October 20, 2023 – Konjit Sitotaw
- በባለስልጣናት ደረጃ በሃሰተኛ ሰነድና በፎርጂድ ስልጣኑን የተቆጣጠሩት በርካቶች ናቸው
- ሰነዶችን ከታች በዝርዝር ይመልከቷቸው
- የመዋሸት ሱስ ፡ በኢቢሲ የ400 ሰራተኞቹ ሰነድ ፎርጂድ/ሀሰተኛ መሆኑን ያረጋገጡ የድርጅቱ ሰራተኞች በባለስልጣናት እየተሰቃዩ ነው።

ኢቢሲ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በተቋሙ ሰራተኞች ላይ ባደረገው የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ የ400 ሰራተኞቹ ሰነድ ፎርጂድ/ሀሰተኛ መሆኑን የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል።
ይህ ሆኖ እያለ የተቋሙ ሀላፊዎች እርምጃ እንዳይወሰድ ይህን መረጃው እንደደበቁ፣ በጥቆማ አቅራቢዎች ላይም ዛቻ እና ማስፈራርያ እያደረሱ እንደኮነ ይህ የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለጠቅላይ አቃቤ ህግ የፃፈው ደብዳቤ ያሳያል።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ይህንን የሃሰተኛ ሰነድ እና የትምሕርት ማስረጃውን በኮሚቴ ተዋቅረው ያጋለጡ ሰራተኞችን ከስራ መባረር ጀምሮ እንከ ዛቻ እና ማሳደድ እንዲሁም በቅርቡ እስከማሳሰር እና ሃሰተኛ ክሶችን እስከመክሰስ የደረሰው የኢቢሲ ባለስልጣናት ቡድን የሙስና ኮሚሽን ያረጋገተውን ሃቅ በመሸፋፈን ጉዳዩን ባታሩና በተቆሙ አካላት ላይ ከፍተኛ በደል እየፈጸሙ ይገኛሉ።
ኮርፖሬሽኑ ይህንኑ አምኖበት ከዚህ አንፃር የ228 ሰራተኞቹን የትምህርት ማስረጃ አግባብነት በኢፌድሪ የትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን፣ በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ ትምህርት ጥራት እና አግባብነት ኤጀንሲ እንዲሁም በኦሮሚያ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ በኩል እንዲጣራለት መላኩን ገልጿል። እስካሁን የ143 የቴክኒክ እና የአስተዳደር ሠራተኞች የትምህርት ማስረጃ ተጣርቶ ለተቋሙ የደረሰው ሲሆን ቀሪውን ውጤት በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኝ የተቋሙ የሰው ሀብት አስተዳደር እና ልማት ዲቪዥን አስታውቋል። ይህንን እንዲደረኛ ማስረጃው እንዲጣራ ግፊት የሚያደርጉ ሃገር ወዳዶችን በየእስር ቤቱ በማንገላታት እና ስማችንን አተፉ ሃሰተኛ መረጃ አሰራጩ በሚል እያሰቃያቸው ነው። የጸረ ሙስና ኮሚሽን እና ኢቢሲ ያመኑበትን ነገር ለምን ተጋለጥኩ በሚል የኢቢሲ ባለስልጣናት ሌላ ወንጀል በንጹሃን ላይ እየፈጸሙ ይገኛሉ።

