ቀጥታ : ሁለት ሳምንት ያስቆጠረው የእስራኤል ጋዛ ጦርነት ዋና ክስተቶች

Related Video and Audio

VIDEO 1 MINUTE 30 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 30 SECONDS1:30

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBCአሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBC

VIDEO 7 MINUTES 59 SECONDSVIDEO 7 MINUTES 59 SECONDS7:59

Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBCከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ

Play video ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ‘ክፍቷ እስር ቤት’ ጋዛ from BBC

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 23 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 23 SECONDS1:23

Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBCሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ?

Play video ሐማስ በእስራኤል ላይ የከፈተው ድንገተኛ የተቀናጀ ጥቃት እንዴት ጀመረ? from BBC

VIDEO 1 MINUTE 33 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 33 SECONDS1:33

Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBCበእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች

Play video በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተፈጠረው ግጭት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች from BBC

ጭምቅ ሃሳብ

  1. የእስራኤል ጋዛ ጦርነት ከጀመረ ሁለት ሳምንት ሆነው
  2. በሐማስ ታግተው የነበሩ አሜሪካዊ እናትና ልጅ ተለቀቁ
  3. የሳዑዲ ልዑል ሐማስን፣ እስራኤልን እና ምዕራባውያንን ተቹ
  4. በጋዛ በርካታ ክርስቲያኖችን ያስጠለለው የኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን በአየር ጥቃት ተመታ
  5. የአሜሪካ ተዋጊ መርከብ ከየመን ወደ እስራኤል የተተኮሰ ሚሳኤል አከሸፈ
  6. በጋዛ የሆስፒታል ፍንዳታ ስፍራ የተፈጠረው ድንጋጤ እና ግራ መጋባት
  7. ዓለም ‘ሰብዓዊነቷን እያጣች ነው’ – የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት
  8. እስራኤል አስካሁን ወደ ጋዛ ዘልቃ እንዳትገባ ያገዳት ምንድን ነው? አራት ቁልፍ ምክንያቶች
  9. በጋዛው አል-አህሊ ሆስፒታል ላይ ስለደረሰው ፍንዳታ ማስረጃዎች ምን ይጠቁማሉ?
  10. ጠቅላይ ሚኒስትር ሱናክ ዩናይትድ ኪንግደም ከእስራኤል ጎን ናት አሉ

