Related Video and Audio

VIDEO 7 MINUTES 59 SECONDSVIDEO 7 MINUTES 59 SECONDS7:59

Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBCከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ

Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBC

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 23 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 23 SECONDS1:23

Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBCሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ?

Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBC

VIDEO 1 MINUTE 33 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 33 SECONDS1:33

Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBCበእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች

Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBC

ጭምቅ ሃሳብ

  1. በጋዛ ሆስፒታል ላይ በተፈጸመ ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሳይገደሉ አልቀረም ተባለ
  2. ጥቃት በደረሰበት ሆስፒታል ውስጥ ያለው ‘አስጨናቂው’ ሁኔታ
  3. ባይደን ከአረብ መሪዎች ጋር ሊያደርጉት የነበረው ስብሰባ ተሰረዘ
  4. እስራኤል በጋዛ ላይ የምትፈጽመው የአየር ጥቃት ዛሬም ቀጥሏል
  5. ተቃውሞ ሊባኖስ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ
  6. ‘የድመት ነፍስ አለው’ የሚባለው የሐማስ ወታደራዊ ኮማንደር ዴይፍ ማን ነው?
  7. “ቤታችንን በላያችን ላይ ቢያፈርሱትም የትውልድ ቀያችንን አንለቅም” የጋዛ ቤተሰቦች

ቀጥታ ዘገባ

  1. የታተመዉ 5:335:33በሐማስ የፖለቲካ ቢሮ የመጀመሪያ እና ብቸኛዋ የሆኑት ሴት መገደላቸው ተነገረጀሚላ አል ሻንቲGetty ImagesCopyright: Getty Imagesበሐማስ የፖለቲካ ቢሮ ውስጥ የመጀመሪያዋ እና ብቸኛዋ ሴት የሆኑት ግለሰብ በእስራኤል አየር ጥቃት መገደላቸውን የፍልስጥኤም መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።የሐማስ የፖለቲካ ቢሮ ዋነኛ ውሳኔ ሰጪ አካል ነው።ጀሚላ አል ሻንቲ በሐማስ ውስጥ የሴቶችን ንቅናቄ መስራች ሲሆን በአውሮፓውያኑ 2021 በፖለቲካው ቢሮው እንዲያገለግሉ የተመረጡ የመጀመሪያ ሴት ናቸው።ጀሚላ የሐማስ መስራች ከሆኑት አንዱ እና በህይወት የሌሉት አብደል አዚዝ አል ራንቲሲ ባለቤት ናቸው። በዘገባዎቹ ውስጥ የአየር ጥቃቱ ስለተካሄደበት ስፍራ ዝርዝር መረጃ አልተጠቀሰም።Article share tools
  2. የታተመዉ 4:574:57እስራኤልን ‘የሚጻረር’ ደብዳቤ ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ ሶስት የህግ ተማሪዎች የስራ እድላቸውን አጡፍልስጥኤምን በመደገፍ አሁን ለተከሰተው ቀውስ እስራኤል ተጠያቂ መሆኗን የሚገልጽ ደብዳቤ ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ ሶስት የሃርቫርድ እና ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ የህግ ተማሪዎች የስራ እድላቸውን አጡ። በደብዳቤውም ምክንያት አንድ ሊቀጥራቸው የነበረ ታዋቂ የህግ ኩባንያም የስራ እድሉን ነፍጓቸዋል ተብሏል። ዴቪስ ፖልክ እና ዋርድዌል የተባለው ኩባንያ በደብዳቤው ላይ የሰፈሩት አመለካከቶች “ከድርጅታችን እሴቶች ጋር የሚቃረኑ ናቸው” ብሏል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  3. የታተመዉ 4:144:14ጠቅላይ ሚኒስትር ሱናክ ዩናይትድ ኪንግደም ከእስራኤል ጎን ናት አሉየዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክReutersCopyright: Reutersበዛሬው ዕለት ወደ እስራኤል ያቀኑት የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ አገራቸው ከእስራኤል ጎን እንደምትቆም ተናገሩ።