ቀጥታ
በጋዛ ሆስፒታል ላይ በተፈጸመ ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሳይገደሉ አልቀረም ተባለ
Related Video and Audio

VIDEO 7 MINUTES 59 SECONDSVIDEO 7 MINUTES 59 SECONDS7:59
Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBCከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ
- BBC
Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBC

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48
Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች
- BBC
Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 23 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 23 SECONDS1:23
Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBCሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ?
- BBC
Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBC

VIDEO 1 MINUTE 33 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 33 SECONDS1:33
Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBCበእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች
- BBC
Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBC
ጭምቅ ሃሳብ
- በጋዛ ሆስፒታል ላይ በተፈጸመ ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሳይገደሉ አልቀረም ተባለ
- ጥቃት በደረሰበት ሆስፒታል ውስጥ ያለው ‘አስጨናቂው’ ሁኔታ
- ባይደን ከአረብ መሪዎች ጋር ሊያደርጉት የነበረው ስብሰባ ተሰረዘ
- እስራኤል በጋዛ ላይ የምትፈጽመው የአየር ጥቃት ዛሬም ቀጥሏል
- ተቃውሞ ሊባኖስ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ
- ‘የድመት ነፍስ አለው’ የሚባለው የሐማስ ወታደራዊ ኮማንደር ዴይፍ ማን ነው?
- “ቤታችንን በላያችን ላይ ቢያፈርሱትም የትውልድ ቀያችንን አንለቅም” የጋዛ ቤተሰቦች
ቀጥታ ዘገባ
- የታተመዉ 5:225:22የጋዛ ሆስፒታል ጥቃት “በሌላኛው ቡድን የተደረገ ይመስላል” – ባይደን
ReutersCopyright: Reutersበመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለውበታል የተባለው በጋዛ በሚገኝ ሆስፒታል ላይ የደረሰወ ፍንዳታ “በሌላኛው ቡድን የተደረገ ይመስላል” ሲሉ ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ።ፕሬዝዳንት ባይደን ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ጋር ለመወያየት ዛሬ ረቡዕ ረፋድ አምስት ሰዓት ገደማ ቴል አቪቭ ገብተዋል።ባይደን በክስተቱ “በጣም አዝኛለሁ፣ ተቆጥቻለሁ” ብለዋል።“ባየሁት ነገር ላይ በመመሥረት ጥቃቱ በእናንተ ሳይሆን በሌላ ቡድን የተደረገ ይመስላል። ነገር ግን እርግጠኛ ያልሆኑ ብዙ ሰዎች በመኖራቸው ብዙ ነገሮችን ማለፍ አለብን” ሲሉ አክለዋል።ቢቢሲ በትናንት ምሽቱን የሆስፒታል ፍንዳታ ዙሪያ አንድ ዘገባ ለመሥራት መረጃዎችን በማጠናቀር ላይ ይገኛል። ሐማስ እና የፍልስጤም ባለሥልጣናት ለጥቃቱ የእስራኤልን የአየር ጥቃትን ተጠያቂ አድርገዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ

- የታተመዉ 4:194:19የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባልተለመደ ሁኔታ ጉብኝት ለማድረግ እስራኤል ገቡ
