉበት ያለቻቸውን 35 የሽብር ተጠርጣሪዎች ማንነት እና ፎቶዎችን ይፋ አደረገች።
ከእነዚህ መካከል የኢትዮጵያ፣ የታንዛንያ፣ የጀርመን እና የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸው እንደሚገኙበት ታውቋል። አብዛኛዎቹ ግን የኬንያ ዜጎች ናቸው ተብሏል።
ስም ዝርዝራቸው ይፋ ከተደረጉት ተጠርጣሪዎች መካከል ጃንጋሌ ሁቴይባ ተባለ ኢትዮጵያዊ እንደሚገኝበት አገሪቱ መገናኛ ብዙኃን የኬንያ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቅሰው ዘግበዋል።
ተጠርጣሪዎቹ ፈንጂዎች በተለያዩ የአገሪቱ መንገዶች ላይ በማጥመድ እና በላሙ-ዊቱ-ጋርሰን ጎዳና ላይ ሠላማዊ ሰዎችን በመግደል መጠርጠራቸው ተነግሯል።
እአአ በ2020 ላሙ በሚገኘው የማንዳ ቤይ የአሜሪካ የጦር ሰፈር ላይ በደረሰው ጥቃት መጠርጠራቸውም ታውቋል።
- ‘የድመት ነፍስ አለው’ የሚባለው የሐማስ ወታደራዊ ኮማንደር ዴይፍ ማን ነው?ከ 5 ሰአት በፊት
- ‘ሃብታም ለመሆን’ ከመቃብር ስፍራ የራስ ቅል ያወጡ አምስት ናይጄሪያውያን በእስራት ተቀጡከ 4 ሰአት በፊት
- ቱርካዊት ሳይንቲስት የፈጠሩት ካንሰርን የሚመረምር ዘመናዊው ጡት መያዣከ 5 ሰአት በፊት
የኬንያ አገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ተጠርጣሪዎቹ “የታጣቁ እና አደገኛ” መሆናቸውን ገልጾ፤ “በላሙ ክልል እና ቦኒ አካባቢ ሕይወት የቀጠፉ ጥቃቶችን ያቀደው እና የመራው የአል-ሻባብ የሽብር ቡድን” አባል ናቸው ብሏል።
ሚኒስትሩ ኪቱሬ ኪንዲኪ “ተጥጣሪዎቹ በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ እጃቸውን እንዲሰጡ እንጠይቃለን። እጃቸውን ካልሰጡ፤ ፈልገን በማግኘት የሚገባቸውን እንሰጣቸዋለን” ማለታቸውን ሲቲዝን የተባለው የአገሪቱ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
ተጠርጣሪዎቹ ያሉበትን ቦታ በተመለከተ መረጃ ላለው ሰው መጠኑ ያልተገለጸ ነገር ግን ትልቅ ሽልማት እንደሚሰጥም ጨምሮ ገልጿል።
በኬንያ ውስጥ ባለፉት ወራት በተፈጸሙ የሽብር ጥቃቶች በርካታ ሰላማዊ ሰዎች እና የፀጥታ ሠራተኞች ተገድለዋል።
የኬንያ መንግሥት እንዳለው ጥቃት ፈጻሚዎችን እና በድርጊቱ የተሳተፉ ሰዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል የሚገባቸውን ቅጣት እንዲያገኙ አስፈላጊውን ነገር ሁሉ ያደርጋል ብለዋል ሚኒስትሩ።
አልሸባብ ከቅርብ ወራት ወዲህ በኬንያ ሰሜን ምሥራቅ እና የባሕር ዳርቻ አካባቢዎች ጥቃቶችን አጠናክሯል።
ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያለው ታጣቂ ቡድኑ በሶማሊያ ከፍተኛ ወታደራዊ ጥቃት እየተካሄደበት ይገኛል።