ቀጥታ ዘገባ

  1. የታተመዉ 5:255:25እስራኤል ዜጎቿ ከግብጽ እና ጆርዳን እንዲወጡ አሳሰበችየእስራኤል መንግሥት በግብጽ እና ጆርዳን ያሉ ዜጎቹ ከአገራቱ በአስቸኳይ እንዲወጡ ማዘዙ ተዘገበ።ኤአፍፒ የዜና ወኪል የእስራኤል ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት ዜጎች ወደ ሁለቱ አገራት እንዳይጓዙ እንዲሁም በአገራቱ ያሉ ከአገራቱ እንዲወጡ የጉዞ ማሳሰቢያ አውጥቷል ብሏል።ባለፈው ሳምንት እንዲሁ በተመሳሳይ የእስራኤል መንግሥት ተመሳሳይ የጉዞ ማስጠንቀቂያ በቱርክ ለሚገኙ ዜጎቹ አስተላልፎ ነበር።Article share tools
  2. የታተመዉ 5:245:24እርዳታ የጫኑ የመጀመሪያዎቹ ተሸከርካሪዎች ጋዛ ገቡእርዳታReutersCopyright: Reutersየእስራኤል እና ሐማስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ለመጀመሪያ ግዜ እርዳታ የጫኑ ተሸከርካሪዎች ከግብጽ ወደ ጋዛ ገብተዋል።እስራኤል ምግብ፣ ውሃ እና መድሃኒት የጫኑ 20 ተሸከርካሪዎች ጋዛ እንዲገቡ ፈቅዳለች። ቴልአቪቭ ነዳጅ ግን ጋዛ እንዲገባ አልፈቀደችም።የተባበሩት መንግሥታት እስራኤል ጋዛን ከበባ ውስጥ በመክተቷ ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ ይፈጠራል የሚል ማስጠንቀቂያ አውጥቶ ነበር።ተንቀሳቃሽ ምስሎች የእርዳታ ቁሳቁስ የጫኑት ተሸከርካሪዎች ከግብጽ የራፋን ደንበር መሻገሪያ አልፈው ወደ ጋዛ ሲገቡ አሳይተዋል።Article share tools
  3. የታተመዉ 3:253:25ግጭቱ ከጀመረ ቢያንስ 22 ጋዜጠኞች መገደላቸው ተገለጸየሮይተርስ ጋዜጠኛ ፋተማ ካንሶ ከተገደለ በኋላ የጋዜጠኛው እናት ሐዘናቸውን ሲገልጹReutersCopyright: Reutersየጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪው ድርጅት የእስራኤል እና ሐማስ ግጭት ከጀመረ አንስቶ ቢያንስ 22 ጋዜጠኞች ተገድለዋል አለ።የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪው (ሲፒጄ) ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከተገደሉት ጋዜጠኞች መካከል 18ቱ ፍልስጤማውያን ናቸው ብሏል።እንደ ሲፒጄ ከሆነ 15 ጋዜጠኞች ሕይወታቸውን ያጡት በእስራኤል የአየር ጥቃት ሲሆን ሁለት ጋዜጠኞች ደግሞ በደቡባዊ እስራኤል በሐማስ ጥቃት የተገደሉ ናቸው።ቡድኑ በመግለጫው 8 ጋዜጠኞች ጉዳት እንደደረሰባቸው የገለጸ ሲሆን ሦስት ጋዜጠኞች የደረሱበት አልታወቀም ወይም በእስር ላይ ናቸው ብሏል።ሲፒጄ ጋዜጠኞች ሰላማዊ ሰዎች መሆናቸውን እና በዚህ አስቸጋሪ ወቅት እጅግ አስፈላጊ ስራን የሚሰሩ በመሆኑ በተዋጊዎች ዒላማ መደረግ የለባቸውም ብሏል።Article share tools
  4. የታተመዉ 3:183:18ግብጽ በእስራኤል እና ሐማስ ግጭት ዙሪያ ዓለም አቀፍ የሰላም መድረክ አዘጋጀችየግብጹ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል-ሲሲGetty ImagesCopyright: Getty Imagesግብጽ ከ20 በላይ አገራት ተሳታፊ የሚሆኑበት ለእስራኤል እና ሐማስ ግጭት መፍትሄ የሚሻ ዓለም አቀፍ የውይይት መድረክ አዘጋጀች።የአገራት መሪዎች እና ተወካዮች ዛሬ በካይሮ በሚጀመረው እና በመከላከለኛው ምስራቅ የሰላም ሁኔታ በሚመክረው ጉባኤ ለመገኘት ግብጽ እየገቡ ነው።ሮይተርስ የዜና ወኪል በዚህ ጉባኤ ላይ የግብጽ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል-ሲሲ፣ የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ሞሐሙድ አባስ፣ የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጄምስ ክሌቨርሊ እና የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒ ጉተሬዝ ከተሳታፊዎች መካከል እንደሚገኙበት ጽፏል።