ዛሬ ጥቅምት 8/ 2016 በቴልአቪቭ አውሮፕላን ማረፊያ በደረሱበትም ወቅት ሐማስ ያደረሰውን ጥቃት “ሊነገር የማይችል አሰቃቂ የሽብር ተግባር ነው” ሲሉ አውግዘውታል።አገራቸው ከእስራኤል ጎንም እንደምትቆም አጽንኦት በመስጠትም ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።ሱናክ ከእስራኤል “ጠቅላይ ሚኒስትር እና ፕሬዚዳንት የማደርጋቸውን ስብሰባዎች በጉጉት እየጠበቅኩ ነው ውጤታማ እንደሚሆኑም ተስፋ አደርጋለሁ” ሲሉም ተደምጠዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በእስራኤል ቆይታቸው ከአመራሮቹ ጋር ተገናኝተው የሚመክሩ ሲሆን በቀጣናው የሚገኙ ሌሎች ሀገራትንም ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክReutersCopyright: ReutersArticle share tools
  4. የታተመዉ 0:270:27ሊባኖስ የሚገኘው የእስራኤል ጠላት ሄዝቦላህ ማን ነው? እንዴትስ ተመሠረተ?ሄዝቦላህ መልከ ብዙ ነው። የፖለቲካ ፓርቲ ብቻ አይደለም። ማኅበራዊ አገልግሎት ላይ ይሠራል፣ ፖለቲካ ላይ ይሳተፋል፤ ሚሊሻም ነው። ድንበር ተሻጋሪ ወታደራዊ ክንፍም አለው። ይህ መልከ ብዙነቱ በሊባኖስም ከሊባኖስ ውጭም አቅም ፈጥሮለታል። ለመሆኑ ሒዝቦላህ ማን ነው? እንዴትስ ለእስራኤል ፈተና ሊደቅን ቻለ?ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  5. የታተመዉ 11:29 18 ጥቅምት 202311:29 18 ጥቅምት 2023“እስራኤል ብቻሽን አይደለሽም፣ አሜሪካ ከጎንሽ አለች” ፕሬዝዳንት ባይደንፕሬዝዳንት ጆ ባይደንReutersCopyright: Reutersየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በእሰራኤል ጉብኝታቸው ወቅት አገራቸው ለእሰራኤል አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደርግ እና አብራት እንደምትቆም ተናግረዋል።ባይደን መካከለኛው ምሥራቅን እንዲሁም ቀሪውን ዓለም ያሳሰበው የእስራኤል ሐማስ ግጭት ከተቀሰቀሰ ከሳምንት በኋላ ወደ እስራኤል ተጉዘው ከጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ ጋር ተነጋግረዋል።ፕሬዝዳንቱ በሰጡት መግለጫ ላይ አሜሪካ በየትኛው ጊዜ ከእስራኤል ጎን እንደምትቆም “እስራኤል፣ ብቻሽን አይደለሽም” በማለት አሜሪካ “በጨለማ ቀናቶች ሁሉ አብራሽ ትራመዳለች” በማለት የአገራቸውን ድጋፍ ገልጸዋል።ጨምረውም እስራኤል ደኅንነቷ የተጠበቀ አይሁዳዊት እና ዴሞክራሲያዊ ሆና “ዛሬ፣ ነገ እና አስከ መጨረሻው” ትዘልቃለች ብለዋል።ሐማስ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ጥቃት በተመለከተም “ለጥቃቱ ምንም ይቅርታ አይኖርም፤ የተፈጸመው ጭካኔ በየትኛውም የዓለም ክፍል ከባድ ቁስልን ፈጥሯል” በማለት ጥቃቱ የተፈጸመበት ዕለት ከአይሁዳውያን እልቂት በኋላ እጅግ አስከፊው ነው ብለውታል።ከሐማስ ጥቃት አንጻርም “ዛሬ፣ ነገ፣ እስከ መቼውም ድረስ ቢሆን ምንም ሳናደርግ ቆመን አንመለከትም” ብለዋል ባይደን።በሐማስ የታገቱ ሰዎችን በሚመለከትም ከታጋች ቤተሰቦች ጎን በመሆን “ታጋቾቹ ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ የተቻለንን ሁሉ እያደረግን ነው።”እስራኤል በድጋሚ ለአይሁዳውያን ሕዝቦች የደኅንነት ቦታ እንድትሆን አሜሪካ “ባላት አቅም ሁሉ የምትችለውን ታደርጋለች” በማለት ቃል ገብተዋል።ለዚህም በሳምንቱ ማብቂያ ላይ የአሜሪካ ምክር ቤት ለእስራኤል ከዚህ በፊት “ያልተደረገ” የመከላከያ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥያቄ እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል።በእስራኤል ላይ በሐማስ የተፈጸመውን ጥቃት ከ20 ዓመታት በፊት በአገራቸው ላይ ከተፈጸመው የመስከረም 11ዱ ጥቃት ጋር ያነጻጸሩት ባይደን፣ ጥቃቱ በብዙ እጥፍ ከዚያ የሽብር ጥቃት የላቀ ነው ብለዋል።ባይደን በተጨማሪም እስራኤልን ለማጥቃት የሚያስብ የትኛውም መንግሥት ወይም “ተቀናቃኝ ኃይል” ካለ እንዳይሞክረው አጽንኦት ሰጥተው አስጠንቅቀዋል።ጥቃቱ በእስራኤላውያን ላይ “ድንጋጤን፣ ህመምን፣ቁጣን” መፍጠሩን “እኔ እና አሜሪካውያን እንረዳዋለን” በማለት፤ ፍትሕ መስፈን እንዳለበት አመልክተው እስራኤላውያን በቁጣ እንዳይዋጡ አስጠንቅቀዋል።ፍልስጥኤማውያንን በተመለከተም “እነሱም በጣሙን ተጎድተዋል” ያሉት ባይደን፣ በግጭቱ ሕይወታቸውን ላጡ ፍልስጥኤማውያን ቤተሰቦች ሐዘናቸውን ገልጸዋል።