ReutersCopyright: Reutersጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ እና ፕሬዝዳንት ባይደንImage caption: ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ እና ፕሬዝዳንት ባይደንየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ጋር ለመወያየት ዛሬ ረቡዕ ረፋድ አምስት ሰዓት አካባቢ እስራኤል ገብተዋል።በእራኤል እና በጋዛ መካከል ግጭት ከተቀሰቀሰ ከሳምንት በኋላ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የተጓዙት ፕሬዝዳንት ባይደን፣ ባለፈው ሳምንት የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊያቸውን ወደ አካባቢ ልከው ነበር።ግጭቱ እየተባባሰ እና የዓለም አገራትን ትኩረት መሳቡን ተከትሎ ባይደን እንደ አሜሪካ ፕሬዝዳንት አሁን ወደ ግጭት አካባቢ ያደረጉት ጉዞ ያልተለመደ ነው እየተባለ ነው።የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ግጭቶች ወደ ሚካሄዱባቸው አካባቢዎች በአጭር ጊዜ ማስታወቂያ እምብዛም ጉብኝት ማድረጋቸው የተለመደ አይደለም።ፕሬዝዳንት ባይደን ከጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ የፍልስጥኤሙ መሪ ማህሙድ አባስን ጨምሮ ከዮርዳኖሱ ንጉሥ እና ከግብፅ ፕሬዝዳንት ጋር አማን ዮርዳኖስ ላይ የመወያየት ዕቅድ ነበራቸው።ነገር ግን ማክሰኞ ምሽት ጋዛ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ላይ የደረሰውን ፍንዳታ ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ከአረብ አገራት መሪዎቹ ጋር ያላቸው ስብሰባ ተሰርዟል።
BBCCopyright: BBCየፕሬዝዳንት ባይደን አውሮፕላን ኤር ፎርስ ዋንImage caption: የፕሬዝዳንት ባይደን አውሮፕላን ኤር ፎርስ ዋንArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:023:02ባይደን ከአረብ መሪዎች ጋር ሊያደርጉት የነበረው ስብሰባ ተሰረዘ
EPACopyright: EPAበእሰራኤል ዛሬ (ረቡዕ) ጉብኝት የሚያደርጉት ፕሬዝዳንት ባይደን ከዋሽንግተን ሲነሱImage caption: በእሰራኤል ዛሬ (ረቡዕ) ጉብኝት የሚያደርጉት ፕሬዝዳንት ባይደን ከዋሽንግተን ሲነሱጋዛ ውስጥ ባለው ሆስፒታል ላይ በደረሰው ፍንዳታ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከአረብ አገራት መሪዎች ጋር የነበራቸው ስብሰባ ተሰረዘ።ባይደን ዛሬ በእስራኤል በሚያደርጉት ጉብኝት ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ጋር ከተወያዩ በኋላ፣ የዮርዳኖሱን ንጉሥ አብዱላህን፣ የግብፁን ፕሬዝዳንት አብደል ፋትህ አል ሲሲን እና የፍልስጥኤም አስተዳደር ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስን በማግኘት ይወያያሉ ተብሎ ነበር።ነገር ግን ማክሰኞ ምሽት በጋዛ ሆስፒታል ላይ ፍንዳታ ከደረሰ በኋላ የዮርዳኖስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትቴር ለጥቃቱ እስራኤልን ተጠያቂ በማድረግ ከባይደን ጋር የሚደረገው ውይይት “በፍልስጥኤማውያን ላይ የሚካሄደው ጦርነት እና ጭፍጨፋ” ሲቆም ብቻ የሚካሄድ ይሆናል ብሏል።የእስራኤል ጦር ኃይል ግን ፍንዳታው የደረሰው በጋዛ ውስጥ ሐማስን ተከትሎ ዋነኛው ቡድን የሆነው የፍልስጥኤም እስላማዊ ጂሃድ በተባለው አማካይነት መሆኑን ገልጿል።ወደ እስራኤል እየተጓዙ ያሉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት በኤክስ (ትዊተር) ላይ “በፍንዳታው መቆጣታቸውን እና በጥልቅ ማዘናቸውን” አስፍረው፣ የብሔራዊ ደኅንነት ቡድናቸው “በትክክል ምን እንደተከሰተ ለማወቅ የሚያስፈልጉ መረጃዎችን መሰብሰብ እንዲቀጥሉ” ማዘዛቸውን ገልጸዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:462:46በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተገደሉበት ሆስፒታል በምስልማክሰኞ ማታ ጋዛ ውስጥ በሚገኘው አል አህሊ በተባለው ሆስፒታል ላይ በተደሰ ፍንዳታ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጥኤማውያን ሳይገደሉ እንዳልቀረ ተሰግቷል።ሐማስ ለአደጋው የእስራኤል የአየር ጥቃት ምክንያት ነው ያለ ሲሆን፣ እስራኤል ግን ፍንዳተው የተከሰተው ሌላኛው የፍልስጥኤም ቡድን ኢስላሚክ ጂሃድ በስህት በተኮሰው ሮኬት የደረሰ ነው ስትል እጇ እንደሌለበት ገልጻለች።በሆስፒታሉ ላይ የደረሰው ከባድ ፍንዳታ ያስከተለውን ጉዳት በጥቂቱ የሚያሳዩ ፎቶግራፎች እነሆ፡
EPACopyright: EPA
EPACopyright: EPA
EPACopyright: EPA
EPACopyright: EPAArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:372:37እስራኤል በጋዛ ላይ የምትፈጽመው የአየር ጥቃት ዛሬም ቀጥሏል