ከላይ ከተጠቀሱት ባለስልጣንት በተጨማሪ የበርካታ የአረብ አገራት መሪዎች እና ተወካዮች በካይሮ እንደሚገኙ ይጠበቃል።ይሁን እንጂ በዚህ ስብሰባ ላይ ከእስራኤል፣ ከሐምስ፣ ከአሜሪካ እና ከኢራን ተወካዮች ስለመገኘታቸው እስካሁን ማረጋገጫ አልተሰጠም።የግብጽ ባለስልጣናት የዚህ ውይይት መድረክ ዋና ግብ የተኩስ አቁም እንዲደረስ ማስቻል ነው ይላሉ። ካይሮ ይህን ተበል እንጂ የግጭቱ ዋና ተሳታፊዎች እና እንደ ኢራን እና አሜሪካ ያሉ ቁልፍ አገራት ተሳታፊ ባልሆኑበት መድረክ ይህን የማሳካት ዕድሉ ጠባብ እንደሚሆን ይጠበቃል።Article share tools
  5. የታተመዉ 1:491:49ትናንት ዓርብ ፍልስጤምን የሚደግፉ ሰልፎች በተለያዩ አገራት ተካሄዱፍልስጤምን የሚደግፉ ሰልፎችGetty ImagesCopyright: Getty Imagesትናንት ዓርብ በበርካታ አረብ አገራት እስራኤል በጋዛ እያደረሰች ያለችውን ድብደባ እንድታቆም የሚጠይቁ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደው ውለዋል።ፍልስጤማውያንን የሚደግፉ ሰልፎ በኢንዶኔዢያ፣ ማሌዢያ እና ሕንድ ጭምር ተካሂደዋል።ለፍልስጤም አጋርነት ለመግለጽ አደባባይ ከተወጣባቸው አገራት መካከል ቱኒዚያ፣ አማን፣ ጆርዳን እና ሞሮኮ ተጠቃሽ ናቸው።ፍልስጤምን የሚደግፉ ሰልፎችReutersCopyright: Reutersሐማስ ከሁለት ሳምንታት በፊት በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ ቴል አቪቭ በወሰደችው የአጸፋ እርምጃ ከ4ሺህ ያላነሱ ሰላማዊ ሰዎች በጋዛ መገደላቸውን በጋዛ ያሉ የጤና ኃላፊዎች ገልጸዋል።ፍልስጤምን የሚደግፉ ሰልፎችEPACopyright: EPAArticle share tools
  6. የታተመዉ 1:401:40የሳዑዲ ልዑል ሐማስን፣ እስራኤልን እና ምዕራባውያንን ተቹየሳዑዲው ልዑል ቱርኪ አል-ፋይሰልGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየሳዑዲው ልዑል ቱርኪ አል-ፋይሰል ሐማስን እና እስራኤልን ንጹኃን ዜጎች ላይ ጥቃት በማድረሳቸው ተችተዋል።“ማንም ጀግና የለም። ተጎጂዎች ናቸው ሁሉም” ብለዋል።እምብዛም አስተያየት ከማይሰማበት የአረቡ ዓለም በተሰጠው በዚህ አስተያየት ምዕራበውያንም ተወቅሰዋል።ልዑሉ በአሜሪካ ራይስ ዩኒቨርስቲ ነው ንግግሩን ያደረጉት።የቀድሞ ዲፕሎማትና የስለላ ኃላፊ የነበሩት ልዑሉ ሐማስ ንጹኃንን እንዳገተና እስልምና ግን ማንንም ሰው አለመጉዳትን እንደሚያስተምር ተናግረዋል።እስራኤልም ንጹህ ፍልስጤማውያንን በጋዛ በቦምብ መደብደቧን እንዲሁም ፍልስጤማውያን ሕጻናት፣ ሴቶችና ወንዶችን በዌስት ባንክ ማሰሯን ኮንነዋል።የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን የሐማስን ጥቃት “መነሻ የሌለው ትንኮሳ” ብለው መዘገባቸውን ልዑሉ ተችተዋል።“ከዚህ በላይ ምን መነሻ ያስፈልጋል? እስራኤል ፍልስጤማውያን ላይ ለሦስት አሥርታት የፈጸመችው መነሻ ነው” ብለዋል።በይዞታው ውስጥ ያሉ ሰዎች ለነጻነታቸው መታገል መብታቸው እንደሆነ ተናግረዋል።የምዕራባውያንን ፖለቲካ ልዑሉ የተቹ ሲሆን፣ “እስራኤላውያን በፍልስጤማውያን ሲገደሉ ታለቅሳላችሁ። ሆኖም ግን እስራኤላውያን ፍልስጤማውያንን ሲገድሉ ለማዘን አትፈቅዱም” ብለዋል።Article share tools
  7. የታተመዉ 1:371:37መውጫ መግቢያው ለተዘጋባቸው የጋዛ ነዋሪዎች ለመድረስ መከፈቱ የሚጠበቀው በርከፍተኛ መጠን ያለው የምግብ እርዳታ ጋዛን ከግብፅ ጋር በሚያዋስነው ድንበር ላይ ቆሞ ባለበት ሁኔታ ምግብ፣ ነዳጅ እና የመጠጥ ውሃ ጋዛ ውስጥ እየተሟጠጠ ስለመሆኑ የመንግሥታቱ ድርጅት አስጠንቅቋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  8. የታተመዉ 1:351:35በሐማስ ታግተው የነበሩ አሜሪካዊ እናትና ልጅ ተለቀቁየተለቀቁት እናትና ልጅ ከባይደን ጋር ሲያወሩUS Embassy JerusalemCopyright: US Embassy Jerusalemበሐማስ ጋዛ ውስጥ ታግተው የነበሩ እናትና ልጅ ተለቀቁ። ጁዲት ራናን እና ናታሊ ይባላሉ እናትና ልጅ።