“በጋዛ ሆስፒታል ላይ በደረሰው ፍንዳታ የብዙዎች ሕይወት በመጥፋቱ ተቆጥቻለሁ፣ አዝኛለሁ። በአሁኑ ጊዜ ያሉ ማስረጃዎች ጉዳቱ የደረሰው ጋዛ ውስጥ ባለ ሽብርተኛ ቡድን በተተኮሰ ሮኬት መሆኑን ያመለክታሉ” ብለዋል።ለጋዛ ነዋሪዎች ምግብ፣ ውሃ እና መድኃኒት ያስፈልጋል ያሉት ባይደን “የእስራኤልን ካቢኔን ጠይቄ. . . ነፍስ አድን የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦቶች ለሐማስ ሳይሆን ለጋዛ ሲቪሎች እንዲደርስ ቁጥጥር እየተደረገበት እንዲገባ ተስማምተዋል።”ለዚህም ከእስራኤል፣ ከግብፅ እና ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር እየሰሩ መሆናቸውንም አመልክተዋል።Article share tools
  6. የታተመዉ 9:11 18 ጥቅምት 20239:11 18 ጥቅምት 2023በጋዛ ሆስፒታል ፍንዳታ 471 ሰዎች ሲገደሉ 314 መቁሰላቸው ተረጋገጠጉዳት በደረሰበት ሆስፒታልGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየፍልስጥኤም ጤና ሚኒስቴር ማክሰኞ ምሽት ጋዛ ውስጥ በሚገኘው ሆስፒታል ላይ በደረሰው ፍንዳታ 471 ሰዎች መገደላቸውን እና 314 መቁሰላቸውን አስታወቀ።ከባድ ውግዘት እና ውዝግብን ላስከተለው ፍንዳታ አስካሁን ኃላፊነቱን የወሰደ ወገን የለም።ሐማስ አስራኤልን ሲከስ፣ እስራኤል ደግሞ የፍልስጥኤሙን ኢስላሚክ ጂሃድ ለፍንዳታው ተጠያቂ አድረጋለች።የእስራኤል ጦር ሠራዊት ቃል አቀባይ ማስረጃዎችን በማቅረብ በሰጡት መግለጫ ፍንዳታው ከእስራኤል በተተኮሰ መሳሪያ ሳይሆን ከጋዛ የተተኮሰ ነው ብለዋል።በፍንዳታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል እየተነገረ ሲሆን፣ ቤተሰቦች ከፍንዳተው ስፍራ እስካሁን የሟቾችን አስከሬን እየሰበሰቡ ነው።Article share tools
  7. የታተመዉ 9:07 18 ጥቅምት 20239:07 18 ጥቅምት 2023አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላኖች የሚሸከም ሁለተኛ የጦር መርከቧን ወደ እስራኤል አንቀሳቀሰችአሜሪካ እስራኤልን ለማገዝ በምሥራቅ ሜዲትራኒያን በኩል አውሮፕላን ተሸካሚ የጦር መርከቦቿን እያስጠጋች ነው። የአሜሪካ የመከላከያ ሚንስቴር ይህ እርምጃ “በእስራኤል ላይ ሊቃጣ የሚችልን ጥቃት ቀድሞ ለመከላከል” ያለመ ነው ብሏል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  8. የታተመዉ 6:13 18 ጥቅምት 20236:13 18 ጥቅምት 2023“ቤታችንን በላያችን ላይ ቢያፈርሱትም የትውልድ ቀያችንን አንለቅም” የጋዛ ቤተሰቦችእስራኤል ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የሰሜን ጋዛ ነዋሪዎችን አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ የጊዜ ገደብ በማስቀመጥ አስገዳጅ ትዕዛዝ አስተላልፋለች። ማስጠንቀቂያውን የሰሙ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩም ወደ ደቡባዊ ጋዛ እየጎረፉ ነው። ነገር ግን እግረኛ ጦር ቢገባም ቤታችንን፣ ቀያችንን አንለቅም ያሉ የጋዛ ነዋሪዎች ግን አልታጡም።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  9. የታተመዉ 5:22 18 ጥቅምት 20235:22 18 ጥቅምት 2023የጋዛ ሆስፒታል ጥቃት “በሌላኛው ቡድን የተደረገ ይመስላል” – ባይደንበReutersCopyright: Reutersበመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለውበታል የተባለው በጋዛ በሚገኝ ሆስፒታል ላይ የደረሰወ ፍንዳታ “በሌላኛው ቡድን የተደረገ ይመስላል” ሲሉ ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ።ፕሬዝዳንት ባይደን ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ጋር ለመወያየት ዛሬ ረቡዕ ረፋድ አምስት ሰዓት ገደማ ቴል አቪቭ ገብተዋል።ባይደን በክስተቱ “በጣም አዝኛለሁ፣ ተቆጥቻለሁ” ብለዋል።“ባየሁት ነገር ላይ በመመሥረት ጥቃቱ በእናንተ ሳይሆን በሌላ ቡድን የተደረገ ይመስላል። ነገር ግን እርግጠኛ ያልሆኑ ብዙ ሰዎች በመኖራቸው ብዙ ነገሮችን ማለፍ አለብን” ሲሉ አክለዋል።ቢቢሲ በትናንት ምሽቱን የሆስፒታል ፍንዳታ ዙሪያ አንድ ዘገባ ለመሥራት መረጃዎችን በማጠናቀር ላይ ይገኛል። ሐማስ እና የፍልስጤም ባለሥልጣናት ለጥቃቱ የእስራኤልን የአየር ጥቃትን ተጠያቂ አድርገዋል።Article share tools