EPACopyright: EPAእስራኤል በሰሜናዊ ጋዛ ዛሬ ጠዋት በፈጸመችው የአየር ጥቃት የተነሳ ጪስImage caption: እስራኤል በሰሜናዊ ጋዛ ዛሬ ጠዋት በፈጸመችው የአየር ጥቃት የተነሳ ጪስጋዛ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ላይ ማከሰኞ ምሽት የተፈጸመውን ጥቃት እንዳላደረሰች የገለጸችው እስራኤል ረቡዕ ጠዋት በተለያዩ ዒላማዎች ላይ የአየር ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች።በሆስፒታሉ ላይ በተፈጸመው ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸው የተዘገበ ሲሆን፤ ሐማስ እስራኤልን፣ አስራኤል ደግሞ የፍልስጥኤም እስላማዊ ጂሃድ የተባለውን ቡድን ለጥቃቱ ተጠያቂ እያደረጉ ነው።የእስራኤል አየር ኃይል ዛሬ ጠዋት በተለያዩ የጋዛ ሰርጥ አካባቢዎች ባሉ ወታደራዊ ያላቸውን ዒላማዎች የመታ መሆኑን ገልጾ፣ በዚህም የፍልስጥኤም ታጣቂ ቡድን ሁለት አባላትን “መደምሰሷን” አሳውቃለች።የእስራኤል ሠራዊት በኤክስ (ትዊተር) ገጹ ላይ ገደልኩ ያላቸውን ሁለት ሰዎችን ስም እና ሚናቸውን ይፋ አድርጓል። አንደኛው ሙሐመድ አልዋዲ የተባለ እና በጋዛ ውስጥ የሐማስ ፀረ ታንክ ቡድን መሪ ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ አክራም ሂጃዝ የሚባል የጦር መሳሪያ ነጋዴ ነው ብሏል።የእስራኤል አየር ኃይል ባለፉት ቀናት በካሄዳቸው የአየር ጥቃቶች የሐማስ ጽህፈት ቤቶችን፣ የሮኬት እና ፀረ ታንክ መሳሪያዎች ማስወንጨፊያዎችን እና ሌሎች የቡድኑ ተቋማትን በዋናነት ዒላማ ማድረጉን አመልክቷል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:302:30‘የድመት ነፍስ አለው’ የሚባለው የሐማስ ወታደራዊ ኮማንደር ዴይፍ ማን ነው?ዴይፍ የድመት ነፍስ ነው ያለው የሚባለው ለምንድነው ካልን መልሱ ማንም የሚገምተው ነው። እስራኤል ገደልኩት ስትል እየተነሳ፣ ሞተ ሲባል እያንሰራራ ስላስቸገረ ነው። ኮማንደር ዴይፍ ላይ እስራኤል ተደጋጋሚ እና ተከታታይ የግድያ ሙከራ ብታደርግበትም አልተሳካላትም። አራት ጊዜ ገደልኩት ብላ አራት ጊዜም ቆስሎ አምልጧል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:091:09ጥቃት በደረሰበት ሆስፒታል ውስጥ ያለው ‘አስጨናቂው’ ሁኔታ
ReutersCopyright: Reutersመሬት ላይ እንዲቀመጡ የተደረጉ ሰዎችን የሚያክም ዶክተርImage caption: መሬት ላይ እንዲቀመጡ የተደረጉ ሰዎችን የሚያክም ዶክተርማክሰኞ አመሻሽ ላይ በተፈጸመበት ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸው በተነገረለት የጋዛው አል አህሊ ሆስፒታል ውስጥ ያለው ሁኔታ “ወደር የሌለው እና ለመገልጽ አስቸጋሪ” መሆኑን በጋዛ ያለው የፍልስጥኤም ጤና ሚኒስቴር ገለጸ።“ዶክተሮች መሬት ላይ እና በመተላለፊያ ኮሪደሮች ላይ ቀዶ ሕክምና እያደረጉ ነው፣ አንዳንዶቹ ታካሚዎችም ካለማደንዘዣ ነው ቀዶ ሕክምና የሚደረግላቸው” በማለት የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ዶክተር አሽራፍ አል-ቁድራ በፌስቡክረ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።“በርካታ ሰዎች ቀዶ ሕክምና ለማግኘት እየተጠባበቁ ሲሆን፣ በጽኑ ሕሙማን ክፍል ያሉትን ሰዎች ሕይወትን ለማትረፍ የሕክምና ባለሙያዎች ጥረት እያደረጉ ነው።”ቃል አቀባዩ ጨምረውም ከጥቃቱ ሰለባዎች አብዛኞቹ “የወደፊት ተስፋቸውን የተነጠቁ” ሕጻናት ናቸው በማለት፣ አብዛኞቹ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችን ለማከም በሆስፒታሉ “ካሉት ሐኪሞች አቅም በላይ ነው” ብለዋል።በሆስፒታሉ ላይ ማን እንደፈጸመው አስካሁን ባልታወቀው የፍንዳታ ጥቃት አምስት መቶ የሚደርሱ ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል።ሐማስ ለጥቃቱ እስራኤልን ተጠያቂ ሲያደርግ፣ የእስራኤል መንግሥት ደግሞ ሌላኛውን የፍልስጥኤም ቡድን ኢስላሚክ ጂሃድን ጥቃቱን ፈጽሟል ብሎ እየከሰሰ ነው።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:240:24ተቃውሞ ሊባኖስ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ
ReutersCopyright: Reutersጋዛ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ላይ በተፈጸመ ጥቃት የተቆጡ ተቃዋሚዎች ሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ውስጥ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ውጪ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ።ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተቃዋሚዎች በኤምባሲው ዙሪያ እሳት በማንደድ እና የፍልስጥኤም ሰንደቅ አላማን በኤምባሲው አጥር ላይ በመስቀል ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።ሮይትርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው ፖሊስ ተቃዋሚዎቹን ለመበተን አስለቃሽ ጋዝ ተኩሷል።በተመሳሳይ እዚያው ቤይሩት ውስጥ በሚገኘው የፈረንሳይ ኤምባሲ ላይ ተቃውሞ ለማሰማት ትንሽ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ተሰብስበው የነበረ ሲሆን፣ በሕንጻው ላይ ድንጋይ መወርወራቸው ተዘግቧል።ሐማስ እና የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላህ ጋዛ ውስጥ በሚገኘው አል አህሊ ሆስፒታል ላይ ለተፈጸመው ጥቃት እስራኤልን እና አሜሪካንን ተያየቂ አድርገዋል፤ እሰራኤል ግን ለጥቃቱ እስላማዊ ጂሃድ የተባለውን የፍልስጥኤም ቡድንን ከሳለች።ሄዝቦላህ ጥቃቱን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ “ታይቶ የማይታወቅ ሕዝባዊ ቁጣ የሚገለጽበት” በማለት ለረቡዕ የተቃውሞ ሰልፍ ጠርቷል።በተጨማሪም ጋዛ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ላይ በተፈጸመ ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ በተለያዩ ስፍራዎች ተቃውሞዎች እየተቀሰቀሱ ነው።
- ዌስት ባንክ ውስጥ የሚገኙ ፍልስጥኤማውያን ማክሰኞ ምሽት በበርካታ ከተሞች ውስጥ ወደ አደባባይ በመውጣት ድንጋይ እየወረወሩ በፍልስጥኤም አስተዳደር ፕሬዝዳንት ላይ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል። የፀጥታ ኃይሎችም ሰልፈኞቹን ለመበተን አስለቃሽ ጋዝ ተኩሰዋል።
- በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ገድሞ በዋና ከተማ ትሪፖሊ እና በሌሎች የሊቢያ ከተሞች ውስጥ የፍልስጥኤም ሰንደቅ ዓላማን በመያዝ የጋዛ ነዋሪዎችን የሚደግፉ መፈክሮችን እያሰሙ አደባባይ ወጥተዋል።
- ተቃዋሚዎች ኢራን ዋና ከተማቴህራን ውስጥ ከሚገኙ የብሪታኒያ እና የፈረንሳይ ኤምባሲዎች ውጪ የተሰበሰቡ ሲሆን፣ በቱርክ እና በዮርዳኖስ ከሚገኙት የእስራኤል ኤምባሲዎች ደጃፍ ሰዎች ለተቃውሞ መሰብሰባቸው ተዘግቧል።
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesተቃዋሚ ሰልፈኞች በትሪፖሊImage caption: ተቃዋሚ ሰልፈኞች በትሪፖሊArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 0:030:03በጋዛ ሆስፒታል ላይ በተፈጸመ ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሳይገደሉ አልቀረም ተባለ
EPACopyright: EPAጋዛ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ላይ በተፈጸመ ጥቃት በደረሰ ፍንዳታ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጥኤማውያን ሳይገደሉ እንዳልቀሩ ተነገረ።ለጥቃቱ ሐማስ የእስራኤል የአየር ጥቃት ምክንያት ነው ሲል፣ እስራኤል ደግሞ የፍልስጥኤም እስላማዊ ጂሃድ የተባለው ቡድን የተኮሰው ሮኬት ኢላማውን ስቶ ሆስፒታሉ ላይ በመውደቁ ነው ብላለች።ነገር ግን እስራኤልም ሆነች ጋዛ ውስጥ ከሐማስ ከቀጥሎ ሁለተኛው ትልቅ ቡድን የሆነው እስላማዊ ጂሃድ ለጥቃቱ ተጠያቂ አለመሆናቸውን አስተባብለዋል።በሐማስ በምትተዳደረው ጋዛ ውስጥ ያሉ ባለሥልጣናት እንዳሉት ሆስፒታሉ ላይ በደረሰው የፍንዳታ ጥቃት 500 የሚሆኑ ሰዎች ተገድለዋል።ሐማስ ድርጊቱን በእስራኤል የተፈጸመ “የጦር ወንጅል” ያለው ሲሆን፣ የተለያዩ አገራት መሪዎች በሆስፒታሉ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በማውገዝ ለጠፋው ሕይወት ሐዘናቸውን ገልጸዋል።