እስራኤል ላይ ጥቃት በተፈጸመ ወቅት ነበር የታገቱት።የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ አል-ቃሲም ብርጌድስ ባጋራው ተንቀሳቃሽ ምሥል ላይ የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማኅበር ሠራተኞች ነጻ የወጡትን ታጋቾች ሲያግዙ ይታያል።በእየሩሳሌም ያለው የአሜሪካ ኤምባሲ እናትና ልጅ ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር በስልክ ሲያወሩ የሚያሳይ ምሥል ለቋል።ኤምባሲው “ፕሬዝዳንቱ ከሐማስ ከተለቀቁ ሁለት ታጋቾች ጋር ተነጋግረዋል። ደኅና ስለሆኑ ደስ ብሎናል። ሌሎች ታጋቾችንም ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመቀላቀል የምንችለውን ሁሉ ማድረግ እንቀጥላለን” ብሏል ኤምባሲው።ዋይት ሀውስ በለቀቀው መግለጫ ባይደን ታጋቾቹ ከቤተሰባቸው ጋር በቅርቡ እንደሚቀላቁ ገልጸው በዚህም “እጅግ ተደስቻለሁ” ማለታቸውን አስፍሯል።Article share tools
  9. የታተመዉ 1:331:33“የእስራኤል ጋዛ ጦርነት ከጀመረ ሁለት ሳምንት ሆነው”GazaEPACopyright: EPAልክ የዛሬ ሁለት ሳምንት ሐማስ ባልተጠበቀ ሁኔታ በእስራኤል ላይ በፈጸመው የተቀናጀ ከባድ ጥቃት የተቀሰቀሰው ጦርነት እንደቀጠለ ነው።አስካሁን በፍልስጥኤማውያን እና በእስራኤላውያን በኩል ሰላማዊ ሰዎች የግጭቱን ዋጋ እየከፈሉ ነው።ለአጭር ጊዜ በቆየው የሐማስ ጥቃት ከ1400 በላይ እስራኤላውያን እና የሌሎች አገራት ዜጎች ተገድለዋል።ከዚያ በኋላ እስራኤል በጋዛ ላይ እየካሄደችው ባለው የአጸፋ የአየር ጥቃት ከ4000 በላይ ፍልስጥኤማውያን ተገድለዋል።የአየር ጥቃቱም እንደቀጠለ ነው፤ የእግረኛ ሠራዊት ወረራ በእስራኤል ሊካሄድ እንደሚችል እየተጠበቀ ነው። ባለፉት ሁለት ሳምንታት የተከሰተው በአጭሩ:• መስከረም 26/2016 ዓ.ም. ቅዳሜ ማለዳ የሐማስ ታጣቂዎች ወደ እስራኤል ዘልቀው በመግባት ድንገተኛ ጥቃት ፈጸሙ።• የሐማስ ታቂዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ግዛት መተኮሳቸውን አስታወቁ።• በጥቃቱ ከ1400 በላይ ከእስራኤል በኩል ሲገደሉ፣ ከዚህ ቁጥር የሚልቁት ጉዳት ደርሶባቸዋል።• ከ200 የሚበልጡ ሌሎች ሰዎች ደግሞ በሐማስ ታጣቂዎች ታግተው ወደ ጋዛ ተወስደዋል።• ጥቃቱን ተከትሎ እስራኤል በሐማስ ቁጥጥር ስር ባለችው ጋዛ ላይ ቀን ከሌት ያልተቋረጠ የአየር ድብደባ እያካሄደች ነው።• ሐማስም ወደ እስራኤል አልፎ አልፎ ሮኬቶችን ማስወንጨፉን ቀጥሏል።Gaza destructionGetty ImagesCopyright: Getty Images• እስራኤል በጋዛ ላይ ያለማቋረጥ እየፈጸመችው ባለው የአየር ድብደባ አብዛኞቹ ሴቶች እና ሕጻናት የሆኑ ከ4000 በላይ ፍልስጥኤማውያን ሲገደሉ፣ ከ13 ሺህ የሚበልጡ ደግሞ ቆስለዋል።• እስራኤል ሰውም ሆነ ምንም ነገር ወደ ጋዛ እንዳይገባ ሙሉ ከበባ ያወጀች ሲሆን፣ ምግብ፣ ውሃ እና መድኃኒት በግዛቲቱ ውስጥ እየተሟጠጠ ነው።• እስራኤል በጋዛ ላይ የእግረኛ ሠራዊት ወረራ ለማካሄድ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን እና የጦር መሳያዎቿን አስጠግታ አመቺ የምትለውን ጊዜ እየተበቀች ነው።• እስራኤል በጋዛ ላይ ለምታካሂደው ወታደራዊ ዘመቻ በሰሜናዊ ጋዛ የሚኖሩ ፍልስጥኤማውያን ቀያቸውን ለቀው እንዲወጡ ያዘዘች ሲሆን፣ አስካሁን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጥኤማውያን ተፈናቅለዋል።• ከሁለት ሚሊዮን በላይ ባላት ጋዛ ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች በአየር ድብደባ ስር ሆነው፣ መሠረታዊ አቅርቦቶች ተቋርጦባቸው በሚገኙበት ሁኔታ አደገኛ ሰብአዊ ቀውስ ሊከሰት እንደሚችል የረድኤት ድርጅቶች እያሳሰቡ ነው።• የአሜሪካ፣ የዩናይትድ ኪንግደም እና የሌሎች አገራት መሪዎች በእስራኤል ላይ ባሳደሩት ግፊት፣ ከግብፅ በኩል ሰብአዊ እርዳታ እንዲገባ ፈቅዳ አቅርቦቱ የሚጀመርበት ጊዜ እየተጠበቀ ነው።Article share tools