  10. የታተመዉ 4:19 18 ጥቅምት 20234:19 18 ጥቅምት 2023የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባልተለመደ ሁኔታ ጉብኝት ለማድረግ እስራኤል ገቡጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ እና ፕሬዝዳንት ባይደንReutersCopyright: Reutersጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ እና ፕሬዝዳንት ባይደንImage caption: ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ እና ፕሬዝዳንት ባይደንየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ጋር ለመወያየት ዛሬ ረቡዕ ረፋድ አምስት ሰዓት አካባቢ እስራኤል ገብተዋል።በእራኤል እና በጋዛ መካከል ግጭት ከተቀሰቀሰ ከሳምንት በኋላ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የተጓዙት ፕሬዝዳንት ባይደን፣ ባለፈው ሳምንት የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊያቸውን ወደ አካባቢ ልከው ነበር።ግጭቱ እየተባባሰ እና የዓለም አገራትን ትኩረት መሳቡን ተከትሎ ባይደን እንደ አሜሪካ ፕሬዝዳንት አሁን ወደ ግጭት አካባቢ ያደረጉት ጉዞ ያልተለመደ ነው እየተባለ ነው።የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ግጭቶች ወደ ሚካሄዱባቸው አካባቢዎች በአጭር ጊዜ ማስታወቂያ እምብዛም ጉብኝት ማድረጋቸው የተለመደ አይደለም።ፕሬዝዳንት ባይደን ከጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ የፍልስጥኤሙ መሪ ማህሙድ አባስን ጨምሮ ከዮርዳኖሱ ንጉሥ እና ከግብፅ ፕሬዝዳንት ጋር አማን ዮርዳኖስ ላይ የመወያየት ዕቅድ ነበራቸው።ነገር ግን ማክሰኞ ምሽት ጋዛ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ላይ የደረሰውን ፍንዳታ ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ከአረብ አገራት መሪዎቹ ጋር ያላቸው ስብሰባ ተሰርዟል።የፕሬዝዳንት ባይደን አውሮፕላን ኤር ፎርስ ዋንBBCCopyright: BBCየፕሬዝዳንት ባይደን አውሮፕላን ኤር ፎርስ ዋንImage caption: የፕሬዝዳንት ባይደን አውሮፕላን ኤር ፎርስ ዋንArticle share tools
  11. የታተመዉ 3:02 18 ጥቅምት 20233:02 18 ጥቅምት 2023ባይደን ከአረብ መሪዎች ጋር ሊያደርጉት የነበረው ስብሰባ ተሰረዘበእሰራኤል ዛሬ (ረቡዕ) ጉብኝት የሚያደርጉት ፕሬዝዳንት ባይደን ከዋሽንግተን ሲነሱEPACopyright: EPAበእሰራኤል ዛሬ (ረቡዕ) ጉብኝት የሚያደርጉት ፕሬዝዳንት ባይደን ከዋሽንግተን ሲነሱImage caption: በእሰራኤል ዛሬ (ረቡዕ) ጉብኝት የሚያደርጉት ፕሬዝዳንት ባይደን ከዋሽንግተን ሲነሱጋዛ ውስጥ ባለው ሆስፒታል ላይ በደረሰው ፍንዳታ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከአረብ አገራት መሪዎች ጋር የነበራቸው ስብሰባ ተሰረዘ።ባይደን ዛሬ በእስራኤል በሚያደርጉት ጉብኝት ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ጋር ከተወያዩ በኋላ፣ የዮርዳኖሱን ንጉሥ አብዱላህን፣ የግብፁን ፕሬዝዳንት አብደል ፋትህ አል ሲሲን እና የፍልስጥኤም አስተዳደር ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስን በማግኘት ይወያያሉ ተብሎ ነበር።ነገር ግን ማክሰኞ ምሽት በጋዛ ሆስፒታል ላይ ፍንዳታ ከደረሰ በኋላ የዮርዳኖስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትቴር ለጥቃቱ እስራኤልን ተጠያቂ በማድረግ ከባይደን ጋር የሚደረገው ውይይት “በፍልስጥኤማውያን ላይ የሚካሄደው ጦርነት እና ጭፍጨፋ” ሲቆም ብቻ የሚካሄድ ይሆናል ብሏል።የእስራኤል ጦር ኃይል ግን ፍንዳታው የደረሰው በጋዛ ውስጥ ሐማስን ተከትሎ ዋነኛው ቡድን የሆነው የፍልስጥኤም እስላማዊ ጂሃድ በተባለው አማካይነት መሆኑን ገልጿል።ወደ እስራኤል እየተጓዙ ያሉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት በኤክስ (ትዊተር) ላይ “በፍንዳታው መቆጣታቸውን እና በጥልቅ ማዘናቸውን” አስፍረው፣ የብሔራዊ ደኅንነት ቡድናቸው “በትክክል ምን እንደተከሰተ ለማወቅ የሚያስፈልጉ መረጃዎችን መሰብሰብ እንዲቀጥሉ” ማዘዛቸውን ገልጸዋል።Article share tools