የዮርዳኖስ፣ የግብፅ እና የፍልስጥኤም መሪዎች ዛሬ ረቡዕ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር ሊያደርጉት የነበረው ስብሰባም ተሰርዟል።ጆ ባይደን ለእስራኤል አጋርነታቸውን ለማሳየት እና ግጭቱ እንዲያበቃ ለማገዝ ዛሬ በእስራኤል ጉብኝት በማድረግ ከአገሪቱ መሪዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።ሐማስ እና የሌባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላህ በሆስፒታሉ ላይ ለተፈጸመው የፍንዳታ ጥቃት አሜሪካ ከአስራኤል ጋር የጥፋቱ ተጋሪ ናት ሲሉ ከሰዋል።ሌሊቱን ቤይሩት ውስጥ ከአሜሪካ ኤምባሲ ውጪ በርካታ ሕዝብ የተሳተፈበት የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 11:54 17 ጥቅምት 202311:54 17 ጥቅምት 2023እስካሁን ጋዛ ውስጥ 3,000 ሰዎች ሲገደሉ ከ12,000 በላይ ተጎድተዋል
EPACopyright: EPAጋዛImage caption: ጋዛየፍልስጥኤም ጤና ሚኒስቴር አዲስ ያወጣው መረጃ ባለፉት ዘጠኝ ቀናት 3,000 የሚደርሱ ሰዎች ጋዛ ሰርጥ ውስጥ በተፈጸሙ የአየር ጥቃቶች ምክንያት መገደላቸውን አመለከተ።መስከረም 26/2016 ዓ.ም. ሐማስ ድንበር ተሻግሮ በእስራኤል ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ፣ በጋዛ ላይ የእስራኤል አየር ኃይል ያለማቋረጥ በፈጸመው የአየር ድብደባ ነው ሰዎቹ የተገደሉት።ከተገደሉት ፍልስጥኤማውያን በተጨማሪ 12,500 የሚሆኑት ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል።በሌላ በኩል ደግሞ ከጋዛ በስተምሥራቅ ተነጥሎ በሚገኘው የፍልስጥኤም ግዛት ዌስት ባንክ ውስጥ 61 ፍልስጥኤማውያን የተገደሉ ሲሆን፣ ከ1,250 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል።በጋዛ ላይ የእስራኤል ጦር ኃይል ሙሉ ከበባ በመጣሉ የመሠረታዊ አቅርቦቶች ችግር የተፈጠረ ሲሆን፤ የውሃ፣ የኤሌክትሪክ እና የነዳጅ አቅርቦት በመቋረጡ በነዋሪው ላይ የበለጠ ችግር ይፈጠራል ተብሎ ተሰግቷል።የፍልስጥኤም የጤና ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እንዳሉት፣ ጋዛ ውስጥ ኤሌክትሪክ በመቋረጡ እና የነዳጅ እጥረት በመፈጠሩ ሆስፒታሎች “ሥራቸውን ወደማቆም ተቃርበዋል።”Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 10:19 17 ጥቅምት 202310:19 17 ጥቅምት 2023የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሐማስ መሪ ጋር ተወያዩ
AFP/REUTERSCopyright: AFP/REUTERSየሐማሱ መሪ ኢስማኤል ሃኒያህ እና የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶርImage caption: የሐማሱ መሪ ኢስማኤል ሃኒያህ እና የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶርየደቡብ አፍሪካዋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሐማስ መሪ ጋር “ወደ ፍልስጥኤም ግዛቶች ሰብአዊ እርዳታ በሚቀርብበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን” ጽህፈት ቤታቸው አስታወቀ።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ናሌዲ ፓንዶር የደቡብ አፍሪካ መንግሥትን በመወከል ከሐማሱ መሪ ኢስማኤል ሃኒያህ ጋር መወያየታቸውን ዛሬ ማክሰኞ አረጋግጠዋል።ነገር ግን ውይይቱ የተደረገው በደቡብ አፍሪካ መንግሥት ጥያቄ ሳይሆን በሐማስ ፍላጎት መሆኑም ተነግሯል።በስልክ በተደረገው ውይይት ወቅት “ሚኒስትር ፓንዶር ደቡብ አፍሪካ ለፍልስጥኤም ሕዝብ ያላትን ድጋፍ በመግለጽ፣ በፍልስጥኤም እና በእስራኤል ሰላማዊ ዜጎች ላይ በደረሰው የሕይወት መጥፋት ማዘናቸውን ተናግረዋል” ብሏል የወጣው መግለጫ።በተጨማሪም “ሚኒስትሯ እና የሐማሱ መሪ አስፈላጊ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ወደ ጋዛ እና ወደ ሌሎች የፍልስጥኤም ግዛቶች እንዴት ሊደረስ እንደሚችል” መወያየታቸው ተገልጿል።ከሳምንት በፊት ሐማስ በእስራኤል ላይ ከባድ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የእስራኤል ሠራዊት በጋዛ ላይ ከበባ በመጣሉ ሐማስ በሚያስተዳድራት በጋዛ ውስጥ የመሠረታዊ አቅርቦት ቀውስ ተፈጥሯል።የሚኒስትሯ ጽህፈት ቤት በአንድ የአገሪቱ የመገናኛ ብዙኃን ሐማስ በእስራኤል ላይ ለፈጸመውን ጥቃት ሚኒስትሯ ድጋፋቸውን ገልጸዋል መባሉን አስተባብሏል።በሐማስ እና በእስራኤል መካከል ግጭቱ ከተጀመረ በኋላ ከታጣቂ ቡድኑ ጋር መወያየታቸውን በይፋ ከተናገሩ ጥቂት አገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ አንዷ ናት።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:44 17 ጥቅምት 20238:44 17 ጥቅምት 2023ጋዛ ውስጥ ያሉ 11 ሺህ ቁስለኞችን ለመርዳት እንድገባ ይፈቀድልኝ፡ የዓለም ጤና ድርጅት