  10. የታተመዉ 11:11 20 ጥቅምት 202311:11 20 ጥቅምት 2023የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር በግብፅጠ/ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ እና ፕ/ት አብዱል ፋታህ አል-ሲሲReutersCopyright: Reutersጠ/ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ እና ፕ/ት አብዱል ፋታህ አል-ሲሲImage caption: ጠ/ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ እና ፕ/ት አብዱል ፋታህ አል-ሲሲየዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ አርብ ከሰዓት በኋላ ከግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አል-ሲሲ ጋር ተገናኝተው ውይይት አደረጉ።ሐሙስ ከእስራኤል ጀምረው በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ሱናክ፣ አርብ ጠዋት ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ከኳታሩ አሚር ጋር በተመሳሳይ ተገናኝተው ተወያይተዋል።የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ እንደተናገሩት ዩናይትድ ኪምግደም “ቅድሚያ” በመስጠት ትኩረት የምታደርገው የራፋህ የድንበር መተላለፊያ ለሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ክፍት በመሆንበት ሁኔታ ላይ ነው።Article share tools
  11. የታተመዉ 8:22 20 ጥቅምት 20238:22 20 ጥቅምት 2023ሐማስ ታጋቾችን ለመልቀቅ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠየቀከታጋቾቹ መካከል ጥቂቶቹBBCCopyright: BBCከታጋቾቹ መካከል ጥቂቶቹImage caption: ከታጋቾቹ መካከል ጥቂቶቹሐማስ ከእስራኤል አግቶ ከወሰዳቸው ከሁለት መቶ በላይ ታጋቾች መካከል የተወሰኑ እስረኞችን በመልቀቅ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ንግግር እየተካሄደ መሆኑ ተዘገበ።ቢቢሲ ከምንጮቹ እንደተነገረው በሐማስ ታግተዋል ተብለው ከሚታመኑት 203 ሰዎች መካከል አብዛኞቹን ለማስለቀቅ የሚደረገው ንግግር መቀጠሉን እና ሐማስ በምትኩ አስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ መጠየቁ ተገልጿል።ነገር ግን እስራኤል እስካሁን በቀረበው ሃሳብ አለመስማማቷ ተነግሯል።በዓለም አቀፍ አሸማጋዮች አማካይነት እየተደረገ ያለው ድርድር ትኩረቱን ጋዛ ውስጥ ተይዘው በሚገኙት በታጋቾች ላይ አድርጎ እየተካሄደ ይገኛል። የዚህን ንግግር ዝርዝር በተመለከተ ከሁለቱም ወገን በይፋ የተሰጠ ማረጋገጫ የለም።በእገታ ስር ያሉት ሁሉም ሰዎች ሐማስ እጅ ያሉ አለመሆናቸው የተነገረ ሲሆን፣ የተወሰኑት በሌሎች ታጣቂ ቡድኖች ቁጥጥር ስር ናቸው ተብሏል።ጋዛ ውስጥ በእገታ ላይ ያሉት ሰዎች ሁኔታ የእስራኤል ጦር አዛዦች ወደ ጋዛ ዘልቆ በመግባት ሊያደርጉት ያሰቡትን ዘመቻ ካወሳሰቡባቸው ምክንያቶች አንዱ ነው።ታጋቾቹን ከወታደራዊ እርምጃ ይልቅ በድርድር እንዲለቀቁ ማድረግ በሕይወት ወደ አገራቸው የመመለስ ዕድላቸውን ከፍ ያደርገዋል።መስከረም 26/2016 ዓ.ም. ሐማስ እስራኤል ውስጥ ዘልቆ በመግባት በፈጸመው ድንገተኛ ጥቃት ከ1400 በላይ ሰዎችን መግደሉ የተዘገበ ሲሆን፣ 200 የሚሆኑ ሰዎችንም አግቶ ወደ ጋዛ ሰርጥ መውሰዱን የእስራኤል ጦር ሠራዊት አስታውቋል።