  12. የታተመዉ 2:46 18 ጥቅምት 20232:46 18 ጥቅምት 2023በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተገደሉበት ሆስፒታል በምስልማክሰኞ ማታ ጋዛ ውስጥ በሚገኘው አል አህሊ በተባለው ሆስፒታል ላይ በተደሰ ፍንዳታ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጥኤማውያን ሳይገደሉ እንዳልቀረ ተሰግቷል።ሐማስ ለአደጋው የእስራኤል የአየር ጥቃት ምክንያት ነው ያለ ሲሆን፣ እስራኤል ግን ፍንዳተው የተከሰተው ሌላኛው የፍልስጥኤም ቡድን ኢስላሚክ ጂሃድ በስህት በተኮሰው ሮኬት የደረሰ ነው ስትል እጇ እንደሌለበት ገልጻለች።በሆስፒታሉ ላይ የደረሰው ከባድ ፍንዳታ ያስከተለውን ጉዳት በጥቂቱ የሚያሳዩ ፎቶግራፎች እነሆ፡በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተገደሉበት ሆስፒታል በምስልEPACopyright: EPAበመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተገደሉበት ሆስፒታል በምስልEPACopyright: EPAበመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተገደሉበት ሆስፒታል በምስልEPACopyright: EPAበመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተገደሉበት ሆስፒታል በምስልEPACopyright: EPAArticle share tools
  13. የታተመዉ 2:37 18 ጥቅምት 20232:37 18 ጥቅምት 2023እስራኤል በጋዛ ላይ የምትፈጽመው የአየር ጥቃት ዛሬም ቀጥሏልእስራኤል በሰሜናዊ ጋዛ ዛሬ ጠዋት በፈጸመችው የአየር ጥቃት የተነሳ ጪስEPACopyright: EPAእስራኤል በሰሜናዊ ጋዛ ዛሬ ጠዋት በፈጸመችው የአየር ጥቃት የተነሳ ጪስImage caption: እስራኤል በሰሜናዊ ጋዛ ዛሬ ጠዋት በፈጸመችው የአየር ጥቃት የተነሳ ጪስጋዛ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ላይ ማከሰኞ ምሽት የተፈጸመውን ጥቃት እንዳላደረሰች የገለጸችው እስራኤል ረቡዕ ጠዋት በተለያዩ ዒላማዎች ላይ የአየር ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች።በሆስፒታሉ ላይ በተፈጸመው ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸው የተዘገበ ሲሆን፤ ሐማስ እስራኤልን፣ አስራኤል ደግሞ የፍልስጥኤም እስላማዊ ጂሃድ የተባለውን ቡድን ለጥቃቱ ተጠያቂ እያደረጉ ነው።የእስራኤል አየር ኃይል ዛሬ ጠዋት በተለያዩ የጋዛ ሰርጥ አካባቢዎች ባሉ ወታደራዊ ያላቸውን ዒላማዎች የመታ መሆኑን ገልጾ፣ በዚህም የፍልስጥኤም ታጣቂ ቡድን ሁለት አባላትን “መደምሰሷን” አሳውቃለች።የእስራኤል ሠራዊት በኤክስ (ትዊተር) ገጹ ላይ ገደልኩ ያላቸውን ሁለት ሰዎችን ስም እና ሚናቸውን ይፋ አድርጓል። አንደኛው ሙሐመድ አልዋዲ የተባለ እና በጋዛ ውስጥ የሐማስ ፀረ ታንክ ቡድን መሪ ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ አክራም ሂጃዝ የሚባል የጦር መሳሪያ ነጋዴ ነው ብሏል።የእስራኤል አየር ኃይል ባለፉት ቀናት በካሄዳቸው የአየር ጥቃቶች የሐማስ ጽህፈት ቤቶችን፣ የሮኬት እና ፀረ ታንክ መሳሪያዎች ማስወንጨፊያዎችን እና ሌሎች የቡድኑ ተቋማትን በዋናነት ዒላማ ማድረጉን አመልክቷል።Article share tools
  14. የታተመዉ 2:30 18 ጥቅምት 20232:30 18 ጥቅምት 2023‘የድመት ነፍስ አለው’ የሚባለው የሐማስ ወታደራዊ ኮማንደር ዴይፍ ማን ነው?ዴይፍ የድመት ነፍስ ነው ያለው የሚባለው ለምንድነው ካልን መልሱ ማንም የሚገምተው ነው። እስራኤል ገደልኩት ስትል እየተነሳ፣ ሞተ ሲባል እያንሰራራ ስላስቸገረ ነው። ኮማንደር ዴይፍ ላይ እስራኤል ተደጋጋሚ እና ተከታታይ የግድያ ሙከራ ብታደርግበትም አልተሳካላትም። አራት ጊዜ ገደልኩት ብላ አራት ጊዜም ቆስሎ አምልጧል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  15. የታተመዉ 1:09 18 ጥቅምት 20231:09 18 ጥቅምት 2023ጥቃት በደረሰበት ሆስፒታል ውስጥ ያለው ‘አስጨናቂው’ ሁኔታመሬት ላይ እንዲቀመጡ የተደረጉ ሰዎችን የሚያክም ዶክተርReutersCopyright: Reutersመሬት ላይ እንዲቀመጡ የተደረጉ ሰዎችን የሚያክም ዶክተርImage caption: መሬት ላይ እንዲቀመጡ የተደረጉ ሰዎችን የሚያክም ዶክተርማክሰኞ አመሻሽ ላይ በተፈጸመበት ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸው በተነገረለት የጋዛው አል አህሊ ሆስፒታል ውስጥ ያለው ሁኔታ “ወደር የሌለው እና ለመገልጽ አስቸጋሪ” መሆኑን በጋዛ ያለው የፍልስጥኤም ጤና ሚኒስቴር ገለጸ።