
ከ 4 ሰአት በፊት
በፖላንድ መዲና ዋርሶው አንድ ግለሰብ የልብስ መስቀያ አሻንጉሊት መስሎ ሱቅ ከተዘጋ በኋላ ጌጣጌጥ ዘርፏል በሚል ተከሷል።
ፖሊስ ስሙን የሸሸገው ይህ የ22 ዓመት ወጣት የእጅ ቦርሳ አንጠልጥሎ እንደ ልብስ መስቀያ ተገትሮ በፎቶ ይታያል።
ፖሊስ እንደገለጠው ተጠርጣሪው የተለያዩ ሱቆችን ካዳረሰ በኋላ ነው በስተመጨረሻ አንድ የጌጣጌጥ ሱቅ ላይ ልቡ ያረፈው።
ከዚህም አልፎ ከአንድ የገበያ ሥፍራ የተለያዩ ቁሶችን ሰርቋል የሚል ክስም ቀርቦበታል።
በስርቆት እና ዘረፋ ወንጀሎች የተጠረጠረው ወጣት ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ እስከ 10 ዓመት እሥር ሊቀጣ ይችላል።
የዋርሶው ፖሊስ እንዳለው የሱቁ ሠራተኞችም ሆኑ ሸማቾች ሰውየው የልብስ መስቀያ መስሎ ከአሻንጉሊቶች ጋር ተደርድሮ ሲቆም ምንም አልጠረጠሩም።
- ባይደን ሐማስ እና ፑቲን እንዲያሸንፉ አልፈቅድም አሉ15 ጥቅምት 2023
- በሰሜን ሸዋ ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለው ከእገታ የተለቀቁት አባት የቀናት ሰቆቃ እና ስጋትከ 5 ሰአት በፊት
- በጋዛ የሆስፒታል ፍንዳታ ስፍራ የተፈጠረው ድንጋጤ እና ግራ መጋባትከ 5 ሰአት በፊት
ተጠርጣሪው ሱቆች እስኪዘጉ ድረስ ይቆምና ማንም አይኖርም ብሎ በሚያምነበት ሰዓት ጌጣጌጥ ይዘርፋል ይላል የፖሊስ ሪፖርት።
ነገር ግን አንድ ቀን አካባቢውን በሚጠብቁ ሰዎች ዓይን ውስጥ ገባ።
ከዚህ ቀደም አንድ ምግብ ቤት ገብቶ ሱቆች እስኪዘጉ ድረስ እራቱን ሲበላ ቆይቶ ከወጣ በኋላ ስርቆት ፈፅሟል።
የከተማዋ ፖሊስ ዘገባ እንደሚያሳየው ከምግብ ቤቱ ወጥቶ የራሱን አሮጌ ልብሶች በአዳዲስ ተክቶ ተመልሶ ሁለተኛ ጊዜ ተመግቦ ሄዷል።
በሲሲቲቪ ካሜራ የሱቁ በር ሙሉ በሙሉ ባለመዘጋቱ ክፍተቱን ተጠቅሞ ነው ወደ ውስጥ የዘለቀው።
የፖሊስ ቃል አቀባይ ሮበርት ስዙሚያታ እንዳሉት በሌላ ሶስተኛ ሥፍራ ደግሞ ሱቆች እስኪዘጉ ጠብቆ ከሱቆች ካዝና ገንዘብና ሌሎች ቁሶችን ሰርቆ ወጥቷል።
ፖሊስ ግለሰቡ በቁጥጥር ሥር ሲውል የሚያሳይ ምስል ይፋ አድርጓል።
ተጠርጣሪው ፈፀመ የተባለው ወንጀል በምርመራ እስኪጣራ ድረስ ለሶስት ወራት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ይቆያል።
