Eyerusalem Tesfaw Enyew

·  ይህ ክስ ዛሬ ለብርሀኑ ተክለያሬድ የቀረበበት ክስ ነው።

ነገር ግን ብርሀኑ በግልፅ ለፍ/ቤቱ ሲያስረዳ የነበረው ይህን ክስ ገና አሁን ችሎት ላይ መስማቴ ነው ለእኔ አዲስ ነው እኔ በምርመራ ላይ ስጠየቅ የነበረው አቡነ ጴጥሮስ ለምን ስልጣን አይለቁም? አቡነ አብርሀም ለምን ስልጣን አይለቁም? ቀጣይ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ የታሰበው ምንድነው …..ወዘተ የመሳሰሉትን ነገሮች ነው ሲጠይቁኝ የነበረው ሲል መርማሪዎቹን አንተ እንዲህ ብለኸኛል አንተ እንዲህ ብለኸኛል በማለት ሞግቷል

ጠበቃዎቹም ክሱ ላይ በግልፅ እንደተቀመጠው ከ 2015 ጀምሮ ነው የወንጀል ድርጊቱ ተፈፀመ የሚለው ለምን እስከዛሬ በቁጥጥር ስር አልዋለም ለምን ሲኖዶስ ስብሰባ ሁለት ሶስት ቀን ሲቀረው ማሰር ተፈለገ ፍ/ቤቱ የዚህን ክስ ዓላማ ተረድቶ ደንበኛችንን በነፃ ካልሆነ በዋስ ተለቅቆ ከሰኞ ጀምሮ ለሚካሄደው የሲኖዶስ ስብሰባ ወደ ኃላፊነቱ ይመለስ ሲሉ ተከራክረዋል

#በመጨረሻም ብርሀኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ሲያልፍ ትፈታለህ እስከዛ አርፈህ ተቀመጥ ብለውኛል ብሏል

ዳኛውም ግራ ቀኙን መርምረን 6 ቀን ፈቅደናል ብሎ ለጥቅምት 15 ተቀጥሯል የሆነው እንደዚህ ነው!