“ዶክተሮች መሬት ላይ እና በመተላለፊያ ኮሪደሮች ላይ ቀዶ ሕክምና እያደረጉ ነው፣ አንዳንዶቹ ታካሚዎችም ካለማደንዘዣ ነው ቀዶ ሕክምና የሚደረግላቸው” በማለት የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ዶክተር አሽራፍ አል-ቁድራ በፌስቡክረ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።“በርካታ ሰዎች ቀዶ ሕክምና ለማግኘት እየተጠባበቁ ሲሆን፣ በጽኑ ሕሙማን ክፍል ያሉትን ሰዎች ሕይወትን ለማትረፍ የሕክምና ባለሙያዎች ጥረት እያደረጉ ነው።”ቃል አቀባዩ ጨምረውም ከጥቃቱ ሰለባዎች አብዛኞቹ “የወደፊት ተስፋቸውን የተነጠቁ” ሕጻናት ናቸው በማለት፣ አብዛኞቹ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችን ለማከም በሆስፒታሉ “ካሉት ሐኪሞች አቅም በላይ ነው” ብለዋል።በሆስፒታሉ ላይ ማን እንደፈጸመው አስካሁን ባልታወቀው የፍንዳታ ጥቃት አምስት መቶ የሚደርሱ ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል።ሐማስ ለጥቃቱ እስራኤልን ተጠያቂ ሲያደርግ፣ የእስራኤል መንግሥት ደግሞ ሌላኛውን የፍልስጥኤም ቡድን ኢስላሚክ ጂሃድን ጥቃቱን ፈጽሟል ብሎ እየከሰሰ ነው።Article share tools
  16. የታተመዉ 0:24 18 ጥቅምት 20230:24 18 ጥቅምት 2023ተቃውሞ ሊባኖስ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ላይየተቃውሞ ሰለፍ ቤይሩት ውስጥReutersCopyright: Reutersጋዛ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ላይ በተፈጸመ ጥቃት የተቆጡ ተቃዋሚዎች ሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ውስጥ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ውጪ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ።ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተቃዋሚዎች በኤምባሲው ዙሪያ እሳት በማንደድ እና የፍልስጥኤም ሰንደቅ አላማን በኤምባሲው አጥር ላይ በመስቀል ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።ሮይትርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው ፖሊስ ተቃዋሚዎቹን ለመበተን አስለቃሽ ጋዝ ተኩሷል።በተመሳሳይ እዚያው ቤይሩት ውስጥ በሚገኘው የፈረንሳይ ኤምባሲ ላይ ተቃውሞ ለማሰማት ትንሽ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ተሰብስበው የነበረ ሲሆን፣ በሕንጻው ላይ ድንጋይ መወርወራቸው ተዘግቧል።ሐማስ እና የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላህ ጋዛ ውስጥ በሚገኘው አል አህሊ ሆስፒታል ላይ ለተፈጸመው ጥቃት እስራኤልን እና አሜሪካንን ተያየቂ አድርገዋል፤ እሰራኤል ግን ለጥቃቱ እስላማዊ ጂሃድ የተባለውን የፍልስጥኤም ቡድንን ከሳለች።ሄዝቦላህ ጥቃቱን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ “ታይቶ የማይታወቅ ሕዝባዊ ቁጣ የሚገለጽበት” በማለት ለረቡዕ የተቃውሞ ሰልፍ ጠርቷል።በተጨማሪም ጋዛ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ላይ በተፈጸመ ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ በተለያዩ ስፍራዎች ተቃውሞዎች እየተቀሰቀሱ ነው።
    • ዌስት ባንክ ውስጥ የሚገኙ ፍልስጥኤማውያን ማክሰኞ ምሽት በበርካታ ከተሞች ውስጥ ወደ አደባባይ በመውጣት ድንጋይ እየወረወሩ በፍልስጥኤም አስተዳደር ፕሬዝዳንት ላይ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል። የፀጥታ ኃይሎችም ሰልፈኞቹን ለመበተን አስለቃሽ ጋዝ ተኩሰዋል።
    • በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ገድሞ በዋና ከተማ ትሪፖሊ እና በሌሎች የሊቢያ ከተሞች ውስጥ የፍልስጥኤም ሰንደቅ ዓላማን በመያዝ የጋዛ ነዋሪዎችን የሚደግፉ መፈክሮችን እያሰሙ አደባባይ ወጥተዋል።
    • ተቃዋሚዎች ኢራን ዋና ከተማቴህራን ውስጥ ከሚገኙ የብሪታኒያ እና የፈረንሳይ ኤምባሲዎች ውጪ የተሰበሰቡ ሲሆን፣ በቱርክ እና በዮርዳኖስ ከሚገኙት የእስራኤል ኤምባሲዎች ደጃፍ ሰዎች ለተቃውሞ መሰብሰባቸው ተዘግቧል።