ReutersCopyright: Reutersራፋህ ውስጥ በእስራኤል ጥቃት ጉዳት የደረሰበትን ሰው የተሸከሙ ሰዎችImage caption: ራፋህ ውስጥ በእስራኤል ጥቃት ጉዳት የደረሰበትን ሰው የተሸከሙ ሰዎችየዓለም ጤና ድርጅት አስራ አንድ ሺህ ሰዎች የመቁሰል ጉዳት ወደደረሰባቸው ጋዛ እርዳታ እና የሕክምና አቅርቦት ለማድረስ አስቸኳይ ፈቃድ እንዲሰጠው ጠየቀ።ድርጅቱ ጨምሮም ጋዛ ውስጥ አሁን ያለው ሁኔታ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ሰብአዊ ቀውስጥ ሊከሰት ይችላል በማለት አስጠንቅቋል።የሐማስን ጥቃት ተከትሎ እስራኤል በጋዛ ላይ የአጸፋ የአየር ድብደባ መፈጸም ከጀመረች ሳምንት ያለፋት ሲሆን፣ ወደ ሦስት ሺህ የሚጠጉ ፍልስጥኤማውያን አስካሁን ተገድለዋል።የዓለም ጤና ድርጅትን ጠቅሶ ሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገባው ጋዛ ውስጥ ከተገደሉት 2,800 ሰዎች መካከል ግማሽ የሚሆኑት ሴቶች እና ሕጻናት ናቸው። በተጨማሪም አስካሁን 11,000 ሺህ ሰዎች በጥቃቱ የመቁሰል ጉዳት ደርሶባቸዋል።ድርጅቱ ምንም አይነት ነገር ለማስገባት እና ለማስወጣት ወደማይቻልባት ጋዛ አስፈላጊው የሕክምና እና የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ለማድረስ የሚያስችል በር በአስቸኳይ እንዲከፈት ለማስቻል “ከውሳኔ ሰጪ አካላት” ጋር እየተነጋገረ መሆኑን ገልጿል።ባለሥልጣናት ጨምረውም በጋዛ ውስጥ ባሉ በ115 የጤና አገልግሎት ተቋማት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፣ አብዛኞቹ የጋዛ ሆስፒታሎች የውሃ እና የኤሌክትሪክ አቅርቦት ችግር ስላለባቸው ሥራቸውን እያከናወኑ አይደለም።የውሃ እና የንጽህን አቅርቦቶች በመቋረጣቸው “የተቅማጥ እና የውሃ ወለድ በሽታዎች ስጋት ከፍተኛ ነው” የመንግሥታቱ ድርጅት የፍልስጥኤም ስደተኞች ተቋም “ካለውሃ ሰዎች መሞት ይጀምራሉ” በማለት ስጋቱን ገልጿል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:23 17 ጥቅምት 20238:23 17 ጥቅምት 2023የተባበሩት መንግሥታት ጋዛ ውስጥ የጦር ወንጀል ሊፈጸም ይችላል ሲል አስጠነቀቀ
ReutersCopyright: Reutersየእስራኤልን ጥቃት በመፍራት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጥኤማውያን ከሰሜን ጋዛ እየወጡ ነውImage caption: የእስራኤልን ጥቃት በመፍራት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጥኤማውያን ከሰሜን ጋዛ እየወጡ ነውየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የእርዳታ ድርጅቶች ወደ ጋዛ መግባት እንዲፈቀድላቸው በድጋሚ በመጠየቅ፣ ጋዛ ውስጥ የጦር ወንጀሎች ሊፈጸሙ ይችላል ሲል አስጠነቀቀ።የድርጅቱ የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ራቪና ሳምዳሳኒ እንዳሉት፣ የእስራኤል ሠራዊት በሰሜን ጋዛ ያሉ ፍልስጥኤማውያን ወደ ደቡብ እንዲወጡ ማዘዙ “ዓለም አቀፍ ሕግን በመጣስ ሲቪሎችን በኃይል ከመኖሪያቸው ማስወጣት ነው” በማለት ሁኔታው የተባበሩት መንግሥታት “እንዳሳሰበው” ገልጸዋል።አንድ አገር በግጭት ወቅት የጦር ወንጀል ፈጽሟል ተብሎ ከታመነ ጉዳዩ በዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ሊታይ ይችላል። ፍልስጥኤም የፍርድ ቤቱ አባል ስትሆን እስራኤል ግን አይደለችም።ቃል አቀባይዋ በሰጡት መግለጫ ከሰሜናዊ ጋዛ ለመውጣት በሚሞክሩ ሲቪል ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች በገለልተኛ ወገን መመርመር አለባቸውም ብለዋል።