ሠራዊቱ ባወጣው አዲስ መግለጫ ላይ የታጋቾቹን ዝርዝር ሁኔታ ይፋ አድርጓል። በዚህም መሠረት ከታገቱት 203 ሰዎች መካከል ከ20 በላይ የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ናቸው።ከአስር አስከ ሃያ የሚደርሱት ደግሞ ዕድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ ሲሆን፣ ከታጋቾቹ መካከል አብዛኞቹ በሕይወት መኖራቸውን የገለጸው የእስራኤል ሠራዊት፣ የሟቾች አስከሬን እንደ ታጋች ወደ ጋዛ መወሰዳቸውንም ጠቅሷል።Article share tools
  12. የታተመዉ 6:10 20 ጥቅምት 20236:10 20 ጥቅምት 2023በጋዛ በርካታ ክርስቲያኖችን ያስጠለለው የኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን በአየር ጥቃት ተመታፍርስራሽGetty ImagesCopyright: Getty Imagesበጋዛ የሚገኝ እና በርካታ ክርስቲያኖችን አስጠልሎ የነበረው የግሪክ የኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን በአየር ጥቃት ተመታ።ጥቃቱን በተመለከተ ሐማስ ባወጣው መግለጫ የቅዱስ ፖርፊየስ ቤተ-ክርስቲያን ያጋጠመው ከፍተኛ ፍንዳታ በሕንጻው ላይ ከባድ ጉዳት ማስከተሉን እና በርካቶችን መጉዳቱን አስታውቋል።ሐማስ ጥቃቱ የተፈጸመው በእስራኤል ጦር ነው ብሏል።የእስራኤል መከላከያ ኃይል ግን ቤተ-ክርስቲያኑን ዒላማ አለማድረጉን ይገልጻል።ጦሩ ለፈንሳይ ዜና ወኪል ኤኤፍፒ እንደገለጸው የተዋጊ ጄቶቹ ጥቃት የታጣቂዎችን የሮኬት እና ሞርታ ጥቃት ትዕዛዝ መስጫ ማዕከለን መምታታቸውን ተከትሎ በአካባቢው ያለችው ቤተ-ክርስቲያን ግድግዳ ወድሟል ብሏል።ቢቢሲ በቤተ-ክርስቲያኗ እና በሰው ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን ማወቅ ባይችልም ኤኤፍፒ ያጋራቸው ምስሎች በእምነት ቤቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።የእየሩሳሌም የኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ጥቃቱን አጥብቀው በማውገዝ ባወጡት መግለጫ ለፍንዳታው ምክንያት የሆነው የእስራኤል የአየር ጥቃት ነው ብለዋል።የሠላማዊ ዜጎች መጠለያ በሆኑት በአብያተ ክርስቲያናት እና በተቋሞቻቸው ላይ የሚፈጸመው ጥቃት “ቸል ሊባል የማይችል የጦር ወንጀል ነው” ብለዋል በመግለጫቸው።ቅዱስ ፖርፊየስ ቤተ-ክርስትያን ከ12ኛው ክፍለ ዘመን በፊት የተመሠረተ ሲሆን፣ ባለፈው ማክሰኞ በከባድ ፍንዳታ ተመትቶ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከተገደሉበት አል አህሊ ሆስፒታል በቅርብ ርቀት ይገኛል።Article share tools
  13. የታተመዉ 5:24 20 ጥቅምት 20235:24 20 ጥቅምት 2023የአሜሪካ ተዋጊ መርከብ ከየመን ወደ እስራኤል የተተኮሰ ሚሳኤል አከሸፈየአሜሪካ ተዋጊ መርከብREUTERSCopyright: REUTERSየአሜሪካ ተዋጊ መርከብ ከየመን ነው የተተኮሰው የተባለ ሚሳኤል እና ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ማክሸፉን የአሜሪካ ባለሥልጣኖች አሳወቁ።የተተኮሰው ከኢራን ጋር ትስስር ባለው የሁቲ ንቅናቄ ነው ተብሏል።የፔንታጎን ቃል አቀባይ ሚሳኤሎቹ የተተኮሱት “እስራኤል ዒላማ በማድረግ ነበር” ብለዋል።ሚሳኤሉ የከሸፈው የአሜሪካ መሣሪያ ዩኤስኤስ ካርኒ የተባለው ሚሳኤል አክሻፊ በቀይ ባሕር ሰሜናዊ ክፍል ነበር እየተንቀሳቀሰ ያለው።ባለፉት ጥቂት ቀናት የአሜረካ ወታደሮች በኢራቅ እና ሶርያ ጥቃት እንደደረሰባቸው ፔንታጎን ገልጿል።በኢራን የሚደገፉ ቡድኖችን አሜሪካ በዐይነ ቁራኛ እየተከታተለች ትገኛለች።የፔንታጎን ብርጋዴር ጀነራል ፓትሪክ ራይደር እንዳሉት፣ ሦስት ሚሳኤሎች እና ብዙ ድሮኖች ከየመን ተተኩሰው ከሽፈዋል።በክስተቱ የተፈጠረ አደጋ ስለመኖሩ ሪፖርት አልተደረገም።Article share tools