    ተቃዋሚ ሰልፈኞች በትሪፖሊGetty ImagesCopyright: Getty Imagesተቃዋሚ ሰልፈኞች በትሪፖሊImage caption: ተቃዋሚ ሰልፈኞች በትሪፖሊArticle share tools
  17. የታተመዉ 0:03 18 ጥቅምት 20230:03 18 ጥቅምት 2023በጋዛ ሆስፒታል ላይ በተፈጸመ ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሳይገደሉ አልቀረም ተባለጋዛEPACopyright: EPAጋዛ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ላይ በተፈጸመ ጥቃት በደረሰ ፍንዳታ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጥኤማውያን ሳይገደሉ እንዳልቀሩ ተነገረ።ለጥቃቱ ሐማስ የእስራኤል የአየር ጥቃት ምክንያት ነው ሲል፣ እስራኤል ደግሞ የፍልስጥኤም እስላማዊ ጂሃድ የተባለው ቡድን የተኮሰው ሮኬት ኢላማውን ስቶ ሆስፒታሉ ላይ በመውደቁ ነው ብላለች።ነገር ግን እስራኤልም ሆነች ጋዛ ውስጥ ከሐማስ ከቀጥሎ ሁለተኛው ትልቅ ቡድን የሆነው እስላማዊ ጂሃድ ለጥቃቱ ተጠያቂ አለመሆናቸውን አስተባብለዋል።በሐማስ በምትተዳደረው ጋዛ ውስጥ ያሉ ባለሥልጣናት እንዳሉት ሆስፒታሉ ላይ በደረሰው የፍንዳታ ጥቃት 500 የሚሆኑ ሰዎች ተገድለዋል።ሐማስ ድርጊቱን በእስራኤል የተፈጸመ “የጦር ወንጅል” ያለው ሲሆን፣ የተለያዩ አገራት መሪዎች በሆስፒታሉ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በማውገዝ ለጠፋው ሕይወት ሐዘናቸውን ገልጸዋል።የዮርዳኖስ፣ የግብፅ እና የፍልስጥኤም መሪዎች ዛሬ ረቡዕ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር ሊያደርጉት የነበረው ስብሰባም ተሰርዟል።ጆ ባይደን ለእስራኤል አጋርነታቸውን ለማሳየት እና ግጭቱ እንዲያበቃ ለማገዝ ዛሬ በእስራኤል ጉብኝት በማድረግ ከአገሪቱ መሪዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።ሐማስ እና የሌባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላህ በሆስፒታሉ ላይ ለተፈጸመው የፍንዳታ ጥቃት አሜሪካ ከአስራኤል ጋር የጥፋቱ ተጋሪ ናት ሲሉ ከሰዋል።ሌሊቱን ቤይሩት ውስጥ ከአሜሪካ ኤምባሲ ውጪ በርካታ ሕዝብ የተሳተፈበት የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል።Article share tools
  18. የታተመዉ 11:54 17 ጥቅምት 202311:54 17 ጥቅምት 2023እስካሁን ጋዛ ውስጥ 3,000 ሰዎች ሲገደሉ ከ12,000 በላይ ተጎድተዋልየፍንዳታ ጭስ በጋዛEPACopyright: EPAጋዛImage caption: ጋዛየፍልስጥኤም ጤና ሚኒስቴር አዲስ ያወጣው መረጃ ባለፉት ዘጠኝ ቀናት 3,000 የሚደርሱ ሰዎች ጋዛ ሰርጥ ውስጥ በተፈጸሙ የአየር ጥቃቶች ምክንያት መገደላቸውን አመለከተ።መስከረም 26/2016 ዓ.ም. ሐማስ ድንበር ተሻግሮ በእስራኤል ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ፣ በጋዛ ላይ የእስራኤል አየር ኃይል ያለማቋረጥ በፈጸመው የአየር ድብደባ ነው ሰዎቹ የተገደሉት።ከተገደሉት ፍልስጥኤማውያን በተጨማሪ 12,500 የሚሆኑት ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል።በሌላ በኩል ደግሞ ከጋዛ በስተምሥራቅ ተነጥሎ በሚገኘው የፍልስጥኤም ግዛት ዌስት ባንክ ውስጥ 61 ፍልስጥኤማውያን የተገደሉ ሲሆን፣ ከ1,250 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል።በጋዛ ላይ የእስራኤል ጦር ኃይል ሙሉ ከበባ በመጣሉ የመሠረታዊ አቅርቦቶች ችግር የተፈጠረ ሲሆን፤ የውሃ፣ የኤሌክትሪክ እና የነዳጅ አቅርቦት በመቋረጡ በነዋሪው ላይ የበለጠ ችግር ይፈጠራል ተብሎ ተሰግቷል።የፍልስጥኤም የጤና ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እንዳሉት፣ ጋዛ ውስጥ ኤሌክትሪክ በመቋረጡ እና የነዳጅ እጥረት በመፈጠሩ ሆስፒታሎች “ሥራቸውን ወደማቆም ተቃርበዋል።”Article share tools