በተጨማሪም ቁጥራቸው ወደ 199 የደረሰው በሐማስ የታገቱ እስራኤላውያን “ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ” እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 6:41 17 ጥቅምት 20236:41 17 ጥቅምት 2023የራፋህ የድንበር ማቋረጫ ምንድን ነው? እንዴትስ የጋዛ ነዋሪዎች ተስፋ ለመሆን በቃ?ከሚጠበቀው የእስራኤል የእግረኛ ጦር ዘመቻ በፊት ፍልስጥኤማውያን ከአካባቢው ለመልቀቅ በማሰብ ከደቡባዊ የጋዛ ሰርጥ ወደ ግብፅ በሚያሻግረው የራፋህ የድንበር ማቋረጫ ላይ እየተሰባሰቡ ነው። የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን በዚህ ጊዜ ባይሉም የድንበር ማቋረጫው ጥምር ዜግነት ያላቸውን ለማስወጣት እና ሰብዓዊ እርዳታ ለማስገባት እንደሚከፍት ዘግበዋል። ሆኖም ድንበር ማቋረጫው እስካሁን ድረስ እንደተዘጋ ነው። የራፋህ የድንበር ማቋረጫ ምንድን ነው?ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 5:53 17 ጥቅምት 20235:53 17 ጥቅምት 2023በደቡባዊ ጋዛ አየር ጥቃት የተገደሉት በርካቶቹ በእስራኤል ትዕዛዝ ከሰሜን የተፈናቀሉ ናቸው
ReutersCopyright: Reutersእስራኤል በደቡባዊ ጋዛ በፈጸመችው የአየር ጥቃት የተገደሉት በርካቶች በእስራኤል አስገዳጅ ትዕዛዝ ከሰሜን የተፈናቀሉ ናቸው።እስራኤል 1.1 ሚሊዮን የሚሆኑ የደቡባዊ ጋዛ ነዋሪዎች ወደ ሰሜን እንዲሄዱ 24 ሰዓታት ሰጥታቸዋለች።የቢቢሲ ዘጋቢ በርካታ ተፈናቃዮችን እያስተናገደች ባለችው ኻን ዩኒስ ይገኛል። ቀያቸውን ለቀው ወደ ደቡባዊ ጋዛ ለተሰደዱ በርካቶች የሆነው ነገር አሳሳቢ ነው።እስራኤል በምሽቱ በፈጸመቻቸው ሶስት የአየር ጥቃቶች ከ100 በላይ ሰዎችን እንደገደለች የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል።አብዛኛዎቹም በእስራኤል ትዕዛዝ ከሰሜን የተፈናቀሉ ናቸው። በርካታ የተፈናቀሉ ፍልስጥኤማውያንን እቃቸውን ሸክፈው ወደ ቤታቸው ለመመለስ እንዳሰቡ በጋዛ ለሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ ተናግረዋል።ለባለፉት ቀናት ጎዳና ለማደር እንደተገደደ የሚናገረው አንድ ግለስብም በውሃ ጥም ከመሞት በክብር መሞትን እንደሚመርጥም ተናግሯል።ቀድሞም በከፍተኛ ህዝብ ተጨናንቃ በነበረችው ኻን ዩኒስ ሁኔታዎች በከፍተኛ ሁኔታ አሳሳቢ ሆኗል። በአሁኑ ወቅት ከሰሜን ጋዛ የተፈናቀሉ 600 ሺህ የሚገመቱ ተጨማሪ ፍልስጥኤማውያንን ማስተናገድ ይጠበቅባታል።እስራኤል ጋዛ ሰርጥን ሙሉ በሙሉ በመዝጋት ከበባ እንዲደረግ ያዘዘች ሲሆን፣ በጋዛ ‘ኤሌክትሪክ፣ ምግብ፣ ነዳጅ አይኖርም ሲሉም የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት ባለፈው ሳምንት ትዕዛዝ መስጠታቸው ይታወሳል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 4:36 17 ጥቅምት 20234:36 17 ጥቅምት 2023ኢራን ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ሰጠች
ReutersCopyright: Reutersእስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ እየፈጸመችው ያለውን ጥቃት ዝም ብላ እንደማትመለከት ኢራን አስታወቀች።እስራኤል በጋዛ ባሉ “ፍልስጥኤማውያንን ላይ እየፈጸመችው ያለችውን የጦር ወንጀሎች” ካላቆመች ኢራን የመከላከል እርምጃም እንደምትወስድም በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል አስታውቃለች።እስራኤል ለሐማስ ጥቃት ምላሽ ነው በሚል እየፈጸመችው ያለውን የአየር ጥቃት ተከትሎ በእስራኤል እና በሊባኖስ ድንበር ላይ ውጥረት ነግሷል።በኢራን የሚደገፈው ሄዝቦላህ በጦርነቱ ተሳታፊ ሊሆን ይችላል የሚልም ስጋት አጭሯል። አሜሪካ ኢራን ግጭቱን ከማባባስ እንድትቆጠብ ማስጠንቀቂያ የሰጠች ሲሆን እስራኤል በበኩሏ ሄዝቦላህ ተሳታፊ ከሆነ የከፋ ምላሽ እሰጣለሁ ብላለች።ባለፈው ሳምንት ሄዝቦላህ እና የእስራኤል ጦር በድንበር አካባቢ የተኩስ ልውውጥ ቢያደርጉም ከቁጥጥር ስር የወጣ አይደለም ተብሏል።የእስራኤል ጦር ትናንት ምሽት ከሄዝቦላህ ጋር የተገናኙ መሰረተ ልማቶችን ዒላማ ማድረጉን ገልጿል። በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ስለመድረሱ ምንም አይነት መረጃ የለም።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:27 17 ጥቅምት 20233:27 17 ጥቅምት 2023በጋዛ- እስራኤል የተከሰቱ ዋና ዋና ጉዳዮች