  14. የታተመዉ 3:30 20 ጥቅምት 20233:30 20 ጥቅምት 2023በጋዛ የሆስፒታል ፍንዳታ ስፍራ የተፈጠረው ድንጋጤ እና ግራ መጋባትየፍልስጤም የጤና ኃላፊዎች ማክሰኞ ምሽት በጋዛ ከተማ በሚገኝ ሆስፒታል በደረሰ ፍንዳታ በትንሹ 471 ሰዎች መሞታቸውን ተናግረዋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  15. የታተመዉ 3:20 20 ጥቅምት 20233:20 20 ጥቅምት 2023ሪሺ ሱናክ ወደ ግብጽ ሊያመሩ ነውጠቅላይ ሚንስትር ሪሺ ሱናክGetty ImagesCopyright: Getty Imagesጠቅላይ ሚንስትር ሪሺ ሱናክImage caption: ጠቅላይ ሚንስትር ሪሺ ሱናክየዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚንስትር ሪሺ ሱናክ እስራኤል እና ጋዛን በመተለከተ በቀጠናው ካሉ አገራት ጋር ውይይት ለማድረግ ወደ ግብጽ ሊያመሩ ነው።የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት ሪሺ ሱናክ በጉብኝታቸው ትኩረት የሚያደርጉት በቀጠናው ውጥረት እንዳይባባስ ማድረግ እና የተጨማሪ ሰላማዊ ሰዎች ሞትን ማስቆም ነው ብሏል።ትናንት ሐሙስ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ልዑል ሞሐመድ ቢን ሰልማን ጋር የተገናኙ ሲሆን ሳዑዲ በመካከለኛው ምሥራቅ መረጋጋት እንዲፈጠር ድጋፏን እንድታደርግ ጠይቀዋል።ሱናክ ቀደም ሲል ወደ እየሩሳሌም በተጓዙ ወቅት አገራቸው ከእስራኤል ጎን እንደምትቆም አስታውቀው ነበር።Article share tools
  16. የታተመዉ 3:06 20 ጥቅምት 20233:06 20 ጥቅምት 2023በጋዛው አል-አህሊ ሆስፒታል ላይ ስለደረሰው ፍንዳታ ማስረጃዎች ምን ይጠቁማሉ?በጋዛ አል-አህሊ ሆስፒታል ላይ የደረሰው ከባድ ፍንዳታ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን እንደገደለ ተዘግቧል። በሐማስ ሥር ያሉ በጋዛ አመራሮች ለፍንዳተው እስራኤልን ተጠያቂ አድርገዋል። ሆነ ተብሎ የተፈጸመ የአየር ጥቃት ነው ሲሉም አውግዘዋል። እስራኤል ግን እጄ የለበትም ብላለች።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  17. የታተመዉ 3:06 20 ጥቅምት 20233:06 20 ጥቅምት 2023በጋዛ ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ የደረሰውን ፍንዳታ የኦርቶዶክስ ፓትርያሪክ አወገዙፍንዳታው ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል።Getty ImagesCopyright: Getty Imagesፍንዳታው ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል።Image caption: ፍንዳታው ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል።በጋዛ ከተማ የቅዱስ ፖርፊየስ ቤተ-ክርስትያን አቅራቢያ የደረሰውን ፍንዳታ ተከትሎ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን እና መጎዳታቸውን ሐማስ አስታውቋል።የፍልስጤም የዜና ወኪል ዋፋ በበኩሉ ቢያንስ ሁለት ሴቶች መገደላቸውን ዘግቧል።የዓይን እማኞች ለኤኤፍፒ የዜና አገልግሎት እንደተናገሩት ፍንዳታው በግሪክ የኦርቶዶክስ በቤተ-ክርስቲያኗ መግቢያ ላይ ጉዳት ሲያደርስ በአቅራቢያው ያለ ህንፃን አወድሟል።የእየሩሳሌም የኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ጥቃቱን “አጥብቆ በማውገዝ” ባወጣው መግለጫ ለፍንዳታው ምክንያት የሆነው የእስራኤል የአየር ጥቃት ነው ብሏል።የሠላማዊ ዜጎች መጠለያ በሆኑት በአብያተ ክርስቲያናት እና በተቋሞቻቸው ላይ የሚፈጸመው ጥቃት “ቸል ሊባል የማይችል የጦር ወንጀል ነው” ብሏል።የእስራኤል ጦር ጉዳዩን እየተመለከተ ነው ሲል ኤኤፍፒ ዘግቧል።Article share tools