  19. የታተመዉ 10:19 17 ጥቅምት 202310:19 17 ጥቅምት 2023የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሐማስ መሪ ጋር ተወያዩየሐማሱ መሪ ኢስማኤል ሃኒያህ እና የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶርAFP/REUTERSCopyright: AFP/REUTERSየሐማሱ መሪ ኢስማኤል ሃኒያህ እና የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶርImage caption: የሐማሱ መሪ ኢስማኤል ሃኒያህ እና የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶርየደቡብ አፍሪካዋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሐማስ መሪ ጋር “ወደ ፍልስጥኤም ግዛቶች ሰብአዊ እርዳታ በሚቀርብበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን” ጽህፈት ቤታቸው አስታወቀ።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ናሌዲ ፓንዶር የደቡብ አፍሪካ መንግሥትን በመወከል ከሐማሱ መሪ ኢስማኤል ሃኒያህ ጋር መወያየታቸውን ዛሬ ማክሰኞ አረጋግጠዋል።ነገር ግን ውይይቱ የተደረገው በደቡብ አፍሪካ መንግሥት ጥያቄ ሳይሆን በሐማስ ፍላጎት መሆኑም ተነግሯል።በስልክ በተደረገው ውይይት ወቅት “ሚኒስትር ፓንዶር ደቡብ አፍሪካ ለፍልስጥኤም ሕዝብ ያላትን ድጋፍ በመግለጽ፣ በፍልስጥኤም እና በእስራኤል ሰላማዊ ዜጎች ላይ በደረሰው የሕይወት መጥፋት ማዘናቸውን ተናግረዋል” ብሏል የወጣው መግለጫ።በተጨማሪም “ሚኒስትሯ እና የሐማሱ መሪ አስፈላጊ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ወደ ጋዛ እና ወደ ሌሎች የፍልስጥኤም ግዛቶች እንዴት ሊደረስ እንደሚችል” መወያየታቸው ተገልጿል።ከሳምንት በፊት ሐማስ በእስራኤል ላይ ከባድ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የእስራኤል ሠራዊት በጋዛ ላይ ከበባ በመጣሉ ሐማስ በሚያስተዳድራት በጋዛ ውስጥ የመሠረታዊ አቅርቦት ቀውስ ተፈጥሯል።የሚኒስትሯ ጽህፈት ቤት በአንድ የአገሪቱ የመገናኛ ብዙኃን ሐማስ በእስራኤል ላይ ለፈጸመውን ጥቃት ሚኒስትሯ ድጋፋቸውን ገልጸዋል መባሉን አስተባብሏል።በሐማስ እና በእስራኤል መካከል ግጭቱ ከተጀመረ በኋላ ከታጣቂ ቡድኑ ጋር መወያየታቸውን በይፋ ከተናገሩ ጥቂት አገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ አንዷ ናት።Article share tools
  20. የታተመዉ 8:44 17 ጥቅምት 20238:44 17 ጥቅምት 2023ጋዛ ውስጥ ያሉ 11 ሺህ ቁስለኞችን ለመርዳት እንድገባ ይፈቀድልኝ፡ የዓለም ጤና ድርጅትራፋህ ውስጥ በእስራኤል ጥቃት ጉዳት የደረሰበትን ሰው የተሸከሙ ሰዎችReutersCopyright: Reutersራፋህ ውስጥ በእስራኤል ጥቃት ጉዳት የደረሰበትን ሰው የተሸከሙ ሰዎችImage caption: ራፋህ ውስጥ በእስራኤል ጥቃት ጉዳት የደረሰበትን ሰው የተሸከሙ ሰዎችየዓለም ጤና ድርጅት አስራ አንድ ሺህ ሰዎች የመቁሰል ጉዳት ወደደረሰባቸው ጋዛ እርዳታ እና የሕክምና አቅርቦት ለማድረስ አስቸኳይ ፈቃድ እንዲሰጠው ጠየቀ።ድርጅቱ ጨምሮም ጋዛ ውስጥ አሁን ያለው ሁኔታ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ሰብአዊ ቀውስጥ ሊከሰት ይችላል በማለት አስጠንቅቋል።የሐማስን ጥቃት ተከትሎ እስራኤል በጋዛ ላይ የአጸፋ የአየር ድብደባ መፈጸም ከጀመረች ሳምንት ያለፋት ሲሆን፣ ወደ ሦስት ሺህ የሚጠጉ ፍልስጥኤማውያን አስካሁን ተገድለዋል።የዓለም ጤና ድርጅትን ጠቅሶ ሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገባው ጋዛ ውስጥ ከተገደሉት 2,800 ሰዎች መካከል ግማሽ የሚሆኑት ሴቶች እና ሕጻናት ናቸው። በተጨማሪም አስካሁን 11,000 ሺህ ሰዎች በጥቃቱ የመቁሰል ጉዳት ደርሶባቸዋል።ድርጅቱ ምንም አይነት ነገር ለማስገባት እና ለማስወጣት ወደማይቻልባት ጋዛ አስፈላጊው የሕክምና እና የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ለማድረስ የሚያስችል በር በአስቸኳይ እንዲከፈት ለማስቻል “ከውሳኔ ሰጪ አካላት” ጋር እየተነጋገረ መሆኑን ገልጿል።ባለሥልጣናት ጨምረውም በጋዛ ውስጥ ባሉ በ115 የጤና አገልግሎት ተቋማት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፣ አብዛኞቹ የጋዛ ሆስፒታሎች የውሃ እና የኤሌክትሪክ አቅርቦት ችግር ስላለባቸው ሥራቸውን እያከናወኑ አይደለም።የውሃ እና የንጽህን አቅርቦቶች በመቋረጣቸው “የተቅማጥ እና የውሃ ወለድ በሽታዎች ስጋት ከፍተኛ ነው” የመንግሥታቱ ድርጅት የፍልስጥኤም ስደተኞች ተቋም “ካለውሃ ሰዎች መሞት ይጀምራሉ” በማለት ስጋቱን ገልጿል።Article share tools