ReutersCopyright: Reutersአስር ቀናት ባስቆጠረው የሐማስ እስራኤል ግጭት የተከሰቱ ዋና ዋና ጉዳዮችን እንቃኝ
- የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ረቡዕ ወደ እስራኤል ያቀናሉ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን እንደተናገሩት ፕሬዚዳንቱ የሚያደርጉት ጉብኝት ለእስራኤል፣ ለአካባቢው እና ለመላው ዓለም ወሳኝ በሆነ ወቅት ላይ ነው።
- የእስራኤልን ከሰሜናዊ ጋዛ ውጡ ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ቤታቸውን ለቀው የተፈናቀሉ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ስደተኞች አስቸኳይ ምግብ፣ ውሃ እና ነዳጅ እንደሚያስፈልጋቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስጠንቅቋል።
- ሩሲያ ለተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ለጋዛ ሰብዓዊ መፍትሄ እንዲበጅ ያቀረበችው ረቂቅ አሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ ምዕራባውያን አገራት ሐማስን ማውገዝ ባለመቻሉ ውድቅ አድርገውታል።
- አሜሪካ ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ጋዛ እንዲደርስ ለማድረግ ከእስራኤል ዋስትና እንዳገኘች የተናገሩት ብሊንከን መቼ እና እንዴት እንደሆነ ዝርዝር ጉዳዮችን አልሰጡም።
- በግብጽ እና በጋዛ መካከል ያለው ራፋህ የተሰኘው የድንበር ማቋረጫንም ለማስከፈት የተጀመሩ ዲፕሎማሲያዊ ንግግሮች አሁንም ቀጥለዋል።
- የአሜሪካ ከፍተኛ ጄነራል ሚካኤል ኩሪላ በይፋ ባይነገርም በአሁኑ ወቅት በእስራኤል ይገኛሉ። ጄነራሉ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ኃይሎችን እንዲሁም የጦሩ ማዕከላዊ እዝ መሪ ናቸው።
- የእስራኤል አየር ኃይል በኢራን የሚደገፈውን የሊባኖሱን ሄዝቦላህ ታጣቂ ቡድንን ኢላማዎችን መምታቱን አስታውቋል።
- ሐማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት በሰነዘረበት ወቅት ካገታቸው ሰዎች መካከል አንዷን የሚያሳይ ቪዲዮ ለቋል። የ21 ዓመቷ ግለሰብ ስሟ ማያ ሼም መሆኑንም በዕብራይስጥ ቋንቋ ስትናገር ይሰማል።
- ባለፉት አስር ቀናት ውስጥ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ እስራኤላውያን እንደተፈናቀሉ ጦሩ አስታውቋል።
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 3:23 17 ጥቅምት 20233:23 17 ጥቅምት 2023ታዋቂው ካርቱኒስት ኔታንያሁን በጋዛ ላይ በሚያሳየው ካርቱን ምክንያት ከሥራው ተባረረስመ ጥሩ የጋርዲያን ጋዜጣ ካርቱኒስት ስቲቭ ቤል በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ዙሪያ በሳለው ካርቱን ምክንያት በተፈጠረ አለመግባባት ከሥራው ተባረረ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:21 17 ጥቅምት 20231:21 17 ጥቅምት 2023በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጋዛ-ግብፅ የድንበር ማቋረጫ በኩል ለመውጣት እየተጠባበቁ ነውበሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ራፋህ በተሰኘው የጋዛ-ግብፅ የድንበር ማቋረጫ በኩል ለመውጣት በተስፋ እየተጠባበቁ ነው።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:13 17 ጥቅምት 20231:13 17 ጥቅምት 2023ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ለእስራኤል ያላቸውን ጥልቅ አጋርነት በድጋሚ አረጋገጡውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን አገራቸው አሜሪካ ለእስራኤል ያላት አጋርነት ጥብቅና ጥልቅ እንደሆነ አረጋገጡ። ብሊንከን በጥቂት ቀናት ውስጥ ለ2ኛ ጊዜ ቴል አቪቭ ለጉብኝት ከገቡ በኋላ እንዳሉት ‘’እስራኤል ራሷን የመከላከል እርምጃዋን አሜሪካ በጥብቅ ትደግፋለች።’’ ሐማስ በእስራኤል ላይ መብረቃዊ ጥቃት ከፈጸመ ወዲህ ብሊንከን ወደ ቴል አቪቭ አቅንተው ቤንያሚን ናታኒያሁን ሲያገኙ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።ተጨማሪ ያንብቡ