  18. የታተመዉ 1:31 20 ጥቅምት 20231:31 20 ጥቅምት 2023ዓለም ‘ሰብዓዊነቷን እያጣች ነው’ – የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትከሐማስ ጥቃት በኋላ እስራኤል በጋዛ መጠነ ሰፊ ጥቃቶችን እየፈጸመች ትገኛለች።Getty ImagesCopyright: Getty Imagesከሐማስ ጥቃት በኋላ እስራኤል በጋዛ መጠነ ሰፊ ጥቃቶችን እየፈጸመች ትገኛለች።Image caption: ከሐማስ ጥቃት በኋላ እስራኤል በጋዛ መጠነ ሰፊ ጥቃቶችን እየፈጸመች ትገኛለች።በእስራኤል እና በሐማስ መካከል እየተካሄደ ባለው ግጭት ምክንያት መካከለኛው ምስራቅ “በገደል አፋፍ ላይ ነው” ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ ኃላፊ የሆኑት ፊሊፕ ላዛሪኒ ለቢቢሲ ተናግረዋል።የተመድ የፍልስጤም ስደተኞች የእርዳታ ኤጀንሲ ኮሚሽነር የሆኑት ላዛሪኒ “ዓለም አሁን ሰብዓዊነቷን እያጣች ነው” ብለዋል። ግጭቱ ወደ ሌሎች ቦታዎችም ሊስፋፋ እንደሚችልም አስጠንቅቀዋል።በጋዛ ያሉ ሰላማዊ ሰዎች ያሉበትን አስከፊ ሁኔታ ያነሱት ላዛራኒ፤ በአካባቢው የሰብዓዊ እርዳታ ኮሪደሮች እንዲከፈቱም ጥሪ አቅርበዋል።ሐማስ በእስራኤል ላይ ያደረሰውን ጥቃት ያወገዙት ላዛራኒ፤ “አሰቃቂው እና አረመኔያዊው እልቂት እስራኤል ውስጥ ድንጋጤን ፈጥሯል” ሲሉ ተናግረዋል።”ይህ ክስተት ግን ጦርነቱ ያለ ምንም ገደብ እንዲካሄድ ምክንያት አይሆንም። ተጨማሪ ሠላማዊ ዜጎችን መግደል ለቀጣይ ሠላም ጠቃሚ ነው ብዬ አላምንም” ብለዋል።Article share tools
  19. የታተመዉ 1:09 20 ጥቅምት 20231:09 20 ጥቅምት 2023እስራኤል አስካሁን ወደ ጋዛ ዘልቃ እንዳትገባ ያገዳት ምንድን ነው? አራት ቁልፍ ምክንያቶችእስራኤል ቆርጣለች። ሐማስን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ሳላጠፋ እንቅልፍ አይወስደኝም ብላለች። ለ300 ሺህ ተጠባባቂ ጦር “ምታ ነጋሪት፣ ክተት ሠራዊት” ብላለች። ከጋዛ የሚጎራበተው የእስራኤል ድንበር እርሻ ቦታው ሁሉ የታንክ ጋጋታ ሞልቶታል። ተወንጫፊ ሮኬቶች እና ሌሎች ጦር መሣሪያዎች ሁሉም አፈሙዛቸው ወደ ጋዛ ከፍተዋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  20. የታተመዉ 0:57 20 ጥቅምት 20230:57 20 ጥቅምት 2023ባይደን ሐማስ እና ፑቲን እንዲያሸንፉ አልፈቅድም አሉጆ ባይደንBBCCopyright: BBCየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከዋይት ሃውስ ሆነው ለአሜሪካውያን ባስተላለፉት የቴሌቪዥን ንግግር ሐማስ እና ፑቲን እንዲያሸንፉ አልፈቅድም ብለዋል።ፕሬዝዳንቱ የአሜሪካ ኮንግረስ ለእስራኤል እና ዩክሬን በቢሊዮን የሚቆጠርየእርዳታ ገንዘብ እንዲፈቅድ እንደሚጠይቁ ገልጸው ወዳጅ አገራት ላይ ፊታችንን ማዞር እንችልም ብለዋል።ባይደን ኮንግረሱ ለሁለቱ አገራት እስከ 100 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ እንዲፈቅድ ሊጠይቁ ይችላሉ የሚል ግምት አለ።ለእስራኤል የሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ የአገሪቱን የአየር ኃይል የሚያጠናክር እንደሚሆን ይጠበቃል። ባይደን አይረን ዶም የእስራኤል ሰማይን ደኅንነት ማስጠበቁን መቀጠል አለበት ብለዋል።ፕሬዝዳንቱ በዚህ ንግግራቸው ሐማስን “አሸባሪ” የሩሲያውን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ደግሞ “አምባገነን” ሲሉ ገልጸዋል።ባይደን “አሸባሪዎች እና አምባገነኖች ዋጋ መክፈል አለባቸው” ብለዋል።ፕሬዝዳንቱ ከጽሕፈት ቤታቸው ሆነው ባደረጉት ንግግር ሐማስ እና ፑቲን የተለያየ አደጋ የደቀኑ ቢሆንም የጎረቤት አገር ዴሞክራሲን ለማጥፋት መነሳታቸው ተመሳሳይ ያደርጋቸዋል ብለዋል።