ጉዳዩን አውቀዋለሁ የሚሉና አሁን በውጪ አገር የሚገኙ አንድ የኢቢሲ ሰራተኛ እንዳሉን መጀመርያ ለአመራሩ በየደረጃው የት/ማ እደተጭበረበረ አሳወቅን 37 ሰው ማሳያ አርገን.ከዛ ተቁዋሙም ባሳየናቸው መንገድ ተጠቅመው 520 የሰራተኛ ስም ወቶ አሙዋሉ ተባለ የላቸውም ት/ም ስልጠናም ተላከ ውጤቱ ያው ሆነ እውቅና የለውም ተባለ ከዛ ማንንም ተጠያቂ አናደርግም የሚል መልስ መለሱልን። በሙዋቅር ሰበብ በአግባቡ የተማሩ ልጆች ጋዜጠኛም ባለሙያም አወረዱት ። ለጠቅላይ ሚኒስተር ጽ/ቤ ጭምር አስገብተናል ከነስም ዝርዝር መልስ ግን የለም። ብለዋል።
የተለያዩ ሰነዶች እንደሚያመለክቱት እና ኢቢሲም 400 ሰራተኞቹ የትምሕርት ማስረጃ ማረጋገጫ እንዲያቀርቡ በተየቀው ማስታወቂያ መሰረት እንዲሁም ጸረ ሙስና ኮሚሽን እንደጻፈው ደብዳቤ በኮፕሬሽኑ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ወንጀል እንደተፈጸመ ያረጋግጣል። በባለስልጣናት ደረጃ በሃሰተኛ ሰነድና በፎርጂድ ስልጣኑን የተቆታተኡት በርካቶች መሆናቸውም ያረጋግጣል።
በዚሁ ጉዳይ የኢቢሲ ባለስልጣናትን ዱላ እየቀመሱና እየተሳደዱ እየተከሰሱ ከሚገኙት አንዱ ኢንጂነር ወገን አበበ ናቸው።

እሳቸውን እንዳናገርነውና በሰጡን መልስ EBC ደብዳቤ አለክ ተብዬ ለመቀበል ዋናው መስርያ ቤት ሄጄ በቀን 16/2/2016 በፖሊስ እድያዝ ተደርጎ ሸጎሌ ፖስተር ፖሊስ ጣብያ ታስሬ ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት በሚል EBC ከሶኝ በ17/2/2016 ፍርድ ቤት ቀርቤ በ5000 ሺ ብር ዋስ ተለቅቅያለው መርማሪ ፖሊስ 14 ቀን ቀጠሮ ቢጠይቅም.
የክሱ ዝርዝ 1: ኤልያስ መሰረት በሚባል የፌስቡክ ገጽ ላይ ሰለ EBC የተሳሳተ መረጃ በመጻፍ.
2:የኔታ ዩትዩብ ሚዲያ ላይ በመቅረብ interview በማድረግ የተሳሳተ መረጃ በመናገር. ይሄ ሁሉ ማሳደድ የመጣብኝ EBC በተጭበረበረ መንገድ ድግሪ የተማሩ/ፎርጅድ ያሰሩትን (EBC በሰጣቸው የዳቦ ስም መስፈርት ያላሙዋሉ የሚላቸውን) ለጸረሙስና እዲሁም ለህዝብ እውነቱን በማሳወቄ ነው.
በኢፌድሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ትምህርት ማስረጃቸው እውቅና የለውም የተባሉትን እራሱ EBC ያመናቸውን በመግለጫው ተጠያቂ ሳያደርግ. የደበቁትን ያወጣነውን ልጆች ማሳደድ ምን ማለት ነው.ስንቱ ተምሮ ስራ አቶ ባለበት ሀገር በየተቁዋማቱ በፎርጅድ ተቀጥረው የሚሰሩትን ሰራተኞች ተጠያቂ እዳይሆኑ ፍርጅድ ከማለት የዳቦ ስም እየሰጡ ሹመኞች እየደበቁ በለበት ሁኔታ በምን አፋችን ነው ሰለትምህርት ጥራት ምናወራው 12ኛ ክፍል በወደቁ ተማሪወች ብዛትስ ትምህርት ጥራት አመጣን ሚባለውስ እዴት ነው ተምረው ስራ እደሚያጡ እያወቁ ባለበት ሁኔታ በፎርጅድ/በተጭበረበረ የት/ም ማስረጃ የተነሳ። ሲሉ የደረሰባቸውን ግፍ አረጋግጠውልናል።

